Tuesday, October 31, 2023

https://youtu.be/PPQ0QJm_FWk?si=VvhinZko6dpgZZpq

በ2 ወራት ውስጥ ከ16ሺህ በላይ ወታደሮች ጠፍተዋል፥ የኢሰመኮ ሪፖርት፥ የካናዳ ማስጠንቀቂያ፥ አብይ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂን ለማስወገድ?
https://amharic-zehabesha.com/archives/186841
የአማራ ሞት ያሳስበኛል!” የኢሱ መግለጫ የኤርትራ | ታሪክ ተሰርቷል ባድል ተሳካ- ጎጃም አብይ ወደቀ- ፋኖ በደማቅ አስመረቀ ስራው ተሰራ
https://youtu.be/wT55NOUMAdI?si=QYSKBXAtZGgoMWHm

https://youtu.be/psAfZUOoKNw?si=BIKvjFHm5GW3LhH1

ታሪክ ተሰርቷል ባድል ተሳካ- ጎጃም አብይ ወደቀ- ፋኖ በደማቅ አስመረቀ ስራው ተሰራ
https://amharic-zehabesha.com/archives/186845
 
https://youtu.be/SOHR_HL7P8g?si=_d5JPgaEeNZxMUaO

ያለ ፋኖ ድል የለም! ያለ ፋኖ አማራነት የለም አርበኛ መሳፍንት ተስፉ
https://amharic-zehabesha.com/archives/186837

Monday, October 30, 2023

አብይ ላይ የባረቀው ወታደራዊ ሰልፍ | በአራጣ የተያዙት የአገዛዙ ጄነራሎች |ከአውሮፓ ህብረት ለአቢይ የተላከው መርዶ
https://youtu.be/9tRD_g40XhM?si=q0CA5k7Q4KdKNSW2

አብይ ላይ የባረቀው ወታደራዊ ሰልፍ | በአራጣ የተያዙት የአገዛዙ ጄነራሎች |ከአውሮፓ ህብረት ለአቢይ የተላከው መርዶ

https://youtu.be/SD6c_5kwuMc?si=zNtkPPpBRM_z0MsD

https://amharic-zehabesha.com/archives/186822
 
https://youtu.be/SOHR_HL7P8g?si=_d5JPgaEeNZxMUaO

ያለ ፋኖ ድል የለም! ያለ ፋኖ አማራነት የለም አርበኛ መሳፍንት ተስፉ
https://amharic-zehabesha.com/archives/186837
ፋኖ አርበኛ መሳፍንት የትግል አባታችን በውጭ ያላችሁ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አንድ በመሆን አግዙን አዲስ አደረጃጀት እየፍጠራችሁ አትከፋፍሉን ብለዋል
ፋኖ አርበኛ መሳፍንት የትግል አባታችን በውጭ ያላችሁ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አንድ በመሆን አግዙን አዲስ አደረጃጀት እየፍጠራችሁ አትከፋፍሉን ብለዋል። #አማራያሸንፍል pic.twitter.com/2dyY72k5RF— ASHEWEGOGO (@AmharaHQ) October 30, 2023

https://amharic-zehabesha.com/archives/186829

Sunday, October 29, 2023

ያግኙን
Please visit us every time, we hope you enjoy it and we welcome any feedback. Send any comments and questions concerning zehabesha.com to us at

aatebeje@gmail.com

admin@zehabesha.com

971- 426 6404

 የzehabesha.com መስራች እና ዋና አሳታሚ እና ስራ አስፈፃሚ ሲሆን ከዚህ ቀደም በቅንጅት ሰሜን አሜሪካ ፣ቅንጅት ፣አንድነት ፓርቲ እና ፍኖተ ነፃነት ድረ-ገጾች ይመራ ነበር።  # እባኮዎትን ለ ዘሀበሻ ፌስቡክ ፣ ዘሀበሻ ኦፊሻል ዩቲዩብ ፣ ዘሀበሻ ሬስቶራንት ፣ለሌላ ማንኛውም የሀበሻ  የሚዲያ አውታር ስልክ አትደውሉ:: ስልክ ቁጥሩ ለ amharic.zehabesha.com ግንኙነት ብቻ ነው የሚያገለግለው።

 አልዩ ተበጀ

Zehabesha.com

2005 - Present

Please Give Your Own Honest Opinion About US

Your opinion matters to us! If you love our work then your reviews helps us to improve our work and enhance the value we stand for. With your help, we can gain greater visibility  Click here to Review 

56 COMMENTS

November 2, 2013 at 7:18 am Edit

I believe you are not balanced and fare since all you focus on is negative news and information. The same is true on the other side as it is only the positive news that gets any air.

Now iit is all polarized, who is going to break this cycle? How are we meant to be civilized? What is wrong in being fair and reasonable?

Reply

November 4, 2013 at 9:08 am Edit

To tell you the truth i am only visiting two wesbsites those are This one and Awramba times are those only two who are showing both side of the story.

The rest are one sided extrimist. I know this website is a bit sided with G7 and Awramba with Woyanne but they both put every news and leave the reader to decide.

Reply

November 2, 2013 at 8:45 am Edit

I think the zehabesha is a web sight with most updated news. Whenever there is an important breaking news, this is where I read it first. I think you provide a balanced and fair reporting. In addition to the political news, you provide you readers with important health information, sport and entertainment. Most importantly you post the daily ESAT news which is awesome. The only thing I would love to read on your Web sight is more inspirational stories of Ethiopians who accomplished in different field. This can be from within Ethiopia or around the world. In addition, one thing I read a lot on people comment, it seems like there lots of people who know little about the history of their country. They rant negatively about ethnic groups. If the zehabesha posts our history of togetherness, our ancestors love to their country and people, our week ability to tolerate one another..etc, this may help most of us to be aware of our true history rather than afe tarik. Keep doing the wonderful job you are doing and I give you a big tumbs up for even asking our opinion.

Reply

November 2, 2013 at 10:44 am Edit

you are doing a good job!!!!you are on the right track!!!!keep on!!!! @kal are you looking for report on hidase gidib, growth and transformation etc!!!Media must not fear anybody and must be fare to nobody!!!Their main objective should be…telling the truth!!!!

Reply

November 2, 2013 at 2:58 pm Edit

you are doing a good job!!!you are on the right track!!!!keep on!!!!@Kal are you looking for a report on hidase gidib,growth and transformation,etc!!!! Media must not fear anybody and must be fair to nobody!!!! ..their main objective should be….telling the truth!!!!!

Reply

November 2, 2013 at 3:19 pm Edit

Just carry on as usual. You are providing a good service to our people are helping to promote democracy through the open forumms that are provided for everybody to have their say. What I suggest is that you sometimes need to look at a particular point of view and judge it on the value that it brings to the discussion at hand. If it does not it should be censored.

Outright insults, uncivilised talk and such like should be banned.

Reply

November 2, 2013 at 6:24 pm Edit

As a diaspora news outlet it is difficult to be fair and balanced. You need to distance your self from other foreign backed websites.

Reply

November 3, 2013 at 9:07 am Edit

Thank you zehabasha you are the number one balanced website.There is no discrimination in your website.Long live to Zehabasha.

Reply

November 3, 2013 at 9:25 am Edit

So far I see little biasedness other wise well and fine web site. When I said little biase you lean toward one group and one religion just like king Haile time. I don’t blame you for this for you are the offspring of that group. I am sure next generation will be free of this/

Reply

Getahunsays:

November 3, 2013 at 9:46 am Edit

You doning a great job with free press, a few may oppose for a few articles, but still we have to learn the other side story, deal with it, and come up with a solution. Hiding is not a solution. We all know what we can do and what we can not do.

Getahun

Reply

MomaEthiopiasays:

November 4, 2013 at 10:27 am Edit

Zehabesha web site is one of the best so far. you guys always give us breaking news way ahead of the others.The other thing is you have your websites both in English and Amharic which makes it easy for every Ethiopian to get latest news. Keep up the good work!!!

November 4, 2013 at 12:05 pm Edit

Zehabesha,

Truly an Ethiopian web site since it entertains the diverse views of the country and the people. I always belived that hypocricy does not serve a coomon good unless we practice what we say. A number of web sites call themselves the “Ethiopian Democratic” web site when we know how biased their coverage is. One notable web site is only interested on the issue of Assab and nothing else about the TPLF government bothers the editorial body. While the issue of Assab is important, reducing the human rights violation of the Tigrean government against non-Tigreans must be of the prime importance if we have to live together.

I can say that your web site is the first I check for any news. I have given up on others and I am pretty sure that many people have done the same.

Reply

:

November 4, 2013 at 1:13 pm Edit

Zehabeshawoch enay betamnew yemtekemwe yenanten metatefe bemulu eketatelalehu,betam gen letenenetay astemarewochay nachuna amesegenachuwalhu.andanday tenshe legha ethiopiaweyan yemaysefelgu negrochin makrebuin betetyafu yebelet ewdachuwalhu.amesegenalhu.

Reply

November 4, 2013 at 2:49 pm Edit

Hi Habesha,

You are doing a great job. Keep it up!!!! Having said that I have two comments. (1) Please do not interefere in church affiars. A few months ago you posted an article about Medhanealem Church (Minneapolis) including the photos of the priests. Although I agree with some of the points raised in the article, let spiritual issues be discussed at the church face to face, with politeness and with the fear fo God, not here behind the computer screen. (2) A few weeks ago, you posted an article mentinoning that Dawit (from Awaramba times) was seen at the Ethiopian Embassy, in DC, on a certain day, probably arranging his return to Ethiopia. However, I read an article by Dawit in which he claimed that he was somewhereelse on that day. As an evidence for this, Dawit sent you the copy of his air ticket. I want you to comment on that.

Thanks again for being a great source of news from the MOTHERLAND. I check your website every hour.

Reply

November 4, 2013 at 3:39 pm Edit

The bad thing about it all is that I was a Late Comer to the Site.Since then I have enjoyed it every bit of it including Tena Adam. . The latest of which was the interview with Lidetu Ayalew. It was an information in clear thinking. It was a political thought ABC.. Besides I always wondered why people just “voted” to misunderstand/hate Lidetu.I also enjoyed the piece by Temegen.

Please Keep up the Good Work

A Luta Conua!!

Reply

Zendosays:

November 4, 2013 at 9:58 pm Edit

Though I`m late comer and rarely post any comments here, your website is much better than many others. Firsts, I was suspicious about your name brand–TheHabesh name– which excludes many Ethiopian nationalities except Amharas and Tigrians groups. I thought an inclusive name would have conveyed the message better to majority of Ethiopian, but it is too late at this juncture. Second, If your website refrains from the negatives of religious hyperbole as some polarizing other sites are doing, especially about Ethiopian Muslims, your site reputation will only increase over time thereby attracting many decent readers. Thanks you guys and good luck for your hard works

Reply

quaraw k5says:

November 5, 2013 at 5:57 am Edit

If yoy really need opinion of your readers. it should be confidential and not in public .if it’s help !!! Any way I like your hard work keep it up bro

Reply

Lej.Mesfinachew Anteneh AKassasays:

November 5, 2013 at 10:04 am Edit

Ze Habeshoech,

I comment rearly and when I do it is in your website, because you provide good source of information and fair selection of comments.Keep up the good work do not always listen to the flock, there are moments the flock could be misgiuded and can end up misguiding you, free thinking is a choice and there are flocks who are scared of this and judge you thier ennemy. what is not apealing to you can be of benefit to others.Give a fair chance to free thinking comments as well.

Thank you I like your work.

Lej.Mesfinachew Anteneh AKassa.

Reply

henoksays:

November 5, 2013 at 12:13 pm Edit

Zehabesha website is the number one choice news media for me for the last three years, compare with other ethiopian related media website, because of well balanced and accommodate all kind of views. Also the most abated and brought true professionalism way of informing to our people! I hope your good work will continue and there are many backwards media are exist for ex ecdaform with full of old school thinkers. All the best zehabesh we love you.

Reply

peacefullsays:

November 5, 2013 at 12:29 pm Edit

Ze-Habesha is the most reliable news source for Ethiopians. I am very pleased with your job. The only problem is with Ze-Habesha magazine. Be on time. It is very informative magazine. I do not think it is a big deal of posting the magazine on time. Previously, I mentioned to the chief editor but no improvement is shown.

Keep up the good job !!!

Reply

peacefullsays:

November 6, 2013 at 4:30 am Edit

Ze-Habesha,

Please read my above comment as “Ze-Habesha Newspaper” instead of “Ze-Habesha magazine”. Sorry!

Talking about magazine, what happened to Madina magazine used to be issued by Ze-Habesha fellows? It was the best Ethiopian magazine in the U.S. Please continue.

Thanks.

Reply

Fairsays:

November 6, 2013 at 6:17 am Edit

Honestly speaking, at the beginning I have never expected fair information from name Zehabesha as this name was used by first class Ethiopianist who want Ethiopia to serve them but doesn’t want to see the people on that earth. I found Zehabesha fair online media as it tries to entertain divers views and opinions. I understand there is massive pressure from self claimed first class ethiopianst who are a curse for that land and rebuffed by majority. At this rate, Zehabesha editor will be a unique person next to Walelign from Abyssinians camp who is naturally gifted to think as human being. Good job. I wish you all the best.

Reply

Tazabisays:

November 6, 2013 at 2:29 pm Edit

የዘ-ሃበሻ ተከታታይ ነኝ ጥሩ የዜና ምንጭ ነው። ከዚህ ውጪ ተጨማሪ አስተያየት አለኝ

– ማድረግም ሆነ ጽሁፎች መምረጥ አይቻልም እና አስተካክሉት

– እንደ ጋዜጠኛ ከሃገር ቤት ዜና ስትሰማ የሚመለከታቸውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ሞክር ቢቻል እየቀዳሃቸው መልሳቸውን አሰማን። አድራሻቸውን እና ስማቸውን መጥቀስ ሳትረሳ

– ከፖለቲካ ውጪ ከማህበራዊ ሚዲያዎች ኢትዮጲያውያን የሚያካፍሏቸውን አሪፍ ቪዲዮዎች እያካተትክ መዝናኛነቱን ጨመር አርገው

– ከታዋቂ ሰዎች ጋር ቃለመጠይቅ ለማድረግ ሞክሩ

Reply

Tazabisays:

November 6, 2013 at 2:30 pm Edit

የዘ-ሃበሻ ተከታታይ ነኝ ጥሩ የዜና ምንጭ ነው። ከዚህ ውጪ ተጨማሪ አስተያየት አለኝ

– Right click ማድረግም ሆነ ጽሁፎች መምረጥ (Select) አይቻልም እና አስተካክሉት

– እንደ ጋዜጠኛ ከሃገር ቤት ዜና ስትሰማ የሚመለከታቸውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ሞክር ቢቻል እየቀዳሃቸው መልሳቸውን አሰማን። አድራሻቸውን እና ስማቸውን መጥቀስ ሳትረሳ

– ከፖለቲካ ውጪ ከማህበራዊ ሚዲያዎች ኢትዮጲያውያን የሚያካፍሏቸውን አሪፍ ቪዲዮዎች እያካተትክ መዝናኛነቱን ጨመር አርገው

– ከታዋቂ ሰዎች ጋር ቃለመጠይቅ ለማድረግ ሞክሩ

Reply

Bonsasays:

November 7, 2013 at 5:17 am Edit

To be honest, you come close to what I call a genuinely ETHIOPIAN media. You put out news as they come. I do not see too much bias in the origin or perspectives.

I have always hoped, rather dreamed, that a day will come when we come out of the chronic segregation disease where Amharas, Oromos, Tigres, Somalis etc, just talk in their own domain, without any exchange of view points with others. Ideally, we have as few as possible websites so that we all get exposed to divergent viewpoints, regardless of the inconveniences this might cause. It is only that way that we progressively get more and more united as a nation.

What is happening now is rather scary, groups talking their own members – preaching the convert. The way we exchange ideas and generate “political thoughts” is equivalent to in-breeding in “biology”. It is weird, it has to change. In that respect, you are doing much better than others.

Having said this, I do not see other well known Ethiopian websites and blogs in your “Ethio Newslinks”. For instance, where are Opride.com, Ayyaantuu.com, Gullelee Post.com, etc?. You must have had some criteria to exclude these and other pages, but then again you are inconsistent because I see OLF in the listing of opposition groups. Just get over it and aspire to become fully Ethiopian.

Best wishes

Reply

Tedlasays:

November 7, 2013 at 6:27 am Edit

I am Eritrean. I read your website almost daily. I appreciate your website for presenting balanced news. I can say it is web site of all “THE HABESHs”,be Ethiopians or Eritreans. Please continue the same.

Reply

GETACHEW REDAsays:

November 7, 2013 at 11:26 am Edit

From- GETACHEW REDA (Editor Ethiopian Semay):

You made me laugh when you asked readers an opinion about your website. Are you serious you respect readers and writers’ opinion?

I sent you two articles for post this year. One commentary was about Tamang Beyene, Islam and its history in Ethiopia. You decline to post it because you claimed you will not post comment in regard to Tamang. I asked you why. You reason was “it will weakened the struggle”. He is God or a king not allowed by opposition media for any critique

The other commentary sent to you to be posted was ድምፃችን ዛሬም ነገም የጎሹ ወልዴ ነው!” This was also focusing Ethi-WEritrea issue that Col. Goshu addressed Ethiopian legal argument opposing Western plots against Ethiopia. You decline to post it (My guess is it deals also with Ginbot 7 and Eritrea and decline to post it- because your Ginbot 7 was mentioned ), that too was declined to be post.

I asked you three times to provide me reason for your refusal. As an editor, you should have given me reason for it- be it- reasonable or not. But, you felt shy to give your reason- because -your reason seemd to be poor for response and declined from answering it. I am asking you still to come up with reason for your decision not to post it.

The sad thing is you give Shaabia agents like Amanuel Beademariam and Sofia (our enemies) many times repeatedly to insult our Ethiopia while you refuse to serve Ethiopian issue that opposed Shaabia and its clicks. I asked you why you decline to response. Are you shy to response because your answer might not be adequate for argument? Why are you asking readers here our comment about your webite when you know you are repressing Ethiopian voices? Your OLF, ONLF, EPLF readers will love to hear your action against Ethiopian voices- because, that is what they are looking for. A subversive media! You still need to answer it why? Check your email for evidence. Boy! you are only fooling yourself, not me. If you are Ethiopian, serve Ethiopians not anti Ethiopian groups. Do nor be a subversive agent for them.

Thanks Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com

Reply

peacefullsays:

November 8, 2013 at 7:26 am Edit

Getachew Reda,

You are blaming Ze-Habesha for declining your articles. On the other hand, you have your own website/blog and you never treated any other openions other than yours (EPRPS). Ask yourself before blaming other. Do you really post an article if I write you about Our hero Tamagne? Have you ever mentioned about Ethiopian Muslims movement. All you are doing is posting negative aticles, back biting and proofless videos in your closed door website. Be out of your box first, Semay man. You are still on “Semay”. You think you are the only one who loves Ethiopia and struggles for Ethiopian. Loving Ethiopian is not just liking Ethiopian Semay only but loving Ethiopian people first. Boy! Land on Ethiopian earth and face the reality and start to like people. The problem with you and your fellow is that no say or write about Ethiopian struggle but your.group. Do you really beleive in FREEDOM OF SPEACH? ask youself.

Reply
https://amharic-zehabesha.com/contact-us
ስለ እኛ
Get to know more about ZeHabesha

Zehabesha.com is an extensive Ethiopian news source. We provide balanced news, perspectives, and issues across the political spectrum to the Ethiopian community and are committed to separating news and views while covering broad areas of health, education, politics, entertainment, and sports, and its editorial section is committed to advocating for Democracy and Human Rights.

We're here for one reason to provide fair and unbiased information to the community and is committed to separating news and views while covering broad areas of health, education, politics, and sports. Zehabesha.com pages are dedicated to informing its readers, and its editorial section is committed to advocating various philosophies and positions regarding the community.  While Zehabesha.com endeavours to take reasonable care in preparing and maintaining the information on this website we do not warrant the accuracy, reliability, adequacy or completeness of any of the website content. The website content is subject to change at any time without notice and may not necessarily be up to date or accurate at the time you view it. This site contains copyrighted material the use of which has not always been specifically authorized by the copyright owner.

We hope you enjoy the amharic.zehabesha.com and welcome any feedback.  Please send any comments and questions to us @    admin@zehabesha.com

Alyou Tebeje is the founder and executive editor of the amharic.zehabesha.com, mahderetena.com, also in the past administered Kinijit North America, Kinijit, Andinet Party and Finote Netsanet Websites.
https://amharic-zehabesha.com/about-us
የኮንጎ፣ የኮሪያ ዘማቾች እና የኢትዮጵያ አብዮታዊ ሰራዊት ሁሌም በክብር ሊዘከሩ፣ ሊታወሱ  ይገባቸዋል!!
አገርህን ጠላት እንዳይደፍራት ወታደር ሆነህ ጠብቃት፣ እንደ አባቶችህ ጀግና ሆነህ አሳያት፣ በጀግንነት ታሪክ ሥራላት። ታሪክ ያለው ከወታደርነት ነው፣ ጀግንነት ያለው ከወታደርነት ነው። ጀብዱ ያለው ከወታደርነት ነው፣ ታላቅ ስም ያለው ከወታደርነት ነው…።›› የሚል የአባቶቻችን የጀግንነት የአደራ ቃል ውርስ አለን እኛ ኢትዮጵያውያን፡፡

በርግጥም ደግሞ ታሪካችንን ስንፈትሽም- ታላቁ የዓድዋ ድል የአርበኝነት፣ የወታደርነት ውጤት ነው፡  የአምስት ዓመቱ የጣልያን ወረራና የኢትዮጵያዊያን ድል የወታደርነት ውጤት ነው፡፡ ካራማራ የወታደርነት ውጤት ነው፣ የኢትዮጵያ የተከበረ ታሪክ የወታደር ታሪክ ነው፡፡ ለምን ሲባል ኢትዮጵያ የተከበረችው በጀግኖች ልጆቿ፤ በወታደሮች ብርቱ ክንድ ነውና፡፡

ዛሬ እኔም፣ አንተም ሁላችንም የቆምንባት የኢትዮጵያ ምድር በቀደሙ ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ደምና አጥንት መሠረትነት የተገነባ ነው፡  ታሪክ እንደሚነግረን በኢትዮጵያ ጉዳይ ሁሉም አርበኛ፣ ሁሉም ጦረኛ ነው፡፡ ሁሉም ሰንደቁን አስቀድሞ ይገሰግሳል፡፡ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን በየዘመናቱ ጀብዱ እየሠሩ ዛሬ ላይ ኮርተን የምንኖርባት አገር፣ ኮርተን  የምንናገረው፣ በአሸናፊነት የምንመሰክረው ታሪክ አኑረውልናል፡፡

ከጉንደት እስከ ጉራዕ፣ ከዓድዋ እስከ ማይጨው፣ ከኦጋዴን እስከ ካራማራ… ያበበ የኢትዮጵያውያን ጀግንነትና እምቢ ለነፃነቴ ባይነት፣ የኢትዮጵያ ድንበር ሳይገድበው አውሮፓ ምድር ሮም/ጣሊያን ድረስ ተሻግሮ ዓለምን ያስደመመ፣ በኮሪያ ልሣነ ምድር፤ በአፍሪካ (በኮንጎ፣ በሩዋንዳ፣ በቡሩንዲ፣ በላይቤሪያ፣ በሱዳንና በሶማሊያ ምድር የኢትዮጵያ ሰራዊት በተጋድሎ ድልና በሰላም አስከባሪነት ትልቅ ስምና ዝናን ያተረፈ ነው።

እነዚያ ጀግኖች ታሪክ ሠርተው፣ ስማቸውን ከመቃብር በላይ ትተው ‹አገሩን ያስደፈረ ታሪክ ይውቀሰው፣ አፅማችንም እሾህ ሆኖ ይውጋው› ብለው ቃል ኪዳን አስረው፣ አደራ ሰጥተው በክብር አልፈዋል። ትናንትና በመስቀል አደባባይ ለ116ኛ ጊዜ በተከበረው የመከላከያ ሰራዊት ቀን በኮንጎና በኮሪያ ዘምተው ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ በጀግንነትና በድል ከፍ ያደረጉና በክብር ያስጠሩ  አባቶቻች ተዘክረው ነበር። በወታደራዊ ሰልፍ ትርዒትም /Military Parade/ ዐይተናቸዋልና ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ክብር ተሰምቶናል። ታሪካችን ምልዑና የተከበረ  ማድረግ የምንችለው  ትናንትናን ጥለን ዛሬን አንጠልጥለን አይደለምና የኢትዮጵያን በነጻነትና በሉዓላዊነቷ አስከብረው ያቆዩልንን የትናንትና ጀግኖቻችንን ሁሌም በክብር ልንዘክራቸው ይገባል፡፡

በዚህ የጀግንነት ገድል ታሪክ ውስጥ ደማቅ ታሪክን አሻራ ከተዉ ኢትዮጵያውያን መካከል- ከበርካታ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ታላቅ አኩሪ ታሪክን ለሀገሩ ያስመዘገበውን አርበኛውንና በተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ በመሆን ኮንጎ ድረስ የዘመተውን የወላጅ አባቴን አኩሪ የታሪክ ቅርስ ፎቶዎች ላጋራችሁ ወድድኹ፡፡

ምስሉ የኢትዮጵያዊው ጀግና አርበኛ እና በኮንጎ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ሆነው ያገለገሉትና እስከ በሕይወታቸው እልፈት ድረስም በጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር በጸሐፊነት ያገለገሉት ወታደራዊ መኮንን፣ አርበኛው፣ የመ/አ ወርቁ ደስታ ምስሎች ናቸው፡፡
https://amharic-zehabesha.com/archives/186725
https://www.youtube.com/live/2U39Q9h9ZaA?si=dIE-Lw95mGfuSvah

ይህ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ ትርክቶችን አስመልክቶ ሶስተኛውና የመጨረሻው ውይይት ሲሆን፣ በውይይቱም፤ 1) የሕገ መንግሥት ለውጥ ማድረግ፤ 2) የትምህርት ሥርዓቱ፤ ትምህርት ቤቶችና የከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች በየደረጃው በመፍትሄነት ሊጫወቱ በሚችሉት ሚና ከአፍ መፍቻ ቋንቋ ሌላ፤ አንድ ብሔራዊ ቋንቋና አንድ ወይም ሁለት ብዙ ሕዝብ የሚናገርባቸው ቋንቋዎች እንዲማሩ ማድረግ ዘር ተኮር ጥላቻን በማስወገድ ስለሚኖረው አዎንታዊ ሚና፤ 3) የጂኦግራፊንና የልማትን መርህ መሠረት ያደረገ አስተዳደር፣ ካንድ ወይም ከዚያ በላይ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ሊያካትት በሚችል የሚዘረጋ አስተዳደራዊ አወቃቀር፤ በቋንቋ ላይ የተመሠረተው የአስተዳደር ሥርዓት በክልልና ክልል መካከል የሚያስከትለውን የወሰንና የይገባኛል የጠብ ምክንያቶችን የማስወገድና የመቀነስ እንዲሁም የጋራ ሥነ ልቦናን በማዳበር የሚኖረው ሚና፤ 4) ሀገር በቀል ባሕላዊ ዕውቀቶች፣ ሽምግልና፤ ሃይማኖታዊ ተቋሞች ወይም ዘመናዊ ሲቪክ ድርጅቶች በሚያበረክቱት አዎንታዊ ተግባር ይህንን የዘር ጥላቻና ክፍፍል ለማቀዝቀዝ የሚኖራቸውን ሚና የዳሰሰ ውይይት ነው፡፡ የቀደሙት ዌብናሮች፤ Webinar 1: ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ ትርክቶች መቸና እንዴት ተጀመሩ? https://youtu.be/ahCDr_7KSvU Webinar 2: ትርክቶቹ ያስከከተሉት ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበረሰባዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳቶች https://youtube.com/live/9Cz0ff7Y1tI Contents -- TIMESTAMPS -- 00:00 Dr. Dr. Badege Bishaw, Moderator 00:05:03 Dr. Erku Yimer, Opening Remarks 00:12:10 Dr. : Prof. Mulatu Wubneh, የጂኦግራፊንና የልማትን መርህ መሠረት ያደረገ፣ ካንድ ወይም ከዚያ በላይ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ሊያካትት በሚችል የሚዘረጋ አስተዳደራዊ አወቃቀር፤ እንደ መፍትሔ፣ 00:45:17 Attorney Dereje Demissie, የሕገ መንግሥት ለውጥ ማድረግ የሚኖረው ፋይዳ 01:15:46 Prof. Messay Kebede, አማራ ያልሆኑ ፖለቲካ መሪዎችና ልሂቃን ፖለቲካዊ አስትሳሰባቸውንና ጥቅማቸውን በፀረ አማራነትና በፀረ ኢትዮጵያዊነት እንዴት ሊገልጹ ቻሉ? 01:46:07 Prof. Solomon Gashaw, ፀሀገር በቀል ባሕላዊ ዕውቀቶችና ፣ ዘመናዊ ሲቪክ ድርጅቶች ለሃገር ግንባታ በሚያበረክቱት አዎንታዊ ተግባር 02:16:53 Prof. Getachew Metaferia, Discussion and, Question and Answer 03:54:05 Dr. Erku Yimer, Closing Remarks About Ethiopiawinnet: Ethiopiawinnet website: https://ethiopiawin.net/ Ethiopiawinnet@gmail.com Telegram: https://t.me/ethiopiawinnetaa Facebook : https://www.facebook.com/ETHIOPIAWINN... Twitter: https://twitter.com/ethiopiawinnet Support Ethiopiawinnet Bank account: Ethiopiawinnet CDCR Dashen Bank Account No. 0155219603011
https://amharic-zehabesha.com/archives/186818

Saturday, October 28, 2023

የአማራ የሕልውና ትግል ላማረኛ ቋንቋ የከፈተው ትልቅ ዕድል
ሳይደግስ አይጣላም

አማረኛ ቋንቋ ማናቸውንም ነገር በቀላሉ ለመገለጽ የሚያስችል እጅግ በጣም ቀና፣ ቅን፣ ተጣጣፊና፣ በዚያ ላይ ደግሞ ውብ ቋንቋ ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር ደግሞ አማረኛ እንዳበጁት የሚበጅ ድንቅ ቋንቋ ነው።  ይህን እንዳበጁት የሚበጅ ድንቅ ቋንቋ በስርዓቱ በማበጃጀት፣ እንግሊዘኛን ጨምሮ ዐበይት ከሚባሉት ከማናቸው የዓለም ቋንቋወች ጋር አቻ እንዲሆን ብቻ ሳይሆን እንዲበልጥም ማድረግ ይቻላል።   አማረኛ የሚበጃጀው ደግሞ የቆሸሸውን በማጽዳት፣ የተሳሳተውን በማረም፣ የተዘበራረቀውን በማደረጃጀትና አስፈላጊወቹን አዳዲስ ቃሎች በመፍጠር ነው፡፡  አስፈላጊወቹን ቃሎች ለመፍጠር ደግሞ ግእዝን የሚያህል ተቀድቶ የማያልቅ የቃላት ምንጭ አለው።

ዐረብኛን ከተለያዩ ቋንቋወች ጋር በማዳቀል ትናንት የተፈጠረው፣ የላቲን ፊደል የሚጠቀመው መናኛው የስዋሂሊ ቋንቋ የምሥራቅ አፍሪቃ ወል ቋንቋ (lingua franca) ለመሆን ሲበቃ፣ አፍሪቃዊ ፊደል ያለው፣ እንዳበጁት የሚበጀው ታላቁ የአማርኛ ቋንቋ ግን ድንበር ሊሻገር ያልቻለው፣ የጦቢያን ቢሮክራሲ ባብዛኛው የተቆጣጠሩት፣ አማረኛን እጅግ አምርረው የሚጠሉት የትግሬና የኦሮሞ ልሂቃን አንቀው ስለያዙት ብቻና ብቻ ነው፡፡  ከነዚህ የኦሮሞና የትግሬ አማራ ጠሎች ጋረ በመተባበር አማረኛን የሚወጉት ደግሞ ባማረኛቸው እንዲያፍሩ ተደርገው ጥራዝ ነጠቅ እንግሊዘኛ መፃፍና መናገርን ከምሁርነት የሚቆጥሩት የነ ዋለልኝ መኮንን ግርፎች ናቸው።

በደርግ ዘመን የአማረኛ ትምህርት ከዩኒቨርስቲ እንዲወገድ ያደረጉት አማራ ጠሎቹ የትግሬና የኦሮሞ ልሂቃንና የነሱ አጫፋሪ አማራ ተብየወች ነበሩ፡፡  ለምሳሌ ያህል በ1976 ዓ.ም የፍልስፍና ትምህርት ባዲሳባ ዩኒቨርሲቲ ባማረኛ ተሰጥቶ አመርቂ ውጤት ቢያስገኝም፣ አማራ ጠሎቹ የትግሬና የኦሮሞ ልሂቃን እንዲሁም አማራ ነን ባይ አጫፋሪወቻቸው  ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስተው ትምህርቱ ባማረኛ መሰጠቱ እንዲቀር አድርገዋል፡፡  በኦነግ ዘመን ደግሞ የጭራቅ አሕመድ የትምህርት ሚኒስቴር የሆነው ብርሃኑ ነጋ አማርኛ ቋንቋ በትምህርት ዐይነት ደረጃ እንኳን እንዳይሰጥ ከፍተኛ ዘመቻ ጀምሯል።  ይህን ዘመቻውን የጀመረው ደግሞ በራሱ ባማራ ክልል ውስጥ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ነው።

በሌላ በኩል ግን ሳይደግስ አይጣላምና የአማራ ሕዝብ ሊያጠፉት የተነሱትን ወያኔና ኦነግን በማጥፋት ሕልውናውን የማስጠበቅ ዘመቻውን እንደ ሰደድ እሳት አቀጣጠሎ ያያቶቹን መሬት ከፀራማሮች እያፀዳ ነጻ ማውጣት ጀምሯል።  ስለዚህም በነዚህ ነፃ በወጡ ቀጠናወች ውስጥ ኦሮሞ ወይም ትግሬ ይቀየማል ብሎ ሳይሰጋ ወይም ደግሞ ይሉኝታ ሳይሰማው እንግሊዘኛን ሙሉ በሙሉ ባማረኛ በመተካት ልጆቹን ሙሉ በሙሉ (ሁሉንም የትምህርት ዐይነቶች) ባማረኛ እያስተማረ እንደ ጃፓንና ኮርያ አገሩን በፍጥነት የሚያሳድግ ትውልድ በፍጥነት የመፍጠር ትልቅ ዕድል ተከፍቶለታል።  ይህ መቸም የማይገኝ ዕድል ሊያመልጠው ስለማይገባ ደግሞ እስክንድር ነጋንና ዘመነ ካሴን ጨምሮ ሁሉም ያማራ ሕዝባዊ ትግል አመራሮች በፍጥነት ሊተገብሩት ይገባል።

እንግሊዘኛ እንግሊዞች በቅኝ ወረራ ዓለም አቀፍ ቋንቋ እንዲሆን ያደረጉት፣  ውስጡ ለቄስ የሆነ፣ በግድ እንጅ በውድ ሊመረጥ የማይችል ቅጥ ያጣ ቋንቋ ነው፡፡  በተለይም ደግሞ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ለሰገል (science) እና ኪንሲን (technology) ሊያገለግል የቻለው አመቺ ሁኖ ሳይሆን በዓለም ልሂቃን ያላሰለሰ ድካም ነው፡፡  ስለዚህም የአሜሪቃ ኃያልነት ሲያከትም፣ የእንግሊዘኛም ዓለም አቀፍ ቋንቋነት እንደሚያከትም ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡  ለምሳሌ ያህል እንግሊዞኝ የዜሌንስኪ (Zelensky) ቀንደኛ ደጋፊወች የሆኑት ለዩክሬን ሕዝብ አስበው ሳይሆን፣ ራሺያ ድል አድርጋ የምዕራባውያንን የበላይነት ላንዴና ለመጨረሻ ከሰበረች፣ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲሁም የራሷ የእንግሊዝ አገር የመጨረሻው መጀመርያ (the begining of the end) መሆኑን በርግጠኝነት ስለሚያውቁ ነው፡፡

የፈረንጅ ቅጥቅጦች የሆኑት የትግሬና የኦሮሞ ልሂቃን እንግሊዘኛን አመለኩ አላመለኩ፣ የአማራን ሕዝብ የማይመለከት የነሱ የራሳቸው ጉዳይ ነው፡፡  ባማንነቱ የሚኮራው የአማራ ሕዝብ ግን የሱ የራሱ የሆነ፣ እንዳበጁት የሚበጅ ምርጥ ቋንቋ እያለለት፣ ሳይቸግረው ጤፍ እየተበደረ፣ ፈረንሳይ ሲነግስ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝ ሲነግስ እንግሊዘኛ፣ ቻይና ሲነግስ ቻይንኛ እየተጠቀመ ከቋንቋ ቋንቋ የሚንጦለጦልበት ምንም ምክኒያት የለውም፡፡

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

https://amharic-zehabesha.com/archives/186722

እነዚያ ጀግኖች ታሪክ ሠርተው፣ ስማቸውን ከመቃብር በላይ ትተው ‹አገሩን ያስደፈረ ታሪክ ይውቀሰው፣ አፅማችንም እሾህ ሆኖ ይውጋው› ብለው ቃል ኪዳን አስረው፣ አደራ ሰጥተው በክብር አልፈዋል።

ትናንትና በመስቀል አደባባይ ለ116ኛ ጊዜ በተከበረው የመከላከያ ሰራዊት ቀን በኮንጎና በኮሪያ ዘምተው ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ በጀግንነትና በድል ከፍ ያደረጉና በክብር ያስጠሩ አባቶቻች ተዘክረው ነበር። በወታደራዊ ሰልፍ ትርዒትም /Military Parade/ ዐይተናቸዋልና ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ክብር ተሰምቶናል። ታሪካችን ምልዑና የተከበረ  ማድረግ የምንችለው  ትናንትናን ጥለን ዛሬን አንጠልጥለን አይደለምና የኢትዮጵያን በነጻነትና በሉዓላዊነቷ አስከብረው ያቆዩልንን የትናንትና ጀግኖቻችንን ሁሌም በክብር ልንዘክራቸው ይገባል፡፡

በዚህ የጀግንነት ገድል ታሪክ ውስጥ ደማቅ ታሪክን አሻራ ከተዉ ኢትዮጵያውያን መካከል- ከበርካታ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ታላቅ አኩሪ ታሪክን ለሀገሩ ያስመዘገበውን አርበኛውንና በተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ በመሆን ኮንጎ ድረስ የዘመተውን የወላጅ አባቴን አኩሪ የታሪክ ቅርስ ፎቶዎች ላጋራችሁ ወድድኹ፡፡

ምስሉ የኢትዮጵያዊው ጀግና አርበኛ እና በኮንጎ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ሆነው ያገለገሉትና እስከ በሕይወታቸው እልፈት ድረስም በጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር በጸሐፊነት ያገለገሉት ወታደራዊ መኮንን፣ አርበኛው፣ የመ/አ ወርቁ ደስታ ምስሎች ናቸው፡፡
https://amharic-zehabesha.com/archives/186725
ሽብርተኛው የኦህዴድ መንግሥት ፋኖን “ሽብርተኛ” ብሎ ሲከስ መላው ዓለም ታዝቦታል፤ንቆታል
አክሎግ ኢራራ (ዶር)

ቅዳሜ October 21, 2023, Tri-State የተባለው ቡድን ባካሄደው ውይይት ተጋብዠ ለብዙ ዓመታት የማውቀው ወዳጀ፤ አገር ወዳዱ ኢትዮጵያዊ እንጂኔር ግደይ ዘራጽዮን ያቀረበውን ማራኪ ትንተናና ምክረ ሃሳብ አዳምጨ ነበር። እንጂኔር ግደይ ከተነተናቸው አርእስቶች መካከል “የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት፤ የፋኖ የህልውና ትግል፤ የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና አስጊ ሁኔታ፤ በተለይ እየሻከረ የሄደው የኤርትራና የኢትዮጵያ መንግሥታት ግንኙነት፤ የትግራይ ክልል ወቅታዊ ተግዳሮቶች” ይገኙበታል።

ኢንጅኔር ግደይ ስለ ፋኖ መነሻና መድረሻ ያቀረበው ትንተና ምክንያታዊና በመረጃ የተደገፈ ነበር። የዐብይ መንግሥት እንደሚሰብከው ሳይሆን፤ ፋኖ የቆመው “ለፍትህ፤ ለነጻነት፤ ለዜጎች እኩልነት፤ ለብሄራዊና ግዛታዊ አንድነት፤ ለዲሞክራሲ” መሆኑን አስምሮበታል። እነዚህ የመላው ኢትዮጵያዊያን ምኞቶችና ተስፋዎች ናቸው።

አማራው ፋኖን የሚደግፍበት መሰረታዊ ምክንያት “የፖለቲካና የኢኮኖሚውን የበላይነት መልሶ ለመያዝ ነው” የሚለውን የፈጠራ ትርክት ሲተች እኔም የምጋራውን “ከአሁን በኋላ በምንም መልኩ ኢትዮጵያን አንድ ብሄር/ዘውግ ሊገዛት አይችልም” ወደሚል ድምዳሜ ደርሷል፤ ደርሰናል። በሌላ አነጋገር፤ እብርተኛው ህወሓት ጀምሮ የፈረሰውና አሁን ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ አሊ በኦሮሞው ሕዝብ ስም “ከአሁን በኋላ የመግዛትና የመብላት ወቅቱ የኛ (ኼኛ) ነው” የሚለው እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን ሊያፈርሳት ጫፍ ላይ ደርሷል።  ይህ ግንዛቤ ትክክል ነው። ህብረ-ብሄራዊነት፤ እኩልነት፤ አንድነት፤ ፍትህና ዲሞክራሲ በአንድ በኩል፤ በሌላ በኩል የአንድ ዘውግ የበላይነት (የኦሮሞ ኼኛነት) አብረው ሊሄዱ አይችሉም።

“ኼኛ፤ የኛ” ተራ የሚለው አደገኛ የዘውግ የበላይነት (Absolute Oromo Hegemony) እንቅስቃሴ ሁሉንም ይደፈጥጣል፤ ያመክናል። እንጂኔር ግደይ “እኔም ፋኖ ነኝ” ብሎ ሲናገር ለይስሙላ ወይንም ለመወደድ አይደለም። ምክንያት አለው። ፋኖ የሚታገለውና የአማራው ሕዝብ ከፍተኛ መስዋእት በመክፈል ላይ የሚገኘው፤ መልሶ ሥልጣን ለመያዝ አይደለም።   “መልሶ ሥልጣን ለመያዝ ነው” የሚለው ኦነጋዊያንና ህወሃታዊየን እስከሚሰልች  ድረስ የሚያስተጋቡት የጸረ-አማራው ትርክት አካል ነው። መብቴ ይከበር፤ ፍትህ ይኑር ማለትና “የኔ ዘውግ ብቻ ይግዛ” ማለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። አማራው “የኔ ብቻ ወይንም ኼኛ” ብሎ አያውቅም።  የአማራው ሕዝብ አንዱ የሚለይበት ከሌላው ብሄር፤ እምነት ጋር የመኖር ችሎታው ነው።

የፋኖውና ደጋፊዎቹ ጥሪ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለእኩልነት፤ ለነጻነት፤ ለፍትህ፤ ለአንድነት፤ ለዲሞክራሲ፤ ለአገራዊ እርጋታ የመቆም ግዴታ አለባቸው የሚል ነው። “እኔም ፋኖ ነኝ” ብየ የምከራከረው እነዚህ መሰረታዊ እሴቶች ስኬታማ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ጽኑ እምነት ስላለኝ ነው። በኢትዮጵያ ዘላቂነት፤ ሉዐላዊነት ኢትዮጵያዊነት የሚያምን ሁሉ ሌላ አማራጭ የለውም። ስድስት ሚልየን የሚገመተው የአዲስ አበባ ሕዝብ ዝም ብሎ በኔ ላይ አይደርስም ከሚል ይልቅ፤ ለፍትህ የሚካሄደውን ትግል መቀላቀል አለበት። “ያልጠረጠረ  ተመነጠረ” እንዲሉ እልቂቱ የአዲስ አበባን ሕዝብም አይምርም።

የፍትህ ትግሉን ስኬታማ ለማድረግ የሚቻለው ግን፤ ሁሉም በዜግነት መብትና ሉዓላዊነት የሚያምኑ፤ ለዘላቂ ሰላምና ፍትህ የቆሙ ፋኖ መሰል እንቅስቃሴዎች ሲጀምሩና በአገር  ደረጃ ለማቀነባበር ሲችሉ ነው። የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ማህበረሰባዊ ስብስቦችም አብረውና ተገናዝበው የሚሰሩበት ወቅት አሁን ነው።

ይህ የፋኖ ብቻ ሃላፊነት አይደለም። በአማራው መስዋእት ብቻ ኢትዮጵያን፤ ፍትህን፤ ሰብአዊ መብትን ለመታደግ አይቻልም።

ህወሓት፤ ኦነግ፤ ኦህዴድ፤ ኦነግ ሸኔ፤ የኦሮሞ ብልጽግናና በዘውግ ፖለቲካ የታነጹ ኃይሎች ሁሉ ከላይ የጠቀስኳቸውን እሴቶት ስኬታማ ለማድረግ ፍላጎትም፤ እምነትም የላቸውም። ቢኖራቸው ኖሮ፤ ባለፉት ሰላሳ ሁለት ዓመታት ብቻ የተከሰተውን አገር አፍራሽ እልቂትና ውድመት ሊያቆሙት ይችሉ ነበር።  የፖለቲካ ፈቃደኛነትና ቅንነት ቢኖራቸው ኖሮ፤ በሰሜኑ ጦርነት ብቻ አንድ ሚልየን የትግራይ ወገኖቻችን አይሞቱም ነበር፤ ከሶስት መቶ እስከ አራት መቶ ሺህ የሚገመት የአፋር፤ የአማራና ሌሎች ዘውግ አባላት አይሞቱም ነበር። ሃያ ስምንት ቢሊየን ዶላር የሚገመት ኢንቨስትመንት አይወድምም ነበር። የኦህዴድ መንግሥት የበላይ ሆኖ አገሪቱን አጣብቂኝ ውስጥ ያስገባው ዐብይ አሕመድና ቡድኑ ከዚህ አስከፊ ጦርነት ይማሩ ነበር።

ጥላቻውን፤ ቂም በቀልነቱን፤ እልቂቱን. ጦርነቱን፤ ውድመቱን ሆነ ብለው የፈጠሩት ራሳቸው የዘውግ ልሂቃን ናቸው። ችግሩን ለመፍታት ፈቃደኛ ይሆናሉ ብሎ ማሰብ ሞኝነትና አድርባይነት ነው። ምክንያቱም ተጠቃሚዎች ፈልፍለዋል። ከተጠቃሚዎቹ መካከል የብልጽግና ፓርቲ የሾማቸው፤ በሙሰኛነት የተበከሉ፤ ለተራው ወገናቸው ደንታ የሌላቸው ጀኔራሉች አሉ።

የዚህ መንግሥት መለያ የዘውግ ጥላቻን ማጠናከር፤ ከፋፍለህ ግዛውንና ብላውን ተቋማዊ ማድረግ፤ ሥልጣንን በኃይል ስኬታማ ማድረግ ወዘተ ነው። ስንት አገራዊ ወይንም ብሄራዊ ተቋም ነው የዘውግ ስርጭቱ በችሎታ ተሰርቶ ሚዛናዊ እና ኢትዮጵያዊያንን የሚወክል የሆነው? ተተኪነትና የበላይነት የሚጠይቀው የዘውግና የፖለቲካ ተአመኔታን ብቻ ነው (The guiding criteria for assignments is loyalty to tribe; and not competence or dedication to the service of Ethiopia and the Ethiopian people). ይህ ደግሞ የሞራል ልእልናን ይጠይቃል።

ፋኖ በምን ይለያል?

ለማንጻጸር፤ የፋኖ መለያዎች ብዙ ናቸው። ፋኖ ጦርነቱን አልፈጠረውም፤ አልጀመረውም። ፋኖ የኦሮሞን ህጻናት፤ ሴቶች፤ እናቶች አዛውንቶች አልጨፈጨፈም። ፋኖ ማንንም ከቀየው አላባረረም። ፋኖ ባንክ አልዘረፈም። ፋኖ የማረከውን ግዙፍ ብር መልሶ ያስረከበው ለሕዝቡ ነው። ፋኖ ዘውግ ሆነ እምነት ሳይለይ፤ የማረካቸውን ግለሰቦች በጨዋነት በመንከባከብ ላይ ይገኛል። ፋኖ መሰረተ ልማት አያወድምም። ፋኖ ሴቶችን አይደፍርም። ፋኖ አገሩን ኢትዮጵያን፤ በአገር ደረጃ እና የኢትዮጵዊነት መለያውን አልካደም። ፋኖ ሌሎች የታፈኑ፤ የሚሰቃዩ ወገኖቹን “ኑ፤ ተነሱ፤ አብረንና ተባብረን ለፍትህ” እንታገል፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ ናት” የሚል የተቀደሰ መርህ ይከተላል። ፋኖ በራሱ ፈቃድ የሚታገለው ለተቀደሰ ዓላማ ነው። ለግል ዝናና ጥቅም አይደለም። ይኼውም አንድ፤ የአማራውን ሕዝብ ከእልቂት ለማዳን፤ ሁለት ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለመታደግ።

ፋኖን የቀሰቀስው ምንድን ነው?  

- በአማራው ላይ የማያባራ እልቂት መካሄዱና መቀጠሉ፤

- በመንግሥት ደረጃ ባለፉት ሰላሳ ሁሉት ዓመታት አማራው ከፖልቲካው፤ ከኢኮኖሚው፤ ከማህበረሰባዊ እድገቱ፤ ከእምነቱ እንዲወገድ፤ ማንነቱና መለያዎቹ ሁሉ እንዲጠፉ መደረጉ፤

- በአማራው ሕዝብ ላይ የሚዘገንን የስም፤ የታሪክና የባህል ማጥፋት ዘመቻዎች በህወሃት መራሹና በኦነግ ወይንም በኦሮሞ ብልፅግና አገዛዝ መካሄዱ፤ “ነፍጠኛ፤ ትቢተኛ፤ ጡት ቆራጭ፤ ቅኝ ገዢ” ወዘተ። ይህ የስነ ልቦና ጦርነት አማራውን ጭራቃዊ ሕዝብ አድርጎታል።

- በዘመነ ዐብይ መንግሥት፤ ከላይ የጠቀስኳቸው ተባብሰዋል። ረገጣው፤ አፈናው፤ ግድያው፤ ማፈናቀሉና ውድመቱ የሚካሄደው በመንግሥት ደረጃ ነው። ይህ የዐብይን መንግሥት ከሌሎች አምባገነኖች ይለየዋል።

- በህወሃት የብሄር ጽንፈኞችና ሽብርተኞች በወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምትና ራያ የተፈጸመው የአማራ ሕዝብ ጭፍጨፋና ከቀየው መባረር በባሰ ደረጃ በወለጋ፤ ኦሮምያ፤ በቤኒ-ሻንግሉ ጉሙዝ፤ በሰሜን ሸውና በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለፉት አመስት አመታት ሲካሄድ ቆይቷል፤ አሁንም እየተካሄደ ነው። ከጀርባው ማን አለበት?

- የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት በአማራው ሕዝብ ላይ የሚካሄደውን ጭካኔ የተሞላበት እልቂትና እስራት አላቆመውም፤ ሊያቆመውም አይችልም። ሕገ መንግሥቱ የተመሰረተው ሕዝብን ከሕዝብ በመለያየት ነው።

- “አማራው ትግል የጀመረው ግዛትን ለማስፋፋት ነው” የሚለው ፈጠራ አይሰራም። አማራው በሚኖርበት አካባቢ እየተጨፈጨፈ እንዴት በመስፋፋት ይከሰሳል? በአማራው ክልል ላይ የሚዘገንን ጦርነት እየተካሄደና አንጹህ ወገኖቻችን በድሮን፤ በሞርታር፤ በታንክና ሌላ ከባድ መሳሪያ በዐብይ መንግሥት ትእዛዝ እየተጨፈጨፉ አማራው በግዛት መስፋፋት እንዴት ይከሰሳል። የግዛት መስፋፋት ስራን የሚሰራው የኦነባዊያን፤ የኦሮሞ ልዩ ኃይልና የፌደራሉ ባለሥልጣንት መሆናቸው በመሬት ላይ እየታየ ለፍትህ የሚታገለው የአማራ ሕዝብ ለምን ይከሰሳል? አጥፊው ከሳሽ፤ ተበዳዩ ተከሳሽ የሆነባት አገር ኢትዮጵያ ናት።

- ባለፉት ሰላሳ ሁለት ዓመታት፤ በትምህርት፤ በጤና አገልግሎት፤ በመሰረተ ልማት፤ በነፍስ ወከፍ ገቢ የአማራው ክልልና ሕዝብ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መሆናቸውን አልጀዚራ ባቀረበው ዘገባ ላይ ለማየት ይቻላል።

- ህወሃት ሥልጣን  ከያዘበት ጀምሮ የአማራው ሕዝብ ቁጥር እየቀነሰ ሂዷል። አማራው እስከ ስድስት ሚልየን የሚገመት ህዝብ አጥቷል። ይህ ሕዝብ የት ሄደ? ማርስ? ብየ የጠየቅሁበት ትንተና ትዝ ይለኛል።

- በ2019 ዩኤስ ኤድ (USAID) የአማራው ሕዝብ ቁጥር፤ ባልታወቀ ምክንያት መቀነሱን አረጋግጧል። የቀነሰብት  ምክንያት የጤን አገልግሎት ስለ ተነፈገው ነው? የአማራ ሴቶች እንዳይወልዱ ስለ ተደረገ ነው? በየቦታው በሚካሄደው የአማራ ብሄር ተኮር እልቂ ስለተካሄደ ነው? በኦሮምያ የሚኖሩ ከአስራ አንድ ሚልየን በላይ የሚገመቱ አማራዎች ማንነታቸውን እንዲክዱ ስለተደረገ ነው? ይህ ሰፊ ጥናትና ምርምር ይጠይቃል። አሁንም የሚካሄደው ጦርነት የአማራው ቁጥር ከመቀነስ ጋር የተያያዘ ነው የሚል እምነት አለኝ።

ለፋኖ እንቅስቃሴ መሰረታዊ የሆኑት ምክንያቶች ከላይ የተጠቀሱት ናቸው። ምክንያቶቹ ትግሉ የህልውና ትግል መሆኑን ያረጋግጣሉ። አማራው የሚጠይቀው አስኳል ጉዳይ የሥልጣን ሳይሆን የፍትህ ጥያቄ ሆኖ ሳለ ባለፉት ሰላሳ ሁለት ዓመታት ስላልተፈታና እንዲውም እየተባባሰ ስለሄደ ነው።

አጠናክሬ ለማሳሰብ የምፈልገው፤ ፋኖ የሚከተላቸው እሴቶችና የመጨረሻ ተልእኮው ያለ ከፍተኛ መስዋእት ስኬታማ ሊሆኑ አይችሉም። ፍትህ፤ ነጻነት፤ እኩልነት ዋጋ ሳይከፈል ስኬታማ የሆነበት አገር የለም። ፍትህ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው። ያለ ፍትህ “መደመር” እና ልማት አይታሰብም። ያለ አገር ወዳድነትና ፍትህ የአገር ዳር ድንበር አይከበርም። ያለ ፍትህ ሌላው ቀርቶ ከቤት ለስራ ወጥቶ በጤና፤ በሰላም ወደ ቤት ተመልሶ መግባት ብርቅ ሆኗል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ህይዎት ማጤን ይጠቅማል። ለዚህ ነው፤ የአዲስ አበባ ሕዝብ “በቃን” የሚልበት ወቅት አሁን ነው የምለው።

እትዮጵያ ወደ የት እያመራች ነው?

ኢትዮጵያ ዛሬ በሁሉም ዘርፎች የተበከለች አገር ናት። አቅጣጫዋ አያምርም። ኢትዮጵያ ወድቃለች ወይንስ አልወደቀችም? በሚል ብዙ ውይይት ይካሄዳል። አንድ አገር ወዳድ ወዳጀ በቅርቡ ያሉትን ምሳሌ ላድርግ። “እኔ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነቴ እንደ አሁኑ አፍሬ አላውቅም።” ያሳፈረን የሚዋዢቀው አመራርና ስርዓቱ ነው። ያሳፈረን የዐብይ ብልጽግና ፓርቲና መንግሥት ነው። ኢትዮጵያ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቷን ለመገምገም፤ በመሬት ላይ ያለው ሃቅ መነገር አለበት።

ዛሬ ኢትዮጵያ የእልቂትና የጦርነት እምብርት ሆናለች። የድህነት እምብርት ሆናለች። ወጣቱ ትውልድ የስራ እድል የለውም። ሰላሳ አንድ ሚልየን ሕዝብ ይራባል። አምስት ሚልየን ሕዝብ ተፈናቅሏል። መካከለኝ መደብ ተብለው የሚጠሩት ኑሯቸውን ለማሟላት አልቻሉም። የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሺፈት አብዛኛውን ሕዝብ በክሎታል። ይህ ብቻ አይደለም።

ከሜያዝያ ወዲህ ብቻ ከመቶ ሽህ በላይ አማራዎች ታስረዋል። ብዙ ሽህ የሚገመት ኦሮሞ ታስሯል። በጦርነቱ በድሮንና ሌላ ከባድ መሳሪያ የተጨፈጨፈው በቅጡ አይታወቅም።   ይባሰውን ብሎ ዐብይ አሕመድና ፊልድ ማርሻል  ብርሃኑ ጁላ ከወዳጅ አገር የኬሚካል መሳሪያ አስገብተዋል የሚል ዘገባ ተሰራጭቱል። ይህ እብድነት ከተካሄደ ዐብይ አሕመድ ሁለተኛው ግራዚያኒ ሆኗል ማለት ነው። ባጠቃላይ ስገመግመው ግን፤ “ኢትዮጵያ የእስር ቤትና የረሃብተኛ ሲዖል አገር ሆናለች” ቢባል ትክክል ነው።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ አሊ የሚመራው የኦነጋዊያን መንግሥት ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተጣልቷል ለማለት እደፍራለሁ። ይህ አገዛዝ የሚክደው ሃቅ አንድ ነው። የፈለገውን ያህል የጦር መሳሪያ ቢያከማች፤ የጦር ትርኢት ቢያሳይ፤ ከሕዝብ ጋር የተጣላ መንግሥት ብዙ ዋጋ ማስከፈሉ ባይቀርም ቅሉ፤ ህይዎቱ ግን አጭር መሆኑን ነው። የደርግ መንግሥት ምሳሌ ነው። የወያኔ ማንግሥት ሌላው ምሳሌ ነው። ክፍ አድርጌ ስገመግመው፤ ዓለምን በበላይነት አሸከረክራለሁ ብሎ የሚፎከረው የአሜሪካ መንግሥት ከአፍጋኒስታን ተሸንፎ የወጣው ሌላ ምሳሌ ነው። ሕዝብ የናቀው፤ የማያምነውና የማያከብረው መንግሥት ይወድቃል።

የፕሪቶሪያው ስምምነት ምን አወንታዊ ውጤት አስገኘ?

የአሜሪካ ባለሥልጣናት፤ የዐብይ አሕመድ መንግስትና ህወሃት ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም ሕዝብ የሰጡት ማዘናጊያ መልእክት ህወሃት መሳሪውን ይፈታል የሚል ነበር። ህወሃት ትጥቅ አልፈታም። ህወሃትና የኢትዮጵያ መንግሥት ትጥቅ ለፈቱትና በጦርነቱ ለተጎዱት የአፋር፤ የአማራና የትግራይ ወገኖቻችን የቁሳቁስ ድጋፍ አልሰጡም። እንዲያውም የሰብአዊ እርዳታውን ነጥቀውታል፤ ስርቀውታል፤ ለራሳቸው ቡድኖች አውለውታል።

ህወሃት ትጥቅ ያልፈታበት ዋና ምክንያት ወይንም ምስጥሪ ምንድን ነው?

ዐብይ አሕመድ ከጅምሩም ህወሃት ትጥቅ እንዲፈታ አልፈለገም። ዋናው ትኩረቱ አማራውን በሁሉም ዘርፎች አምክኖ፤ አምበርክኮ፤  ቢቻል ጨፍጭፎ የኦሮሙማን አጀንዳ ስኬታማ ማድረግ ስለሆነ ህወሃትን እንደ ስትራተጂክ አጋር ሲጠቀምበት ይታያል። በተጨማሪ፤  ለህወሃት ምን አይነት የውስጥ ቃል ኪዳን ተነግሮታል? ብለን መጠየቅ አለብን። ታዛቢዎችና የውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉትና እኔም እንደ ገመገምኩት፤ የዐብይ መንግሥትና የአማራው ብልጽግና የበላይ ካድሬዎች ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምትንና ራያን በሬፈረንደም አመካኝተው ለህወሃት ለመመለስ ተመሳጥረዋል። ካልተማማሉ ለወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠልመትና ራያ ህዝብ የማንነትና የሰባዊ መብት መከበር ጥያቄ፤ አወንታዊ መልስ ሊሰጡ ይገባል።

ጦርነቱ የተካሄደው ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ናት በሚል እምነት ነው። ዐብይ ለኢትዮጵየ “እቀላለሁ” ሲል ሰምቻለሁ። ይህ ከሆነ ኦነጋዊያን በበላይነት የሚመሩት የኢትዮጵ ፌደራል መንግሥት ሰራዊት ለምን መቀሌ አልገባም? የትግራይ ሕዝብ መብት ተከብሮ  ለምን የራሱን የሺግግር መንግሥት ለመምረጥ እንዲችል አልተደረገም? ዓብይ ሥልጣኑን እንዲያዝ ያመቻቸው ሕዝቡን ሳይሆን ለሱ ሥልጣንና የበላይነት ሊያገለግል ይችላል ብሎ ያመነንበትን አዲስ አገልጋይና ታዝዥ ህወሃትን ነው። ዐብይ ሁልጊዜም የሚኮተኩተውና ሥልጣን እንዲይዝ ጫና የሚያደርገው በታዛዢነቱ፤ በታማኝነቱ፤ በአገልጋይነቱ፤ በሆዳምነቱ የማያሻማውን ክፍል ብቻ ነው። በአማራው ክልል ስንት ፕሬዝደንት ተቀይሯል?” እነ ዶክተር አምባቸው መኮነንና ጀኔራል አሳምነው ጽጌ በምን ምክንያት ሞቱ? ማን ከጀርባ ሆኖ አስገደላቸው ወይንም እርስ በእርሳቸው እንዲገዳደሉ አደረገ? ሃቁ ይፋ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይመስለኝም።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከጽንሰ ሃሳቡ የተወላገደና የተጎዱቱን ክፍሎች የማይወክል ነው። አግላይ ነው። እርቅና ሰላም እንዲሰፍን ከተፈለገ የአፋር፤ የአማራና የኤርትራ ተወካዮች ተሳታፊ መሆን ነበረባቸው። ቢሳተፉ ኖሮ ስምምነቱን የማስፈጸም ግዴታ ይኖርባቸው ነበር። አለተሳተፉም፤ ግዴታ የለባቸውም ማለት ነው።

በህወሃትና በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ጦር ኃይል መካከል የሚካሄደው ጦርነት መቆሙ ሃቅ ነው። ይህንን በተናጥል ስናየው ስኬት ልንለው እንችላለን። ሆኖም፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት ዘላቂ እርቅና ሰላም አስገኝቷል ለማለት አልችልም።

የዐብይ ኦነጋዊያን መንግሥት ዋና ግቡ ኦሮሙማን መምስረት ነው። ኦሮሙማ ግን የእምቧይ ካብ መሆኑ አይቀርም። የአብይን አጀንዳ የሚቃወሙ ኦሮሞች፤ ጋሞዎች፤ ጉራጌዎች፤ ደቡቦች፤ አኟኮች፤ ትግሬዎች ወዘተ አሉ። እነዚህ ወገኖቻችን ቀስ በቀስ ፋኖ መሰል እንቅስቃሴና ሕዝባዊ እምቢተኛነት እንደሚቀሰቅሱ አምናለሁ። ጋሞውና ደቡቡ እኮ ፋኖን እየመረቀ ነው። ይህ የሆነበት ዋና ምክንያት፤ ፋኖ መንፈስ ስለሆነ፤ ፋኖ የነጻነት ተምሳሌት ስለሆነ፤ ፋኖ አገር ወዳድ ስለሆነ፤ ፋኖ የአማራው ሕዝብ የሚፈልገውና የሚታገለው፤ ፍትሃዊ፤ ህብረብሄራዊና ዲሞክራሳዊ የሆነች ኢትዮጵያን ለመመሰረት ስለሆነ ነው።

ፋኖ የሚታገለው ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይና ኦነጋዊያን ኢትዮጵያን በዓለም ደረጃ ስላዋረዷትና ዐብይ ጠቅላይ ሚንስትር ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ በበጎ ነገር ስትጠቀስ የሰማ ሰው ስለሌለ ጭምር ነው።

በህወሓት አመራርና በዐቢይ አህመድ መካከል የተካሄደው የፕሪቶሪያ ስምምነት በሕዝቦች መካከል እርቅና ሰላምን አስገኝቷል ለማለት አይቻልም። የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠልምትና ራያ የማንነት ጥያቄ አሁንም አልተፈታም። የትግራይ ሕዝብ ሮሮ ድምጽ እላገኘም። በሃላፊነት ለፍርድ የቀረበ የለም። የትግራይ ሕዝብ አሁንም ይታፈኗል፤ ይዘረፋል፤ ይራባል። የትግራይ እናቶች በሃዘን ላይ ናቸው። መዘዙ ለብዙ አስርት ዓመታት የሚቆይ ነው።

አሁንም እኔ የምጠይቀው፤ ጦርነቱ ለምን ተካሄደ? ለምን ብሄራዊ አላማ? ለማን ጥቅም? በጦርነቱ ለረገፉት ወገኖቻችን ተጠያቂው ማነው? የወደመውን ኢኮኖሚ ማን መልሶ እንዲያንሰራራ ያደርገዋል? ኢኮኖሚው እንዲያንሰራራ በማድረግ ፋንታ ለምን ጠቅላይ ሚንስትሩ የቅንጦት ቤተ መንግሥት በ 15 ቢልየን ዶላር ይሰራል? የፓርላማው ሃላፊነት ከምን ላይ ነው?

የዐብይ ስሌት የዜጎች መብት መከበር አይደለም። ስሌቱ አማራውና ትግራዩ እርስ በእርሱ እንዲዋጋና እንዲመክን ማድረግ ነው። ይህ ሲሆን የኦሮሞ ዘውጋዊ የበላይነት ስር ይሰዳል የሚል ስሌት ነው።

ከህወሃት ጋር የተካሄደውን የሚዘገንን የእርስ በእርስ ጦርነት እንደ ምእራፍ አንድ ብናየው፤ ምእራፍ ሁለት ህወሃትን የተካው የዐብይ አህመድ አሊ ብልጽግና በበላይነት የሚያሽከረክረው የኦህዴድ መንግሥት በአማራው ሕዝብ ላይ የሚያካሂደው እልቂት፤ ውድመትና አገር አፍራሺ ዘመቻ ነው።

ይህ ዘመቻ ግን ይከሽፋል። ምክንያቱም፤ ህወሃትም ሆነ ኦነጋዊያን አማራውን ለይተው ማሳደድና መጨፍጨፍ የጀመሩት ባለፉት አስርት ዓመታት ስለሆነ፤ አማራው ከዚህ አማራ ጠል ከሆነ እብሪተኛ፤ ዘረኛና ዘግናኝ ስርዓት ትምህርት ተገኝቷል። አማራው ከአሁን በኋላ እንደ ፈለጋችሁ “ልጀን፤ ሚስቴን፤ እህቴን፤ እናቴን፤ አባቴን፤ ቤቴን፤ መሬቴን፤ ክብሬን፤ ማንነቴን፤ ኃይማኖቴን” ወዘተ ልታመክኑ አልፈቅድም ብሎ ዳር እሰክ ዳር ተነስቷል።

ይህ እብሪተኛነት ይከሽፋል ያልኩበትን ምክንያቶች ላቅርብ፤

- የትግራይ ሕዝብፈቅዶና ተስማምቶ ወደ ሌላ ጦርነት ይሄዳል የሚል እምነት የለኝም። በተለይ፤ እንዳለፈው በፍላጎትና በስሜት ከአፋሩና ከአማራው ሕዝብ ጋር መዋጋት ከጥቅሙ ኪሳራው ያይላል የሚሉት ብዙ ናቸው። ይህ ማለት እብሪተኞችና ጠባብ ብሄርተኞች ለሌላ ጦርነት አልተዘጋጁም ማለት አይደለም። በአማራውና በትግራዩ ሕዝብ መካከል የተከሰተው ችግር በውይይት፤ በድርድር፤ በመቻቻል፤ በጋራ ጥቅም ሊፈታ ይችላልል። አማራጩ ጦርነት ሊሆን አይችልም።

- የአማራው ሕዝብ የሚታገለው ፈልጎና መርጦ አይደለም። በአንድነት ሆኖ በመዋጋት ላይ የሚገኘው በኦህዴድ እብሪተኞችና ተተኪዎች ጸረ-አማራ ጦርነት የህልውና ጉዳይ ስለ ሆነ ነው። ዝንጀሮ መጀመሪያ መቀመጫየን እንዳለችው ሁሉ፤ የመጀመሪይው የአማራው ትኩረት ራሱን ከእልቂት ማዳን ነው። በአንድነት ከመታገል ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም። በውጭ የሚኖረው አማራ በአንድነት፤ ለአንድ ዓላማ ከመስራት ውጭ ሌላ አማራጭ ሊኖረው አይገባም።

- የኢትዮጱያ ዳር ድንበር ፈተና ውስጥ ገብቷል። በጋምቤላና በምእራብ ሰሜን ጎንደር የኢትዮጵያ ድንበር ተጥሷል። የዐብይ ሰራዊት ትኩረት አማራውን ማንበርከክ ስለሆነ ዳር ድንበሩን ለማስከበር ችሎታውም፤ ብቃቱም፤ ፈቃደኛነቱም አይታይም። የመሳሪያ ትርኢት በተደጋጋሚ ማሳየትና የአገርን ዳር ድንበር ማስከበር የተለያዩ ክስተቾች ሆነዋል። ይህ ትርኢት ፋኖውንና የኤርትራን መንግሥት መጣንብህ፤ ወዮልህ፤ ለማለት ሆኖ አየዋለሁ። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከጎረቤት አገር ጋር፤ በተለይ ከኤርትራ ጋር ወደ ሌላ ጦርነት እንዲገባ ቀይ ባህርን፤ ወደብን ምክንያት አድርጎ መስበካን ማቅረብ እጂግ የተሳሳተና አደገኛ ሴራ ሆኖ አገኘዋለሁ።

- በወለጋ፤ በቤኒ-ሻኑል ጉሙዝ፤ በሰሜን ሸዋና በአዲስ አበባ ዙሪያ በአማራው ላይ የሚካሄደው እልቂትና መፈናቀል ቀጥሏል። ይህ የሆነበት አንዱ ምክንያት የኦነጋዊዉ የዐብይ መንግሥት፤ የኦሮምያ ክልል ባለሥልጣናት ተባባሪ ስለሆኑ ጭምር ነው። እኔ ኦነግ ሸኔን ከኦነግ ሰራዊት፤ ከፌደራሉ መንግሥት ስራዊት፤ ከኦሮሞ ክልል ሰራዊት ለመለየት አልችልም።

- በዐብይ መንግሥት ደረጃ የተቀነባበረው የኦሮሙማ አጀንዳ አቀንቃኝና ጽንፈኛ ኃይል በመናበብ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ፤ በተለይ በአማራው ላይ ትኩረት አድርጎ እልቂት (Genocide) እያካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ሰብአዊ መብት ካውንስል፤ የዋናው ጸሃፊ ልዩ አማካሪ፤ ሌምኪን (Lemkin Institute for the Prevention of Genocide) እልቂቱ እንደ ተፈጸመና የከፋ እልቂት እንደሚከሰት አስጠንቅቀዋል።

- የዐብይ መንግሥት ባለሥልጣናት፤ የአዲስ አበባ ከተማን ከንቲባን ጨሞሮ የአማራ ሕዝብ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ በተደጋጋሚ እገባ አድርገዋል።

- የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የዜጎችን ደህንነት፤ ነጻነትና መብት በማስከበር ፋንታ፤ ዐብይ አሕመድ አሊ የሚመራው መንግሥት ራሱ ሽብርተኛ መሆኑ በዓለም ደረጃ ያልተከሰተ ሁኔታ ፈጥሯል።

በዚህ ትንተና፤ ሽብርተኛ ምን ማለት እንደሆነ ልጥቀስ። “አንድን የማህበረሰብ ክፍል ለይቶ በዘውግ፤ በዘር፤ በሃይማኖት፤ በፖለቲካ አመለካከትና ተዛማጅ ምክንያቶች ይህንን ሕዝብ እንዲጠቃ ማመቻቸት፤ ያልሰራውን ግፍ ሰርቷል ብሎ ማዋከብ፤ ማሰር፤ ማንገላታት፤ ከቀየውና ከስራው ማባረር፤ ሕግን አስከብራለሁ በሚል ሰበብ በተራው ሕዝብና በመሪዎቹ ላይ እልቂት ማካሄድ፤ መብቱን ሁሉ መግፈፍ፤ ንብረቱን ማውደም፤ ፍትህ ሲጠይቅ የሌለ መረጃና ሃሰተኛ ምስክሮችን እያቀረቡ ክሱ እንዲጸድቅ ጫና ማድረግ” የሚሉትን ይጨምራል። የዐብይ መንንግሥት በአማራው ላይ የሚያካሂደው የሚዘገንን ግፍና በደል ይኼው ነው። ሌላው ቀርቶ በአገሪቱ ሕገ መንግሥትና የፓርላማ መመሪያ መብታቸው መከበር ያለባቸውን አማራዎች አስሯል።

የዐብይ መንግሥት ሽብርተኛ መንግሥት ነው የምለው ለዚህ ነው። መስፈርቱን ያሟላል። ተጠያቂነት የለም።

- በኦሮሞ እሬቻ በዓል ለአማራውና ለአገር ወዳዱ ሌላው ኢትዮጵያዊ የተከለከለው ባንዲራና ሌላ የኢትዮጵያዊነት መለያ ተከልክሎ፤ ለሬቻው ግን አዲስ አበባ በኦሮሞ ባንዲራ እንድታሸበርቅ ተደርጓል። ይህ ፍጹም የሆነ የተተኪነትና የበላይነት ተምሳሌት ነው።

ለዚህ ነው፤ ፋኖ እንቅስቃሴውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው። እንጂኔር ግደይ “እኔም ፋኖ ነኝ” በሚል የብዙውን ታዳሚ አድናቆት ያገኘው። “አዲስ አበባ ኼኛ፤ የኦሮሞ ባንዲራ ኼኛ” ወዘተ የሚያሳየው ሃቅ አንድ ነው። ፍጹም የሆነ የአንድ ዘውግ የበላይነት። ይህ የበላይነት ጉዞ ስኬታማ ቢሆን ምን ይከሰታል? ብለን መጠየቅ አለብን። በኔ ግምገማ የኦሮሙ ጽንፈኞች፤ ብሄርተኞችና አሸባሪዎች የበላይነቱን ከያዙ ወላይታው፤ ጋሞው፤ አኟኩ፤ ጉራጌው፤ ሶማሌው፤ አፋሩ፤ ትግራዩ፤  አማራው ወዘተ ይዋጣል፤ ማንንነቱ ሙሉ በሙሉ ይወድማል።

የወደፊቱን በሚመለከት ባጠቃላይ ለማለት የምችለው፤ የዘውግ፤ የቋንቋና የዘር ፖለቲካ እስካልተቀየረ ድረስ እንኳን አገራዊ ልማት ቀርቶ፤ ኢትዮጵያ ሰላምና እርጋት አይኖራትም። ለዚህ ነው፤ የአሁኑ ሕገ መንግሥት፤ የአገዛዝ ስርዓት፤ ተቋማትና መዋቅሮች ሙሉ በሙሉ መፍረስና የዜጎችችን ሉዐላዊነት በሚያንጸባርቅ ስርአትና እውነተኛ የሆነ የፌደራል መንግሥት አወቃቀር መቀየር አለባቸው የምለው።

ፋኖ ትጥቅ እንዲይዝ የተገደደበት መሰረታዊ ምክንያት አማራው የመኖር አለመኖር ወይንም የህልውና አደጋ ስለ ተጋረጠበት ነው። በአንድ በኩል ፋኖን ትጥቅ ማስፈታት፤ በሌላ በኩል የኦሮሞን ልዩ ኃይል ማጠናከርና እስክ አፍንጫው ማስታጠቅ፤ ዝነኛውን የኢትዮጵያን መከላከያ በኦሮሞ ጀኔራሎች የበላይነት ማዋቀር ኢትዮጵያን ከድጡ ወደ ማጡ አሸጋግሯታል።

ሁሉም ለኢትዮጵያ ዘላቂነት፤ ለመላው ሕዝቧ ደህንነት፤ ለፍትህና ለእኩልነት፤ ለዲሞክራሳዊ ስርኣት እታገለለሁ የሚል “ፋኖን መሰል” እንቅስቃሴዎች እንዲያብቡ ድርሻውን ማበርከት አለበት። የኢትዮጵያንና የዓለምን ሕዝብ አድናቆት ያገኘው ፋኖ ሕግን፤ ስርዓትን፤ ጨዋነትን፤ እኩልነትን፤ ሰብአዊነትን፤ ሃላፊነትንና ተጠያቂነትን ያስተጋባል። በተጻራሪው ግን፤ የኦሮሙማን አጀንዳ የሚያስተጋቡት ጽንፈኞች የሚመሩት ፍጹም በሆነ፤ ጊዜ ባለፈበት፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን በማይመጥንና በማይወክል የፖለቲካ ፍልስፍና ነው።

ለፍትህ ቆመናል ካልን የፋኖን ትግል መደገፍ ብቻ ሳይሆን፤ ፋኖ መሰል እንቅስቃሴዎች በመላው ኢትዮጵያ እንዲያብቡ የማድረግ ግዴታ አለብን። ፋኖ ለምን አላማ ቁሟልና ነው እንደዚህ የምትለው? ለሚለው ጥያቄ የሚከተሉትን አቀርባለሁ

ይህ እንዳለ ሆኖ እኔን እጅግ ያሳሰበኝ ጉዳይ የዐብይ ባለሥልጣናት፤ ኦነጋዊያን፤ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ ወዘተ በተደጋጋሚ ጦርነቱን በአማራና በኦሮሞ መካክል ነው የሚል ትርክት ማሰራጨታቸው ነው። የአማራ ገበሬ ወደ ኦሮሞያ ክልል ገብቶ ኦሮሞ አልጨፈጨፈም። የኦሮሞ ገበሬ ወደ ጎንደር ሂዶ አማራውን አልጨፈጨፈም። በዘመነ ዐብይ አህመድ አሊ ያለትጎዳ የሕዝብ ክፍል የለም። ለምን ይህንን ሃቅ አይናገሩም? ሕዝብ ለመቀስቀስና ዐብይ ለኦሮሞ ሕዝብ ታጋይ ነው ለማለት ሆኖ አየዋለሁ። የኢትዮጵያ መንግሥት አለ ለማለት የማልችለውም ለዚህ ነው።

ለማጠቃለል፤

- የዐብይ ኦነጋዊያን መንግሥት አሸባሪ መንንግሥት ነው። ይህንን ሃቅ ሳንሰለች ለመላው ዓለም ሕዝብ ማሰራጨትና ማሳመን  አለብን።

- በፋኖውና በኦህዴድ ጦር ሰራዊት መካከል የሚካሄደው የሚዘገንን ጦርነት እንዲያከትም ለማመቻቸት ከተፈለገ ሰራዊቱ ሙሉ በሙሉ ከአማራው ክልል መውጣት አለበት። በዐብይ መንግሥት የሚካሄድው ጦረነት ማቆም አለበት።

- በአማራው ሕዝብና በኦነጋዊያን መንግሥት መካከል እርቅና ሰላምን ለማመቻቸት ወይንም በሩን ለመክፈት ከተፈለገ ከመቶ ሽህ በላይ የሚገመተው የአማራ ፖለቲካ እስረኛ ሳይውል ሳያድር መፈታት አለበት።

- አማራ ያልሆኑ “ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች” ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ ፋኖ መሰል ተቋማትን መመስረት አለባቸው።

- “ኼኛ፤ የኛ” የሚለው የኦሮሞ ፖለቲካ ልሂቃንና ስብስቦች የበላይነት የጭፍን ጉዞ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን አያዋጣም፤ ቀጠናውን ሙሉ በሙሉ ወደ አላስፈላጊ እልቂ ያመራዋል።

- ፋኖ ሁሉን ያማከለ፤ ግልጽነት ያለውና ዲሞክራቲክ የሆነ ተቋምና ፍኖተ ካርታ መመስረት አለበት። ይኼ እኔ ብቻ የምመክረው አይደለም። ፋኖን የሚደግፉ ሁሉ ግለስቦችና ስብስቦች የሚለግሱት አግባብ ያለው ምክረ ሃሳብ ነው።

- ፋኖን በረባ ባልረባ ምክንያት፤ በአማራው ስም ሰበብ አድርጎ መከፋፈል መቆም አለበት። ለፋኖ  የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ ሁሉ በአንድ ቋት ገብቶ ፋኖ በአንድነት በሚያምንበት መንገድ መላክ አለበት።

- በውጭ አገር የፋኖው አመራር እና ተቋም የሚያምኑበት፤ የሚያምኑባት አንድ ቃል አቀባይ አይስፈልገዋል። ይህ ክፍተት በአስቸኳይ መሰራት አለበት።

- የፋኖን ታጋዮች፤ ደጋፊዎችና መሪዎች የምመክራቸው በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ለአንድ ዓላማና ለአንድ ተልእኮ በአንድነት እንዲሰሩ ነው። “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” የሚለው የብልሆች ምክርን መተግበር ወሳኝ ሆኗል።

- ለፋኖ ምክር የሚሰጡ በአገር ቤት ሆነ በውጭ የሚኖሩ ምሁራን የፋኖው እንቅስቃሴ የመጨረሻ ግቡ ኢትዮጵያ ስለሆነች፤ ፍኖተ ካርታው ሁሉን አቀፍ እንዲሆን ቀን ከሌት መስራት ይኖርብናል።

- ፋኖና ደጋፊዎቹ ጊዚዊ የሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት ጥሪ ማድረግ አለባቸው። ይህ ጊዚያዊ መንግሥት ሁሉን ኢትዮጵያዊያን ወይንም ባለድሻዎች የሚውክል መሆን አለበት። ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ የማህረሰብ ድርጅቶች፤ አገር ወዳድ ምሁራን በአንድነት ድርሻቸውን እንዲወጡ አደራ እላለሁ።

October 27, 2023
https://amharic-zehabesha.com/archives/186793

Friday, October 27, 2023

የዐቢይ ጄኔራሎች የዝርፊያ ገመና | ለአልሻባብ መሣሪያ የሚሸጠው አበባው ታደሰ | ታከለ ኡማ እና አዳናች አቤቤን የጋበዘው…
https://youtu.be/fnUnC8KqBhE?si=qz6VZvauK0LCiMOP

 የዐቢይ ጄኔራሎች የዝርፊያ ገመና | ለአልሻባብ መሣሪያ የሚሸጠው አበባው ታደሰ | ታከለ ኡማ እና አዳናች አቤቤን የጋበዘው…
https://amharic-zehabesha.com/archives/186729
የአማራ የሕልውና ትግል ላማረኛ ቋንቋ የከፈተው ትልቅ ዕድል
ሳይደግስ አይጣላም

አማረኛ ቋንቋ ማናቸውንም ነገር በቀላሉ ለመገለጽ የሚያስችል እጅግ በጣም ቀና፣ ቅን፣ ተጣጣፊና፣ በዚያ ላይ ደግሞ ውብ ቋንቋ ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር ደግሞ አማረኛ እንዳበጁት የሚበጅ ድንቅ ቋንቋ ነው።  ይህን እንዳበጁት የሚበጅ ድንቅ ቋንቋ በስርዓቱ በማበጃጀት፣ እንግሊዘኛን ጨምሮ ዐበይት ከሚባሉት ከማናቸው የዓለም ቋንቋወች ጋር አቻ እንዲሆን ብቻ ሳይሆን እንዲበልጥም ማድረግ ይቻላል።   አማረኛ የሚበጃጀው ደግሞ የቆሸሸውን በማጽዳት፣ የተሳሳተውን በማረም፣ የተዘበራረቀውን በማደረጃጀትና አስፈላጊወቹን አዳዲስ ቃሎች በመፍጠር ነው፡፡  አስፈላጊወቹን ቃሎች ለመፍጠር ደግሞ ግእዝን የሚያህል ተቀድቶ የማያልቅ የቃላት ምንጭ አለው።

ዐረብኛን ከተለያዩ ቋንቋወች ጋር በማዳቀል ትናንት የተፈጠረው፣ የላቲን ፊደል የሚጠቀመው መናኛው የስዋሂሊ ቋንቋ የምሥራቅ አፍሪቃ ወል ቋንቋ (lingua franca) ለመሆን ሲበቃ፣ አፍሪቃዊ ፊደል ያለው፣ እንዳበጁት የሚበጀው ታላቁ የአማርኛ ቋንቋ ግን ድንበር ሊሻገር ያልቻለው፣ የጦቢያን ቢሮክራሲ ባብዛኛው የተቆጣጠሩት፣ አማረኛን እጅግ አምርረው የሚጠሉት የትግሬና የኦሮሞ ልሂቃን አንቀው ስለያዙት ብቻና ብቻ ነው፡፡  ከነዚህ የኦሮሞና የትግሬ አማራ ጠሎች ጋረ በመተባበር አማረኛን የሚወጉት ደግሞ ባማረኛቸው እንዲያፍሩ ተደርገው ጥራዝ ነጠቅ እንግሊዘኛ መፃፍና መናገርን ከምሁርነት የሚቆጥሩት የነ ዋለልኝ መኮንን ግርፎች ናቸው።

በደርግ ዘመን የአማረኛ ትምህርት ከዩኒቨርስቲ እንዲወገድ ያደረጉት አማራ ጠሎቹ የትግሬና የኦሮሞ ልሂቃንና የነሱ አጫፋሪ አማራ ተብየወች ነበሩ፡፡  ለምሳሌ ያህል በ1976 ዓ.ም የፍልስፍና ትምህርት ባዲሳባ ዩኒቨርሲቲ ባማረኛ ተሰጥቶ አመርቂ ውጤት ቢያስገኝም፣ አማራ ጠሎቹ የትግሬና የኦሮሞ ልሂቃን እንዲሁም አማራ ነን ባይ አጫፋሪወቻቸው  ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስተው ትምህርቱ ባማረኛ መሰጠቱ እንዲቀር አድርገዋል፡፡  በኦነግ ዘመን ደግሞ የጭራቅ አሕመድ የትምህርት ሚኒስቴር የሆነው ብርሃኑ ነጋ አማርኛ ቋንቋ በትምህርት ዐይነት ደረጃ እንኳን እንዳይሰጥ ከፍተኛ ዘመቻ ጀምሯል።  ይህን ዘመቻውን የጀመረው ደግሞ በራሱ ባማራ ክልል ውስጥ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ነው።

በሌላ በኩል ግን ሳይደግስ አይጣላምና የአማራ ሕዝብ ሊያጠፉት የተነሱትን ወያኔና ኦነግን በማጥፋት ሕልውናውን የማስጠበቅ ዘመቻውን እንደ ሰደድ እሳት አቀጣጠሎ ያያቶቹን መሬት ከፀራማሮች እያፀዳ ነጻ ማውጣት ጀምሯል።  ስለዚህም በነዚህ ነፃ በወጡ ቀጠናወች ውስጥ ኦሮሞ ወይም ትግሬ ይቀየማል ብሎ ሳይሰጋ ወይም ደግሞ ይሉኝታ ሳይሰማው እንግሊዘኛን ሙሉ በሙሉ ባማረኛ በመተካት ልጆቹን ሙሉ በሙሉ (ሁሉንም የትምህርት ዐይነቶች) ባማረኛ እያስተማረ እንደ ጃፓንና ኮርያ አገሩን በፍጥነት የሚያሳድግ ትውልድ በፍጥነት የመፍጠር ትልቅ ዕድል ተከፍቶለታል።  ይህ መቸም የማይገኝ ዕድል ሊያመልጠው ስለማይገባ ደግሞ እስክንድር ነጋንና ዘመነ ካሴን ጨምሮ ሁሉም ያማራ ሕዝባዊ ትግል አመራሮች በፍጥነት ሊተገብሩት ይገባል።

እንግሊዘኛ እንግሊዞች በቅኝ ወረራ ዓለም አቀፍ ቋንቋ እንዲሆን ያደረጉት፣  ውስጡ ለቄስ የሆነ፣ በግድ እንጅ በውድ ሊመረጥ የማይችል ቅጥ ያጣ ቋንቋ ነው፡፡  በተለይም ደግሞ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ለሰገል (science) እና ኪንሲን (technology) ሊያገለግል የቻለው አመቺ ሁኖ ሳይሆን በዓለም ልሂቃን ያላሰለሰ ድካም ነው፡፡  ስለዚህም የአሜሪቃ ኃያልነት ሲያከትም፣ የእንግሊዘኛም ዓለም አቀፍ ቋንቋነት እንደሚያከትም ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡  ለምሳሌ ያህል እንግሊዞኝ የዜሌንስኪ (Zelensky) ቀንደኛ ደጋፊወች የሆኑት ለዩክሬን ሕዝብ አስበው ሳይሆን፣ ራሺያ ድል አድርጋ የምዕራባውያንን የበላይነት ላንዴና ለመጨረሻ ከሰበረች፣ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲሁም የራሷ የእንግሊዝ አገር የመጨረሻው መጀመርያ (the begining of the end) መሆኑን በርግጠኝነት ስለሚያውቁ ነው፡፡

የፈረንጅ ቅጥቅጦች የሆኑት የትግሬና የኦሮሞ ልሂቃን እንግሊዘኛን አመለኩ አላመለኩ፣ የአማራን ሕዝብ የማይመለከት የነሱ የራሳቸው ጉዳይ ነው፡፡  ባማንነቱ የሚኮራው የአማራ ሕዝብ ግን የሱ የራሱ የሆነ፣ እንዳበጁት የሚበጅ ምርጥ ቋንቋ እያለለት፣ ሳይቸግረው ጤፍ እየተበደረ፣ ፈረንሳይ ሲነግስ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝ ሲነግስ እንግሊዘኛ፣ ቻይና ሲነግስ ቻይንኛ እየተጠቀመ ከቋንቋ ቋንቋ የሚንጦለጦልበት ምንም ምክኒያት የለውም፡፡

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

https://amharic-zehabesha.com/archives/186722

https://amharic-zehabesha.com/home
"ራሳችሁን ቻሉ ለናንተ የሚሞት ወታደር የለም" ዐቢይ | ከወሎ ግምባር!/ 2 ፓትሮል ተማረከ/ፖሊስ ጣቢያው ተሰበረ!
https://youtu.be/e3Sb56H6drM?si=KMvXscZZ5KvqpV41

https://youtu.be/MxjcziB8PRU?si=lG-vv5zMlPB1005T

ከወሎ ግምባር!/ 2 ፓትሮል ተማረከ/ፖሊስ ጣቢያው ተሰበረ!
https://amharic-zehabesha.com/archives/186713

Thursday, October 26, 2023

የኢትዮጵያ የአገር መከላከያ ሠራዊት ዕድሜ “፻፲፮ ወይስ ፴፫ ” ?
ዕዉነተኛዉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እና ህዝባዊ መከላከያ ኃይል ምድር ጦር፣ ሰማይ ኃይል እና  ባህር ኃይል የተቆቋመበት ዘመን ጥቅምት ፲፭ ቀን ሽ ዘጠኝ መቶ ዓ.ም መሆኑ ሀቅ ነበር ፤ነዉ፡፡

ይሁን እና የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል እንደነበር አለ ማለት ግን ክህደትም ፤ዉሸትም ስለመሆኑ አይጠረጠርም ፡፡

ግንቦት ፳ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት የጥልመት  ዕለት ጀምሮ በኢህዴግ ጥርስ የተነከሰበት ብሄራዊ እና ህዝባዊ ጦር ቀርቶ ዛፉ ሳይቀር ተነቅሏል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሠራዊት አባላት ከዚያች ዕለት ጀምሮ አስካዛሬ የት እንዳለ ታሪክን ፣ ህዝብን እና ባለቤቱን የቀድሞዉን ሠራዊት እና ቤተሰቦችን መጠየቅ ይበጃል፡፡

የኢህዴግ በተለይም የትህነግ ታጋዮች ስም አዲስ አበባ አበባ ይዞ የተቀበለ ሁሉ ወደ ኋላ የአስራ ሰባት ዓመት ደምወዝ እና ጡረታ አበል እንዲታሰብ እና እንዲከፈል ሲደረግ የቀድሞዉ ብሄራዊ ህዝባዊ ጦር የ፹፫ ዓመት ዐድሜዉን ይዞ በ ፹፫ ዓ.ም. እንደ ዘገ ብረት ከመሬት ወድቆ እና ከአፈር ተቀላቅሏል፡፡

አንኳንስ ለአገር ዳር ድንበር እና ክብር ሲፋለም የነበረ ቀርቶ ሠላማዊ እና በዉጊያ ምንም ዓይነት ተካፍሎ ያልነበረዉ ህዝብ፣ ግዑዝ ነገር እና ዛፍ ተነቅሎ መጣሉን ወይም መጋዙን መርሳት እንዴት ይቻላል፡፡

በአንድ ወቅት ከ አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓ.ም ድህረ ኢህዴግ በኋላ የአቅም ግንባታ የነበሩት በበቃ ቡና ተክል ተገኝተዉ የተናገሩት “ይህ ቡና ነበር ሲዋጋን የነበረዉ በአስቸኳይ ሊወገድ ይገባል „ በማለት ቀጭን ትዕዛዝ በምሽት ጨረቃ መስጠታቸዉን በጊዜዉ የድርጂቱ ባልደረባ የነበሩ እና በምሽት ሲያስተናግዷቸዉ የነበሩ ሠዉ ሚዛን ፤ዓማን ዙሪያ በአንድ አጋጣሚ  ያጫወቱኝን ሳስታዉስ ኢህአዴግ አገር እና ህዝብ ብቻ ሳይሆን ጠፈጥሮም ጠል መሆኑን የተረዳሁበት ጊዜ ነበር ፡፡

ተራራ የሚያንቀጠቅጥ በሚል ተራራ ለመዋጥ፤ መሬት ለመሰልቀጥ …..እንዲያዉ ምኑ ነበር ያልተሞከረዉ ዓባይን ለማድረቅ ፤ ዳሽንን ካለበት ለማላቀቅ ሲቅት በወረቀት መሞከሩ የዚህ የዉጭ ምንዛሬ ምንጭ /አስገኝ አረንጓዴ  ብር በለዉ ዶላር በጥላቻ ስም ባልበለዉ ላጥፋዉ መባሉ ያኔም አሁንም ድመት መንኩሳ ዓመሏን አትረሳ ነዉ ፡፡

ርግጥ ነዉ ምሽት እና አረቂ ሰኔ እና ሰኞ ሆነዉ ሆድ ያበዉን …….እንዲሉ ቢሆንም ቂም የተቋጠረበት የኢትዮጵያ ህዝብ እና ህዝባዊ ብሄራዊ ጦሩ ብቻ እንዳልነበር ዕልፍ አዕላፍ ጉዳዮችን በመሬት ላይ ላለ እና ለነበር ብዙ ዕማኝ አያስፈልገዉም ፡፡

ሁላችንም በኢትዮጵያ የነበሩ እና ያሉ ህዝባዊ ተቋማት እንደ ጥንቱ፣ አንደ ስያሜ፣ እንደ ስራቸዉ እና ግብራቸዉ ቢሆን ሁላችንም ኢትዮጵያዉያን አንድም ቀን ደስ ባለን ዳሩ ፍየል ዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ….ሆኖ ነገሩ ሁሉም  በሁሉ ባይተዋር ሆኗል በአገሩ ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !

አለን !

https://amharic-zehabesha.com/archives/186708

Wednesday, October 25, 2023

አብይ አህመድ ሀገራችን ኢትዮጵያን ገደል ለመክተት በከፍተኛ ፍጥነት እየተንደረደረ ነው
ስለ ኢትዮጵያ

ጥቅምት 2016 ዓ.ም

አብይ አህመድ ሀገራችን ኢትዮጵያን ገደል ለመክተት በከፍተኛ ፍጥነት እየተንደረደረ ነው :: ነገ ዛሬ ሳይባል የመንግስት ሃላፊነቱን በሀገር አቀፍ የምክክር ሸንጎ ለሚታቀፍ የሽግግር መንግስት ማስረከብ አለበት :: ኢትዮጵያን እንደሀገር ለማስቀጠልና ሕዝቡን አሁን ከሚታየው የባሰ እልቂት ለማዳን ሌላ አማራጭ የለም :: በአንድ ወፈፌ አምባገነን ማን አለብኝነትና የጥፋት ውርጅብኝ ኢትዮጵያን የሚያክል ሀገር ሊፈርስ አይገባም ::

የሀገራችን ሕዝብ : አእምሮው የታወከ ፍፁም ጨካኝ አምባገነን የሀገር መሪ ነኝ ባይና : እሱ ሥር በተኮለኮሉ አሽከሮቹ : ለከት የለሽ የሥልጣንና የዘረፋ ፍላጎት : ሥር የሰደደ ክፋትና የማያቋርጥ የደም ጥማት የተነሳ : ዛሬም እንደገና በጦርነት እሳት እየተለበለበ መሆኑ እጅግ ያሳዝናል : ልብ ያቆስላል ::

ባለፉት አምስት አመታት በተካሄዱት ፍፁም አላስፈላጊ የእርስበርስ ጦርነቶችና የሰላማዊ ዜጎች አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች : በመላው ኢትዮጵያ በከንቱ የፈሰሰው ተሰፍሮ የማያልቅ የምስኪን ሕዝብ ደምና : የወደመው የሀገርና የሕዝብ ንብረት : በዚያም ሂደት የደበዘዘው የአብሮነት እሴት ያነሰ ይመስል ፤ የመንግስት ሥልጣን በያዙ ጥቂት ጨካኝ ግለሰቦችና ቡድኖች እኩይ ዓላማና ማንአለብኝነት የተነሳ : ሀምሳ አመት ሙሉ እፎይታ ያጣው ሕዝባችንና ድሃ ሀገራችን : እንደገና ሌላ ዙር ጦርነት ውስጥ መነከራቸው የግፍ ግፍ ነው ::

   ቀጣዩን ያንብ ቡ   
https://amharic-zehabesha.com/archives/186695
በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን ግብረ-ኃይል በየሁለት ሳምንቱ የሚወጣ ልሳን ፋኖስ ቁጥር 2፣ 25.10 2023
ፋኖስ ቁጥር 2፣ 25.10 2023

ስልጣን በጠመንጃ ወይስ በምርጫ !

በመጀመሪያ የፋኖስ ዕትማችን በመግቢያው ላይ ለማብራራት እንደተሞከረው የፋኖስ ዋና ዓላማና ተግባር በተለይም በአገራችን ምድር በፖለቲካው ዙሪያ ያለውን ከፍተኛ ውዥንብር መልክ ለማሲያዝና ትክክለኛውን የትግል ፈር ለማሳየት ነው።  ከታሪክ እንደምንማረው ዛሬ በአውሮፓ ምድር በሳይንስና በቴክኖሎጂ የሚገለጸው ስልጣኔ ከመታየቱ በፊት በዚሁ በአውሮፓ ምድር፣ በ14ኛው ክፍለ-ዘመን በተለይም በኢጣሊያን ምድር ከፍተኛ ውዥንብር ስለነበር ሰፊው ህዝብ የሚሰራውንና የሚያደርገውን የሚያውቅ አልነበረም። አንድ የሚግባባትም ቋንቋ ስላለነበር እርስ በርሱ የማይግባባውንና ሃሳቡ የተበታተነውን ህዝብ ዕውነተኛውን መንገድ በማሳየት ራሱን እንዲያገኝ ዳንቴ የሚባለው ታላቅ ምሁር “የአምላኮች ኮሜዲ” በሚባለው መጽሀፉ ውስጥ ሰፊው ህዝብ ጭንቅላቱ እንዲያይ ከታገደበት ሁኔታ በመላቀቅ ብርሃንን በመጎናፀፍ አምላክ የሰጠውን የማሰብ ኃይል በመጠቀም ታሪክን እንዲሰራና እንደሰው እንዲኖር እጅግ በሚያምር ጽሁፉ የመጀመሪያውን ለጣሊያን ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለተቀረውም የአውሮፓ ህዝብም የሚሆን የዕውነተኛውን የስልጣንኔ መመሪያ መንገድ አሳየ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በብዙ ችግሮች የተወጠረው የጣሊያንም ሆነ የተቀረው የአውሮፓ ህዝብ ከገባበት ውዥንብርና መደናበር ቀሰ በቀስ በመላቀቅ ከተማዎችንና መንደሮችን መገንባትና የዕደ-ጥበብ ሙያን በማዳበር ለተከታታዩ የስልጣኔ መሰረት መጣል ቻለ።

በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን ግብረ-ኃይል በየሁለት ሳምንቱ እየታተመ የሚወጣው ፋኖስ በመባል የሚታወቀው ዕትም እንደ ዳንቴው “የአምላኮች ኮሜዲ” ሊስተካከል ባይችልም በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለውን ውዥንብርና መደነባበር መልክ ለማሲያዝ ይችላል የሚል ዕምነት አለን። የአገራችንን ሁኔታ አስመልክቶ በብዛት የሚነሱና በቀላሉም መቋጫ ሊያገኙ የማይችሉ አርዕስቶች ቢኖሩም ለጊዜው በአብዛኛዎቻችን ጭንቅላት ውስጥ ከሚሽከረከሩትና ከሚብላሉት ከሁለት ቀናት በፊት ሶስት ሰዓት ያህል የፈጀውን ክርክራችንና ውይይታችንን አስመልክቶ የተነሳውን ስልጣን “በጠበንጃ ወይስ  በምርጫ” በሚለው አርዕስት ስር አጠር መጠን ያለ ማብራሪያ እንደንሰጥ ተገደናል። ይህም የሆነበት ምክንያት የሽግግር መንግስት እያሉ የሚወተውቱ ስላሉ፣ ይህ ዐይነቱ ውትወታ አገራችን ውስጥ ከሚደረገው የብዙ እህቶቻችንና ወንድሞቻችንን ህይወት ከሚቀጽፈው ትግል ጋር እንዴት ሊጓዝ ይችላል? መቅደምስ ያለበት ጉዳይ የትኛው ነው? በአሁኑ የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታስ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ወይ? አስፈላጊም ነው ወይ? አገዛዙን የሚጋፈጠው የፋኖዎች ጥምር  ኃይል በአሸናፊነት ቢወጣስ ለምርጫ ከመሽቀዳደም ይልቅ የጋራ ግምባር በመፍጠር በመጀመሪያ ደረጃ ቅድሚያ መሰጠት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ መረባረቡ የሚሻል አይደለም ወይ? ምርጫ ይካሄድ ቢባልስ ለውድድር የሚቀርቡ በማንኛውም ረድፍ የተዘጋጁ ፓርቲዎች አሉ ወይ? ምርጫ ቢካሄድና አንዱ ፓርቲ በአሸናፊነት ቢወጣስ ህዝባችን የሚፈልገውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሌሎችን የተወሳሰቡ ችግሮችን ቀስ በቀስ በመፍታት ለከታታይ ዕድገት የፀና መሰረት ሊጥል ይችላል ወይ? አገራችንና ህዝባችን አሁን ባሉበት እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በዚህም በዚያም ብለው ስልጣን ላይ ለመውጣት የሚፈልጉ ኃይሎች የህዝባችን አገልጋይ ከመሆንና ታሪክን ከህዝቡ ጋር ሆነው ከመስራት ይልቅ በውጭ ኃይል በመጠለፍና የእሱ አገልጋይ በመሆን የህዝባችንን የስልጣኔና የነፃነት ጥማት እያራዝሙበትም ወይ?

የህዝብ ብሶት ተነሳስቶ የአገዛዝ ለውጥ በተደረገባቸው የአፍሪካ አገሮችም ሆነ፣ ከ37 ዓመትታት በፊት ምርጫ በተካሄደባትና በፈርዲናንድ ማርኮስ ዲይናስቲ ስትገዛ በነበረችው ፊሊፒን በተከታታይ ምርጫ ቢካሄድም ስልጣን ላይ የሚወጡት ኃይሎች በሙሉ የፊሊፒንን ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን አላጎናጸፉትም፤ ከድህነትም በማላቀቅ የስልጣኔ ባለቤት እንዲሆን አላዳረጉትም። በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ውስጥም ከቅኝ-አገዛዝ ነፃ ለመውጣት ሲባል ከረጅም ጊዜ የጠበንጃ ትግል በኋላ ነፃነታቸውን በተቀዳጁ አገሮች፣ አንጎላ፣ ሞዛምቢክ፣ ዚምባብዌና ደቡብ አፍሪካ በእነዚህ አገሮች ውስጥ ሁሉ የተትረፈረፈ የጥሬ-ሀብት ቢኖርምና መሬቶቻቸውም ለእርሻ ምርት የሚያገለግሉ ቢሆኑም ሀብትን የሚቆጣጠሩና ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በመቆላለፍ የጥሬ ሀብቶቻቸውን የሚያዘርፉት፣ የየአገራቸውን የመንግስት መኪናዎችና የጥሬ-ሀብቶችን የግል ሀብታቸው በማድረግ እንደልባቸው የሚንደላቀቁት የየአገሩ አምባገነን አገዛዞች  ብቻ ናቸው። ህዝቦቻቸው ዕውነተኛ ነፃነትን የተጎናጸፉና ከድህነት የተላቀቁ ሳይሆን በአገራቸው ምድር ባይተዋር በመሆን በፍርሃትና በድህነት ዓለም ውስጥ እንዲኖሩ ተገደዋል። አልፎ አልፎ ምርጫ በሚካሄድባቸው እንደናይጀሪያ በመሳሰሉትና በሌሎች የምዕራብ አፍሪካ አገሮችም ውስጥ አዳዲስ ገዢዎችን ከማፈራረቅ በሰተቀር የስርዓት ለውጥ በማምጣት ህዝቦቻቸው ከድህነትና ከኋላ-ቀርነት የተላቀቁበት ሁኔታ የለም። ይህም ማለት የሰለጠኑ ተቋማት፣ ጥልቀትና ብሰለት ያላቸው ምሁራዊ ኃይሎች በሌሉበት አገር፣ የሲቪል ማህበረ-ሰብ በተደራጀ መልክ በማይገኝበት አገር፣ ውስጠ-ኃይሉ ጠንካራ የሆነና ሰፋ ያለ የኢኮኖሚ አወቃቀር በሌለበት አገር ውስጥ ለይስሙላ ምርጫ  ማካሄዱ በተዘዋዋሪ ላለው ጨቋኝ ስርዓት ዕውቅና እንደመስጠት ይቆጠራል። ለዚህም ነው በአገሮች ውስጥ አለመረጋጋት የሚታየውና በእስላም አክራሪነት ስም በሚካሄድ የርስ በርስ ጦርነት የውጭ ኃይሎች ሁኔታውን እናረጋጋለን በማለት ጣልቃ-በመግባት ሁኔታውን የሚያባብሱት። ለዚህም ነው አዲስ በተመረጡ አገዛዞች የማይደሰቱ ወጣት መኮንኖች ወይም ወታደሮች የአገዛዝ ግልበጣ እንዲያደርጉ የሚገደዱት። ቀደም ብሎ ማሊ፣ አሁን ደግሞ በቅርቡ በሐምሌ ወር በኒይጀር የተደረገው የመንግስት ግልበጣ የሚያረጋግጠው በምርጫ ስልጣን ላይ የሚወጡ መሪዎች የውጭ ኃይሎችን ከማገልገል በስተቀር ለሰፊው ህዝብ የሚሰጡት ግልጋሎት ባለመኖሩ ብቻ ነው።

ወደ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣ ወያኔ 27 ዓመታት ያህል ስልጣን ላይ በቆየበት ዘመን ከውጭ ኃይሎች ጋር በመመሰጣጠር አገራችንን በጎሳ ከከለለ በኋላ በቀጥታ ትዕዛዝ በመቀበል ተግባራዊ ያደርግ የነበረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ አገዛዙንና ካድሬዎችን የሚጠቅም ብቻ ሲሆን፣ በዚያው መጠንም ህዝባችንን ወደ ድህነት ዓለም በመገፍተር አቅመ-ቢስ ያደረገ ነው። በነፃነት ስም ትግል ያደረገው ወያኔ የውጭ ኃይሎች ተገዢና ተጠሪ በመሆን በተለይም በአማራው ወገናችን ላይ ጦርነት በማወጅና በጨቋኝነት በመፈረጅ ስቃዩን ሲያሳየው ከርሟል። የወያኔ የጎሳ ክልላዊ አገዛዝ ለራሱ የከፋፍለህ ግዛና የዘረፋ ፖሊሲ የጠቀመው በመሆኑ በተለያዩ ክልሎች የሚኖረው ህዝባችን የዕውነተኛ ዕድገትና የነጻነት ባለቤት ለመሆን አልቻለም። በተለይም በኦሮሚያና በበኔሻጉል ክልል የየክልሉ አስተዳዳሪዎች ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በመመሰጣጠር ወደ ውጭ ሊወጡ የሚችሉ ፍራፍሬዎችንና አበባዎችን በመትከል የየክልሉን ኗሪ ህዝብ ወደ ባርነት የለወጡበትን ሁኔታ እንመለከታለን።

ወያኔ 27 ዓመታት ያህል እንደልቡ ከጨፈረና አገራችንን ከአዋረደ በኋላ ለህዝቡ የሚሰጠው ምንም ነገር ባለመኖሩ ከስልጣን መወገዱ የታሪክ ግዴታ ለመሆን በቃ። በአብዛኛው ህዝባችን ተስፋ የተጣለበት በአቢይ አህመድ የሚመራው የኦሮሙማ አገዛዝ ለጥቂት ጊዜያት ህዝባችንን ካታለለ በኋላ ስልጣኑን የሚያደላድልበትን ተንኮል መሸረብ ጀመረ። ለህዝባችን የሚፈልገውን ዕውነተኛ ስልጣኔ ከመለገስ፣ የነፃነቱን ፈለግ ከማሳየትና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ከመገንባት ይልቅ የበለጠ አምባገነናዊ በመሆን፣ አሁን እንደምናየው ሙሉ በሙሉ ፋሺሽታዊ ስርዓት ለመመስረት በቅቷል። ከስድስት ወራት ጀምሮ የአማራን ልዩ ኃይልና ፋኖዎችን ትጥቅ አስፈታለሁ በማለት የከፈተው እልክ አስጨራሽ ጦርነት በአማራው ወገናችን ላይ ከፍተኛ ዕልቂት እንዲፈጽም አድርጎታል። በአቢይ አህመድና በግብረ-አበሮቹ የተከፈተባቸውን ጦርነት ለመመከት ሲሉ በተለይም ፋኖዎች በመደረጃት በአገዛዙ በመገደድና የአማራውን ህዝብ ህልውናና ባህሉን ለማስጠበቅ ሲሉ ከፋሺሽታዊ አገዛዝ ጋር በመፋለም ላይ ይገኛሉ። አቢይ አህመድና ግብረ-አበሮቹም እንደተመኙት የአማራውን ህዝብ ሊያንበረክቱት በፍጹም አልቻሉም። እንዲያውም በየቦታው ድል በድል በመሆን የፋሺሽታዊውን አገዛዝ ወታደሮች እየመቷቸውና መሳሪያዎቻቸውንም እየቀሙባቸው ነው። እንደምንከታተለው ከሆነ በፋኖዎች የሚደረገው ትግል መልክ እየያዘ በመምጣት ለአማራው ወገናችን ብቻ ሳይሆን፣ ለጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብም ተስፋ የሚጣልበት ለመሆን በመብቃት ላይ ነው። እንደሚታወቀው የፋኖ ትግል በመጀመሪያ ደረጃ የአማራውን ህልውና ለማስጠበቅ ሲሆን፣  በተጨማሪም የአገራችንን አንድነት ለማስጠበቅ ነው። የአማራውን ህልውናና የአገራችንን አንድነት ለማስጠበቅ ደግሞ የግዴታ በህዝብ የታገዘ አመጽ ለድሉ  ወሳኝ ነው። ድል ሲባልም የአገዛዙን ቁንጮ ብቻ በማስወገድ እፎይ ተብሎ አርፎ መቀመጥ ሳይሆን፣ አገዛዙ እስካሁን ድረስ ሲመራበት የነበረውን በውሸት ትረካ ላይ የተመረኮዘውን የጥላቻ መርዝና የመጨቆኛ መሳሪያውን ቀስ በቀስ አኮንታኩቶ በመጣል ብቻ ነው ማረጋገጥና ማብሰርም የሚቻለው።

በአብዛኛዎቻችን ዕውነተኛ ነፃነትንና ስልጣኔን በምንፈልግ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ይህ ዐይነቱ የትግል ስልት ከተጨባጩ የአገራችን ሁኔታ ስንነሳ፣ ሎጂክንና አርቆ አሳቢነት የሌለውን አገዛዝ ከስልጣን ላይ ማስወገድ የሚቻለውና የሚገባውም በጠበንጃ ብቻ ነው። አንድ አገዛዝ ጦርነት አውጆ እንደልቡ ህዝብ ሲጨፈጭፍና አገር ሲያፈራርስ ዝምብለህ ተመልከት፣ ዕጣህም ነው የሚል የተፈጥሮም ሆነ የእግዚአብሄር ህግ የለም። አንድ አገዛዝም ስልጣን ላይ በአጋጣሚ ስልተቀመጠ አንድን ህዝብም ሆነ ግለሰብን እንደፈለገው የማሰር፣ ከቀዬው የማፈናቀል፣ ሀብቱን የመዝረፍና የመግደልም መብት የለውም። ማንኛውም አገዛዝ ከህዝብና ከህግ በላይ ሊሆን በፉጹም አይገባውም። ማንኛውም አገዛዝ በማንኛውም ጊዜ የህዝብ አገልጋይ እንደመሆኑ መጠን፣ አገሩንም በጸና መሰረት ላይ የመገንባት ግዴታና ኃላፊነት አለበት። አንድ አገዛዝ ከዚህ ውጭ ልዩ መብት የለውም፤ ሊኖረውም አይገባም። ስልጣንን የሚይዙ ኃይሎች ሰዎች እንደመሆናቸው መጠን ህገ-መንግስትን በመጣስ ከእያንዳንዱ ዜጋ በልጠው ሊታዩ አይችሉም፤ መብትም የላቸውም።

ከዚህ ዐይነቱ ተጨባጭ የአገራችን ሁኔታ ስንነሳና ፋሺሽታዊ አገዛዝ ሰፍኖ የአማራውን ወገናችንን ብቻ ሳይሆን ጠቅላላውን ህዝባችንን ፍዳውን በሚያሳይበት ወቅት የምርጫ ጉዳይ ብዙ ጥናትና ዝግጅትን የሚጠይቅ  ቢሆንም ከረጂም ጊዜ አንጻር የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም። በሌላ ወገን ደግሞ የዛሬውን በአገራችን ምድር የሰፈነውን ፋሺሽታዊ አገዛዝና የውጭ ኃይሎች ተጠሪ በመሆን በአማራው ህዝባችን ላይ ጦርነት በመክፈት ህዝባችንን የሚገድለውንና በጠቅላላው በአገሪቱ ምድር ውስጥም የባህል ውድመትና ዘረፋ የሚያካሂደውን የአቢይ አህመድን የፋሺሽታዊ አገዛዝ ከስልጣን መወገድ ያለበት ጉዳይ ነው። ይህ ዐይነቱ አገዛዝ ከቅኝ-ግዛት ባላነሰ ከወያኔ የወረሰውን የከፋፍለህ ግዛ ስልት ጥልቀትና ስፋት በመስጠት  ህዝባችን በሰላም እንዳይኖርና አገሩን ቀስ በቀስ፣ ግን ደግሞ አስተማማኝ በሆነ መሰረት ላይ እንዳይገነባ በማድረግ የድህነቱንና የጥገኘነቱን ዘመን እያራዘመው ነው።

ይሁንና ግን ይህ ዐይነቱ አገዛዝ በተቀነባበረ የጦርነት ትግል ስልጣኑን እንዲለቀቅ ከተገደደ በኋላ በሁሉም ዘንድ ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት ነገር ይህ ዐይነቱ ድል የጠቅላላው ትግል የመጀመሪያው ደረጃ ነው። እንደሚታወቀው ከእንደዚህ ዐይነቱ አረመኒያዊ አገዛዝ ጋር የሚደረግ ትግል ፖለቲካዊም እንደመሆኑ መጠን፣ በሁለተኛ ደረጃ በአገራችን ምድር የተረጋጋ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የሰላም፣ እንዲሁም የአንድነት ሁኔታና ስሜት ለመፍጠር ከተፈለገ የግዴታ  የሽግግር ስርዓት/አስተዳደር በህዝብ ተወካዮች የመመስረቱ ጉዳይ አስፈላጊ ነው። ይህ እንደ ሸንጎ የሚቆጠር ስብስብ ሁሉም ተገዢ የሚሆንበት ሕገ-መንግስት የማርቀቅ ተግባር ሲኖረው፣ አርቃቂዎችም ከሁሉም ማህበረሰብ የተውጣጡ የህገ-መንግስት ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም የሚፈጠረውን የአስተዳደር ክፍተት የሚሞላ የፖለቲካ ኃይል ወይም ተወካይ መኖር መዘንጋት የለበትም። ይህ ዐይነቱ የሽግግር መንግስትም ለህዝቡና ለአገራችን በቆራጥነት የታገሉትን አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን የሚያካትትና የሽግግር ፍትህነትንም ተግባራዊ የሚያደርግ መሆን አለበት። የአስተዳደሩም ዘመን በተቻለ መጠን አጭር መሆን ይኖርበታል። ለምርጫ አስተማማኝ ሁኔታ ከተፈጠረ በኋላ በቁጥር ከሶስት በላይ የማይበልጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተፈጥረው ለምርጫ ሲበቁ ምርጫ ተካሂዶ አሸናፊው የስልጣኑ ባለቤት ይሆናል። የስልጣን ዘመኑም በህግ ይደነገጋል። ይህ ዐይነቱ ሂደትም ለሲቪል ማህበረሰብ መመስረት አስፈላጊ ሲሆን፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የባህል ክፍተት እንዳይኖር በማድረግ ማንኛውም ኃይል በአመጽ ስልጣንን እንዳይዝ ለማገድ ይቻላል። እንደሚታወቀው የጦርነት ትግልና የህዝብ ዕምቢተኘት አስፈላጊ የሚሆኑት በህገ-መንግስት ውስጥ የሰፈሩት የመብት፣ ማለትም የዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎች፣ የህዝቡ መሰረታዊ ፍላጎቶች፣ ማለትም የተመጣጠነ ምግብ፣ ንጹህ ውሃ፣ ቤት፣ የጤንነት መስክና ትምህርትን ለልጆት በተሟላ መልክ ማዳረስ በማይቻልበት ጊዜና፣ በተጨማሪም ደግሞ ለስራ ፈላጊው የህብረተሰብ ክፍል በቂ የስራ መስክ በማይከፈትበት ጊዜና ሰፊው ህዝብ በአጠቃላይ ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ በሚወድቅበት ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ሃቅ ስንነሳ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ቀውሶች እንዳይፈጠሩ ከተፈለገ  ለፖለቲካ ስልጣን እንወዳደራለን የሚሉ ፓርቲዎች በእርግጥም የህዝብን ጥያቄዎች የሚመልሱና የአገራችንንም ብሄራዊ ነፃነት ለማስጠበቅ የሚችሉና ኃላፊነትም የሚቀበሉ መሆን አለባቸው። የሞራል ብቃትም እንዲኖራቸው ያስፈልጋል። የለውጡ ሂደትም ደረጃ በደረጃ የሚካሄድ ሲሆን ብሄራዊ ባህርይ እንዲኖረው መደረግ አለበት፤ ወይም ጠቅላላውን የአገሪቱን ህዝብ የሚያሳትፍ የብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ የለውጥ ሂደት ይሆናል። ምክንያቱም ሰፊው ህዝብ የማይሳተፍበት፣ ቅሬታውንም የማያሰማበትና መሻሻልም እንዲደረግ መብቱ በሚነፈግበት አገር ውስጥ ስለተሟላ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ማውራት በፍጹም አይቻልምና። ሰፊው ህዝብ በአገር ግንባታ ውስጥ ሲሳተፍ፣ ተቋማት ሲገነቡና መብቱንም ሲጠቀም ብቻ ነው ስለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና  ተግባራዊነት ማውራት የሚቻለው።

በእኛ ዕምነት በመጀመሪያ ደረጃ የዛሬው አገዛዝ አስተማማኝ በሆነ መንገድ በግዴታ ከስልጣኑ መወገድ አለበት እንላለን። ብዙ ማዋከብም ሳይበዛ ከውጭ የሚመጣውን ግፊት በስርዓትና በብልህነት ለመቋቋም ከተፈለገ ተገደው ወደ ጫካ እንዲገቡ ለተገደዱት ፋኖዎች ለሽግግር መንግስት መመስረት አመቺ ሁኔታ እስኪፈጠር ድረስ የጠቅላላውን የፖለቲካ ሁኔታ ረጋ ባለ መልክ መመልከትና አገር ወዳድ ምሁራንም ሊሳተፉ የሚችሉበት የስትራቴጂ ጥናትና ቅየሳ መደረግ አለበት። ይህ ዐይነቱ የስትራቴጂ ጥናት አስፈላጊነትም የአገራችንን የተመሰቃቀለ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ፣ እንዲሁም የሰላም እጦት መንሰኤዎች በማጥናት ደረጃ በደረጃ መፍትሄ ለመፈለግ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን እስካሁን ድረስ በአገራችን ምድር ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዳይሰፍንና ዕውነተኛ ለህዝቡ አለኝታ የሚሆን ሁለ-ገብ የኢኮኖሚ ዕድገት ተግባራዊ እንዳይሆን በአገራችን የውስጥ ፖለቲካ በመግባት የሚፈተፍተውንና ለዚህም አመቺ ሁኔታ የሚፈጥሩትን ጠጋ ብሎ ለማጥናት ነው። በተለይም አሜሪካን አገር በአማራውም ሆነ በሌላው ብሄረሰብ ስም የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ስላሉና፣ አንዳንዶችም የአሜሪካንን አገርን የማመሰቃቀል አጀንዳ ለማስፈጸም ደፋ ቀና የሚሉ ስለሆነ እነዚህ ዐይነት እርኩስ ዓላማ ያላቸው ኃይሎች ሰርገው በመግባት የትግሉን ዓላማ እንዳያሰናክሉ ከአሁኑ መጠንቀቅ ይገባል የሚል ዕምነት አለን። በአገር ቤትም ሆነ በውጭው ዓለም በአማራዎችና በፋኖዎች፣ እንዲሁም ደግሞ በጠቅላላው ህዝባችን ስም የሚደረገው ትግል በከፍተኛ ደረጃ በምስጢር የሚካሄድ መሆን አለበት። ዲፕሎማሲያዊ ትግል እናደርጋለን እያሉ እዚህና እዚያ የሚደረገው መቅበዝበዝ የህዝባችንን የነፃነት ፍላጎት ድምጥማጡን የሚያጠፋው መሆኑን መታወቅ አለበት። በአሁኑ የዓለም ሁኔታና አገራችንም ተዳክማ በምትገኝበት ዘመን ዲፕሎማሲ የሚባል ነገር አይሰራም። የምዕራቡ ካፒታሊስት ዓለምም በዲፕሎማሲ የሚያምን አይደለም። የምዕራቡ ካፒታሊስት ዓለም ዲፕሎማሲ ሲል የእኔን የበላይነት ተቀበል፣ የምልህንም ዝምብለህ ተግባራዊ አድርግ ማለቱ ብቻ ነው። በተለይም ግሎባል ካፒታሊዝም አገሮችን በሚያተረማምስበት ዘመን ትግሉ የግዴታ ምስጢራዊና በከፍተኛ ምሁራዊ ብቃትነት የታጠቀ መሆን አለበት እንላለን።

ስለሆነም በጠበንጃ ስልጣን ላይ ከወጡ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች አገዛዞች ፋኖዎች መማር ያለባቸውው ጉዳይ ከራሳቸው ባሻገር ለህዝባቸውና ለአገራቸው የቆሙ መሆን ያለባቸው መሆናቸውን ቀስ በቀስ ማረጋገጥ አለባቸው። የአገራችንንም ሆነ የአብዛኛዎችን የአፍሪካ አገሮች ሁኔታ ታሪክንና የህብረተሰብ አወቃቀር ስንመለከትና ስንመረምር በሚገባና በሁሉም አቅጣጫ የሰለጠነና የዳበረ ምሁራዊ ኃይል ባለመኖሩ ስልጣን ላይ የሚወጡት ኃይሎች ክመጀመሪያውኑ በቅደም ተከተል መወሰድ ያለባቸውን ተግባሮች አያውቁም። ባለው የበሰለና የሰለጠነ ምሁራዊ ኃይል ክፍተት የተነሳ ስልጣንን በጠበንጃ የተቀዳጁና የሚቀዳጁ ኃይሎች በካፒታሊስት አገሮችና ኤክስፐርቶች ነን በሚሉ በቀላሉ የሚታለሉበት ሁኔታ ይፈጠራል። ይህም ማለት ለነፃነት የተደረገውና ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለበት ትግል የመጨረሻ መጨረሻ የውሃ ሽታ ይሆናል ማለት ነው። ከዚህ ዐይነቱ አስቸጋሪ ሁኔታ ስንነሳ ከበሰሉና አገር ወዳድ ከሆኑ ምሁራን ምክር በመቀበል ስፈው ህዝብ የሚነቃበትና የሚደራጅበት ሁኔታ መፈጠር አለበት። ሰፊውንም ህዝብ ሊያገለግሉና ለአገርም መሰረት ሊሆኑ የሚችሉ ትላልቅና ትናንሽ ተቋማት በየቦታው መገንባት አለባቸው። ሰፊውንም ህዝብ በአገር ግንባታ ላይ ለማሳተፍ ሰፋ ያለ ስትራቴጂ መቀየስ ያስፈልጋል። ከዚህ ዐይነቱ አስቸጋሪ ሁኔታ ስንነሳ ቅድሚያ የሚሰጠውና ከአንዳንድ የኃያልነትን ደረጃ ላይ ከደረሱ አገሮች የምንማረው ነገር አንድን አገር በጋራ ለመገንባትት ከተፈለገ ለጊዜውም ቢሆን የጋራ-ግምባር የሆነ በአገር ወዳዶች፣ በሰለጠኑና በዕውቀት በዳበሩ ኃይሎች የሚመራ አገዛዝ መመስረቱ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው። በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በአስቸኳይ  ምርጫ እያሉ መወትወት የአገራችንን ተጨባጭ ሁንታ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን፣ ከፍተኛ ውዥንብርም እንደመንዛት ይቆጠራል። አገር ወዳድ ነኝ የሚል ካለ ስልጣን አካባቢ ሳይደርስም ወይም ለስልጣን ሳይታገል በዕውቀቱ ለአገሩ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማበርከት ይችላል የሚል ዕምነት አለን። ይሁንና ምርጫ ይካሄድ የሚባል ከሆነ ደግሞ ልዩ የአሰራር መካኒዝም በመፍጠር አንድ ሰው ከስምንት ዓመት በላይ ስልጣን ላይ እንዳይቆይ በማድረግ የሰለጠነ ስራ መስራት ይቻላል። በየሎካሎች ቀስ በቀስ ህዝቡ ሊሳተፍ የሚችልበትና ህዝባዊ ኃላፊነትም ሊቀበሉ የሚችሉ ኃይሎች የሚሳተፉብት ምርጫ ሊካሄድ ይችላል። ያም ሆነ ይህ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው በምን መንገድና እንዴትስ ነው በአገራችን ምድር ዘላቂነት ያለው ሰላም ማስፈን የሚቻለው? በምን ዐይነት መንገድና የገንዘብ ምንጭ ዘዴ ነው አገርን በጋር መገንባት የሚቻለው? የሚሉት ከፍተኛ አትኩሮ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው። ምክንያቱም ስልጣንን ከመያዝ ባሻገር ህዝባችን የመጀመሪያ መጀመሪያ አስተማማኝ  ሰላምን ስለሚሻና፣ ከድህነት የሚላቀቅበትን ዘዴ ስለሚመኝ ብቻ ነው።

https://amharic-zehabesha.com/archives/186705
 “መደብ ሳይኖር ወደብ ”
ስለ እኛ አገር ዳር ድንበር እና የባህር በር ሁሉም ጤናማ ዜጋ ያሳስበዋል ፡፡ ነገር ግን ከንግግር በላይ በተግባር ለአገራቸዉ ዳር ድንበር ፣ ለባህር በር ፣ ለዜጎች ሉዓላዊ ክብር ዕድሜ ዘመናቸዉን ያሳለፉ ፤ ህይታቸዉን የሰጡትን ስናስብ ያኔ መተማመን ይኖራል ፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል አባላት (ቅድመ 1983 ዓ.ም) በኤርትራ መድር የተከሰከሰ አጥንት፣ የፈሰሰ ደም ፣ የጎደለ አካል እና የጠፋ ህይወት ስንት እንደሆነ ቢቆጠር እና ለምን እንደሆነ ዕዉነቱን ብንረዳ ኖሮ ዛሬ ላይ ባልደረሰን ነበር ፡፡

የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ (ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም)፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እና ለእናት አገራቸዉ ክብር እና ዳር ድንበር ሲሉ ዕልፍ አዕላፍ ጀግኖች የተወደቁት እና የሞቱት ከሰሜን አስከ ደቡብ ፤ ከምዕራብ አስከ ምስራቅ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር እና ክብር ለማስጠበቅ ብቻ ነበር ፡፡

ሁሉም ለኤርትራ እና የኢትዮጵያ ዘላቂ እና ታሪካዊ ጥቅም እና ስም እንጂ ለአገራቸዉ በሞቱ እና በተሰደዱ ጊዜ የቀይ ባህርን ዉኃ ሆነ የኢትዮጵያን ስም አስከብረዉ ለማለፍ እንጂ በግል የሚያገኑት ጥቅም አልነበረም የለም ፡፡

ለአብነት በምፅ እና አሰብ በነበረዉ የሞት ሽረት ትግል እና ትንቅንቅ የአገራቸዉን ዉድቀት ለማየት ያልፈለጉት የወቅቱ ከፍተኛ አዋጊ መኮንኖች ከ/ል በላይ አስጨናቂ እና ተሾመ ደስታ)  የሞት ፅዋ የመረጡት በከፍተኛ ብሄራዊ ፍቅር እና አደራ ያለማወላወል ነበር ፡፡

እንደሌሎች የዘመናችን እና የያን ጊዜ ከኃዲዎች  የአገራቸዉን ጥቅም እና ስም በንዋይ ለዉጠዉ በሰማይ በረዉ የተንደላቀቀ ህይወት መኖርን ሳያዉቁ ቀርተዉ አልነበረም ፡፡

ግን ላገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ ከነበራቸዉ ብርቱ ፍቅር እና ክብር ነበር ፡፡ ይህም በምድር የዓለም ነገር ሆኖ ስራቸዉ ቢዳፈንም በሰማይ ክብር ያለዉ ስራ መስራታቸዉ ከፍ  ያለ ዋጋ የሚያሰጥ ነዉ ፡፡

ያ የአስራ ሰባት ዓመት ትግል የተካሄደዉ ለሁለቱ ህዝቦች ጥቅም እንጂ ለማንም የተለየ ጥቅም ፋይዳ እንዳልነበር ላለፉት ሠላሳ ዓመታት የስቃይ እና የፋዳ ዓመታት ምስክሮች ናቸዉ ፡፡

ለዚህም ነበር ታላቁ እና ልበ ብርኃኑ ኢትዮጵያዊ የህክምና፣ የሰባዊ ፣ አብራሪ እና አርበኛ ፕ/ር አስራት ወልደ የስ ከዘመነ ጥልመት (ግንቦት ፳ ቀን ሽ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓ.ም) ጀምሮ አስከ ዕልፈተ ህይወት ለኢትዮጵያ ዳር ድንበር ፣ ለባህር በር እና ለዜጎች ክብር እንደሞገቱ በክብር ያለፉት ፡፡

ሌላዉ ቢቀር በሽግግር መንግስት ምስረታ ወቅት ያሳዩትን ቁርጠኝነት ፣ ዕቢባይነት እና ዕዉን የሆነ ትንቢት ክዶ ዛሬ ላይ ወደፊት መራመድ የዕንቅልፍ ሩጫ ነዉ ፡፡ በጥላቻ እና በክፋት ወደ ኋላ እያየን ወደ ፊት መራመድ እና ትክክለኛ መንገድ መሄድ ስለሚያዳግት መጀመሪያ የጥላቻ እና ክፋት መጋረጃ መወገድ ይኖርበታል፡፡

የኢትዮጵ ህዝብ በተለይም የዓማራ ማህበረሰብ (AMARA Society) በሁሉም የአገሪቷ ማዕዘን የማርያም ጠላት ሆኖ ሲሳደድ የነበረዉ አሁን እና ላለፉት የፍዳ ዘመናት ለሆነዉ እና ሊሆን ስለሚችለዉ አስቀድመዉ በተነበዩ እና ለዚህም አስከ ህይወት መስዋዕት በከፈሉ ከአብራኩ በወጡ ቅን አሳቢ ኢትዮጵያዉያን ብቀላ መሆኑን መርሳት አያስፈልግም ፡፡

እንግዲያማ ህዝቡስ እናቴን ያገባ አባቴ ብሎ ሁሉን አሜን ከማለት ያደረገዉም ፤ያጠፋዉም አልነበረም የለም ፡፡

ግና ሰርቶ መኖር አይደለም ሞቶ ለመኖር፤ ለመቀበርያ መደብ (ማረፊያ)በአገሩ በርስቱ የተከለከለ ህዝብ ዛሬ ወድብ ፣የባህር በር ቢባል መጀመሪያ …..እንዳለችዉ  ዛሬ ላይ የመኖር እና መደብ  ጉዳይ ቢል ምን ይገርማል፡፡

የሞቱትን እና የአሞራ ሲሳይ የሆኑትን እየረሳን የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት …..ምን ረባ የሚል ትዉልድ ይዞ መደብ ሳይኖር  ወደብ የቆጡን አወርድ ባይ የብብቷን እንዳይሆን …………..፡፡

“አንድነት ኃይል ነዉ ፡፡”

Allen!
https://amharic-zehabesha.com/archives/186701
https://youtu.be/GOSqp5O9Z08?si=_l-NPTCbZ9jOfO5z

የቪዲዮ ስርጭት!/ ጦርነት ለታወጀበት የአማራ ህዝብ ወደብ ምኑ ነው?/ ቅድሚያ ወደብ ወይስ አደብ?
https://amharic-zehabesha.com/archives/186685
ፋኖነት የኢትዮጵያ እና የአማራ ሕዝብ ሕልውና አስጣባቂ ነው!
እንደሚታወቀሁ ሁሉ ሃገረ ኢትዮጵያን እና የተገፋውን የአማራ ሕዝብ እየደረሰበት ካለው ግፍ ፣ መከራ ፣ መሰደድ እና ፍጅት ለማዳን የተለያየ አቋም ፣ አስተሳሰብ እና አወቃቀር ይዘው ለዘመናት የታገሉ እና እየታገሉ ያሉ የአማራ የትግል አደረጃጀቶች አንዳሉ የሚታወቅ ነው።

ኢትዮጵያ ሃገራችን ሆነ የአማራ ሕዝብ መራር ፈተና ባጋጠመ ጊዜ መዳኛችን ፋኖነት እና የፋኖ የትግል ቀመር መሆኑ የማይታበል ሃቅ ነው።

በዓለም ላይ ብዙ ስያሜ እና ዕድሜ አስቆጥረው የተዋቀሩ የትግል አደረጃጀቶች እንዳሉ ሀሉ የፋኖ አደረጃጅትም እረጅም ዕድሜ ያስቆጠረ እና ሞልሁ በሆነ መልኩ ሕዝብ እና ሃገርን ድል በማጎናፀፍ በኩል ከፍተኛ ማና የተጫወተ የትግል ፋና ወጊ ፣ መከታ እና ነፃነት አጎናፃፊ አደረጃጀት ነው።

የኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች በአብዛኛው ኢትዮጵያን ሊወሩ ሲያኮበኩቡ መግቢያ በራቸው የሰሜኑ ክፍል ስለሆነ ፋኖነት በተለይ በአማራው መሬት የተወለደ የመታገያ እንጓ ነው ቢባል ሃሰት የለውም።

የህውሃትን የ27 ዓመታታ የጭቆና ቀንበር እንዳይነሳ አድርጎ መቀመቅ የከተተው ፣ “እጁ አመድ ሃፋሽ” ሆነ እንጂ “ህግ ማስከበር” በሚል የዳቦ ስም በትግራይ ፣ በአማራ እና በአፋር ምድር አዋሳኝ ደንበሮች የተደረጉት ጦርነቶች ኃይል እና መጠናቸው ሰፍቶ ህወሃት መሃል አዲስ አበባን እንዳይቆጣጠር የገታው ፣ ወልቃይት ፣ ጠገዴ ፣ ጠለምት እና ራያ ወደ አፅመ ዕርስት ምድራቸው ወደ አማራ ክልል ተመልሰው እንዲካተቱ ያደረገው ከአማራ ልዩ ኃይል ጋር በመቀናጀት የአማራ ፋኖ መሆኑ የማይታበል ሃቅ ነው።

ፋኖ የሕዝብ ልጅ “ይችላል” ሲባል ከመሬት ተነስቶ በዘፈቀደ የሚነገር ህሳባዊ አባባል አይደለም።

ከሶስት ሽህ ዓመታት በላይ ለነፃነት ፣ አግባብ ያለው የመንግስት ስርዓት እና ተቋም በኢትዮጵያ እንዲሰፍን ፋኖ ያከናወናቸው ተጋድሎዎችን እና ፍልሚያዎችን ለጊዜው ገታ አናድርገን የቅርቦችን እንዳስስ።

ከ1895 እና በ1935 ሁለት ጊዜ ለወረራ የመጣውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ድባቅ የመታው የፋኖ የትግል መርህ እና መዋቅራዊ ስልት መሆኑ የማይታበል ሃቅ ነው።

ስለዚህ የፋኖ ትግል የ1895ዓ.ም. ፣ የ1935ቱን የፋሽሽቱ የጣሊያን ጦርነት አካተን በአሁኑ ሰዓት በ2023 እያካሄደ ያለውን የሞት የሽረት ፍልሚያ ማለትም የ18ኛው ዘመን መገባደጃ ፣ የ19ነኛ እና የ20ኛውን ምዕተ ዓመት ተጋድሎዎቹን አይተን ስንገመግም የአማራ ፋኖ ትግል ከ130 ዓመት በላይ የሚዳሰስ የትግል ታሪክ ፣ የሃገር ጋሻ ፣ መከታ እና አልኝታ የሆነ ኃይል መሆኑን እንገነዘባለን።

የፋኖ ትግል ምሉህ ነፃነትን የማጎናፀፍ ልምድ እና ረጅም ታሪክ ያለው በመሆኑ የአማራን ሕዝብ ከመጣበት የሞት ሽረት ትግል አፈፍ አድርጎ ለድል እንደሚያበቃው ጥርጥር የለውም ።

ታሪክም የሚመሰከረው እውነታ ይሄ ነው ፣ አማራ ፋኖነትን አንግቦ ከተነሳ መዳረሻው ነፃነት ፣ ድል እና የማያዳግም አሸናፊነት ነው።

ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ እና የሰው የአስተሳሰብ ልዕቀት እየናረ እና እየሰፋ ሲመጣ እንደማንኛውም የህይወት የቁልቁለት እና የአቀበት ክስተቶች አሁን ፣ አሁን የትግሉ ጥያቄዎች የሕዝብ የህልውና ፣ የመኖር እና ያለመኖር ጥያቄዎች ላይ ትግሉ እያጠነጥነ ይገኛል።

የአምና እና የታች አምናው በፓለቲካ ፓርቲዎች እና በፖለቲከኞች ይከወን የነበረው ምድር ያረገጠ ፣ የሰርክ ፣ የደቦ እና በጊዜ ኢደት ይፈቱ ዘንድ ይቀርቡ ከነበሩ አማራጮች እና የትግል ጥያቄዎች እና አቅጣጫዎች አንፃር ስንገመግመው በአሁኑ ስዓት እየተካሄደ ያለው የአማራን ሕዝብ የማዳን ፣ የህልውና ፣ የሞት ሽረት እና የነፍጥ የፍልሚያ አካሄድ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ቀጣዩ አዋጭው የትግል አቅጣጫ እየቀረቡ ካሉት ውይይቶች ፣ የመፍትሄ ሃሳቦች ፣ የድርድር እና የሽግግር መንግስት ይቋቋም ከሚለው አማራጭ ሃሳቦች ጋር አሰላስሎ እና አገናዝቦ በማየት የትኛው የትግል አማራጭ ሚዛን ይደፋል የሚለውን ለመወሰን የተገፋው የአማራው ህዝብ ብቻ ውሳኔ ይስጥበት ዘንድ እናሳስባለን።

የኢኮኖሚ የጋራ ተጠቃሚነት ፣ የዲሞክራሲ ልዕልና ፣ ስልጣንን የመጋራት ፣ አንፃራዊ ሰላም የማስፈን ሂደት ፣ ስራ የማግኘት ፣ የደሞዝ ጭማሪ ፣ ብልቶ የማደር መሰል ወ.ዘ.ተ. ጊዚያዊ ጥያቄዎች አሁን አሁን እድሜ ለብልፅግና መንግስት የቅንጦት ትግል እያደረጋቸው መጥቷል ።

የብልፅግና መንግስት ተብየው በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ሞት ፣ መከራ ፣ የጀምላ ፍጅት ፣ የድሮን ጥቃት ፣ የጀት ድብደባ ፣ የሮኬት ውርጅብኝ ወ.ዘ.ተ. ለአንድ አፍታ እኒያ የዛ ዘመን ፣ የአምና ፣ የታች አምና ፣ የአምሳዎችና የስልሳዎቹ ታጋዮች አንዴ ቀና ብለው ቢያዩት “ምን ይሉ ይሆን” ብለን ራሳችን የምንጠይቅበት ዘመን ደርሰናል።

የአማራ ሕዝብ “መነሻችን አማራ ማዳን መዳረሻችን ኢትዮጵያ ናት” ብሎ ሲነሳ “ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንዲሉ ለሃገሩ ቀናይ የሆነው መላው ወንድም የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን የትግል እና የነፃነት መፈክር በአጋርነት አግቦ መነሳት የግድ የሚለው ይሆናል እንላለን ።

የአሁኑ ትውልድ የአማራ ፋኖዎች ከአያቶቻችን እና ከአባቶቻችን ፋኖዎች የትግል አካሄድ አንፃር ሲታይ የሚለያቸው ምን ይሆን ብለን ስናይ ፣ አያቶቻችን ፋኖዎች ይፋለሙ የነበሩት እንደ ጣሊያን ፣ ድርቡሽ ፣ ግብፅ እና መሰል የውጭ ሃገር ወራሪዎች ጋር ነበር ፣ የአሁኑ ትውልድ ፋኖዎች ግን ፍልሚያ የሚያደርጉት ኢትዮጵያን አስተዳደራለሁ እና እመራለሁ ብሎ በተሰየመ ዘረኛ ፣ አረመኔ እና ኢትዮጵያዊ ፣ ኢትዮጵያዊ ከማይሸቱ ወሮበላ ፣ ዘራፊ እና ወራሪ ብድኖች ጋር ነው። ይህም በመሆኑ እነዚህ “ወፍ ዘራሽ” በግል ስሜት እና ተነሳሽነት የተሰባሰቡ እንደ ብልፅግና ያሉ ስብስቦች የማንነታቸው የዘር ግንድ /DNA/ ማጣራቱ የግድ የሚል ይሆናል እንላለን።

የትግል መርህ እና የታጋዮች የወደፊት የማንሰራራት ዕጣ ፈንታ እና ተስፋ የሚወሰነው ባበረከተቱ ውጤት እና በህዝብ ዘንድ ባላቸው ቅቡልነት የሚመዘን እና የሚታይ ይሆናል።

የህን መስፈርት መሰረት አድርገን የፋኖን የዘመናት የትግል ዕምርታ እና ቅቡሉነት አዋድረን ስናይ ፋኖ የኢትዮጵያም ከዚያም አልፎ የአማራ ትግል ፋና ወጊ ፣ የክፉ ቀን ደራሽ ፣ መከራን አስወጋጅ ፣ የአርነት ተምሳሌት እና የሞት ፣ የሽረት እና የነፃነት አላባሽነትን ካባ የተላበሰ የዘመናት ስድር የትግል ውጤት እና ውቅር ነው እንላለን።

ከዚህ በፊት በተለያየ የአማራ አደረጃጀት ስም የተዋቀሩ ክንፎች እስከዛሬ ድረስ ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና ሊቸራቸው የሚገባ ይሆናል ። ነገር ግን አሁን ካለው ተጨባጭ የአማራ ትግል አቅጣጫ አንፃር የተበጣጠሰ ፣ የተዳከመ እና እንደ ግል ድርጅት በሚመስል መልኩ መንቀሳቀሱ እና “ከኔ ፖርቲ እና መርህ ወዲያ ላሳር” የሚለውን አስተሳሰብ ሙጭጭ አርጎ የመያዝ አባዜ አዋጭ ባለመሆኑ ዘመኑ ከሚዋጀው ፣ የህዝብ ቅቡልነት እና ነፃነት ሊያጎናፅፍ እየተንደረደረ ካለው የፋኖ “መናሻችን አማራ ፣ መዳረሻችን ኢትዮጵያ” ከሚለው ፅንሰ አሳብ ጋር በአንድነት መራመዱ በይደር የሚቆይ ጉዳይ አይደለም።

ይህ የጋራ ሃሳብ እና የትግል አካሄድ የማይገዛቸው ካሉ የትግሉ እንቅፋት እንዳይሆኑ በተገፋው ፣ እየታረደ ፣ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ እና በድል እያሸበረቀ እና እየተጓዘ ባለው የሰፊው ሕዝብ አሌንታ በሆነው ታጋይ ፋኖ እና ታጋዮች የአማራ ሕዝቦች ስም ቆም ብለው እንዲያስቡበት ከአደራ ጭምር እናሳስባለን።

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ
https://amharic-zehabesha.com/archives/186680
ቀይ ባህር - ኢሬቻ
ጥንት፣

አይደለም ውጊያችን ከስጋና ከደም

ይልቅስ እንጂ ነው ከሰማይ ኃያላት፣

በመንፈስ ቅኝት

በሰው ውስጥ አድረው በሚወከሉበት፡፡

ኦ ኤርት-ራ!

ለፈረኦን የፀሐይ አምላክ

የአይኑ ብሌን የአምላክ ራ፤

የእግዜር ውሃ ፍርድ መገለጫ

ግፉአን የወደቁብሽ፣

የራማ ጩኸት ምላሽ

ቀንበር ሰባሪ አንቺ ነሸ፡፡

ቀይ ባህር፣

አፈ ታሪኩ ሲነገር

ደም የመምሰሉ ምስጥር

ነበር አሉ፣

ከሰማይ በወረደ የደም ጠብታ

ተንጸባረቆ ሲታይ ከባህር፡፡አሁን፣

የራስን ምስል ፍለጋ

ከጥቁር ውሃ መስታወት ስር፣

እንዲህ እንዲያ ነው እያሉ

ይጠቅሳሉ ከአፈ ታሪክ ስንክሳር፤

አማረህ አሉ ዘንድሮ

ልጎርፍበት ውቂያኖስ ባህሩን፣

ልትሰለቀጥ እንደሆን እንጂ

አትችለውም ግብረመልሱን፡፡

በምረቃና ፈረስ ጋላቢ

አንተ ጉራብቻ፣ጉራብቻ፣

የመከር ወራት ውቂያ

ትበላለህ ቀይ ኢሬቻ፡፡

ተፈጥሯዊ መቼት፣

አይ አዋሽ፤ምነው ጨነገፍክ

ሳትደርስ ከእናት ውሃ መህፀን፣

አባይን መምሰል አታስብ

አልቻልክም ዋቢሸበሌ፣ ገናሌን መሆን፡፡

ከእናት ምድር እንብርት ብትነሳም

ታጁራ እንደናፈቀህ፣አሰብም እንደራቀህ፣

የእትብት ገመድህ አጥሮ

አፋር አቤ ሃይቅ ላይ፣ እንደተቀበርክ ትኖራለህ፡፡

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮ ቫንኩቨር ካናዳ
https://amharic-zehabesha.com/archives/186676

Tuesday, October 24, 2023

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...