Wednesday, December 20, 2023
ከአልማዝ አሸናፊ
IMZZASSEFA5@GMAIL.COM
WYOMING, USA
ፀሐፊውን ወይም ፀሀፊዎቹን ባላውቅም ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ዛሬ ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ የሚጦቁሙትን እነዚህን ገራሚ አጭር ግጥሞች ለዚህ ዌብሳይት አንባቢዎች ማካፈል ወደድኩኝ::
----------------------------------------------
እሳትና ውሀ
የታፈነ ውሀ - በብረት ድስት ገብቶ
በጭቆና ሲኖር - ነፃነቱን አጥቶ
ስንት ስቃይ አይቶ - ታጋሽ ሆኖ ሳለ
አንድ ጉልበተኛ - እሳት የተባለ
ብረት ድስቱን ሊያግል - እየተቀጣጠለ
እራሱን አግዝፎ - ድንገት ከተፍ አለ::
ቃጠሎ ንዳዱ - ውሀው ሲበዛበት
የስቃዩ ማብቂያ - ጊዜው ሲረዝምበት
ትግስቱ ተሟጦ - የሚገነፍል ለት
የእሳቱ ግለት - ምን ያክል ቢከፋ
የታፈነው ውሀ - በምሬት ሲደፋ
ሀያሉም ነበልባል - አብሮት ነው ሚጠፋ::
(እሳት :- የአብይ አህመድ መንግስት
ውሀ:- የኢትዮጵያ ምስኪን ሕዝብ)
----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ፓለቲካችን
ፖለቲካው ሆኖ~ቅጥ ያጣ ብልሹ
መስራት ስለሚከብድ~ገብተው ሳይቆሽሹ
ልበ ቀናዎቹ~አዋቂዎች ሸሹ።
ታዲያ ምን አገኘን~እኛ በምላሹ?
ፓለቲካ እያሉ~በግላቸው አሰራር
በዘመድ በገንዘብ~ሚሆኑ አመራር
ለራሳቸው ሚመች~መንገድ ሚቀልሱ
ሀላፊ ሆኑልን~ሰዉን ሊያጫርሱ።
(ሀላፊ የተባሉት አብይ አህመድና ሹማማምንቶቹ)
---------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጊዜ የሰጠው ቅል
እንዴት አንዘን~እንዴት አንከፋ
አጭሩ ረዝሞብን~ጉራውን ሲነፋ
ቀጭኑ ደረቱን~እኛ ላይ ሲያሰፋ
ሁሉም በየፊናው~ስልጣኑን ሊያሳየን~
ሚያደርገው ሲከፋ።
እኛም እንኖራለን~ጥርሳችን እየሳቀ~
ሁሉን በሆድ ይዘን
ጊዜ የሰጠው ቅል~ትልቁን ድንጋይ (ትልቋን ኢትዮጵያ)~
ልስበር ሲል እያየን።
(ቅል:- አብይ አህመድና ግብረአበሮቹ
እኛም:- የኢትዮጵያ ምስኪን ሕዝብ)
---------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ከድጡ ወደ ማጡ
ሲበሉ አድርሰኝ
ሲጣሉ መልሰኝ
ብሎ ሁሌ ሲመኝ
ምኞቱ ተሰሳክቶ ~ የልቡ ሆኖለት
ከቦታዎች ርቆ ~ ፀቦች ከበዙበት
ሄዶ ይኖር ጀመር~ወደ ሚበላበት
መጥገብ በሌለበት
ሆድ ከማይሞላበት።
እናም የምኞቱ ~ መከራው እየባሰ
ሰላምን ፍለጋ ~ ወቶ እያሰሰ
ባለወንበሮቹ ~ ሲበሉ ደረሰ
ይብላኝልን !!
(ምኞተኛው:- የኢትዮጵያ ምስኪን ሕዝብ
በላተኞቹ :- አብይ አህመድና ሹማምንቶቹ)
https://amharic-zehabesha.com/archives/187730
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment