Tuesday, December 19, 2023
ግርማ ካሳ
ኦነግን በተመለከተ ሰዎች የተለያዩ አመለካከቶች አሏቸው፡፡ ለኔ ኦነግ ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛው ድርጅቱ ወይም ድርጅቶቹ ናቸው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አስተሳሰቡ፣ የፖለቲካ ፍልስፍናው ነው፡፡ እነ አብይ አህመድ ኦነግ ናቸው ስንል፣ ኦነግ የተባለው ድርጅት ውስጥ ያሉ ናቸው ማለታችን አይደለም፡፡ የኦነግ አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው ማለታችን እንጂ፡፡ እነ ጃል መሮና እነ ሺመለስ አብዲሳ አንድ ናቸው ስንል፣ በአንድ ድርጅት ውስጥ ያሉ ናቸው ማለታችን አይደለም፡፡ ለስልጣን ይኸው እየተገዳደሉ አይደለም እንዴ ? ነገር ግን ሁለቱም አንድ አይነት ኦነጋዊ አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው ማለታችን ነው፡፡
የኦነግን አመሰራረት ከሜጫና ቱሉም ማህበር ጋር፣ የኦሮሞ ብሄረተኞች ያገናኛሉ፡ ያ በጣም የተሳሳተ ነው፡፡ ምንም አይገናኙም፡፡ የሜጫና ቱሉማ ማሀበር በዋናነት ገበሬው የመሬት ባለቤት እንዲሆን፣ በኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጥ፣ በኦሮምኛ ቋንቋ አገልግሎቶች እንዲሰጡ፣ የኦሮሞ ቅርስ፣ ባህልን ማሳደግ እንዲቻል የሚታገል፣ ኦሮሞን ለመጥቀም፣ ለ እኩልነት የሚሰራ የነበረ ማህበር እንደሆነ ነው የሰማሁት፡፡ የሜጫና ቱሉማ ማህበር ጥያቄዎች፣ በወቅቱ መመለስ የነበረባቸው የሁሉም ዜጎች ጥያቄዎች ነበሩ፡፡
እዚህ ማህበር ውስጥ እውቁ ጀነራል ታደሰ ብሩም እንደነበሩበት ይነገራል፡፡ ጀነራል ታደሰ ኢትዮጵያን ያገለገሉ፣ ኢትዮጵያን የሚወዱ ትልቅ ሰው ነበሩ፡፡ ኔልሰን ማንዴራልና ጓዶቹ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጡ ጊዜ ስልጠና የሰጧቸው እነ ጀነራል ታደሰ ብሩ ነበሩ፡፡ ጀነራል ታደሰን አሳንሰው ፣ የኦሮሞ ብሄረተኛ አድርገው ለማቅረብ ለማቅረብ የሚሞክሩ ማፈር ነው ያላባቸው፡፡ ጀነራል ታደሰ ብሩ፣ እንደ ጀነራል ጃጋም ኬሎና ሌሎች ፣ የኢትዮጵያ ጀግና ነበሩ፡፡
በ1959 ዓ/ም በጃንሆይ ዘመን፣ ሜጫና ቱሉም ችግር ያጋጥመዋል፡፡ አመራሮቹም ይበታተናሉ፡፡ ጀነራል ታደሰ የቁም እስረኛ ይሆናሉ፡፡ በኋላ በገለምሶ አካባቢ ይታሰራሉ፡፡ የሜጫና ቱሉማ አንዱ አመራር፣ አቶ ሁሴን ሶራ ወደ ሶማሊያ ይሄዳል፡፡ በሶማሊያ ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ( ENLF - Ethiopian National Liberation Front) የሚል ያቋቁማል፡፡ ትንሽ እንቆየ፣ ኢትዮጵያ ጠሎች እየበዙ፣ የነ ሲያድ ባሬ ተጽኖ ተጨምሮበት፣ ኢትዮጵያ የሚለውን በኦሮሞ ቀይረው፣ የኦሮሞ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር፣ ONLF- Oromo National Liberation Front) የሚል ድርጅት ይፈጠራል፡፡ (እዚህ ጋር አሁን ONLF ከሚባለው የኦጋዴን ነጻ አውጭ ጋር እንዳንደባልቀው፡፡ ያኔ የኦጋዴን ነጻ አውጭ የሚባል አልነበረም፡፡ የምእራብ ሶማሎያ ነጻ አውጭ የሚባል እንጂ፡፡ ) አቶ ሁሴን ሶራ የ ONLF ዋና ጸሃፊ ሆነ፡፡ ዋና ጸሃፊ ማለት መሪ ማለት ነበር፡፡ ኮሎኔል መንግስቱ የኢሰፓ ዋና ጸሃፊ እንደነበሩት፡፡
አቶ ሁሴን ግንባራቸውን ከሶማሊያ ወደ ሃረርጌ ለማስገባት ሞከሩ፡፡ የሶማሌ ፖሊስ ችግር እንዳይፈጠር በሚል አከላከላቸው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ሞከሩ፡፡ ተሳካላቸው፡፡ አብዱል ክሪም ሃጂ ኢብራሂም በሚባለውና ጃራ አባገዳ የሚል የጦር ስም በነበረው፣ ጽንፈኛ የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን የሙስሊም አክራሪ መሪነት በሃረርጌ መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፡ ሆኖም እንቅስቃሴያቸው ተደርሶበት እርምጃ ተወሰደባቸው፡፡ ተበታተኑ፡፡ እነ ጃራም ሸሹ፡፡ ሁሴን ሶራ በየመን አድርጎ ወደ ቤህሩት ሄደ፡፡ በ1960 አካባቢ ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ የመጀመሪያው በኦሮሞ ስም የተደረገ የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ነበር፡፡ ከጅማሬው የከሸፈው የትጥቅ ትግል፡፡ሙሉ ለሙሉ የሃረርጌ ሰዎችን ብቻ ያቀፈ፡፡
እስከ 1966 ድረስ፣ በውጭ አገር ከሚደረጉ ስብሰባዎችና፣ ውይይቶች በቀር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት፣ በኦሮሞ ስም ተደራጅቶ የሚንቀሳቀስ ድርጅት አልነበረም፡፡ በየካቲት 1966 አብዮቱ ሲፈነዳ፣ ስልጣን የያዘው ደርግ በውስጥ ትልቅ ችግር ውስጥ ስለነበረ፣ በባሮ ቱምሳ አቀነባባሪነት በሚስጥር በአዲስ አበባ ስብሰባ ተደረገ፡፡ እነ ሁሴን ሶራ ከቤህሩት፣ ሌላ ደገሞ ሃሰን ኢብራሄም የሚባል፣ በየመን የኦሮሞ አክቲቪስቶችን ቤቱ ሲሰበስብ የነበረ፣ ከየመን መጥተው በስብሰባው ተካፈሉ፡፡ አሁን የሚታወቁ እነ ሌንጮ ለታ፣ ገላሳ ዲልቦ ዲማ ነግዎ የመሳሰሉትም እንደዚሁ፡፡ ያኔ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (OLF) በሃረርጌ ኦሮሞዎችና በወለጋ ኦሮሞዎች በይፋ ተመሰረተ፡፡ የወታደራዊ ዊንጉም በሃረርጌ ገለምሶ አካባቢ፣ ጨርጨር ተራራች ላይ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት OLA፣ ተባለ፡፡ ሃሰን ኢብራሄም ፣ የትግል ስሙ ኤሌሞ ቂልጦ የኦላ መሪ ተደረገ፡፡
ጀነራል ታደሰ ብሩ፣ አብዮቱ ሲፈነዳ ተፈቱ፡፡ እዚህ ጋር ልብ እንድትሉልኝ የምፈልገው፣ እነ ባሮ ቱምሳ በሚስጥር የጠሩት ስብሰባ ላይ አልነበሩበትም፡፡ ኦነግ ከሚባለው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አልነበራቸው፡፡ ሳይጋበዙ፣ ሳይጠየቁ ቀርተው አይመስለኝም፡፡ እነ ጀነራል ታደሰ ኢትዮጵያዊነታቸው ከኦሮሞነታቸው ጋር ስለማይጋጭባቸው፣ የጸረ ኢትዮጵያ ቡድን አካል የመሆን ፍላጎት ስለሌላቸው፣ ስለሌላቸው ብቻ ሳይሆን ይታገሉትም ስለነበር እንጂ፡፡
በወቅቱ ደርግ ጀነራል ታደሰ የአገር አስተዳደር ሚኒስቴርነት እንዲሆኑ ሁለት ጊዜ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡ ጀነራሉ ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ፣ ደርጎች ጥርስ ነክሰውባቸው፣ ያው ነፍሰ ገዳዮችና ዱርዬ ስለነበሩ፣ እነ ጀነራል አማን አንዶምን፣ ልጅ እንዳልካቸውን እንደረሸኑት፣ ጀነራል ታደሰ ብሩንም ገደሏቸው፡፡ የርሳቸውም መገደል ከኦሮሞነታቸው ጋር ምንም አይጋናኝም፡፡
እነ ኤሌሞ ቂልጡ ፣ ኦላዎች፣ በጨርጨር ተራሮች እንቅስቃሴ ጀመሩ፡፡ በባለስልጣናት ላይ ጥቃት ፈጸሙ፡፡ ደርግ ጦር ሰራዊት ልኮ፣ የአጸፋ ምላሽ ሰጣቸው፡፡ ተደመሰሱ፡፡ ኤሌሞ ቂልጡም ተገደለ፡፡ ኦነጎች ከጅምራቸው ከፍተኛ ውዥንብር ውስጥ ወደቁ፡፡ ያለቻቸው ትንሿ ጦር ተበታተነች፡፡
በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው፣ ያ አልበቃ ብሎ፣ ሌላ ትልቅ ችግር ኦነጎች አጋጠማቸው፡፡ ሲያድ ባሬ ኢትዮጵያን ለመውረር በዝግጅት ላይ እያለ፣ ቆቱዎች (የሃረር ኦሮሞዎች) እንዲያግዟቸው፣ ኦነጎችን ማግባባት ጀመረ፡፡ አብዛኛውን ኦጋዴን ወደ ሶማሊያ የቀላቀለ ካርታ አሳያቸው፡፡ ያኔ እነ ባሮ ቱምሳ ተቃወሙ፡፡ ወለጋዎቹ፡፡ ሃረሮቹ እነ ጃራ አባ ገዳ ከሲያድ ባሪ ጎን ቆሙ፡፡ በኦነጎች መካከል ትልቅ መከፋፈል ተፈጠረ፡፡ እነ ጃራ አባገዳ ፣ ባሮ ቱምሳን ሃረርጌ ላይ ገደሉት፡፡ ከባሮ ቱምሳ ጋር የነበሩ የኦነግ ሰዎች፣ ከሞት የተረፉት፣ ሃረርጌን ጥው፣ ወደ ቦረና ሄዱ፡፡ በሃረርጌ እስላማዊ ኦነግ፣ የነ ጃራ ኦነግ ብቻ ቀረ፡፡ ያው ብዙዎቹ የወለጋ ሰዎች ስለሆኑ፣ ከቦረና የተወሰነ ኃይል ወደ ምእራብ ወለጋ ሄደ፡፡ አብዛኛው ከፍተኛ አመራርም ከአገር ለቆ ጠፋ፡፡ ቦረና ኬኒያ ድንበር፣ ወለጋ ሱዳን ድንበር አካባቢ ፣ በየጫካ እንደ ሽፍታ ውርውር ከማለት በቀር፣ ከ1970 እስከ 1983 ዓ/ም ኦነግ የሚባል ያን ያህል ተሰምቶ አያውቅም ነበር፡፡በበርሊን፣ ሜኒሶታ፣ ግብጽ .. የኦነግ ጽ/ቤቶች አሏቸው፡፡ በውጭ ይጽፋሉ፣ ይታገላሉ፣ ይጮሃሉ፡፡ ግን አገር ቤት ሜዳ ላይ ብናኞች ነበሩ፡፡
ህወህትና ሻእቢያ ደርግን ለማዳከም በወለጋ በኩል፣ የኦነግ ሰራዊት መስለው ፣ ካሉት የኦነግ ጥቂት ሽፍታዎች ጋር በመሆን፣ በደርግ ዘመን መጨረሻ ሰሞን፣ በአሶሳ ከ200 በላይ ዜጎች በአንድ ቤት አድርገው አቃጠሉ፡፡ እንግዲህ ኦነግ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ በብዙ ህዝብ ዘንድ የተሰማው የአሶሳውን እልቂት ተከትሎ ነው፡፡ በእልቂትና በጭፍጨፋ ነው ኦነግ ለመጀመሪያ ጊዜ በገሃድ የታወቀው፡፡
ህወሃት ለአዲስ አበባ፣ ሻእቢያ ለአስመራ ሲቀርቡ፣ ኦነግም በለስ እየቀናት መጣ፡፡ ህወሃቶችና ሻእቢያዎች የአንድነት ኃይል የሚሏቸውን ለማዳከም፣ ኦሮሞን ከሌላው መለየትና የኦሮሞ ብሄረተኝነትን ማጠናከር ብቸኛ አማራጭ አድርገው ወሰዱት፡፡ ያኔ እማራ ምናምን አይባል ነበር፡፡ ለዚህ ስትራቲጂያቸው ኦነግ ስላሰፈለጋቸው ኦነግ ከነርሱ ጋር አብሮ መቀመጥ ጀመረ፡፡ አብዛኛው ኦነግ የሚፈልገውን ፣ ኦሮሚያ የሚል ክልል ተሰጠው፡፡ የላቲኑን ፊደል እንዲጠቀም ተፈቀደለት፡፡
ህወሃቶች ኦነግ ላይ እምነት ስለሌላችው፣ በአንድ በኩል ኦነግን እየተለማመጡ፣ በሌላ በኩል በብዛት የአርሲ ሰዎች የበዙበትን ኦህዴድን ማጠናከር ጀመሩ፡፡ ከሁለት አመት በኋላ፣ ኦነጎችን በካልቾ ብለው፣ አዋርደው ካባረሩ በኋላ ፣ ኦሮሚያ ብለው የሸነሸኑትን፣ ኦህዴድ እንዲያስተዳደር አደረጉ፡፡ እነርሱ ከበላይ ኦህዴዶችን እየተቆጣጠሩ፡፡
ኦነግ እንደ ድርጅት ከየውጭ አገራር ተለቃቅሞ ነበር ወደ ኢትዮጵያ የገባው፡፡ ሁለት አመት በአገር ቤት ሲንቀሳቀስ ፣ የቀድሞ ኦሮሞ የሆኑ የተበተኑ የደርግ ወታደሮች ሰብስቦ ጦር አለኝ ማለት ጀምሮም ነበር፡፡ ሆኖም በቀላሉ ህወሃቶች ጦሩን የኦነግን ጦር በተኑት፡፡ አመራሮቹም እነ ሌንጮ ወደ መጡበት ተመለሱ፡፡ እነ አብይ አህመድ ስልጣን እስኪይዙ ድረስ ኦነግ በውጭ የሚጮህ ብቻ ድርጅት ሆኖ ቀጠለ፡፡ የትጥቅ ትግል አድርጋለሁ እያለ በወያኔ ዘመን አንዲተ ቀበሌ ተቆጣጥሮ አያውቅም ነበር፡፡ አመራሮቹ የተወሰኑት በተሰነይ ፍየል ጠባቂ፣ የተቀሩት አንዲ በርሊን፣ ሌላ ጊዜ ሚኔሶታ የሚንከራተቱ ሆኑ፡፡ እርስ በርስ ተከፋፈሉ፡፡ እነ ሊንጮ ለታ፣ ዲማ ነግዎ ኦነግ ለቀው ወጡ፡፡
እነ አብይ አህመድ ስልጣን ሲይዙ፣ ልጅ ወያኔ አዲስ አበባ ስትገባ እንደሆነው አሁን የኦነግ መሪዎች ተለቃቅመው ወደ አገር ቤት ገቡ፡፡ አስመራ አለን ይሉት የነበረውም ጦራቸው ወደ አገር ቤት ገባ፡፡ አንዳንድ አመራሮቻቸው ስልጣን አገኙ፡፡ እነ ዳዎድ ኢብሳ ያለው ሁኔታ አልተመቻቸውም፡፡ በኦነግና በብልጽግና መካከል እንደገና ጠበ ተፈጠረ፡፡ መዓከላዊ መንግስቱ ደካማ ስለነበረም፣ የኦነግ ወታደራዊ ዊንግ ኦላ፣ በተለይም በወለጋና በጉጂ ጫካ ገብቶ መታገል ጀመረ፡፡ አሁን ኦላ በብዙ ቦታ ውጊያ እያደረገ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ይኸው አምስት አመት ሆነ እየተዋጋን ነው ማለት ከጀመሩ፣ የሚጨበጥ ውጤት ያመጡበት ሁኔታ የለም፡፡
ኦነግ እንደ ድርጅት እዚህ ግባ የማይባል ቢሆንም፣ አንድ የተፈጠረ ግን ትልቅ አደገኛ ነገር ነበር፡፡ ኦነግ ከአገር ቤት በነ አቶ ስዬ አብርሃ ሲባረር፣ የኦነግ ፖለቲካን፣ የኦነግን አስተሳሰብ ግን ኦህዴዶች በኦሮሞ ክልል ሙሉ ለሙሉ ተግብረዉታል፡፡ እነ ዳዎድ ኢብሳ፣ ሌንጮ ለታ ባይገዙም፣ በነርሱ ርዮት አለም ነበር ኦህዴዶች ሲገዙ የነበሩት፡፡
ወያኔ አዲስ አበበ ከገባች 32 ዓመት ሆነ፡፡ ያኔ 8 አመት የነበረ ሰው፣ አሁን 40 አመት ይሆናል፡፡ ምን ማለት ነው ከ40 አመት በታች ያሉ ኦሮሞዎች በኦነግ አስተሳሰብ ነው ያደጉት ማለት ነው፡፡ የቁቤ ትውልድ የምንላቸው፡፡
ይህ የኦነግ አስተሳሰብ ደግሞ በጥላቻ ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ ነው፡፡ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የሚጠላ አስተሳሰብ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ሰንደቅ፣ የኢትዮጵያ ፊደል፣ ኢትዮጵያን የሚያሳይ ማናቸውን ነገር የሚጠላ አስተሳሰብ፡፡ አማራ ኢትዮጵያ የሚል ስለሆነ፣ የኦነግ ፖለቲካ አማራን በመጥላት ላይ ያተኮረ ፖለቲካ ነው፡፡
የነ ጀነራል ታደሰ ብሩ ሜጫና ቱሉም አጀንዳ ኦሮሞን በመጥቀም ፣ ኦሮሞን empower በማድረግ ላይ የተመሰረተ PRO OROMO አጀንዳ ነበር፡፡ የኦነግ አጀንዳ ግን ኢትዮጵያዊ የሆነን ነገር በመጥላት ፣ በተለይም አማራ፣ አማርኛ በመጸየፍ ላይ ያተኮረ፣ ANTI AMHARA፣ ANTI ETHIOPIA የጥላቻ አጀንዳ ነው፡፡
ይህ የኦነግ አስተሳሰብን አጀንዳው ያደረገ የቁቤ ትውልድን ፣ ራሳቸው የቀድሞ የኦነግ አመራሮች፣ እነ ሌንጮ ለታ ፣ ዲማ ነግዎ ሊቆጣጠሩት የሚችሉት ነገር አልሆነም፡፡ እነርሱ ቀላል መስሏቸው፣ በጀርመን ሚሺነሪዎች ሆይ ሆይ ተብለው፣ የቀሰቀሱት እሳት፣ መልሶ ኦሮሞን እያቀጠለው መሆኑን እያዩ ፍርሃት ውስጥ የወደቁበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
ይህ የኦነግ አስተሳሰብ ስር ሰዶ፣ ጭፍጨፋዎችን ፣ መፈናቅሎችን፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች፣ ጦርነቶች ቀስቅሷል፡፡ ይህ የኦነግ የዘርና የጥላቻ ፖለቲካ የኦሮሞ ማህበረሰብ በቀጥታ ከሌላው ማህበረሰባት ጋር እንዲጋጭ፣ እንዲካረር፣ ደም እንዲፋሰስ፣ በሌሎች ማህበረሰባት እንዲጠላ፣ እንዲፈራ፣ እንደ ጭራቅ እንዲታይ እያደረገ ነው፡፡ የኦነግ አስተሳሰብና ፖለቲካ፣ አብሮነት፣ እክሉነት፣ መቻቻል፣ ፍቅር፣ አንድነት የሚሉትን ቃላቶች አያውቅም፡፡ የዚህ አስተሳሰብ ሰለባ የሆኑ ብዙ ወጣቶችም፣ እራሳቸውንም፣ አገርን ገደል ውስጥ እየከተቱ ነው፡፡
የኦሮሞ ልሂቃን፣ ነገሮችን እናገናዝባለን የሚሉ ፣ በርግጥም የህዝብ ጥቅም የሚአስቀድሞ ቆም ብለ ማሰብና ነገሮችን ማስተካከል አለባቸው፡፡ የተበላሸ አይምሮ እንዲፈወስ መስራት አለባቸው፡፡ የኦነግ አስተሳሰብ ናዚዛዊ፣ ሰይጣናዊና ክፉ አስተሳሰብ ነው፡፡ ከዚህ አስተሳሰብ በቶሎ መውጣት ባይቻልም፣ መውጣት እንዲቻል ማስተማር መጀመር አለበት፡፡
አገር ለሁሉም ትበቃለች፡፡ የነርሱ መብት እንዲከበር እንደሚፈልጉት የሌላውን መብት ማክበር መቻል አለባቸው፡፡ እነርሱ ከማንም አናንስም እንደሚሉት፣ ከሌላው እነርሱ እንደማይበልጡ ማወቅ አለባቸው፡፡ እነርሱ ራሳቸው ከደቡብ ባሌ መጥተው ሰፋሪና ወራሪ እንደነበሩት፣ ሌላው መጤ፣ ወራሪ የማለት አምስት ሳንቲም መብት የለቸውም፡፡
ተከባብረን እንኑር፡፡ ከኦነግ ፖለቲካ፣ ከኦነግ አስተሳሰብ ስካራቸው ሰከን ያድርጉ፡፡ ይሄ ኦሮሚያ ክልል ታግለው ያመጡት አይደለም፡፡ ህወሃት ጠፍጥፎ የሰራላቸው አፓርታይዳዊ ክልል ነው፡፡ ህወሃት እስኪመጣ ድረስ በታሪክ ኦሮሚያ የሚባል ኖሮ አያውቅም፡፡ በመሆኑ ይህ ዘረኛ ክልል ምፍረስ አለበት፡፡ አምራዎች፣ ጉራጌዎች፣ ሶማሌዎች ሌሎች በብዛት የሚኖርባቸውን አካባቢዎች የኦሮሞ ነው በሚል ፌዝ፣ ኦሮሚያ ያውስጥ አጠቃለው ፣ ሌላው እየገፉ የሚኖሩበት ጊዘ አክቷሟል፡፡ ይሄን ማወቅ አለባቸው፡፡ ክልሉ አይፈርሱም፣ ደም እንፋሰሳለን ካሉ፣ እንግዲህ ለዚያም ይዘጋጁ፡፡
https://amharic-zehabesha.com/archives/186665
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment