Thursday, June 1, 2023

"አማራን በጥበብ የተደራጀ ኃይሉን እንዲበተን አድርገንበታል!" ጌታቸው ረዳ




ትንጊርቱ ገብረፃዲቅ ተክሌ

የኔ ምልከታ፦

የፋሺሽቱ አገዛዝ የአማራ ህዝብ ላይ ይፋዊ ጦርነት እንዲያውጅ ክፉ ምክር የሆነ አካል መክሮት ሊሆን እንደሚችል እንገምት ነበር። በርግጥ የፋሺሽቱ ቡድን በራሱ ህዝብ ላይ ጦርነት ማወጅን ስራው ስላደረገው በዚህ ረገድ መካሪ አያሻውም።

የሆነ ሆኖ ይህ የእብደት ውሳኔው አገዛዙን ከወደማይጣው ጣጣ ውስጥ ከቶታል። እንሆ አስር ነጥቦች፦

አንድ፦ ፋኖንና አማራን ትጥቅ እናስፈታለን ብለው በህዝብ ላይ ጦርነት ያወጁት እብሪተኛ ጀነራሎች ባልጠበቁት ሁኔታ ፋኖንና የአማራን ህዝብ ድጋሚ ደጁ ድረስ ሄደው ከባድ መሳሪያ ሳይቀር አስታጥቀውታል፤

ሁለት፦ መከላከያውን እንደ ተቋም ብቻ ሳይሆን ዩኒፎርሙንም ጭምር የሚያከብረውን የአማራን ህዝብ በእብሪት ጦርነት አውጀውበት ለመጀመሪያ ግዜ በታሪኩ በተቋሙ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥና የተቋሙን ዘረኝነትና አድሏዊነት በተግባር እንዲረዳ በማድረግ ውለታ ውለውለታል፤

ሶስት፦ ከጦርነቱ በተጨማሪ የፋሺሽቱ አገዛዝ ገበሬው የማዳበሪያና የዘር አቅርቦት እንዳያገኝ በማድረጉ ወጣቱንና አርሷደሩ ወደ ህልውና ተጋድሎው በፍቃዱ እንዲቀላቀል በማድረግ ተጨማሪ ውለታ ውለዋል፤

አራት፦ አስበውም ይሁን ሳያስቡት የነብስ ወከፍ ትጥቅ ያልነበረውን ወጣት እና አርሶአደር ሁሉ ሚሊሻ ሆነህ ፋኖን ተዋጋ በሚል ቅዠት ተጨማሪ ትጥቅ በማስታጠቅ የዳበረ አቅም እንዲፈጠር አድርገዋል፤

አምስት፦ የአገዛዙ የጥፋት ጦርነቱ ህዝባዊ ሀይሉ የአገዛዙን አቅም በሚገባ እንዲረዳና በዛውን መጠን እንዲዘጋጅ እድል ተፈጥሮለታል፤

ስድስት፦ይህ የእብሪት ውሳኔ ከአማራው ውጪ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብም በአገዛዙ ላይ ፈጽሞ ተስፋ እንዲቆርጥና የአገዛዙንም አቅም በሚገባ እንዲረዳ አድርጎታል፤

ሰባት፦ ጦርነቱ የአማራውን አንድነት ከምንጊዜውም በላይ አጠናክሯል፤

ስምንት፦ አማራ እያደረገ ያለው ተጋድሎ ከአገዛዙ በተጨማሪ ሌሎች በቀጠናው ላይ የተለየ ፍላጎት ያላቸውን ሀገራትም ጭምር አማራ በኢትዮጵያ ውስጥ ተገዳዳሪ የፖለቲካ ሀይል ሆኖ እየመጣ መሆኑን ሳይወዱ በግዳቸው እንዲረዱና መነጋገር እንዲጀምሩ አድርጓቸዋል፤

ዘጠኝ፥ ጠንካራ የአማራ የፖለቲካ ሀይል እንዲወለድና ህዝባዊ ተቀባይነት እንዲያገኝ ጦርነቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፤

አስር፥ በመጨረሻም አቶ ጌታቸው ረዳ እንደተናገሩት ሳይሆን በተቃራኒው ጦርነቱ የአማራ ሰራዊት በተጠናከረ ቁመና ላይ እንዲገኝና የጸና አንድነት በመካከሉ እንዲፈጠር ያስቻለ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ መግለጽ ያስፈልጋል።

ነጻነታችን በፋሺሽቶች ችሮታ ሳይሆን በምናደርገው ተጋድሎ ብቻ ይረጋገጣል!
https://amharic-zehabesha.com/archives/183081

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...