የሃገር መሪዎች በዘመናት መካከል የራሳቸውን አሻራ ጥለው ማለፋቸው እሰየው የሚያስብል ሲሆን ይህን አሻራቸውን መጭው ትውልድ ሲያስታውሰው ይኖር ዘንድ ፣ በስማቸው ቤተመንግስቶችን ፣ ሃውልቶቻቸውን እና መሰል ቋሚ ህንፀቶችን ገንብተውና አቁመው ማለፋቸው ክፋትነት የለውም።
ዋናው ቁምነገር ከነዚህ ቤተመንግስት ፣ ሃውልቶች እና እንፀቶች ጀርባ የተከወኑ ሃገራዊ ፋይዳ ያላቸው ጉዳዮች ፣ እፁብ ድንቅ ታሪኮች እና የሕዝብን እሴቶች አማክለው ታንፀዋል ወይ?የሚለው ነው ዋናው ጥያቄ።
ከዚህ አለፍ ብሎ በዘመኑ የነበሩትን የሃገር ተጨባጭ ሁኔታዎች፣ የማህበረሰቡን ክሳቴዎች ፣ የአስተዳደር ቁመና እና በወቅቱ የነበሩትን ነባራዊ ሁኔታዎች የዋጁ ናቸው ወይ? በዙህ መልክ ተገንብተዋል ፣ እየተገነቡ ነው ወይ? የሚሉትን ጥያቄዎች ሊመልሱ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
ምክንያቱም ሃውልቶች ፣ ቤተመንግስቶች እና ዕንፀቶች የኪነ ጥበብ አካል እንደመሆናቸው ብዛት ባለው ገፅ የተፃፈን የመፅሃፍ ታሪክ በአጭሩ ፣ በተወሰኑ ሰዓትታት እና ዐይነ ግቡ በሆነ መልኩ ማስረዳት የሚችሉ ባህላዊ የእሴት ውጤቶች በመሆናቸው ይህም ግንዛቤ ውስጥ ሊገባ የግድ ይላል።
ከዚህ ባሻገር ዕውነታን ያዘሉ/Realistic/ ፣ የውሸት ምዕናባዊ ትርክቶችንና ፈጠራዎችን /Myths/ ያላካተቱ መሆን አለባቸው። አሁን የኦሮሞ ብልፅግና በቦሌ እና ሸገር ተብሎ በተሰየመ ቦታ ውስጥ ሊገነቡት ያሰቡት ቤተመንግስት እውነታን መሰረት ያላደረጉ ፣ በውሸት ትርክትና በቅናት መንፈስ ተነሳስተው የሚገነቧቸው ከሆ እንደ “ አኖሌ “ ሃውልት “ ሃክ እንትፍ” ተብለው እንደሚተፉ ጥርጥር የለውም።
በቀደምት ዘመን ኢትዮጵያዊያን ነገሥታትና ዐፄዎች ሆነ ሡልጣኖች የገንቧቸው ቤተ-መንግስቶች ፣ ሃውልቶችና ቋሚ ህንፀቶች በማን ተገነቡ? በምን አይነት የህንፀት አቅርቦት ታነፁ? ወጫቸውስ በማን ተሸፈነ? ሊያስተላልፉት የፈለጉት መልዕክቶችስ ምን ይመስላል? ህንፀቶቹስ ሃገር በቀል ወይስ የተኮረጁ ናቸው ወይ ? ፣ ለወደፊቱ ለትውልዱ የሚተውት ፋይዳ ወ.ዘ.ተ. ምን ይመስላል የሚለውን በተመለከተ መላ ኢትዮጵያዊያን ፣ የዓለም ማህበረሰብ ፣ ታዋቂ ግለሰቦች ፣ የዓለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች የመሰከሩላቸው እና እውቅና የሰጧቸው በመሆኑ ይህን በመዘርዘር ጊዜ አናጠፋም ።
እንደ እንግሊዙ ባኪግንሃም ፖላስ ፣ እንደ ዋሽንግተን ዲሲው ነጩ ቤተመንግስት ወዘተ እኛም ኢትዮጵያውያን የዐፄ ፋሲል ግንብ / the 17th-century castles of the historic city of Gondar, dubbed the Camelot of Africa, and go back to a time of powerful kings, Ethiopia” አለን ፣ ያውም እድሜ ጠገብ ፣ በሃገር በቀል ግንብኞች ፣ በራስ የእንፀት አቅርቦት የተገነባ ፣ የራሱ መንፈሳዊ ፣ ማህበራዊ እና ባሕላዊ መገለጫ ፣ መዕልቅና መሰረት ያለው የህንፀት ባለቤቶች እኛ ኢትዮጵያዊያኖች ነን።
ንጉስ ላሊበላ ዓለምን እና የሕንፀት ጠቢባንን በሚያስደምም መልኩ ከአንድ አለት ፈልፍለው ልዩ የሆነ የላሊበላ ቤተክርስቲያንን አንፀውልን አልፈዋል።
እንዲህ እንዲህ እያልን የሐረር ግንብን እና መሰል ኢትዮጵያዊ ቁመና ያላቸውን ቤተመንግስቶች ፣ ሃውልቶችን እና እንፀቶችን ማስፈር እንችላለን።
ከላይ የዘረዘርነው መዘርዝር ለፅሁፉ መደርደሪያ ያግዝ ዘንድ እና ሃገር በቀል /Indiginoues/ የኢትዮጵያውያን የህንፀትና የእጅ ጥበብ ውጤቶች መሆናቸውን ግንዛቤ እንዲኖረን ተዘረዘሩ እንጂ ዓለም በዮኒስኮ /UNISCO/ በዓለም አቀፍ ቅርፅነት መዝግቦ ያስቀመጣቸው እና በቱሪስት መስህብነት እየተጎበኙ የሃገርን የውጭ ምንዛሬ ካዝና እየደጎሙ በመሆኑ ለማስተዋወቅ አይዳዳንም ።
አሁን አብይ እና ሽመልስ ሊገነቧቸው ያሰቧቸው ቤተ-መንግስቶች ከዚህ በፊት የነበሩ ዕፄዎችን ለመሆን እና ለመምሰል ታስቦ ከሆነ ስሌቱና ሃሳቡ የተሳሳተ ፣ ፈር የለቀቀ እና ዐፄነት “ከንጉስ ሰለሞን” ዘር ግንድ መሳብን ስለሚጠይቅ ዳርዳርታው ፉርሽ ነው።
በዐፄዎች ዘመን የታነፁት ቤተ-መንግስቶች በእግዚአብሔር ኃይል ፣ ባአባቶች ፀሎት ፣ በሃገር በቀል የስነ -ሕንፃ ባለሙያዎች ( Architectures)፣ በሕዝብ ተሳትፎ ፣ በሃገር ቁሳቁሶች እና ኢትዮጵዮጵያዊነት ቁመና ኑሯቸው የታነፁ ናቸው። የፈረጅ ገፅታና በፈረጆች የሚሰሩ ቤተ-መንግስቶችና ህንፀቶች ለአገር ውስጥ ሆነ ለውጭ ሃገር ጎብኝዎች የማይመቹና መስህብ መሆን የማይችሉ የቀኝገዥዎችን ስነ-ልቡና ይዘው ከታነፁ ከልፋትና ከመዋለ ንዋይ ማፍሰስ ውጭ ፋይዳነታቸው ያን ያህል ነው።
ሃገረ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ችግር እንፃር ሲታይ ቤተ-መንግስት ማነፅ ለሃገርም ሆነ ለህዝብ ደንታ ቢስነትን ያሳያል።
ከዚህ ሌላ ቤተ-መንግስቶች የሚታነፁበት የመሬት የባለቤትነት ጥያቄንም ማንሳት የግድ ይላል ።
ከአንኮበር ፣ ደብረ ዘይት ናዝሬት አለፍ ብሎ እና ከአባይ ወዲህ እስከ አዲስ አበባ ያለው ቦታ የተቆረቆረው በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ዳዊት በ17 ኛው ምዕተ ዓመትና ቀደም ብሎ “በረራ” የሚለውን ስም ከሰጡት በኋላ በአፄ ሚኒልክና እትጌ ጣይቱ ዘመነ ንግስና “አዲስ አበባ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶት የኢትዮጵያ መናገሻ እንዲሆን ቢያደርጉም በፊትም ሆነ በኋላ የመሬቱ የውርስ ባለቤቶች አማራዎች መሆናቸው ታሪክ የዘገበውና የሚመሰክረው ሃቅ ነው።
ይህን መሰረት አድርጎ አማራ የኢትዮጵያ ካስማ እና ማገር እንደመሆኑ አዲስ አበባ የሁሉ ኢትዮጵያዊያን ዋና ከተማ እና መናገሻ ሆና ብትዘልቅ የማይከፋውና በዐይን ሙሉነት የሚቀበለው ቢሆንም የአዲስ አበባ የባለቤትነት መብት አለን በሚል ፈር የለቀቀ አካሄድ የኢትዮጵያውያዊነትን ፈር ለቆ እና ደንበር አልፎ የአማራን የሕጋዊ ሆነ የታሪክ ባለቤትነት ወደ ጎን በማለት ፣ በማናለብኝነትና ተደርጎ በማያውቅ አጉራ ዘለልነት “የኦሮሚያ” ቤተ- መንግስት በሚል “በበረራ” እና በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የብሔር ስም ለጥፎ የወረደ ፣ ዘመኑን ያልዋጀ እና ኋላ ቀር ድርጊት መፈፀም ትርፉ ኪሳራ እና ትዝብት ነው።
በአጠቃላይ “እራስ ስይጠና ጉትና “ እንዲሉ በወጉ እና በቅጡ ሃገርን ሳይመሩ እና መንግስት የሚለውን ቅቡልነት ሳያገኙ “ዐፄነትን” ማሰብ እና በስማቸው “ቤተ-መንግስት” ማነፅ አልቦነት ፣” ዐፄ በጉልበትነት” እና የበታችነት ስሜት የፈጠረው “የአንቱ” በሉኝ መፈራገጥ አካሄድ እንደሆነ ሊረዱ ይገባል።
በ22ኛው ክፍለ ዘመን ይህን እጓጉል እና ኋላቀር ኩነት ለመፈፀም ሕዝብን ማፈናቀል ፣ ቤት ማፍረስ፣ ቤተክርስቲያንን ፣ መስጊድን እና ተቋማትን መደረማመስ “የድርቡሽነት” ባህሪ እና ከዘር ማጥፋት ወንጀል ያልተናነስ አካሄድ መሆን ድርጊት ፈፃሚዎች እነ ብልፅግና ሊረድት ይገባል።
ይህን መሰሬ እና እኩይ ተግባር ለመፀም ይቻላቸው ዘንድ አማራውን ለማውረድ እና መድረሻ ለማሳጣት ከሚያደርጉት አካሄድ ባሻገር የቤተ እሞነቶች ህንፃዎች ማፈራረስ በሰማዮም ሆነ በምድሩ ዋጋ የሚያስከፍል ፣ እያስከፈለ ያለ ውርደትን የሚያስከትል ክሳቴ ነው እንላለን።
ተዘራ አሰጉ
ከምድረ እንግሊዝ።
https://amharic-zehabesha.com/archives/182962
Sunday, May 28, 2023
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment