Friday, June 2, 2023
ወያኔ ኢትዮጵያ ጥሩ ዜጋ እንዳይወጣላት በርትቶ ከሰራባችው ጉዳዮች አንዱ ወጣቱን የማሰብ አቅሙን ማዳከም በማቴሪያላዊ ኑሮው እንዲያተኩርና ረብ በሌለው አስተሳሰብና እምነት መበረዝ ነበር። ይሄም የሚተገበረው ወጣቱ በጠንካራ እውቀት ተገንብቶ እንዳያድግ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ሰበዞች በርትቶ መምዘዝን ያካተተ ነበር። ለዚህ ለክፋት ፕሮጀክት ከተመረጡት መሃል ዮናታን አክሊሉ አብይ አህመድ ሽመልስ አብዲሳ ጁዋር መሃመድ አህመዲን ጀበል አወል አሎ የመሳሰሉት ይገኙበታል።
እንደ ፕሮፌሰር ሓይሌ ላሬቦና ፤አቻምየለህ ታምሩን የመሳሰሉ ወገኖች አብይ አህመድ በህወአት ንጥረ ነገር ተበጥብጦ ተቦክቶ የተጋገረ በመሆኑ ከህወአት አስተሳሰብ ልውጣ እንኳን ቢል ስሪቱ ስለማይፈቅድለት ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል ረጋ በሉ ቢሉንም በወቅቱ በአብይ ፍቅር አብደን ኢትዮጵያን እንዲያጠፋ ፈቃድ ሰጠነው።
ከላይ ያተትነውን በማዛመጃነት እንጅ የዛሬው ባለጉዳያችን እስከ ሙሉ ክብሩ ፓስተር ነብይ ዮናታን አክሊሉ ነው ። ስለ ዮናታን አክሊሉ ማንነት ሲዳሰስ ግለሰቡ ክብረ መንግስት ተወልዶ ነገሌ ቦረና ከማደጉ በስተቀር ወያኔ ስለሰጠው ስልጠና በዚህ አጭር ጊዜ አዘጋጅተን ማቅረብ አልቻልንም። ይህ ግለሰብ የትምህርት ዝግጅቱን በተመለከተ ከራሱ አንደበት እንደሰማነው በአንድ ወቅት የታሪክ ተማሪ መሆኑን ሲናገር በሌላ ጊዜ ደግሞ የፋይናንስ ተማሪ መሆኑን ገልጿል። የትምህርት ስልጠናውን ማወቅ አስፈላጊ ባይሆንም መጭውን ጊዜ እተነብያለሁ ለአምላክ ይሁን ለሌላ መንፈስ የቀረብኩ ነኝ የሚል ነብይ ያልተጣጣመ ነገር ሲናገር ሊታለፍ ስለማይገባ አደባባይ ላይ ገሃድ መውጣቱ ግድ ይላል።
መጽሃፉ የሚለው “ወደ አለሙ ዳርቻ ሂዱ ወንጌልንም ስበኩ ያላመኑትንም በስሜ አጥምቁ” ነው በተጻራሪው ዮናታን አክሊሉ ወደ መድረክ ሲወጣ አፉን የሚያሟሸው የክርስትና እምነት አንዱ ክንፍ በሆነው ቀዳማዊውን ኦርቶዶክስን በመስደብ በማንቋሸሽና በማንጓጠጥ ነው። የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጥልቅ ዶክተሪኑን ለጊዜው ወደ ጎን ትተን ኦርቶዶክስ በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድነትና ሶስትነትን የሚያምን ሲሆን የነዮናታን አክሊሉም አዲሱ እምነት ክርስትና ከሆነ ይህንን ያምናል ብለን እንገምታለን። እነ አቶ ዮናታን አክሊሉ ስንል (እነ አቶ ግርማ ዘውዴ፤እነ ወ/ሮ ሶፍያ ሽባባውን እነ አቶ አብይ መሃመድን እስከ ባለቤታቸው፤እነ እስራኤል ዳንሳን እዩ ጩፋን የመሳሰሉትን ያካትታል)። እነዚህ መዳን በኛ እምነት ብቻ ነው ብለው በሰላም የሚኖረውን ክርስቲያን የሚያጨናንቁት የባእዳን ተወካዮች በነሱ ሃይማኖት ስም 47000 የተለያዩ ዲኖሚኔሽኖችን መኖራቸውን ስንቶቻቸው እንድሚያውቁ ማወቅ አስቸጋሪ ነው። ለነገሩ ይህንን የሚመረምሩ ተከታዮች ስለሌሉዋቸው ባእዳን የሚሰጡዋቸውን ሁሉ ሳያላምጡ የሚውጡ በመሆኑ እውቀትን ለማጥራት ብዙም ግድ የላችውም። እንግዲህ እነዚህ ስብስቦች ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ሌት ተቀን ክአለቆቻቸው ጋር ከሚደክሙ ከኦርቶዶክስ በፊት የእነሱን የተበታተኑ ሃይማኖቶችን ወደ አንድ ቢያመጡ ምክንያታዊ ይሆን ነበር እንላለን። በአንጻሩ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ግን አንድ ሁኖ ልዩነት ሳይኖረው በሃገሩ ስም ተቀጥላነት ብቻ ይጠራል (የግብጽ ኦርቶዶክስ/የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ/የራሽያ ኦርቶዶክስ/የግሪክ ኦርቶዶክስ.....)Centre for Global Christianity at Gordon-Conwell Theological Seminary, which is evangelical Protestant, estimates that there are currently 47,000 denominations.
እነ አቶ ግርማ ዘውዴና ዮናታን አክሊሉ ካምፓኒያቸውን ጨምሮ የሚመጻደቁበት ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሃፍ ቅዱስም ፈረንጅ ለወረራና ለቅኝ ገዥነት ሊጠቀምበት ታትሞ የወጣው በ1611 አ.ም ነበር። በአንጻሩ ዮናታን አክሊሉና የፈረንጅ የመንፈስ ልጆች የሚያላግጡበት ኦርቶዶክስና መጽሃፉ መሰረት ይዞ ክርስትናን መስበክ የጀመረው ፈረንጅ በሰጣቸው መጽሃፍ ቅዱሱ ውስጥ ዘመኑ ስለተካተተ ሌላ ማስረጃ ያስፍልጋቸዋል ብለን አንገምትም። እዚህ ላይ አሜሪካዊዉ ማርቲን ሉተር ኪንግ የተናገረውን መጥቀስ ግድ ይላል እነ ፈረንጅ አምላኪዎች ሊገባቸው ከቻለ። እንደ ኪንግ አባባል ክርስትና ቴርሞ ሜትር ሳይሆን ቴርሞ ስታት ነው። ያ ማለት የተቀበለውን ተቀብሎ የሚያስተላልፍ እንጅ ይሄ ለእኔ አኗኗር ዘዬ የተመቸ አይደለም ብሎ መቀነስም መጨመርም የሚታሰብበት አይደለም ይህም በዮሃንስ ራእይ ተካትቷል። ስለዚህ ነገሮች በጊዜ ሲለኩ ኦርቶዶክስ የፕሮቴስታንት አባት ይሆናል ማለት ነው ኦርቶዶክስ ፕሮቴስታንትን ያርም እንደሆን እንጅ ፕሮቴስታንት ወደ ላይ ማንጋጠጥ አይችልም።
ዮናታን አክሊሉ ጊዜው የሚፈልገው ጩሉሌ ሰው ነው ሲናገር ይዋሻል፤ሲታመን ይከዳል። ገንዘብና ስልጣን የት እንዳለም ጠንቅቆ ያውቃል ስብከቱም የተነጣጠረው ተጋላጭነት ባላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ነው። ስብከቱም የሚያተኩረው ከሞት በኋላ ስላለው ህይወትና ስለ ደህንነት ሳይሆን በስጋዊው አለም ላይ ያተኮረና የሚያቋምጥ(tantalized) ተስፋ ለተክታዮቹ በመስጠት ነው። ለዚህም ጎበዝ ጎብዝ ስልጠና የወሰዱ ተዋንያንን ከጎኑ አሰማርቷል እነሱም ሲክዳቸው ብቅ እያሉ ጉዱን ዘክዝከውታል። በአንድ የዩ ቲዩብ ስርጭት ዳግም የተባለ ወጣት ከዮናታን አክሊሉ ጋር የተዋዋልነውን ውሌን አፍርሶብኛል አገር ይዳኘኝ በማለት ክአንድ ጋዜጠኛ ጋር ውይይት አድርጎ ነበር። ይህ ወጣት ከነብይ ዮናታን አክሊሉጋር የነበረው የኮንትራት ውል ወጣት ዳግም በዮናታን አክሊሉ ስብከት ተፈውሻለሁ ብሎ አስመስሎ መተወን ሲሆን አቶ ዮናታን አክሊሉም በመድረክ ለተጫወተው ትወና መኪና ማስረከብ ነበር። ሆኖም በሚያሳዝን ሁኔታ የድካሙን ሳይሰጠው ቀርቷል።
ወደ አቶ ዮናታን አክሊሉ የሚተምመው ጀማ ኦርቶዶክስ በአቶ ዮናታን አክሊሉ ከተብጠለጠለለት በኋላ ሞቅ ባለ በአደንዛዥ ሙዚቃ ጀማው ሲደነዘዘ (hypnotized) ነብይ ዮናታን ከላይ በፋክስ የተላለፈለትን መልእክት በቀጥታ ስርጭት ፈቅደው ለመደንዘዝ ለመጡ ተስፈኞቹ እንዲህ ሲል ያስደምጣል፦
“በገንዘብ ማጣት ህይወትህ የተመሰቃቀለው ጠይም ወጣት 3000000 ብር ሰተት ብሎ ሂሳብህ ውስጥ ሲገባ ይታየኛል”
“መልክሽ ቀላ ያለው እህት ልጅ ለመውለድ ብዙ ሞክረሽ ተስፋ የቆረጥሽ ዛሬ ጸሎትሽ ተሰምቷል ማህጸንሽ ጤናማ ወንድ ልጅ ይዟል”፤
“በስተግራ ካላችሁት መሃል ባል ለማግባት አይነ ጥላ የተጋረደብሽ ከዛሬ በኋላ ያ መንፈስ ተሰብሯል ሃብታም ባል ታገቢያለሽ”
“ከመሃል ወደ ቀኝ የተቀመጥከው ስራ ለማግኘት ብዙ ብትጥርም አልሆንልህ ያለው በቅርብ ጊዜ ስራ ተቀጥረህ በስልጣን መስላል ተወጣጥተህ ትልቅ ሰው ትሆናለህ”፤
“ከወደ መጨረሻ አካባቢ የተቀመጥከው ውጭ ሃገር ለመሄድ ሞክረህ ያልተሳካልህ የተጣለብህ ጥላ ዛሬ ተገፍፏል”
በማለት ትምቢቱን በማጽናት ተስፈኞቹን ከባጥ በላይ ያስጨበጭባል አንባቢ እንደሚያስታውለው እነዚህ ትምቢቶች ባለቤት ስለሌላቸው ሁሉም ለእኔ ነው በሚል ግምት የተስፋ ዳቦውን መጋጥ ይጀምራል። ታዲያ እነዚህን የተረጋገጠ ባለቤት የሌላቸውን የተስፋ ትንቢቶች አጅሬው ካበሰረ በኋላ አዳራሹ በአሜን፤ በሃሌ ሉያ፤ በልቀሶና በደስታ ድብልቅልቁ ሲወጣ ይህ ስሜት ሳይበርድ መባ ሰብሳቢዎች እየዞሩ ትንቢቱ ለኔ ነው ከሚል እሳቤ ተከታዮቹ ያላችውን አራግፈው እነ ዮናታን ቋት ውስጥ ይጨመራሉ እነ ዮናታንም እየሳቁ እያሾፉ ጀማውን ሳምንት ለጸሎት እንዳትቀሩ ብለው ይሸኟቸዋል ይህ ነው እንግዲህ እየተደረገ ያለው። ጎበዝ ይህ አሰራር ከጥንቆላ (ከታምራት ገለታ) ምን ይለየዋል?
በውነቱ ህግና ስርአት ያለበት አገር ቢሆን እነዚህ ማጅራት መችዎች ቦታቸው ከርቸሌ ሁኖ ህብረተሰቡም እረፍት ባገኘ ነበር። አረመኔው ህወአት እንኳን ታምራት ገለታን ቆልፎበት ነበር አዲሶቹ መሪዎቻችን ግን በአንጻሩ ዜጋን እንዲያታልሉ ልዩ ፍቃድና ቦታ ከማግኘታቸው ባሻገር የቤተ መንግስቱም ባለሟል ሁነዋል።
መቼም የአቶ ዮናታን አክሊሉ ትያትሩ ተነግሮ አያልቅም ደግነቱ እያንዳንዱ ትምህርቱ ትቢቱም ሆነ ትምቢቱ አማተር ተዋንያን መሆኑን ከማሳየት ባሻገር አብዛኛው አላዋቂነቱን የሚያሳብቅበት ነው።በአንድ ትያትሩ ኦርቶዶክስን ለማንጓጓጠጥ ነጠላ ለብሶ መቋሚያ ይዞ አጎንብሶ ሲያላግጥና በእውቀት የተጎዱ ተከታዮቹንም ሲያስፈነድቅ ተመልክተናል አይ ድንቁርና ደጉ። ዮናታን አክሊሉ ሊያገናዝብ ያልቻለው መቋሚያው አቅመ ደካምች የኦርቶዶክስ ምእመናን ከክርስቲያን ህብረት ጋር ሆነው ጸሎት ለማድረስ፤ንስሃ ለመግባት፤ትምህርት ለመማር በመቋሚያው ተደግፈው ቆመው የጌታን ቃል ለመስማት ነበር አላማው። ታዲያ ይህ አድናቆትን ያሰጣቸዋል እንጅ ይላገጥባቸዋል? አለባበሳቸውን በተመለከተ ነጠላውና ኦርቶዶክሳዊው አለባበስ ደግሞ በማቴሪያል እቃዎች ምእመኑ እንዳይሰለብ ከደምብ በወጣ አለባበሳቸውም ሌሎች እንዳይሰናከሉ ታስቦ ነው።
በአንጻሩ የነ ዮናታን አክሊሉ ቸርች (ቤተክርስቲያንን አይወክልም ምን ማለታቸው እንደሆነም መረዳት ይክብዳል) አለባበስ ሴቶቹ ማይክሮ ሚኒ ቀሚስ እየለበሱ ወንዶቹም ወንድነትን በሚያሳይ ጥብቅብቅ ባለ አለባበስ በመታየት ከመንፈሳዊ እሳቤ ይልቅ ወደ ሴክሹዋላይዜሽን ያተኮረ ሆኖ ተቃራኒና ተመሳሳይ ጾታዎች የሚሳሳቡበት መጤ የአለባበስ ዘይቤ ነው። ይህንን ኦርቶዶክስ አልፈቀደችም ወደፊትም አትፈቅድም። ስለ አለባበሱና መቋሚያው የተረዳህ መሰለኝ።
ዮናታን አክሊሉና ካምፓኒው የኢትዮጵያን አምድ ሲያፈርሱ በመናበብ ነው። የጠሚኒስትሩም ቀጥተኛ እገዛ አለበት። ዮናታን አክሊሉ ጠብ በማይለው ትምቢቱ (ትእቢቱ) የኦርቶዶክስ አእማዳት ሲፈርሱና ሲሰነጠቁ አየሁ ብሎ ከአብይ ያገኘውን መረጃና እቅድ ሰማያዊ በማስመሰል ሲቀላምድ ዶር አብይ በተራው የተባረሩትን ተኩላዎች ወደ በጎቹ ልቀላቅል ነው የመጣሁት ብሎ ሲያፌዝም ተመልክተናል። በዛው ንግግሩ በህዝብ ቁጣ የተገለሉትን ተኩላዎች በድርድር መልክ ካስገባ በኋላ በተናገረው ንግግሩ የሚመጣውን ጊዜ “እንኳን ብቻችሁን አብራችሁ ሁናችሁም አትችሉትም” ማለቱ አብይ ያሰበውን ነገር የሚጠቁም ነበር።ሌላ መጨመር ካስፈለገ በአንድ ወቅት አብይን አባቶች ሊያነጋግሩት በሄዱ ጊዜ “እናንተም ጥላቻችሁን አቁሙ” ብሎ በፌዝና በቁጣ አስተናግዷቸው እንደነበር በመንግስት ቲቪ ተላልፎ ተመልክተናል። ጎበዝ ነቃ በል አገርህ ተኝተህ ስትነሳ ያንተ የማትሆንበት ጊዜ ላይ ደርሰሃል።
በመሰረቱ የምንኖርበት አገር ለዮናታን አክሊሉ ሃይማኖቱንና መጽሃፉን ባደሉት ሰዎችና ሃገርነው። ታዲያ እንደነ ዮናታን አክሊሉ አይነት ትውልድ ለወደፊቱ ወረራ እንዲያደነዝዙበት እምነቱንና መጽሃፉን ሰጡዋቸው እንጅ እነሱ ሃይማኖቱን ከተውት ውለው አድረዋል። እነ ዮናታን አክሊሉም እነ አቶ(ቄስ) ግርማ ዘውዴም ምን ይሰሩ እንደነበረ ከማህበራዊ ሚዲያዎች ተመልክተናል የነሱ መጽሃፍ የሰው ሚስት ማማገጥ ይፍቀድ አይፍቀድ የምናውቀው ነገር የለም። በምእራብ አገሮች ቅድመ አያቶቻቸው የሰሩት ማምለኪያ ቦታዎችም ለሌሎች እምነቶች ከመሸጣቸውም ባሻገር ገሚሱ መጨፈሪያ ቤት ሁኗል።
ለጊዜው በአለም አቀፍ ደረጃ ኦርቶዶክስ ላይ ተዘምቷል ራሺያ፤ ዩጎዝላቪያ ምስራቅ አውሮፓን ጨምሮ ውስጥ ለውስጥ ተከፋዮችን በመጠቀም በጸረ ኦርቶዶክስ ላይ የተከፈተ አለም አቀፍ ዘመቻ ኦርቶዶክስን እየፈተነ ነው። አብይም ሆነ ዮናታን ደቀ መዝሙሮቻቸው እነ እስራኤል ዳንሳ እዩ ጩፋ አቶ ግርማ ዘውዴ ዋና ስራቸው ወንጌሉን ሰብኮ ከወንጌሉ ያልተዋወቁትን ወደ መዳን መመለስ ሳይሆን ያመኑትን ኦርቶዶክሳውያን አላመናችሁም ብሎ ከመንጋው መበተን ነው። ይህ የማን ስራ እንደሆነ ሃይማኖቱን ያወቅው ያወቀዋል።
ባጠቃላይ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ከጠንካራ አለት የተሰራና እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ የተቃኘ ዘመናትን የተሻገር ሃይማኖት ነው። ስታሊን ዲያቆን ነበር ሃይማኖቱን ከተወ በኋላ የኮሚኒስት ፓርቲውን ለማስደሰት ኦርቶዶክስንና ኦርቶዶክሳውያንን ክሳላዲን በላይ ጨፍጭፏል አሳድዷል ዛሬ ራሽያ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ዳግም ተመልሶ ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ተከታይ ሁኗል ጠንካራው የኮሚኒስት አጠባም ሊያቆመው አልቻለም። እንዲህ ነው ኦርቶዶክስ ሲወጠር ይወጠራል ወደ ቦታው ግን ይመለሳል(elastic)።
ዮናታን አክሊሉና መሰሎቹ የእውቀት ክፍተት አለባችው በማነብነብ ሳይሆን በማንበብ እና በመመራመር ክፍተታችውን ቢሞሉት ባለማወቃቸው የሚያደርስባቸው አደጋ ሊቀንስ ይችላል። ዮናታን አክሊሉ እነ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሐይሌን፤ እነ ኢንተርናሽናል ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ፤እነ መምህር ፋንታሁን ዋቄን፤ እነ ወጣት ፕሮፌሰር መስከረም ሊቺሴን እነ መጋቢ ሃዲስ ዶር ሮድያስ ታደሰን፤ እነ ዶ/ር ዘበነ ለማ ባሉበት አገር እንደዚህ እራስህን ትዝብት ውስጥ መጣልህ ተንኳኪ እንጅ አሳቢ አለመሆንህን በግልጽ ያሳያል። ስለነዚህ ሰዎች የእውቀት ልቀትና የትምህርት ዝግጅት የስጋዊውንም ሆነ የመንፈሳዊውን ማሰቢያ ካለህ ትረዳው ይሆናል። እነዚህ ሰዎች በስጋዊውም ሆነ መንፈሳዊው እሳቤ ልቀትን የተካኑ ከመሆናቸውም ባሻገር ነገር መለኮትን ክአስትሮሎጅ ከቲዎሎጅና ክህግና ከፍልስፍና በማጣመር በሚነሳው ርእስ ሁሉ ከአንዱ አርእስት ወደ ሌላው እራሳቸውን የሚወረወሩ እንቁ ኮከቦች መሆናቸውን መረዳት ለአንተም ድካምን ይቀንስልሃል እነዚህ ምሁራን አንተን የላባ ሚዛን ተጋጣሚ አድርገው ንቀው ስለተውህ የበላይነት ያስቆጠርክ እንዳይመስልህ የደፈረ ሊነግርህ ይገባል።
የነዮናታን ሰዎች ስለ ኦርቶዶክስ ቄሶች ሲያስቡ ቀደም ባለው ጊዜ አዳፋ ጋቢ ለብሶ የሚያገለግለውን ካህን ሊሆን ይችላል እነዚህ ካህኖች በነ ዮናታን የፈረንጅ አለባበስ ደረጃ ያለመገኘታቸው ምስጢሩ ህዝብን ያለመዝረፋቸው ከስጋ ይልቅ ወደመንፈስ በማድላታቸውና እያረሱ ወንጌልን በመስበካቸው ነው። ስለ ትምህርታቸውና በሃይማኖቱ ላይ ያላቸውን ልቀት ለመገንዘብ የተጓዙበትን ጉዞ የሚያመላክትህ ትዝታዬ የምትል በመርሴ ሃዘን ወልደ ቂርቆስ የተጻፈች አነስተኛ መጽሃፍ ስላለች ስለ እውቀት ጉዟቸውና ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያ ምስረታ ላይ ምን ያህል እንደ ደከመች ቅን ልብ ካለህ ትረዳው ይሆናል ብለን እንገምታለን ለተሻለ እውቀት ፈልገህ አንበበው። ዛሬ አንተ ክርስትና ብለህ የምታስተምረውን አስተምሮ መሰረቱን የጣለልህ የመጣውን መአት ሁሉ የተቋቋመልህ ይኸው የምታላግጥበት ኦርቶዶክስ በመሆኑ ውለታውን ልትረሱት አይገባችሁም ነበር ዳሩ ግን በክብር ከመቆም ይልቅ ማቴሪያላዊ ጥቅማችሁ ስለበለጠባችሁ ክቻችኋታል።
ባጠቃላይ በሚያሳዝን ሁኔታ ኦርቶዶክስ ጠል በሆኑ ሃይሎች አገሪቱ ከውጭም ከውስጥም ስትከበብ የሃይማኖቱ የበላይ ሰው አቡነ ማቲያስ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳውያን ግድያ፤ጭፍጨፋ፤የቤተክርስቲያን ቃጠሎና ውድመት በላይ የትግሬ ፖለቲከኞች እንቅስቃሴ የበለጠ ማሰቢያቸውን ስለያዘው ኦርቶዶክሳውያን ትላንት እንዳደረግነው ሁሉ ዛሬም ተስፋችን በአምላካችን ብቻ ይሆናል።
እዚህ ላይ እንደ ግርጌ ማስታወሻ በአብሮነት መንፈስ ከጸር ኦርቶዶክሳውያን ጋር ያለው ህብረት ለሃገርም ለሃይማኖቱም ስለማይጠቅም ይህን የሚያሳልጡ ኦርቶዶክሳውያን መንገዳቸውን እንዲመረምሩ ማሳሰብ እንወዳለን። በቅርቡ ለኦርቶዶክሳውያን አማኞች ብቻ የተከለለን የገዳም ስፍራ ዳንኤል ክብረት አብይ አህመድን ይዞ መሄዱና ማስጎበኘቱ በእጅጉ አሳዝኖናል አብይ አህመድ ኦርቶዶክስ ካለመሆኑም በላይ ኦርቶዶክስ ጠል በመሆኑ ወደዚህ ቦታ ድርሽ ማለት ባልተገባው ነበር። የጉዞው አላማም ግልጽም አይደለም ወደፊትም ወደዛ ቦታ እንዳይደርስ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። መጋቢ ሃዲስም ምንም እንኳን አቀራረብዎን ብንወደውም ቤተ ክርስቲያኑን አምቦግቡጉት አቃጥሉት ሲሉ ከነበሩ ኡስታዞች ጋር ጦርነት ግጠሙ ባንልም ወንጀላቸውን እውቅና ባይሰጡት መልካም ነው። ዛሬ ቤተክርስቲያንን አስመልክቶ የእስልምና ተከታይ የሆነው የጁዋር መሃመድ ራዲዮ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ ጣልቃ በመግባት በማያገባው ሲፈተፍት ነገሮችን ሲያወሳስብ የእሱ ጠብ መንዣ ራዲዮ (ኦ ኤም ኤን) በርታ እየተባለና ድጎማ እየተሰጠው የማህበረ ቅዱሳን ራዲዮ ግን በንቀትና በማንአለብኝነት በኦሮሙማው መንግስት መዘጋቱ ያበሳጫል ምእመኑም ያሉትን እሴቶቹን በየጊዜው ሲሸረሽሩበት ዝም ብሎ መመልከቱ ያሳዝናል። አቡነ ማትያስም የትግሬን ፖለቲካ ልዩ ቦታ ሰጥተው በመከታተል ላይ በመጠመዳቸው በዚህ በኩል ያለውን ነገር ችላ ብለውታል ወይም ይፈልጉታል። እንደ እውነቱ ከሆነ የእሳቸው በዛ ቦታ መቀመጥ ከእስክንድሪያ እንደመጡ የውጭ ጳጳሳት ሊታሰብ ይገባዋል።
ባጠቃላይ ለዮናታን አክሊሉ የምንመክረው ልክህን እወቅ ነው አንብብ ነው ጊዜ ሰጥተህ ተመራመር ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
Semere.alemu@yahoo.com
ፍትህ አላግባብ ለታሰሩት ዜጎቻችን
https://amharic-zehabesha.com/archives/183099
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment