Tuesday, May 30, 2023
“በደብረ ኤሊያስ ጥንታዊ ገዳም ላይና በአካባቢው ኗሪዎች ላይ የጦር ወንጀል እየተፈጸመ ነው!” ከአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ
(ግንቦት 22 ቀን 2023 ዓ/ም)
የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ አገዛዝ የኦሮሚያ ልዩሃይል አባላትን የመከላከያ ዩኒፎርም አልብሶ በማሰማራት በአማራ ክልል በደብረ ኤሊያስ ወረዳ አርሶ አደሮች ላይ እና በደብረ ኤልያስ ገዳማትና በመነኮሳት ላይ የሚፈጽመውን ፍጅት መላው ኢትዮጵያዊና የዓለም አቀፋ ሕብረተሰብ እንዲያወግዘው በጥብቅ እናሳስባለን::
ከስድስት መቶ አመታት በላይ ያስቆጠረው የደብረ ኤሊያስ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም በውስጡ ካሉ ቅዱሳት መጻሕፍት፣ መንፈሳዊ ንዋየ ቅዱሳን እና ታሪካዊ ቅርሶች ለከፍተኛ ጥፉት ተጋልጠዋል:: በአብይ አህመድ የሚታዘዘው ጨፍጫፊው ሠራዊት በዚህ ትልቅ የሀይማኖት እና የባህል ቦታ ላይ እያደረሰው ያለው የቦምብ ጥቃት ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን የዓለም ማህበረሰብንም ሊያሳስብ ይገባል።
አብይ አህመድ የመከላከያ ልብስ አልብሶ ያሰማራው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ከአለም አቀፍ ድንጋጌዎች እና ከወታደራዊ ስነምግባር ውጭ በንጹሃን አርሶ አደሮች እና በገዳማዊ መነኮሳት ላይ እንደ ዙ-23 ሞርታር ዲሻቃ ያሉ ከባድ መትረየሶችን በመተኮሱ በገዳሙ እና በአካባቢው ከ7 ያላነሱ ንፁሀን ዜጎች ህይወታቸውን ለማጣት በቅተዋል። በደብረ ኤልያስ ይህን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት ስለመፈጸሙ አገዛዙ እስካሁን ይፋዊ ማብራሪያ ባይሰጥም ከአካባቢው ከደረሰን ተጨባጭ ማስረጃ ተረድተናል።
ፉሽስታዊው የብልጽግ/ኦሮሙማ አገዛዝ ኢንተርኔትና ስልክ አጥፍቶ በደብረ ኤሊያስ የስላሴ ገዳም አብያተ ክርስቲያናት፣ መነኮሳት፣ ተማሪዎች እና በደብረ ኤልያስ ወረዳ ነዋሪዎች ላይ የጦር ወንጀል በከባድ መሣሪያ እየፈጸመ ስለሆነ የዓለም ማህበረሰብ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ በጥብቅ እናሳስባለን።
በተጨማሪም የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ አገዛዝ ሆን ብሎ በታሪካዊው የደብረ ኤልያስ ገዳማት እና በወረዳው ኗሪዎች ላይ እያደረሰ ያለውን በከባድ መሳሪያ የታጀበ ከፍተኛ ጥቃት በማውገዝ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተቃውሟችሁን እንድታሰሙ የአማራ ሕዝባዊ ግንባር (አሕግ) ጥሪውን ያቀርብላችኋል።
መነሻችን የአማራ ሕልውና መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት!
https://amharic-zehabesha.com/archives/183014
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment