Tuesday, May 30, 2023

 " አንበሳ ለማጥፋት ደኑን ለዕሳት" እንዳንሰሳት ?   
እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት ከዉስጥ እና ከዉጭ በቀል ጠላቶች የተለያየ ክህደት እና ጥቃት በህቧ ላይ ደርሷል ፡፡

በዘመናችን የሆነዉ እና እየሖነ ያለዉ ግን በዓይነቱም፤ በብዛቱም  ሆነ በአሰዘኝነቱ የሚለይ እና በህዝብ እና በአገር ላይ የተፈፀመ የክ/ ዘመናችን  በራስ  ራስ ሁለት ምላስ ሆኖ ዝንተ ዓለም በትዉልድ የማይዘነጋ  የክህደቶች ቁንጮ ክህደት ነዉ ፡፡

በቀደሙት የኢትዮጵያ የመንግስት ስርዓቶች የተደረጉ ጦርነቶች የአገሪቷን የግዛት አንድነት እና የህዝቦቿን/ዜጎቿን ሉዓላዊነት ፣ነፃነት እና ህልዉና ለማስከበር  ብሎም ዳር ድንበር ለማስከበር ነበር ፡፡

ይህ ሲሆን መንግስታት ወይም ፖለቲከኞች የስልጣን መንበራቸዉን ለማስጠበቅ አልተጉም ማለት አይደለም ነገር ግን አገር ኢትዮጵያ ፤ወገን የኢትዮጵያ ህዝብ አስካሉ እና ለዕዉነተኛ ብሄራዊ ዕድገት እና ሉዓላዊነት አስከሰሩ ድረስ የማቱሳላን ዕድሜ ሰጥቷቸዉ በኖሩ ኖሮ የሚባልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ፡፡

#image_title

ምነዋ ካሉ ዛሬ የመከራ እና የደም ጎራ  ቢያመሳቅላት አገር ዜጎች ከዘመነ ኢህአዴግ የጥልመት ዕለት እስከ ዛሬ በባዕድነት በሚታዩባት፣ በስደት እና በሞት በሚቀጡባት ፣ የባህር በር የነበራት አገር ወደብ አልባ ሆና መዉጫ መግቢያ በር ያጣ ህዝብ ፣ በራሱ አገር በነፃነት ለመኖር ተፈጥሯዊ  ህልዉናዉን በተነፈገ ህዝብ …የተሞላች አገር አንድነቷን እና ክብሯን አስጠብቀዉ ያለፉትን ነገስታት እና መንግስታት በዚህ በሞት እና በህይወት መካከል ሆኖ የግፍ ቀንበር ለተሸከመ ኅዝብ  ወደ ኋላ መመልከቱ ምኑ ነዉ ጥፋቱ ፡፡

ድሮ የኢትዮጵያን አንድነት እና የዜጎችን ብሄራዊ ጥቅም የማስቀደም ርዕዮተዓለም ሲሆን በዘመነ ኢህአዴግ (ቀዳሚ /ተከታይ)  አገሪቷ እና ህዝቧ የፖለቲከኞች የግል ንብረት ሆነዉ  የጡረተኛ ፖለቲከኞች አገልጋይ መሳሪያ ሆነዉ የሚስተዋሉበት መሆኑን ያለፉት ረጂም የጭለማ ዘመናት ምስክሮች ናቸዉ ፡፡

የቀደሙት ለኢትዮጵያ አንድነት እና ዜጎች ሉዓላዊነት ቀናይ ሲሆኑ የዘመናችን ጥገኛ ፖለቲከኞች ስለ አገር ብሄራዊ አንድነት ፤ ስለ ህዝብ   ደህንነት ፣ ስለ ትዉልድ መፃኢ ሁኔታ ሊያስብ ቀርቶ የቆመበትን የማያዉቅ በአገር እና በህዝብ ስቃይ የፖለቲካ ሥልጣን እና የቁሳቁስ ምኞት የሚያባዝነዉ ተጧሪ ሆኗል፡፡

የዘመናችን ፖለቲካ እና ፖለቲከኞች ከራሳቸዉ ሰፈር  መራቅ  የማይችሉ  ከራሳቸዉ  ድምፅ  ዉጭ ሌላዉ የማይሰማቸዉ  የቀንድ አዉጣ እና የቁራ መንፈስ ያሸነፋቸዉ ከሆኑ ቢቆዩም አስከለተ ሞታቸዉ "ክህደት እና ጥፋት አስከ ዕለተ ሞት " ብለዋል ፡፡

በዘመናችን የአንድን የፖለቲካ ድርጂት እና ስብስብ ጥቅም በህዝብ ደም  እና በአገር መታመም ኪሳራ ለማስቀጠል የመፈለግ አባዜ እኔ" ከሞትኩ……"እንዳለችዉ የአልጠግብ ባይነት የራስ ወዳዷ እንስሳ  "አንበሳ ለማጥፋት ጫካዉን በዕሳት " ማቃጠል ይህ ከአገር እና ህዝብ ጥቅም በተቃራኒ ለቡድን እና ለግል ስልጣን ስጋት የሚደረግ በሠላም ስም ማዉደም ስለሚሆን ሊታሰብበት እና ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል ፡፡

ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ለፖለቲካ ጥቅም እና ስልጣን ማስጠበቂያ ሲባል በተለያ ጊዜያት እና ጦርነት የርኩስ መዉጊያ በመሆን ሠባዊ ፣ ምጣኔ ሀብታዊ ፣ ኃይማኖታዊ ፣ ባህላዊ እና ሁለንተናዊ ብሄራዊ መገለጫዎች መጥፋት አይደለም መነካት እንደማይኖርባቸዉ ሁሉም ኃላፊነት መዉስደ አለበት ፡፡

ድሮ የሃይማኖት ተቋማት የዕምነት ስርዓት መፈፀሚያ እና ማስፈፀሚያ ከመሆናቸዉ በላይ የአገር እና የህዝብ ጉዳይ ቀዳሚ እና ዋና ጉዳያቸዉ ነበር ፡፡ ዛሬ ግን በተለይም ከአስራ ዘተኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓም ጀምሮ የፖለቲካ መሳሪያ ከመሆናቸዉ አልፎ ዕጉም ብሎ የጠጠጋን ሠዉ አሳልፎ የመስጠት እና  ከመንፈሳዊ መተጊያ እና በየጊዜዉ የቡድን ዓላማ ጋሻ እየሆኑ ነዉ ፡፡

ለዓመታት ኢትዮጵያዉያን በአገራቸዉ ባይተዋር ፣ ገባር ፣ በማንነታቸዉ ጥቃት ሲደርስ፣ የኃይማኖት እና ዕምነት ቤቶች /ቤተ ዕምነቶች ከጥንት አስከዛሬ በጉልበተኞች ሲደፈሩ ከህዝብ ፊት የማይኖሩ እና ማይመሩ  ከዚህ በላይ ምን ሊሰሩ ያስባሉ ፡፡

ዛሬ ቤተ ዕምነቶች በተለይም አብያተ ክርስቲያናት እና መኢመናኑ በዘመናት ጅረት ያልደረሰበት የጥፋት እና ጥቃት  ጎርፍ ሲያጥለቀልቀዉ እያዩ ዝም የሚሉ ነገር ግን የአገር እና ህዝብ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ የት አሉ ፡፡ ዕምነትም ፤ ስልጣንም ……በአገር ነዉ አንበሳዉን ለማጥፋት ጫካዉን በዕሳት ሲቀጣጠል አይቶ የማያይ እንዴት ከሠማያዊ አይደለም ከዚሁ ከጫካዉ ዕሳት ሊድን ይችላል፡፡

ቢሆን ብሎ አንበሳ ለማጥፋት የማይጠፋ ዕሳት ለጫካ መመኘት ማይጠፋ የታሪክ ሰደድ ዕሳት እና የትዉልድ ከምንጊዜም ፀፀት ለመዳን ሁሉም ስለ ራሱ እና አገሩ ይመለከታኛል ባይ በጫካዉ ዉስጥ መሆኑን አዉቆ ሳይጠፋ ሰደዱን ሳይስፋፋ ለእኔ ብሎ ያጥፋ ፡፡

ይህ ሳይሆን ቀርቶ አንበሳ ፍርቶ ደንን ለዕሳት ላይቀሬ ተያይዞ መጥፋት በገለባ እና ንፋስ ዕሳት መያዝ ነዉ ፡፡

"ለአገር ለሠላም እና ዕድገት ሠላም እና አንድነት እንጂ ዕብሪት እና ጦርነት አይደለም ፡፡ "

"አንድነት ኃይል ነዉ !"

Allen T. silassie

 

 

 

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/182999

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...