Wednesday, October 25, 2023

 “መደብ ሳይኖር ወደብ ”
ስለ እኛ አገር ዳር ድንበር እና የባህር በር ሁሉም ጤናማ ዜጋ ያሳስበዋል ፡፡ ነገር ግን ከንግግር በላይ በተግባር ለአገራቸዉ ዳር ድንበር ፣ ለባህር በር ፣ ለዜጎች ሉዓላዊ ክብር ዕድሜ ዘመናቸዉን ያሳለፉ ፤ ህይታቸዉን የሰጡትን ስናስብ ያኔ መተማመን ይኖራል ፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል አባላት (ቅድመ 1983 ዓ.ም) በኤርትራ መድር የተከሰከሰ አጥንት፣ የፈሰሰ ደም ፣ የጎደለ አካል እና የጠፋ ህይወት ስንት እንደሆነ ቢቆጠር እና ለምን እንደሆነ ዕዉነቱን ብንረዳ ኖሮ ዛሬ ላይ ባልደረሰን ነበር ፡፡

የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ (ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም)፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እና ለእናት አገራቸዉ ክብር እና ዳር ድንበር ሲሉ ዕልፍ አዕላፍ ጀግኖች የተወደቁት እና የሞቱት ከሰሜን አስከ ደቡብ ፤ ከምዕራብ አስከ ምስራቅ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር እና ክብር ለማስጠበቅ ብቻ ነበር ፡፡

ሁሉም ለኤርትራ እና የኢትዮጵያ ዘላቂ እና ታሪካዊ ጥቅም እና ስም እንጂ ለአገራቸዉ በሞቱ እና በተሰደዱ ጊዜ የቀይ ባህርን ዉኃ ሆነ የኢትዮጵያን ስም አስከብረዉ ለማለፍ እንጂ በግል የሚያገኑት ጥቅም አልነበረም የለም ፡፡

ለአብነት በምፅ እና አሰብ በነበረዉ የሞት ሽረት ትግል እና ትንቅንቅ የአገራቸዉን ዉድቀት ለማየት ያልፈለጉት የወቅቱ ከፍተኛ አዋጊ መኮንኖች ከ/ል በላይ አስጨናቂ እና ተሾመ ደስታ)  የሞት ፅዋ የመረጡት በከፍተኛ ብሄራዊ ፍቅር እና አደራ ያለማወላወል ነበር ፡፡

እንደሌሎች የዘመናችን እና የያን ጊዜ ከኃዲዎች  የአገራቸዉን ጥቅም እና ስም በንዋይ ለዉጠዉ በሰማይ በረዉ የተንደላቀቀ ህይወት መኖርን ሳያዉቁ ቀርተዉ አልነበረም ፡፡

ግን ላገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ ከነበራቸዉ ብርቱ ፍቅር እና ክብር ነበር ፡፡ ይህም በምድር የዓለም ነገር ሆኖ ስራቸዉ ቢዳፈንም በሰማይ ክብር ያለዉ ስራ መስራታቸዉ ከፍ  ያለ ዋጋ የሚያሰጥ ነዉ ፡፡

ያ የአስራ ሰባት ዓመት ትግል የተካሄደዉ ለሁለቱ ህዝቦች ጥቅም እንጂ ለማንም የተለየ ጥቅም ፋይዳ እንዳልነበር ላለፉት ሠላሳ ዓመታት የስቃይ እና የፋዳ ዓመታት ምስክሮች ናቸዉ ፡፡

ለዚህም ነበር ታላቁ እና ልበ ብርኃኑ ኢትዮጵያዊ የህክምና፣ የሰባዊ ፣ አብራሪ እና አርበኛ ፕ/ር አስራት ወልደ የስ ከዘመነ ጥልመት (ግንቦት ፳ ቀን ሽ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓ.ም) ጀምሮ አስከ ዕልፈተ ህይወት ለኢትዮጵያ ዳር ድንበር ፣ ለባህር በር እና ለዜጎች ክብር እንደሞገቱ በክብር ያለፉት ፡፡

ሌላዉ ቢቀር በሽግግር መንግስት ምስረታ ወቅት ያሳዩትን ቁርጠኝነት ፣ ዕቢባይነት እና ዕዉን የሆነ ትንቢት ክዶ ዛሬ ላይ ወደፊት መራመድ የዕንቅልፍ ሩጫ ነዉ ፡፡ በጥላቻ እና በክፋት ወደ ኋላ እያየን ወደ ፊት መራመድ እና ትክክለኛ መንገድ መሄድ ስለሚያዳግት መጀመሪያ የጥላቻ እና ክፋት መጋረጃ መወገድ ይኖርበታል፡፡

የኢትዮጵ ህዝብ በተለይም የዓማራ ማህበረሰብ (AMARA Society) በሁሉም የአገሪቷ ማዕዘን የማርያም ጠላት ሆኖ ሲሳደድ የነበረዉ አሁን እና ላለፉት የፍዳ ዘመናት ለሆነዉ እና ሊሆን ስለሚችለዉ አስቀድመዉ በተነበዩ እና ለዚህም አስከ ህይወት መስዋዕት በከፈሉ ከአብራኩ በወጡ ቅን አሳቢ ኢትዮጵያዉያን ብቀላ መሆኑን መርሳት አያስፈልግም ፡፡

እንግዲያማ ህዝቡስ እናቴን ያገባ አባቴ ብሎ ሁሉን አሜን ከማለት ያደረገዉም ፤ያጠፋዉም አልነበረም የለም ፡፡

ግና ሰርቶ መኖር አይደለም ሞቶ ለመኖር፤ ለመቀበርያ መደብ (ማረፊያ)በአገሩ በርስቱ የተከለከለ ህዝብ ዛሬ ወድብ ፣የባህር በር ቢባል መጀመሪያ …..እንዳለችዉ  ዛሬ ላይ የመኖር እና መደብ  ጉዳይ ቢል ምን ይገርማል፡፡

የሞቱትን እና የአሞራ ሲሳይ የሆኑትን እየረሳን የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት …..ምን ረባ የሚል ትዉልድ ይዞ መደብ ሳይኖር  ወደብ የቆጡን አወርድ ባይ የብብቷን እንዳይሆን …………..፡፡

“አንድነት ኃይል ነዉ ፡፡”

 

Allen!
https://amharic-zehabesha.com/archives/186701

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...