Friday, June 2, 2023
በወቅታዊ የሀገራችን ኢትዮጵያ ጉዳይ
የዳግም ትግል አንድነት እና አጋርነት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
እንደሚታወቀው ለ27 አመታት የነበረውን ዘረኛ የህወሓት አገዛዝ ለመቀየር እና በምትኩ ፍትህ እኩልነት ነፃነት እና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆ የጎሣ ሥርዓት ተወግዶ መልካዓምድራዊ አስተዳደር ለመመስረት ከመሰል አላማና ግብ ካላቸው ድርጅቶች ጋር ስንታገል መቆየታችን ይታወሣል:: በሕዝባዊ አመጽ እና ከውስጥም ከውጭም በተቀናጀ የተቃውሞ ትግል ዘረኛውን የሕወሃት አገዛዝ ከስሩ ነቅሎ ለማስወገድ ሕዝባችን በተቃረብንበት ወቅት ከአሮጌው አገዛዝ ውስጥ በወጡ የራሱ ሰዎች ለውጡ ተቀልብሶ ጥገናዊ ለውጥ ተደረገ ።
በአጋጣሚው ወደ ስልጣን የወጣው የአብይ አስተዳደር ሕዝባችን እና የተቃዋሚ ድርጅቶች በነበረው የነፃነት ጥማት ሙሉ ድጋፍ አግኝቶ በዓለም ለይ በየትኛውም ሀገር ታይቶ በማይታወቅ ከፍተኛ አድናቆት አግኝቶ ነበር:: ሆኖም ከህወሓት የፖለቲካ ፕሮግራም ያልዘለለውን ህገመንግስት እና ያለአግባብ የተቀየረውን የሀገራችንን ታርካዊ ሰንደቅ ዓላማ እንኳን በቦታው ሳይመልስ ቆይቶ ከዕለት ዕለት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገውን ሃገራዊ አንድነት ትቶ ወደ ከፉ ተረኛ የጎሣ ፖለቲካ ወርዷል:: በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዜጎች በዘራቸው ተለይተው ሲፈናቀሉና ሲገደሉ ማየትና መስማት የዕለት ተዕለት ዜና ሆኖአል ። በመሆኑም እኛ "የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት" የሰሜን አሜሪካ ተጠሪዎች ። ከጊዜ ወደ ጊዜ ከምናያቸው ሁኔታዎች መንግስት ይታረማል በሚል ጊዜ ስንሰጥና ስንከታተልና አልፎም ተርፎም መንግስትን ለማገዝ ስንሞክር ቆይተናል:: ሆኖም በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ፖለቲካዊና መንግስታዊ መዋቅሩ አቅጣጫውን ስቶ መበላሸቱን በማመን ዳግም ወደትግል ለመመለስ ተገደናል ። በመሆኑም መሠል የትግል አላማ ካላቸው ድርጅቶች ጋር በሀገራችን ኢትዮጵያ ጉዳይ መሥራቱ ወቅቱ የሚጠይቀው አማራጭ የለለው ጉዳይ ሆኖ አግኝተናል ። በመሆኑም አዲስ ለተቋቋመው የአማራ ሕዝባዊ ግንባር (አሕግ) የትግል አጋርነትና ድጋፋችንን መስጠታችንን የደቡብ ምዕራብ ሕዝብም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አውቀው ከጎናችን እንድትሰለፉ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።
ግልባጭ :- እንዲአውቁት " ለአማራ ሕዝባዊ ግንባር"
ፍትህ እኩልነትና ነፃነት ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
ደ ም ኢ ሕ ህ
ሰሜን አሜሪካ =====
https://amharic-zehabesha.com/archives/183097
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment