Wednesday, October 25, 2023

አብይ አህመድ ሀገራችን ኢትዮጵያን ገደል ለመክተት በከፍተኛ ፍጥነት እየተንደረደረ ነው
ስለ ኢትዮጵያ

ጥቅምት 2016 ዓ.ም

አብይ አህመድ ሀገራችን ኢትዮጵያን ገደል ለመክተት በከፍተኛ ፍጥነት እየተንደረደረ ነው :: ነገ ዛሬ ሳይባል የመንግስት ሃላፊነቱን በሀገር አቀፍ የምክክር ሸንጎ ለሚታቀፍ የሽግግር መንግስት ማስረከብ አለበት :: ኢትዮጵያን እንደሀገር ለማስቀጠልና ሕዝቡን አሁን ከሚታየው የባሰ እልቂት ለማዳን ሌላ አማራጭ የለም :: በአንድ ወፈፌ አምባገነን ማን አለብኝነትና የጥፋት ውርጅብኝ ኢትዮጵያን የሚያክል ሀገር ሊፈርስ አይገባም ::

የሀገራችን ሕዝብ : አእምሮው የታወከ ፍፁም ጨካኝ አምባገነን የሀገር መሪ ነኝ ባይና : እሱ ሥር በተኮለኮሉ አሽከሮቹ : ለከት የለሽ የሥልጣንና የዘረፋ ፍላጎት : ሥር የሰደደ ክፋትና የማያቋርጥ የደም ጥማት የተነሳ : ዛሬም እንደገና በጦርነት እሳት እየተለበለበ መሆኑ እጅግ ያሳዝናል : ልብ ያቆስላል ::

ባለፉት አምስት አመታት በተካሄዱት ፍፁም አላስፈላጊ የእርስበርስ ጦርነቶችና የሰላማዊ ዜጎች አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች : በመላው ኢትዮጵያ በከንቱ የፈሰሰው ተሰፍሮ የማያልቅ የምስኪን ሕዝብ ደምና : የወደመው የሀገርና የሕዝብ ንብረት : በዚያም ሂደት የደበዘዘው የአብሮነት እሴት ያነሰ ይመስል ፤ የመንግስት ሥልጣን በያዙ ጥቂት ጨካኝ ግለሰቦችና ቡድኖች እኩይ ዓላማና ማንአለብኝነት የተነሳ : ሀምሳ አመት ሙሉ እፎይታ ያጣው ሕዝባችንና ድሃ ሀገራችን : እንደገና ሌላ ዙር ጦርነት ውስጥ መነከራቸው የግፍ ግፍ ነው ::

   ቀጣዩን ያንብ ቡ   
https://amharic-zehabesha.com/archives/186695

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...