Thursday, June 1, 2023

ካላመረርን፣ ካልጨከንን እንጠፋለን - ግርማ ካሳ
ይህ ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረ ኤሊያስ ወረዳ ነው፡፡ ራሱን መከላከያ ነኝ ብሎ የሚጠራው ኦነጋዊ አሸባሪ ሰራዊት በከባባድ መሳርያና በድሮች፣ ከርቀት ቤተ እምነቶችም፣ ገዳማትን በዚ መልኩ እያወደመ ነው፡፡ መንኮሳት እየሞቱ ናቸው፡፡ ይሄ ሉ ሲያደርግ፣ ከደጀን ወደ አማኑእል ባለው መንገድ መንገዶች ታጣቂዎችንና ከባባድ መሳሪያዎች አስጨኖ ፣ ያለ ምንም ችግር በማመላለስ ነው፡፡

የስደት ኑሮ የጀመርኩት ከ30 አመት በፊት ነው፡፡ በ23 ዓመቴ፡፡ ወጣት እያለሁ፡፡ እስከ ምርጫ 97 ድረስ ብዙም በአገር ጉዳይ ትኩረት አልሰጥም ነበር፡፡ በ97 ነው እንደ አጋጣሚ አዲስ አበባ ስለነበርኩ፣ የተግባረ እድ ተማሪዎች በሰደፍ ሲደበደቡ አይቼ፣ እንዲህ አይነት ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ እስኪቆም የድርሻዬን አበረክታለሁ ብዬ በአገር ጉዳይ መንቀሳቀስ የጀመርኩት፡፡

ከ97 ጀምሮ በነበረኝ እንቅስቃሴ በሰላማዊ ትግል ብቻ የማምን ሰው ነበርኩ፡፡ ያኔ ወያኔዎች ጋር የነበረን ችግር የፖለቲካ፣ የዲሞክራሲ ችግር ነበር፡፡ በወያኔዎች ጊዜ አንድ ሰው አርፎ ፣ ከፖለቲካው ርቆ ከተቀመጠ ማንም አይነካዉም ነበር፡፡ በወያኔዎች ጊዜ አሁን መብት ይረገጥ ነበር፣ ግን መኖር ይቻል ነበር፡፡ በማንነት ግድያ አልነበረም፡፡ መፈናቀል አልነበረም፡፡ ምንም ዜጋ በማንኛውም የአገሪቷ ግዛት ያለ ምንም ችግር ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ስለዚህ በሰላማዊ ትግል ለውጦች እንዲመጡ ማድረግ ይቻላል በሚል ሰላማዊ ትግል ነበር የምደግፈው፡፡ህወሃት ወደ መቀሌ የተሰናበተችው በሰላማዊ የ እምቢተኝነት ትግል ነበር፡፡

አሁን የተለየ ነገር ነው ያለው፡፡ አሁን ጉዳይ የፖለቲካ መብትን፣ የዴሞክራሲ ጥያቄን የማከበርና ያለማስከበር አይደለም፡፡ ጉዳዩ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው፡፡ አሁን አራት ኪሎ ያሉት መብት የሚገፉ ብቻ ሳይሆን የሚያስጨፈጭፉ፣ የሚጨፈጭጭፉ አረመኔዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ክፉና ጨካኝ፣ ናዚዛዊና ዘረኛ ቡድኖችን በማንኛውም መንገድ መታገልና ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ሊገድሉ ሲመጡ መግደልንም ጨምሮ፡፡

"ጸሎት ነው የሚያስፈልገው፣ ጦርነት አያስፈልግም፡፡ ውጊያ አያስፈልግም፡፡ መገዳደል አያስፈልግም፡" ብለው ሞራሊቲንና ሃይማኖትን ሊሰብኩ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ፡፡ ""ሽምግልና፣ እርቅ" የሚሉ፡፡ ገዳዮች ሲገድሉ ዝም ብለው፣ የሚገደለው አልገደልም ብሎ እርሱም መግደል ሲጀምር ፣ስለ ሰላም ማውራት፣ ከገዳይነት በምንም አይተናነስም፡፡ ግብዝነትና አደርባይነት ነው፡፡

ክርስቲያን ነኝ፡፡ የክርስትና እምነቴ በህይወቴ እጅግ በጣም ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ሰው ሲጎዳ ዝም አልልም በሚል በገር ጉዳይ እሳተፍለሁ እንጂ፣ ከምን ነገር በላይ የሚያስደስተኝ ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ቃለ አምላክን ማዳመጥ፣ ቃለ አምላክን ማካፈል፣ መዝሙሮች መስማትና መዘመር ነው፡፡ የሰላምና የእርቅ አስፈላጊነት በሚገባ እረዳለሁ፡፡ ግን ለሁሉም ነገር መርህ ያስፈልጋል፡፡

ለነዚህ ሰዎች አንድ ጥያቄ ላቅርብላቸው፡፡ ቤታቸው ተቀምጠዋል፡፡ መሳሪያ አላቸው፡፡ የታጠቁ፣ የመንግስት ደህንነቶች ነን የሚሉ፣ የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ፣ የቤት በር ሰብረው ይገባሉ፡፡ ወንድ ልጆችን እየደበደቡ ይወስዳሉ፡፡ ሚስቶቻቸውንና ሴት ልጆቻቸውን ለመድፈር ይነሳሉ፡፡ ምንድን ነው የሚያደርጉት ? ጸሎት ማድረግ፣ ሰዎቹን መለመንና መለማመጥ፣ ከዚያ በኋላ ሰዎቹ ያደረጉት ወንጀል ፈጽመው፣ "ወንድ ልጆቼን ወሰዱብኝ፣። ሚስቴንና ሴት ልጆቹእ ደፈሩብኝ" ብሎ ማለቃቀስና እንደ ኢትዮ360 ያሉ ሜዲያዎች ጋር ደውሎ ብሳቶ ማሰማት ነው ???? ቤታቸው ያለውን መሳሪያ ተጠቅመው ሌላው ቢቀር የሚስቲቻቸውንና የሴት ልጆቻቸውን ክብር አያስጠብቁም ???

ቤታችን ቅያችን፣ ሰፈራችን፣ አካባቢያችን፣ በበአሸባሪዎች፣ በዘረኞች፣ በክፉዎች፣ በናዚዎች፣ በጨፍጫፊዎች ሲደፈር፣ መሳሪያ ያለን መሳሪያችንን ወልውለን፣ የሌለንም በእጃችን እየቧጨርን፣ ሌላው ቢቀር ራሳችንን ማዳን ባንችልም፣ ልጆቹን፣ ሚስቶቻችንን አረጋዊ እናትና አባቶቻችን ማዳን መቻል አለብን፡፡

ደግሞ እመኑኝ፣ ሁሉም ሰው በሁሉም ቢታ ካመረረና ከጨቀነ፣ ከተነሳ እነዚህ ጉጅሌ የኦነግ/ኦህዴድ አሸባሪዎች፣ የአብይ አህመድና የኢጆሌ ጁላ ታጣቂዎች እንደ ጉም ነው የሚተኑት፡፡

ይህ ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረ ኤሊያስ ወረዳ ነው፡፡ ራሱን መከላከያ ነኝ ብሎ የሚጠራው ኦነጋዊ አሸባሪ ሰራዊት በከባባድ መሳርያና በድሮች፣ ከርቀት ቤተ እምነቶችም፣ ገዳማትን በዚ መልኩ እያወደመ ነው፡፡ መንኮሳት እየሞቱ ናቸው፡፡

ይሄ ሉ ሲያደርግ፣ ከደጀን ወደ አማኑእል ባለው መንገድ መንገዶች ታጣቂዎችንና ከባባድ መሳሪያዎች አስጨኖ ፣ ያለ ምንም ችግር በማመላለስ ነው፡፡
https://amharic-zehabesha.com/archives/183068

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...