Monday, March 18, 2024

ወልቃይት ተጀምሯል | እነኮሎኔል ደመቀ ወዴት...? “ከሞት ያመለጥኩት ለጥቂት ነው” አበባው | ጎንደር ፋኖ 2 ከተማ ተቆጣጠረ | ወልቃይት ውጥረት ነግሷል ደ | ኤፌሳር ሙሉ የጁላ ሰራዊት ተደመሰሰ | ከመቀሌ እስከ ሰቆጣ ከፍተኛ የአብይ የጦርነት ዕቅድ |
https://youtu.be/UNgdSIUKbVI?si=L4CnzkCFeSuvj_Bf

https://youtu.be/5X3ZhY9Bsk8?si=-tqH-uecKcvKAGDA

 ወልቃይት ተጀምሯል | እነኮሎኔል ደመቀ ወዴት...?

https://youtu.be/MjEgRq574cE?si=Mrnhynq7i9ejG-1w

https://youtu.be/Ci7yh9H05wI?si=MXhQxgC8_mOiU1sX

 ጎንደር ቀውጢ ሆናለች ፋኖ 2 ከተማ ተቆጣጠረ | ወልቃይት ውጥረት ነግሷል ደመቀ ዘውዱ ነፍጡን አነሳ | ኤፌሳር ሙሉ የጁላ ሰራዊት ተደመሰሰ

https://youtu.be/VtV7l2PeRBo?si=bAca3cpvoJFU5E3E

 በFSR ተጭኖ የሄደው ሙሉ በሙሉ አለቀ | ከመቀሌ እስከ ሰቆጣ ከፍተኛ የአብይ የጦርነት ዕቅድ | “የአብይን እቅድ በሚገባ አክሽፈናል”

https://amharic.zehabesha.com/archives/189366
ጎንደር ፋኖ 2 ከተማ ተቆጣጠረ | ወልቃይት ውጥረት ነግሷል ደ | ኤፌሳር ሙሉ የጁላ ሰራዊት ተደመሰሰ | ከመቀሌ እስከ ሰቆጣ ከፍተኛ የአብይ የጦርነት ዕቅድ |
https://youtu.be/UNgdSIUKbVI?si=L4CnzkCFeSuvj_Bf

https://youtu.be/Ci7yh9H05wI?si=MXhQxgC8_mOiU1sX

 ጎንደር ቀውጢ ሆናለች ፋኖ 2 ከተማ ተቆጣጠረ | ወልቃይት ውጥረት ነግሷል ደመቀ ዘውዱ ነፍጡን አነሳ | ኤፌሳር ሙሉ የጁላ ሰራዊት ተደመሰሰ

https://youtu.be/VtV7l2PeRBo?si=bAca3cpvoJFU5E3E

 በFSR ተጭኖ የሄደው ሙሉ በሙሉ አለቀ | ከመቀሌ እስከ ሰቆጣ ከፍተኛ የአብይ የጦርነት ዕቅድ | “የአብይን እቅድ በሚገባ አክሽፈናል”

https://amharic.zehabesha.com/archives/189366

Sunday, March 17, 2024

መቶ አለቃው የኮማንዶ አዛዥ ተማረከ | ከጎጃም ምደር የተሰማ ሰበር ዜና | አብይ 3ቱን ጀኔራሎች አጣ 4ኪሎ ትርምስ ተፈጥሯል | የታሰሩ በርካታ ፖሊሶች በፋኖ ኦፕሬሽን ተፈቱ |
https://youtu.be/grAXGuqp3O8?si=CAgJRwTVnSH0JWfr

https://youtu.be/A701KMOT3LE?si=PMRZ-kcBIel55Yc-

አብይ 3ቱን ጀኔራሎች አጣ 4ኪሎ ትርምስ ተፈጥሯል | የታሰሩ በርካታ ፖሊሶች በፋኖ ኦፕሬሽን ተፈቱ |

https://youtu.be/bt5CLbgIOQo?si=CW8uctJh6-lIgV49

የታሰሩ በርካታ ፖሊሶች በፋኖ ኦፕሬሽን ተፈቱ |
https://amharic.zehabesha.com/archives/189351

Saturday, March 16, 2024

‹‹አብይ ማደሪያ የለው፣ ግንድ ይዞ ይዞራል!!!›› አንድ ለእናቱ እስክንድር ነጋ!!! እና የደም ነጋዴዎች!!!  (ክፍል ሁለት)
ኢት-ኢኮኖሚ  /ET- ECONOMY

ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

(ለሻለቃ መሣፍንት ልጅ መታሰቢያ ትሁን)

የኃላው ከሌለ የፊቱ የለም!!! ታሪክ አልባዋ ከተማ A City Without Its Past

‹‹ወይ አዲስአበባ፣ ወይ አራዳ ሆይ፣

አገርም እንደሰው፣ ይናፍቃል ወይ!!!

አዲስ አበባ ከተማ ያለ ጥንታዊ ታሪክ!!! A City Without Its Past ………. Demography Change የእስክንድር ቃል ጠብ አላለችም!!! ‹‹ከሰው በፊት የአዲስ አበባ ህዝብን አታፈናቅሉ፣ ቅርሳችንን አታውድሙ፣ አረንጎዴ፣ቢጫ ቀይ ባንዲራችንን አትንኩ፣ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት እየተደረገ ነው›› እያለ በአገር ውስጥ በአደባባይ የሞገተ፣ ዘጠኜ የታሠረ፣ በዓለም አቀፍ አደባባይ በተባበሩት መንግሥታት ፊት ከፕሮፊሰር ጌታቸው ኃይሌ ጋር የአማራን ጀኖሳይድ ያስመዘገበ ባለ ራአዩ የጥንት የጠዋቱ ቆራጥ ታጋይ ታላቁ እስክንድር ያሉት ፕሮፊሰር መስፍን ወለወደማርያም ናቸው፡፡ የእስክንድር ስምና ብዕር ለመለስ ዜናዊ ለወያኔ ኢህአዴግ ፋሽስታዊ አገዛዝ መቅሰፍት ነበረች፣ የእስክንድር ስምና ብዕር ለኮነሬል አብይ አህመድ የኦህዴድ ብልፅግናም ዘረኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ የማትዋጥ የማትተፋ መርዝ ናት፡፡ የታላቁ እስክንድር ትንቢተ ቃል ተፈፅሞል…..በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት (ጀኖሳይድ) ተፈፅሞል!!!

እስክንድር የሞቀ ትዳሩንና ቤቱን ከሃገረ አሜሪካ ጥሎ አገር ቤት በርሃ ወርዶ፣ ህዝብቀስቅሶ፣ ፋኖን አደራጅቶ ባይመክት የአማራ ህዝብ ዛሬ ለኦሮሙማ ሥርዓት! ለኦህዴድ ብልፅግና እንቁላል ይገብር ነበር፡፡ የእስክንድር ብዕር ኮነሬል አብይን አሥር ክፍለጦር ድባቅ ይመታል፣ እስክንድር የህዝብ መከታና የደሃ አሌንታ፣ ሰው ሰው የሸተተ ስብእና የተላበሰ የህዝብ ልጅ በወያኔ፣ ኦህዴድና ብአዴን ማንም ምናምቴ ስሙ አይጠራም፡፡ እስክንድር በብዕሩ ሲወድቅ ሲነሳ፣ ሲታሰር ሲፈታ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለእኩልነትና ለነፃነት እድሜ ልኩን የታገለ የኢትዮጵያ ፋኖ አርበኛ ነው፡፡  አንድ ለእናቱ! እስክንድር ዱር ቤቴ ብሎ እናንተን አምኖ፣ ለእናንተ ለመሞት፣  የዘር ፍጅትን ለማስቆም፣ የሃገር ጥፋትን ለማስቆም፣ ሁላችንም ፈርተን በራድን ጊዜ፣ ለኮነሬል አብይ አገዛዝን እንቢ አሻፈረኝ  ያለ ለመሠረታዊ ለውጥ የታገለ ጀግና የጥንት የጠዋቱ እሱ ብቻ ነው፡፡ ቤታችንን ሲያፈርሱ ከእኛ ጋር ነበር!!!.......... ሲርበን ሲጠማን ከእኛ ጋር ነበር!!! ባንዲራችንን ሲያወርዱ የሰቀለ እሱ ነበር፡፡ የእስክንድር ግፍ ብዙ አለብን!!! ከሰው በፊት የተገለጠለት እሱ ነበር!!!……….የእስክንድር ራዕይ ህዝብን ለማዳን እንጂ ለሥልጣን አልነበረም፡፡   ኮነሬል አብይ እስክንድርን ለማስገደል ዶልቶ፣ ከጎጃም ምድር ፣ አንዴ አሳፍኖ ሊወስደው ሲል ህዝብ አስለቀቀው እስክንድር የህዝብ ልጅ ነውና!!! ኮነሬል አብይ ሴጣን ካልገደለ አይተኛምና እስክንድርን ከደብረ ኤልያስ ገዳም በደም ነጋዴዎች ጠቆሚነት አሳዶ ሊገለው ሲል በጎዶቹ ብርታት አመለጠ፡፡ እስክንድር

‹‹በርከክ በርከክ አሉ፣ አውሬ መስያቸው

ከሰው መፈጠሬን ማን በነገራቸው

ወንደድሙን ሲገለው፣ ወንድሙን ካልከፋው፡፡

ሱሪውን አምጡለት፣ ደሙ እንዲከረፋው›› ተባለለት፡፡

እስክንድር የሃገሪቱ ታሪካዊ ቅርሶች በኮነሬል አብይ አህመድ ኦህዴድ ብልፅግና ካድሬዎች እየፈረሰ ነው ህዝብ ተነስ ተቃውሞህን አሰማ ብሎ ከፊት እመራ ሲታገል ሁሉም ፈርቶ፣ተከታይ አጣ፡፡ ዛሬ ሜክሲኮ ሠንጋተራ አካባቢ ሸበሌ ሆቴል ጎን የፈረሰው የዘጠና አመት ያስቆጠረው ቅርስ ሎምባርዲያ ሬስቶራንት ህንፃ  በዓይናችን አይተናል፡፡ ዛሬ ለገሃር አካባቢ የፈረሰው ቅርብ ጊዜ የተሠራው የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅትና፣ የቬርኔሮ ህንፃ መኪና ተራ ጎን የነበረ ህንፃ ወደ አመድነት ተቀይረው፣ በዓይናችን አይተናል፡፡ ለአረብ ኢምሬትስ ኤግልስ ሄልስ ፕሮጀክት (Eagle Hills project – La Gare in Ethiopia) በስድስት አመት ተሰርቶ የሚያልቅ ህንፃዎች ሰዕልለላንቲካ የሚሆን ፎቶግራፍ አሳይተውን ወፍም የለ!!! አብይ ሦስት ሽህ ስድስት መቶ ሜትር ካሬ ቦታ ለአረብ ወዳጆቹ ሸጠ፡፡ ዛሬ አራት ኪሎ የተፈጥሮ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ ህንፃ አፈረሰው፡፡

የሥነ-ሕዝብ ለውጥ (Demography Change) የኮነሬል አብይ መንግሥት የአዲስ አበባ ህዝብ የሥነ-ህዝብ ለውጥ ማድረግ የፈለገው የአዲስ አበባ ብሔር ብሔረስብ ስብጥር በ2007 እኤአ Ethnic groups of Addis Ababa (2007) አማራ Amhara (47.05%)፣ ኦሮሞ Oromo (19.51%)፣ ጉራጌ  Gurage (16.34%)፣ ትግራይ  Tigrayan (6.18%)፣ ስልጤ  Silt'e (2.94%)፣ ጋሞ Gamo (1.68%)፣ ልዩ ልዩ Other (6.3%) በመሆኑ የአማራ፣ የጉራጌ ህዝብ ቁጥር በቤት ማፍረስ ለመቀነስ፣ ከአዲስ አበባ ለማስወጣት ብሎም የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ለመጨመር በአዲስ አበባ ማስፈር ጀመሩ፡፡ ኮነሬል አብይ መንግሥትን የኦሮሞ ህዝብ አንቅሮ ስለተፋው እቅዳቸው ከሽፎል፣ በፍቅርና በአንድነት የኖረውን የኢትዮጵያን ህብረ-ብሔር ህዝብ መለያየት የኦህዴድ ብልፅግና ካድሬ  አይችልም፡፡ የወያኔ ኢህአዴግ ካድሬም ወድቆልና!!!

2019 እኤአ ጀምሮ የኮነሬል አብይ የኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ ዘመን ከፍተኛ የቤት ማፍረስ ዘመቻ በ‹‹ህገወጥ ንብረት ስም››በአዲስ አበባ ከተማና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ፣ለገዳዲ፣ሱሉልታ፣ኢልሞጆና፣ ገላን ከተሞች ንዎሪዎች የነበሩ አስራሁለት ሽህ አባወራዎች ቤት ፈረሰ፡፡ እስክንድርና ባልደራስ ድርጅት ብቻ ነበሩ በግንባር ቀደምትነት የቤት ፈረሳውን የተቃወሙት፡፡ Since early 2019, the Ethiopian government under Abiy Ahmed administration begun large-scale house demolition that deemed "illegal property" in Addis Ababa and the Oromia Region in the area of Sebeta, Buraryu, Legetafo, Legedadi, Sululta, Ermojo, and Galan towns, with 12,000 houses destroyed by the government, which led to further unrest in the country…………………..(1)

በፌብሪዎሪ 19 ቀን 2019እኤአ ማለዳ ጠዋት የለገጣፎ ከተማን ቡልዶዘሮች ወረሮት የሦስት ሽህ አባወራዎችን ቤቶች ዶጋ አመድ አደረጉት፡፡ ሦስት ሽህ ቤት አልባ ዜጎች፣ ከነመተዳደሪያ ንግድ ቤታቸው ተዘጉ፡፡ የለገዳዲና ለገጣፎ ከተሞች ከንቲባ ሐቢባ ሲራጂ የቤቶቹ መፍረስ በ2017 እኤአ ማስተር ፕላን መሰረት የከተማ ስትራቴጂ መሆኑን በመደገፍ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠጭ፡፡ On 19 February 2019, bulldozers were raid into Legetafo area and demolished 3,000 homes, leading to thousands homelessness and ruin business activities. Mayor of Legetafo Legedadi Habiba Sirajs supported the demolition as a necessary steps corresponding to the 2017 master plan, which was part of urban strategies.

ኮነሬል አብይ አህመድ ሃገር ለመሸጥ፣ የሰው ጎጆ ለማፍረስ፣ እናቶችን ለማስለቀስ የመጣ ሴጣን ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ደሓዎቹን ጠራርጎ በማፈናቀል ለዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ኤግል ሒልስ ኩባንያ (Eagle Hills) 360000 (ሦስት መቶ ስልሳ ሽህ) ካሬ መሬት ቦታ የሸጠ ነውረኛ ሰው ነው፡፡ ለኤግልስ ሒልስ ፕሮጀክት ሲባል የፈረሱ ህንፃዎች ከላይ ከፎቶግራፍ ላይ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ማየት ይቻላል፡፡ ኢምሬትስ ኤግል ሒልስ በፈረሰው ቦታ ላይ ከአንድ ፎቅ ሌላ የሠራው የለም፡፡ ቦታው ድረስ ሄዶ በማየት ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት አብይ፣ አዳነች አቤቤ፣ ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ የአዲስ አበባን ከተማ ንዋሪዎች በማፈናቀል ላይ እንዳሉ መገንዘብ ያሻል፡፡

{1} በዳግማዊ ዐፄ ምኒሊክ ዘመን በ1917እኤአ የተገነባው የመቶ አመታት ታሪካዊው ፍራንኮ ኢትዮጵያ ምድር ባቡር  ይፈርሳል፣ ኮነሬል አብይ የምኒልክን ታሪካዊ ውርስና ቅርስ በማጥፋት ቤተመንግስታቸውን በአንድነት ፓርክ ብሎ ሰይሞታል፣ ከመቶ አመታት ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ መንግሥት ምድር ባቡር ቅርስ አጥፍተዋል፣

{2} የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ብዙ መቶ ሚሊዩን ብር የወጣበት አዲስ ህንጻ ፈርሷል፣

{3} የቡፌ ደ ላጋር ታሪካዊ ባህላዊና ዘመናዊ የመዝናኛ ሥፍራ ፈርሷል፣

{4} የቬርኔሮ ህንፃ ባለ ስድስት ፎቅ ህንፃ  ፈርሷል፣

{5} የሞዓ አንበሳ ሃውልት  ከጣልያን ሃገር የተመለሰው ሐውልት፣ በሮም የጀግናው ዘርዓይ ድረስ የተሠዋበት ታሪካዊ ሃውልት በደንብ አልተያዘም፣ ወዘተ

ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ (United Arab Emirates)፡- የአቡ ዳቢ ኩባንያ፣ ኤግል ሒልስ  (Eagle Hills launches project – La Gare in Ethiopia) በአዲስ አበባ ከተማ ለገሃር  ሠፈር  ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት 360,000 sq metres  (ሦስት መቶ ስልሳ ሽህ) ካሬ  ሜትር ባለ ይዛታ ሲሆን የቦታው የስፋቱ ትልቅነት ሃምሳ የአዲስ አበባ ስታዲየምን ያክላል፡፡ ኤግልስ ሒልስ ኩባንያ በተሰጠው ቦታ ላይ ባለ አራትና አምስት ኮኮብ ሆቴሎች ለመገንባት፣ የመዝናኛ ሥፍራዎች ለመስራት፣ አራት ሽህ ቤቶች ለመስራት እቅድ ነድፎ ነበር፡፡ ኤግልስ ሒልስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ወጪ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት 27% (ሃያ ሰባት) በመቶ ድርሻ አለው ተብሎል ነበር፡፡ ኤግልስ ሒልስ ኩባንያ ስልሳ ስምንት ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ በጀት በመመደብ ለአንድ ሽህ ስድስት መቶ አባወራዎች የመኖሪያ ቤቶች እንደሚሰራና ምንም ዓይነት መፈናቀል እንደማይኖር ለንዋሪዎቹ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ ኤግልስ ሒልስ ኩባንያ የለገሃር ፕሮጀክት ለሃያ አምስት ሽህ ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥርና በሰባት አመት ፕሮጀክቱ ተሠርቶ እንደሚያልቅ ተገልጾ ነበር፡፡ ወፍም የለ!!! ወሬ ነው ኮነሬል አብይ አገር የሸጠ ባንዳ መውደቂያው ደርሶል፡፡ “Abu Dhabi firm, Eagle Hills has launched a massive integrated community development project, La Gare in Ethiopia. La Gare will cover 360,000 sq metres of the Ethiopian capital, Addis Ababa and would include multi-star hotels, leisure outlets, commercial units, and 4000 homes. The estimated value of La Gare is $2 billion and the Ethiopian government is reported to hold a 27% share in the project. According to the Ethiopian Prime Minister, Abiy Ahmed, Eagle Hills has set aside an additional budget of $68 million for 1600 households that would be uprooted during the development process……..Reportedly, apart from creating a new city center, La Gare would also lead to an increase of approximately 25,000 jobs. The project is said to finish its first phase of development, mainly the construction of malls, in three years. The overall estimated time for project completion is reported to be seven years.”………………………………….(2)

ኤግልስ ሒልስ (Eagle Hills)፡- የጡት አባታቸው ኮነሬል አብይ አህመድ በተገኘበት  አቡዳቢ መሠረቱን ያደረገ የግል ሪል ስቴት ኢንቬስተር ወደ ኢትዮጵያ ምድርና ንግዱ ህብረተሰብ ሠተት ብሎ ገባ፡፡ በአዲስ አበባ ለገሐር ባቡር ጣቢያ እንዲከትም ኮነሬል አብይ ኢንቨስት እንዲያደርግ ተመቻቸለት፡፡ በለገሐር ባቡር ጣቢያ ሦስት ሽህ ስድስት መቶ ካሬ ሜትር ኩታ ገጠም ቦታ በኮነሬሉ ያለ አንዳች ጨረታ ገጸ-በረከት ተበረከተለት፡፡ የለገሃር አራት ሽህ ንዋሪዎችን ያፈናቀለ ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት ለንዋሪዎች መኖሪያ ቤት ይሠራል ተብሎ በውሸት ተሰበከ፡፡

ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት በስድስት አመታት የግንባታ ጉዞው አንድ የመኖሪያ ኮንዶሚኒየም በመስራት ገና ተጠናቆ ሳያልቅ በሙሉ መሸጡ ታውቆል፡፡  ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት የገነባውን እየሸጠ በሚያገኘው ገንዘብ ሌላ በመገንባት ላይ የሚገኝ ደሃ ደላላ ድርጅት ነው፡፡ ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት ሌላ ቦታ አንድ አምስት የመሠረት ግንባታ የሠራባቸው ሥፍራዎች በተለያዩ ሳይቶች ይስተዋላሉ፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ጋዜጠኞች፣ የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የከተማችን የፓርላማ አባሎች ካሉ ይሄን ሥፍራ ጎብኝተው፣ የሚሠራውን የወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት  ላለፉት ስድስት አመታት የተሠራ  የኤግል ሒልስ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት በመመልከት ኃላፊነታቸውን እንዳልተወጡ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ኤግል ሒልስ ሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ድርጅት ሥፍራውን ተነጥቆ  ለኢትዮጵያዊያን  አገር በቀል ሪል ስቴት ኢንቨስተሮች በጨረታ ቦታውን እንዲያለሙ እድል ቢያገኙ ተዓምር መሥራት ይችልሉ፡፡ አገር በቀል ሪል ስቴት ኢንቨስተሮች፣ ሦስት መቶ ስልሳ ሽህ ካሬ ሜትር  ቦታ ሊዝ ገዝተው እንዲያለሙና በግፍ ለተፈናቀሉ ደሃ የህብረተሰብ ቤት ጨምሮ በመገንባት፣ ኤግል ሒልስ ከአገር እንዲወጣ ማድረግ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው እንላለን፡፡  የኮነሬል አብይ አህመድና የሼክ መሃመድ ቢን ዛአይድ አል ናህያን ሚስጢራዊ ግንኙነት አገራችንን  ወደ ማያባራ ጦርነት በማሸጋገር ላይ ይገኛል፣ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ደግሞ ሰው አልባ ድሮውን በመስጠት  ንፁሃን ዜጎች እንዲጨፈጨፉ አድርገዋል፡፡ ዲያስፖራው በየአረብ ኢምሬትስ ኢንባሲዎች ሠላማዊ ሠልፍ በማድረግ ሼክ መሃመድ ቢን ዛአይድ  የኮነሬል አብይ አህመድን መንግስት መቃወም ይገባቸዋል፡፡  ኢምሬትስ ሰው ዓልባ አውሮፕላኖች በመስጠትና በመሸጥ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን ጦርነት በማቀጣጠል እንድትወገዝ ማድረግ ያሻል፡፡  የኢትዮጵያ ህዝብ ተቃውሞውን ማሰማት ይጠበቅበታል እንላለን፡፡

እስክንድር ነጋ ዳግማዊው ጥቁር ሰው በአማራ ለመሠረታዊ ለውጥ፣ ጠቅላይ ጦር ሠፈሩን አውድም (Bombard the Headquarter) የወያኔን የኦህዴድና ብአዴን ካድሬዎች ለፍርድ እናቅርብ!!! የሻለቃ መሣፍንት ልጅ መሆንን በሰማን ጊዜ ልባችን ክፉኛ አዘነ፣ እኛ ተቀምጠን የአስራሰባት አመት ልጅ ስለእኛ መሞቱ በምን እዳው አስባለን፤ መልካም አገር አላወረስናችሁም እና አዘንን፣ በጀግንነትህ በኮነሬል አብይ መቃብር ላይ ከአዲስ አበባ የአንተን ኃውልት የፋኖ አርበኛ እሸቴ ሞገስና የልጅ የታገሱ እሸቴ ኃውልት እናቆማለን፡፡ በኮነሬል አብይ ፋሽታዊ አገዛዝ በማያባራ ጦርነት ልጃቻቸውን የተነጠቁ የትግራ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ ወዘተ እናቶች የልጆቻችሁን ኃውልት በኮነሬል አብይ መቃብር ላይ እናቆማለን፡፡ የልጆቻችሁ  ታሪክ በወርቅ ቀለም ይፃፋል፡፡ ትላንት የፋሽስቱ ኮነሬል መንግሥቱ የቀይ ሽብር ሠማእታት የጋራ ኃውልት ቆሞልና፡፡ ቃል ለምድር ለሠማይ!!! ይህ ጊዜም ያልፋልና!!!

የእስክንድር ትንቢተ-ራዕይ ከሩቅ ይሰማል!!! የአማራን ጀኖሳይድ እናስቁም፣ የቤት ፈረሳን እናስቁም!!! ህዝባዊ መንግስት እንመሠርታለን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ እናብስ!!! ለሥልጣን አንጣላ፣ ሥልጣን በህዝብ ምርጫ የሚመጣ ታላቅ ኃላፊነት ነው፡፡ የደም ነጋዴዎች ሴራን እንበጣጥስ!!!  ስልጣን ከእውቀት ጋር ለአዲሱ የዲጂታል ቴክኖሎጅ ዘመን ወጣት ፖለቲከኞች የሃገራችንን ችግሮች በጠረጴዛ ዙሪያ ብቻ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ብቃት ያላችሁ አዲስ ትውልድ ስልጣኑን መጨበጥ ታሪክ የጣለባችሁ አደራ ነው፡፡ አንባገነኑ የኮነሬል አብይ መንግሥት በአዲስ አበባና በሸገር ከተሞች ከ111(መቶ አስራአንደ) ሽህ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አስታውቆል፡፡ ግማሽ ሚሊዮኝ ህዝብ ተፈናቅሎል፡፡ ገና የኮነሬል አብይ ቤተመንግሥትና የሽመልስ አብዲሳ ቤተመንግሥት ሲገነባ የሚሊዮኖች ቤት ፈርሶ ተፈናቃዬች ቁጥር የትየለሌ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ከፋኖ አርበኛ  ጋር ዛሬውኑ ቆርጠ ለትግል በመነሳት  የኮነሬል አብይ መንግሥት   ግፍ ማስቆም ታሪካዊ አደራ አለብን፡፡ የፖለቲካ እስረኞችን ጋዜጠኞችን፣ ምሁራኖች የእስር ቤቶቸ በር ሠብረን ማስፈታት ታሪካዊ ስራ አለብን!!! የእስክንድር ግፍ ብዙ አለብን ….ብዙ አለብን…. እስክንድርን ከነ ድክመቱ እንውደደው፣ እናርመው፣ እንደግፈው፣ የኃላው ከሌለ፣ የፊቱም የለምና!!!   እንበል አሥራሁለት!!!

የኮነሬል አብይ ኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት ከአማራ ክልል ይውጣ!!! ከትግራይ ክልል እንደወጣ ሁሉ!!!

ምንጭ

House demolition in Ethiopia (2019–present)

(2)Abu Dhabi Based Eagle Hills Invests in Ethiopia/By  D&B Bureau/  November 21, 2018
https://amharic.zehabesha.com/archives/189355

Friday, March 15, 2024

 ህብረት ይሻላል (Better Together) ጥሪ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ!
መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት

ምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ላይ የተሰየመችው ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ካሉ እድሜ ጠገብ ሃገራት መካከል ቀዳሚ ሃገር ናት። ይህቺ ሃገር በአፍሪካ ክፍለ ዓለም ውስጥ እንደ በረሃ አበባ ብቻዋን በቅላ ብቻዋን ነጻ ሃገር ሆና የኖረች ብርቅዬና የነጻነት ምልክት ናት። በተለይ በቅኝ ግዛት የማቀቁ የአፍሪካ ሃገራት በሥሥት የሚያዩዋት እናታቸው ናት።

ኢትዮጵያ በረጅም ጊዜ ታሪኳ ውስጥ ከውጭ የሚመጣባትን ጥቃት ለማለፍ አያሌ ውጣ ውረዶችን ብታልፍም፣ ውስጣዊ አለመረጋጋቶች ብዙ ዋጋ ቢያስከፍሏትም በየዘመኑ የተፈጠሩ ልጆቿ “ህብረታችን ይበልጣል በሚል ሃያል መረዳት ሁል ጊዜም አብረው ታግለው አኩሪ የነጻነት ታሪክ ጽፈዋል። በአድዋ ተራሮች ላይ በአባቶቻችን ደም የተጻፈው ታሪክ ህብረታችን! ኢትዮጵያችን! እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ የሚሉ ሃይለ ቃሎች ናቸው። ካራማራ ተራሮች ላይ የተጻፈው የዚህኛው ዘመን ታሪካችም እንደዚሁ ተመሳሳይ ሃይለ ቃል ያስተጋባል። ህብረታችን! ኢትዮጵያችን! እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ የሚለው የአድዋው መሪ ቃል ነው ካራማራ ላይም የተደገመው። ለዚህ ነው የካራማራው ድላችን ዳግማዊ አድዋ እየተባለ የሚጠራው።

ኢትዮጵያ የእድሜዋንና የስልጣኔ ፈርቀዳጅነቷል ያህል ለመራመድ እንዳትችል ያደረጋት ነገር፣ በአንድ በኩል ከውጪ የሚነሱ ጦሮችን ለመመከት ዘወትር ዘብ ቆማ የቆየች ሲሆን በሌላ በኩል የውስጥ አለመረጋጋቶች ሃገረ መንግስቱን እገጭ እጓ እንዲል እያደረጉት ስለቆዩ ነው።

ከሁሉም የሚከፋው ግን ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ልጆች በህብረት የጻፉት ታሪክ አያሌ ቢሆንም በቅርብ ጊዜ ታሪካችን አዲስ ህገ መንግስት ስንጽፍ አብሮነታችንንና ህብረታችንን አቃሎ ልዩነቶቻችንን የሚያደምቅ ሆነ። ያቺን ሃያል ሀገር እንደ አንድ የማትከፋፈል ሃያል አገር ሳይሆን እንደ ዛኔ ጋባ ቤት፣ አንዳችን ባኮረፍን ጊዜ አፍርሰናት የምንሄድባት ጊዚያዊ ቤት አድርገን ሰራን። “ህብረት ይሻላል” የሚለው የኢትዮጵያውያን ሃይለ ቃል ተገስሶ ልዩነት ይልቃል ወደሚል ማህበረ ፖለቲካ መውረዳችን በአራቱም አቅጣጫ ያለንን ኢትዮጵያውያንን ሁሉ አንገት ያስደፋ የታሪክ ጠባሳችን ነው።

ይህ ልዩነትን የሚያጎላው አስተምህሮ ተቀይሮ ልዩነትም አንድነትም እርስ በርስ ሳይፈራረሱ የሚኖሩበትን የፖለቲካ ምህዋር ማቆም የሚገባን ቢሆንም ዛሬ ድረስ ልዩነቶች እየሰፉ ኢትዮጵያዊ ህብረታችን እየተሸረሸረ እየተሸረሸረ እየተሸረሽረ መጥቷል።

ሃገችንን ለዚህ አደገኛ የህብረት መሰረት መናጋት የጣላት ዋና ችግር አንዱ ይህ ህገ መንግስት ላይ የተጻፈው ህብረታችንን ፈራሽ ያደረገው ክፉ ሃሳብ ሲሆን በሌላ በኩል መንግስት የሚጠቀመው የከፋፍለህ ግዛ የአገዛዝ ስልት ነው። በተለምዶ ከፋፍለህ ግዛ የሚለው ፍልስፍና ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ ሆኗል። የወቅቱ ጠቃላይ ሚንስትር  ዶክተር አብይ አህመድ ዋና የአገዛዝ ስልት ይሄ ነው። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ፈልጎ ከፍተኛ ትግል ያደረገ ቢሆንም የቀድሞው የኢንሳ ድሬክተር የነበሩት አብይ አህመድ የኢትዮጵያውያንን ለውጥ በመጥለፍ ወደ ስልጣን በመጡ በወራት የመንግስትን መዋቅር የሚጠልፍ (state capture የሚያደርግ) የደህንነት መዋቅር ፈጥረው ስሙን ኮሬ ነጌኛ ብለው የኢትዮጵያውያንን የዴሞክራሲና የሽግግር ተስፋ አጨናግፈዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን እኚህ ሰው ወደ ስልጣን ከመጡ ማግስት ጀምሮ ችግሮችን በብልሃት ከመፍታት ይልቅ በኮሬ ነጌኛ ኮሚቴው አማካኝነት በሴራና በመጠላልፍ ዘዴ ስልጣን ላይ ለመቆየት በመሞከራቸው ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ ተዋግተው በትግራይ ጦርነት ወቅት አያሌ ዜጎች ረገፉ፣ የብዙ ወገኖቻችን ቤት ተዘጋ፣ ረሃብና መፈናቀልን አተረፍን። ህብረት ይበልጥብናል፣ እኔ የመንድሜ ጠባቂ ነኝ የሚሉ ሃይለ ቃሎች በአባቶቻችን ደም የተከተበባቸው የአድዋ ተራሮች ላይ እርስ በርስ ተዋግተን አንገት የሚያስደፋ ታሪክ አስጽፈውናል። የኮሬ ነጌኛው መሪ አብይ አህመድ የትግራዩ ጦርነት ጋብ ባለ በማግስቱ ከአማራ ህዝብ ጋር ሌላ ጦርነት ውስጥ ገብቶ ይታያል። የዚህን ህዝብ ጥያቄ ለመፍታት ፖለቲካዊ መፍትሄ እንደመፈለግ በጦር ሃይል አንበርክኬ እገዛዋለሁ በማለቱ ዛሬ የአማራ ህዝብ በከፍተኛ ሁኔታ ከአብይ አህመድ አገዛዝ ጋር መራራ ትግል ላይ ይገኛል።

ኮሬ ነጌኛ የተሰኘው ህቡዕ ኮሚቴ ዋና ማዕከሉን አድርጎ የነበረው የኦሮሞን ህዝብ በመሆኑ ዛሬ ኦሮምያ ውስጥ ቅጥ ያጣ አስተዳደር፣ ዝርፊያና እንግልት፣ እስራትና ግድያ ቁም ስቅሉን እያሳየው ይገኛል። የኦሮሞ ህዝብ የሚያነሳው የእኩልነትና የፍትህ ጥያቄ የጠለፉት ኮሬ ነጌኛዎች ይህ ህዝብ የሞተላትን ሃገሩን እያጠቁበት ይገኛሉ። ከሌላው ወገኑ ጋር እንዲጋጭና የስርዓቱ ዘበኛ እንዲሆን በኦሮምኛ ቋንቋ እየተናገሩ ሌት ከቀን ሊከፋፍሉት ይሞክራሉ።

የደቡቡ ወገናችንን ሁናቴ ስናይ አንዴ ጋሞን፣ አንዴ ወላይታን፣ አንዴ ሲዳማን ወዘተ. በየተራ የአብይ አህመድ መንግስት በኮሬ ነጌኛ አሰራሩ ቁም ስቅሉን እያሳየው ነው። ረሃብና መፈናቀል በዙር መከራውን እያሳየው ነው። አብይ አህመድ ስልጣን ላይ በመጣ በጥቂት ጊዚያት የጌዲኦ ወገኖቻችን ተፈናቅሎ መከራና ስቃይ ማየቱ አይዘነጋም። ጋምቤላ ውስጥ አኙዋክን ከኑየር ለማጋጨት የዚያን አካባቢ ህዝብ አንድነትና ሰላም በመንሳት የተባበረ የልማትና የሰላም ጥያቄ እንዳያነሳ ሁል ጊዜም ይጥራል። ይህ ክልል ከፍተኛ የተፈጥሮ ጸጋ ያለው ቢሆንም መንግስት ከልማት ይልቅ ግጭት ጠመቃ ላይ ተጥዶ በመኖሩ ዛሬ በዚህ ክልል ውስጥ ሰላም ወጥቶ መግባት፣ አምርቶ በምርት መደሰት የማይቻልበት ክልል ሆኗል። የሶማሌ ክልል ወገናችን በግጭትና በመገናቀል በረሃብ ይሰቃያል። በተለይ ባለፉት አምስት ዓመታት ግጭት፣ መፈናቀል፣ ረሃብ ያላገኘው የሃገራችን ክፍል ከቶ የትኛው ነው? የግጭትና የመፈናቀል መራራ ጽዋ ያልጠጣ ከቶ የትኛው ብሄር፣ ከቶ የትኛው ክልል ነው?

እውነት ነው ይህ ህዝብ በየፊናው ብዙ ዋጋ እየከፈለ ባለበት በዚህ ሰዓት እንደገና የስርዓት ለውጥ ለማምጣት ትግል ላይ ነው። ይሁን እንጂ ትግላችን በየብሄራችን የታጠረ በመሆኑ በአንድ በኩል የስርዓት ለውጥና የሽግግር ጊዜ ፈጥረን እፎይ ለማለት እንዳንችል፣ በጋራ ታግለን በፍጥነት የተሻለ ስርዓት ለመገንባት እንዳንችል አድርጎናል። በሌላ በኩል ይህ የተበጣጠሰ የትግል መስመራችን ድንገት የመንግስት መውደቅ ቢከሰት እንደገና በተባበር ሁኔታ አዲስ የሽግግር ስርዓት ለመፍጠር እንዳንችል የሚያደርግ ስጋትን ደቅኖብናል። በዚያም አለ በዚህ የኢትዮጵያውያን ትግል መከፋፈሉ የጠቀመው ስልጣን ላይ ላለው ኮሪ ነጌኛ ብቻ ነው። መከፋፈላችንና ትግላችን መበጣጠሱ የኮሬ ነጌኛ ኮሚቴ ህልም እስካሁን እንዲቆይ አድርጎብናል።

ኢትዮጵያውያን ጋሞዎች፣ አኙዋኮች፣ ኮንሶዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ትግራዮች፣ አማሮች ወዘተ እንደ ከበረ  እንቁ ይዘነው የነበረው አብሮነታችን፣ ህብረታችን እነሆ ዛሬ በብሄር ፖለቲካና በኮሬ ነጌኛ መዋቅር ምስጦች እየተበላና እየተሸረሸረ አገራችን አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ወድቃብናለች ። መንግስት ከፋፍለህ ግዛ የሚለውን ስልት ሲጠቀም ኢትዮጵያውያን ሊኖራቸው የሚገባው የትግል ስልት የመንግስትን ስልት የተቃረነ አደረጃጀት በመፍጠርና ተከፋፍሎ ለመገዛት አለመመቸት ነው።  ህብረትን የበለጠ ማጥበቅ ነው የትግሉ መጀመሪያ። ይህ የትግል ስልት ነው ጌም ቸንጀር የትግል ስልት የምንለው። በብሄር እየከፋፈለ ሊገዛን ያሰበውን ስርዓት ለመታገል ከተለያዬ ብሄር የመጣን የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት በህብረት ቆመን ከተነሳን ያን ጊዜ አሸንፈን ተነሳን ማለት ነው። የፖለቲካ አሸናፊ ሆነን ተነሳን ማለት ነው።

እኛ ኢትዮጵያውያን ህብረታችን የተጎዳው በመንግስት ከፋፍለህ ግዛው ስልት ብቻ ሳይሆን ከፍ ሲል እንደተጠቆመው አንዱ ስለራሱ ብቻ ሳይሆን ስለሌላው የሚያኖር ህገ መንግስት ስለሌለን ነው። ሃገር የሚባለው ስብስብ ሲቋቋም ዋና መተሳሰሪያ መርሆ መሆን ያለበት እንደ ብሄር ለራስ ብቻ ሳይሆን ስለሌላው መኖር ትልቅ ዋጋ የሚሰጠውና የህብረታችን መልህቅ ሆኖ መቀረጽ አለበት። አንዱ ስለ ራሱ ብቻ ሳይሆን ስለሌላውም የሚያኖረው ስርዓት ያልገነባ ሃገር ህብረቱ እንደምን አይፈርስም? እንዲህ ዓይነት ደካማ መተሳሰሪያ መርሆ ከጫንቃው ላይ የተጫነበት ህዝብ የገዛ ህብረቱ ሁልጊዜም አንካሳ ይሆናል።  የጋራ ተብሎ የተሰራለት ቤትም በአሸዋ ላይ የተሰራ የሰነፍ ሰው ቤትን የሚመስል ይሆናል። እንዲህ አይነት መተሳሰብ የጎደለው ህገ መንግስት የተጫነበት ህዝብ ጠንካራ የጋራ ተቋማትን ዘርግቶ ወደ ልማትና ወደ ሰላም እንደምን አድርጎ ወደፊት  መራመድ ይችላል? ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ዛሬ ስለ ህብረታችን በጥብቅ የምናስብበት ወሳኝ የታሪክ መታጠፊያ ምዕራፍ ላይ ነን። መዘናጋትና መታለል በቅቶ የህብረታችንን ስጋቶች ለመቅረፍ የምንነቃበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነን። የተጫነንን ነገር ሁሉ ፈንቅለን ተነስተን ህብረት! ህብረት! ህብረት! የምንልበት ጊዜ ላይ ነን።  ለስርዓት ለውጥ የሚደረጉ ትግሎችን ሁሉ  እርስ በእርስ ለማያያዝ ደፋ ቀና የምንልበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ነን።

ዛሬ በአማራ ክልል አካባቢ የተነሳውን የፋኖ ትግል ሁላችን ልንደግፍና አንድ ላይ ሆነን ይህንን ትግል የጋራ አድርገን ልንቀርጸው ይገባል። አንዱ ወገናች ትግል ሲጀምር ህብረትን ማሳየት፣ አብሮነትን ማሳየት ይገባል እንጂ አንዱ የአንዱን ትግል አይጥለፈው። የኦሮሞው ትግልና የአማራው ትግል፣ የትግራዩ ትግልና የደቡቡ ትግል፣ የጋምቤላው ትግልና የሃረሬው ትግል ሁሉ መደጋገፍና አንድ ትልቅ ጥላ ወደ መፍጠር ማደግ አለበት። ኢትዮጵያዊ ጥላ ፈጥረን ትግሎችንን አሰባስበን ህብረታችንን አጠናክረን እነሆ ከወደቅንበት ልንነሳ ይገባል። ፋኖነት አኙዋክነት፣ ኑየርነት፣ አማራነት፣ ኦሮሞነት፣ ጋሞነት፣ ወላይታነት፣ ቡርጂነት፣ ትግራይነት፣ ወዘተ ነው። ሁላችን ኢትዮጵያውያን ህብረታችንን እንደገና ለማደስ የተበላሸውን ሽግግር እንደገና ቀና ለማድረግ ህብረታችንን እንጠብቅ። ህብረት ይሻላል (better together) የሚለው ስሜት በእኛ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሃይለ ቃል ሆኖ ይግነን፣። መለያየትና እርስ በርስ ያለመናበብ የተሻለ ስርዓት እንዳንገነባ አድርጎናል። የዴሞክራሲ ትግላችንን እድሜውን አስረዝሞታል።የተለያዬና የተበጣጠሰ ትግል ውስጥ ገብተን አንድ አሸናፊ ሃይል ስልጣን ቢይዝም የረጋ ሃገረ መንግስት ሳንገነባ ቀርተን እንዲሁ በግጭት ውስጥ እንቆያለን።

ውድ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ይህንን ደብዳቤ የምንጽፈው ኢትዮጵያውያን አንዳንዶቻችን የጋሞ ልጆች ነን፣ አንዳንዶቻችን የአኙዋክ ልጆች ነን፣ አንዳንዶቻችን የኑየር ልጆች ነን፣ አንዳንዶቻችን የትግራይ ልጆች ነን፣ አንዳንዶቻችን የኦሮሞ ልጆች ነን፣ አንዳንዶቻችን የሲዳማ ልጆች ነን፣ አንዳንዶቻችን የአማራ ልጆች ነን.... ሁላችንም ከአራቱም ማዕዘናት የመጣን የተለያዬ ቋንቋ ተናጋሪ ብሄር የመጣን የኢትዮጵያ ልጆች ነን።  እኛ ከተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ ማህበረሰብ የመጣን ኢትዮጵያውያን ዛሬ እነሆ ህብረት ይሻላል (better together) የሚለውን መሪ ቃል ይዘን የተበጣጠሰውን የኢትዮጵያውያንን ትግል ለማሰባሰብ ቆርጠን ተነስተናል። ከተለያዬ ብሄር የተገኘነው እኛ ኢትዮጵያውያን የአንድ እናት ልጆች ነን። ህብረታችንን ነው እናታችን የምንለው። ህብረታችን ሲጎዳ እናታችንን ጎዳን እንላለን። ስለዚህ እኛ የኢትዮጵያ ልጆች በአንድ በኩል የተበጣጠሰውን ትግል በማቀናጀት ለጋራው በጎነት (common good) ትልቅ ሃይል ሆኖ እንዲወጣ የምንጥረው ጥረት የሚቀጥል ሆኖ በሌላ በኩል ይህ በአብይ አህመድ የሚመራው ስርዓት ሲወገድ ሊመጣ የሚችለውን የመከፋፋል አደጋ ቀልብሶ ህብረትን ለመጠበቅ የሽግግር ፍኖቶች ላይ ለመስራት አበክረን እንሰራለን። ስለዚህ ህብረታችን ለሁለት ታላላቅ ግቦች ያስፈልጋል። አንደኛው ለተባበረ ትግል መሰባሰብ ሲሆን ሌላው ስርዓት ለመገንባት የኢትዮጵያን ትንሳኤና ሽግግር ለማሳለጥ የተሻለ ስርዓት ለመትከል ነው።

ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን! ዛሬ ይህንን የህብረት ሀይል ቃል መልዕክት የምናስተላልፈው ኢትዮጵያውያን በአራቱም ማዕዘናት ያላችሁ በተለይም ወጣቶች ህብረት ይሻላል፣ ህብረት ይልቃል (better together) የሚለውን ሃይለ ቃል ከፍ አድርጋችሁ እርስ በእርስ መተሳሰብን እንድታዳብሩ፣ ህብረትን ከፍ እንድታደርጉ ለማበረታታት ነው። በተለያዩ የትግል አውድማ ውስጥ ያላችሁ ወገኖቻችን ህብረት ይሻላል የሚለውን መሪ ቃል ከፍ አድርጋችሁ በመያዝ የትብብር ጥሪ እንድታደርጉ ነው። ምሁራን፣ ተማሪዎች፣ ገበሬዎች፣ ሁላችን ኢትዮጵያውያን ህብረትን ከፍ እናድርግ። በልቦናችን ውስጥ እንጻፈው። በቤታችን ግድግዳ ላይ፣ በጊቢያችን አጥር ላይ እንጻፈው። ህብረት ይሻላል! Better together! ወቅቱ ክፉ ጊዜ ነውና ሁላችን ተጠጋግተን እንቁም፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን ህብረት፣ ህብረት፣ ህብረት እንበል።

Better together

Teko Hatanu !

እስፔተስ ሎኦ !

ዳቶ ቢር !

ህብረት ይጮኝኖ !

ብሐባር  ይሐይሽ !

ህብረት ይሻላል !

መልዕክት ካለዎ bettertogetherethiopia@gmail.com ያግኙን

https://amharic.zehabesha.com/archives/189331

https://youtu.be/UNgdSIUKbVI?si=L4CnzkCFeSuvj_Bf https://youtu.be/5X3ZhY9Bsk8?si=-tqH-uecKcvKAGDA        ወልቃይት ተጀምሯል | እነኮሎኔል ደመቀ ወዴት...? ...