Wednesday, October 25, 2023

ፋኖነት የኢትዮጵያ እና የአማራ ሕዝብ ሕልውና አስጣባቂ ነው!
እንደሚታወቀሁ ሁሉ ሃገረ ኢትዮጵያን እና የተገፋውን የአማራ ሕዝብ እየደረሰበት ካለው ግፍ ፣ መከራ ፣ መሰደድ እና ፍጅት ለማዳን የተለያየ አቋም ፣ አስተሳሰብ እና አወቃቀር ይዘው ለዘመናት የታገሉ እና እየታገሉ ያሉ የአማራ የትግል አደረጃጀቶች አንዳሉ የሚታወቅ ነው።

ኢትዮጵያ ሃገራችን ሆነ የአማራ ሕዝብ መራር ፈተና ባጋጠመ ጊዜ መዳኛችን ፋኖነት እና የፋኖ የትግል ቀመር መሆኑ የማይታበል ሃቅ ነው።

በዓለም ላይ ብዙ ስያሜ እና ዕድሜ አስቆጥረው የተዋቀሩ የትግል አደረጃጀቶች እንዳሉ ሀሉ የፋኖ አደረጃጅትም እረጅም ዕድሜ ያስቆጠረ እና ሞልሁ በሆነ መልኩ ሕዝብ እና ሃገርን ድል በማጎናፀፍ በኩል ከፍተኛ ማና የተጫወተ የትግል ፋና ወጊ ፣ መከታ እና ነፃነት አጎናፃፊ አደረጃጀት ነው።

የኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች በአብዛኛው ኢትዮጵያን ሊወሩ ሲያኮበኩቡ መግቢያ በራቸው የሰሜኑ ክፍል ስለሆነ ፋኖነት በተለይ በአማራው መሬት የተወለደ የመታገያ እንጓ ነው ቢባል ሃሰት የለውም።

የህውሃትን የ27 ዓመታታ የጭቆና ቀንበር እንዳይነሳ አድርጎ መቀመቅ የከተተው ፣ “እጁ አመድ ሃፋሽ” ሆነ እንጂ “ህግ ማስከበር” በሚል የዳቦ ስም በትግራይ ፣ በአማራ እና በአፋር ምድር አዋሳኝ ደንበሮች የተደረጉት ጦርነቶች ኃይል እና መጠናቸው ሰፍቶ ህወሃት መሃል አዲስ አበባን እንዳይቆጣጠር የገታው ፣ ወልቃይት ፣ ጠገዴ ፣ ጠለምት እና ራያ ወደ አፅመ ዕርስት ምድራቸው ወደ አማራ ክልል ተመልሰው እንዲካተቱ ያደረገው ከአማራ ልዩ ኃይል ጋር በመቀናጀት የአማራ ፋኖ መሆኑ የማይታበል ሃቅ ነው።

ፋኖ የሕዝብ ልጅ “ይችላል” ሲባል ከመሬት ተነስቶ በዘፈቀደ የሚነገር ህሳባዊ አባባል አይደለም።

ከሶስት ሽህ ዓመታት በላይ ለነፃነት ፣ አግባብ ያለው የመንግስት ስርዓት እና ተቋም በኢትዮጵያ እንዲሰፍን ፋኖ ያከናወናቸው ተጋድሎዎችን እና ፍልሚያዎችን ለጊዜው ገታ አናድርገን የቅርቦችን እንዳስስ።

ከ1895 እና በ1935 ሁለት ጊዜ ለወረራ የመጣውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ድባቅ የመታው የፋኖ የትግል መርህ እና መዋቅራዊ ስልት መሆኑ የማይታበል ሃቅ ነው።

ስለዚህ የፋኖ ትግል የ1895ዓ.ም. ፣ የ1935ቱን የፋሽሽቱ የጣሊያን ጦርነት አካተን በአሁኑ ሰዓት በ2023 እያካሄደ ያለውን የሞት የሽረት ፍልሚያ ማለትም የ18ኛው ዘመን መገባደጃ ፣ የ19ነኛ እና የ20ኛውን ምዕተ ዓመት ተጋድሎዎቹን አይተን ስንገመግም የአማራ ፋኖ ትግል ከ130 ዓመት በላይ የሚዳሰስ የትግል ታሪክ ፣ የሃገር ጋሻ ፣ መከታ እና አልኝታ የሆነ ኃይል መሆኑን እንገነዘባለን።

የፋኖ ትግል ምሉህ ነፃነትን የማጎናፀፍ ልምድ እና ረጅም ታሪክ ያለው በመሆኑ የአማራን ሕዝብ ከመጣበት የሞት ሽረት ትግል አፈፍ አድርጎ ለድል እንደሚያበቃው ጥርጥር የለውም ።

ታሪክም የሚመሰከረው እውነታ ይሄ ነው ፣ አማራ ፋኖነትን አንግቦ ከተነሳ መዳረሻው ነፃነት ፣ ድል እና የማያዳግም አሸናፊነት ነው።

ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ እና የሰው የአስተሳሰብ ልዕቀት እየናረ እና እየሰፋ ሲመጣ እንደማንኛውም የህይወት የቁልቁለት እና የአቀበት ክስተቶች አሁን ፣ አሁን የትግሉ ጥያቄዎች የሕዝብ የህልውና ፣ የመኖር እና ያለመኖር ጥያቄዎች ላይ ትግሉ እያጠነጥነ ይገኛል።

የአምና እና የታች አምናው በፓለቲካ ፓርቲዎች እና በፖለቲከኞች ይከወን የነበረው ምድር ያረገጠ ፣ የሰርክ ፣ የደቦ እና በጊዜ ኢደት ይፈቱ ዘንድ ይቀርቡ ከነበሩ አማራጮች እና የትግል ጥያቄዎች እና አቅጣጫዎች አንፃር ስንገመግመው በአሁኑ ስዓት እየተካሄደ ያለው የአማራን ሕዝብ የማዳን ፣ የህልውና ፣ የሞት ሽረት እና የነፍጥ የፍልሚያ አካሄድ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ቀጣዩ አዋጭው የትግል አቅጣጫ እየቀረቡ ካሉት ውይይቶች ፣ የመፍትሄ ሃሳቦች ፣ የድርድር እና የሽግግር መንግስት ይቋቋም ከሚለው አማራጭ ሃሳቦች ጋር አሰላስሎ እና አገናዝቦ በማየት የትኛው የትግል አማራጭ ሚዛን ይደፋል የሚለውን ለመወሰን የተገፋው የአማራው ህዝብ ብቻ ውሳኔ ይስጥበት ዘንድ እናሳስባለን።

የኢኮኖሚ የጋራ ተጠቃሚነት ፣ የዲሞክራሲ ልዕልና ፣ ስልጣንን የመጋራት ፣ አንፃራዊ ሰላም የማስፈን ሂደት ፣ ስራ የማግኘት ፣ የደሞዝ ጭማሪ ፣ ብልቶ የማደር መሰል ወ.ዘ.ተ. ጊዚያዊ ጥያቄዎች አሁን አሁን እድሜ ለብልፅግና መንግስት የቅንጦት ትግል እያደረጋቸው መጥቷል ።

የብልፅግና መንግስት ተብየው በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ሞት ፣ መከራ ፣ የጀምላ ፍጅት ፣ የድሮን ጥቃት ፣ የጀት ድብደባ ፣ የሮኬት ውርጅብኝ ወ.ዘ.ተ. ለአንድ አፍታ እኒያ የዛ ዘመን ፣ የአምና ፣ የታች አምና ፣ የአምሳዎችና የስልሳዎቹ ታጋዮች አንዴ ቀና ብለው ቢያዩት “ምን ይሉ ይሆን” ብለን ራሳችን የምንጠይቅበት ዘመን ደርሰናል።

የአማራ ሕዝብ “መነሻችን አማራ ማዳን መዳረሻችን ኢትዮጵያ ናት” ብሎ ሲነሳ “ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንዲሉ ለሃገሩ ቀናይ የሆነው መላው ወንድም የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን የትግል እና የነፃነት መፈክር በአጋርነት አግቦ መነሳት የግድ የሚለው ይሆናል እንላለን ።

የአሁኑ ትውልድ የአማራ ፋኖዎች ከአያቶቻችን እና ከአባቶቻችን ፋኖዎች የትግል አካሄድ አንፃር ሲታይ የሚለያቸው ምን ይሆን ብለን ስናይ ፣ አያቶቻችን ፋኖዎች ይፋለሙ የነበሩት እንደ ጣሊያን ፣ ድርቡሽ ፣ ግብፅ እና መሰል የውጭ ሃገር ወራሪዎች ጋር ነበር ፣ የአሁኑ ትውልድ ፋኖዎች ግን ፍልሚያ የሚያደርጉት ኢትዮጵያን አስተዳደራለሁ እና እመራለሁ ብሎ በተሰየመ ዘረኛ ፣ አረመኔ እና ኢትዮጵያዊ ፣ ኢትዮጵያዊ ከማይሸቱ ወሮበላ ፣ ዘራፊ እና ወራሪ ብድኖች ጋር ነው። ይህም በመሆኑ እነዚህ “ወፍ ዘራሽ” በግል ስሜት እና ተነሳሽነት የተሰባሰቡ እንደ ብልፅግና ያሉ ስብስቦች የማንነታቸው የዘር ግንድ /DNA/ ማጣራቱ የግድ የሚል ይሆናል እንላለን።

የትግል መርህ እና የታጋዮች የወደፊት የማንሰራራት ዕጣ ፈንታ እና ተስፋ የሚወሰነው ባበረከተቱ ውጤት እና በህዝብ ዘንድ ባላቸው ቅቡልነት የሚመዘን እና የሚታይ ይሆናል።

የህን መስፈርት መሰረት አድርገን የፋኖን የዘመናት የትግል ዕምርታ እና ቅቡሉነት አዋድረን ስናይ ፋኖ የኢትዮጵያም ከዚያም አልፎ የአማራ ትግል ፋና ወጊ ፣ የክፉ ቀን ደራሽ ፣ መከራን አስወጋጅ ፣ የአርነት ተምሳሌት እና የሞት ፣ የሽረት እና የነፃነት አላባሽነትን ካባ የተላበሰ የዘመናት ስድር የትግል ውጤት እና ውቅር ነው እንላለን።

ከዚህ በፊት በተለያየ የአማራ አደረጃጀት ስም የተዋቀሩ ክንፎች እስከዛሬ ድረስ ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና ሊቸራቸው የሚገባ ይሆናል ። ነገር ግን አሁን ካለው ተጨባጭ የአማራ ትግል አቅጣጫ አንፃር የተበጣጠሰ ፣ የተዳከመ እና እንደ ግል ድርጅት በሚመስል መልኩ መንቀሳቀሱ እና “ከኔ ፖርቲ እና መርህ ወዲያ ላሳር” የሚለውን አስተሳሰብ ሙጭጭ አርጎ የመያዝ አባዜ አዋጭ ባለመሆኑ ዘመኑ ከሚዋጀው ፣ የህዝብ ቅቡልነት እና ነፃነት ሊያጎናፅፍ እየተንደረደረ ካለው የፋኖ “መናሻችን አማራ ፣ መዳረሻችን ኢትዮጵያ” ከሚለው ፅንሰ አሳብ ጋር በአንድነት መራመዱ በይደር የሚቆይ ጉዳይ አይደለም።

ይህ የጋራ ሃሳብ እና የትግል አካሄድ የማይገዛቸው ካሉ የትግሉ እንቅፋት እንዳይሆኑ በተገፋው ፣ እየታረደ ፣ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ እና በድል እያሸበረቀ እና እየተጓዘ ባለው የሰፊው ሕዝብ አሌንታ በሆነው ታጋይ ፋኖ እና ታጋዮች የአማራ ሕዝቦች ስም ቆም ብለው እንዲያስቡበት ከአደራ ጭምር እናሳስባለን።

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ
https://amharic-zehabesha.com/archives/186680

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...