Saturday, December 17, 2022
የኦሮሚያ ክልል መዝሙር / የአማርኛ ትርጉም /
ኦሮሚያ ( 2)የትልቅ ህዝብ ታሪክ እናት
የኦሮሞዎች እምብርት ፥ የገዳ ስርአት አዳራሽ
የህግና ስርአት መሬት ፥ የጨፌ ኦዳ እናት
የብልጽግና ልምላሜ ፥ ሁሉን አብቃይ እናት
የመቶ አመት እድፍ ፥ በደማችን አጠብንልሽ
በብዙ እልፍ እልቂት ፥ ባንዲራሽን ከፍ አደረግን
ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ ፥ ስልጣንን መልሰን አገኘን
ሰላምና ዴሞክራሲ ፥ የሰብአዊነት መብት
አስተማማኝ ልማት ፥ ዘላቂ ልማት
ከህዝቦች ጋር ሰላምና ፍቅር
ለመኖር ዋስትና ትልቅ አላማ አድርገን
ኃይላችንን አሰባስበን ፥ ተነስተናል ተማመኚብን
ኦሮሚያ አብቢ ፥ ለምልሚና ኑሪ!
ኦሮሚያ ማናት ? እንደዚህ የተንቆላጰላጠሰችው ? አንድ ቋንቋ ተናጋሪ እንደ ተፈጥሮ ዛፍ ፤ በ1983 ዓ/ም በአሜሪካ ኢፔሪያሊሥቶች እርዳታ ሥልጣን በያዙ እናቸንፋለን ባዮች ኦሮሞ የተባለ ሰው ፣ ከመሬት የበቀለባት ናት እንዴ ? የዓለም የሣይንሥም ሆነ የኃይማኖት ታሪክ ይህንን ቅጥፈት ፅድቅ ነው በማለት የሚደግፈው ይመሥላቸዋል እንዴ ? ከሣይንሥ እና ከዳሪዊን ህሳቤ እንኳን ሥንነሳ የመጀመሪያው ዝንጀሮ ማነው ? ከኃይማኖት አንፃርሥ የመጀመሪያዎቹ አዳምና ሄዋን ኦሮሞች ናቸውን ? ናቸው ከተባለ ፣ የዓለም ሰው ሁሉ ኦሮሞ ነው ። ማለት ነው ።
ደግነቱ በፈጣሪ ዘንድ መላው ዓለም ላይ የሚገኘው በአርያ ሥላሤ የተፈጠረ በሙሉ መጠሪያው ሰው ነው ። ቋንቋ አይደለም ። ፖለቲከኞች ያልነቃውን ህዝብ ለማሞኘት የፈጠሩት የቆዳ ማዋደድ ፖለቲካ ሲኦል እንጂ ገነተ አያሥገባም ። የዛሬ ገንዘብህ በእንኮኮ ኪሊማንጃሮ ሊያሶጣህ ይችላል ። ሆኖም የኪሊማንጃሮን ግዙፍነት አያጎናፅፍህም ። “ ሾሾህን “ እዛ ጣለው ። ከኢትዮጵያ ጠላቶች የተቀበልከውን የቤት ሥራ በቢሊዮን ዶላር በህቡ እንደምታቀሳቅሥ ፣ ባንኩን እንደተቆጣጠርክ ሁሉ ፣ ታንኩን ለመቆጣጠር ና የድሮኑንም ቁልፍ በእጅህ ለማሥገባት የተነቃበትን ሿሿ ይዘህ በድጋማ መምጣትህ ያሣፍራል ።
በመጠኑ ሞዲፋይ በሆነ ሿሿ በአዲስ አበባ ብጥብጥ የፈጠርከው ራሥህ ነህ ። “ What's Lov got to do , got to do with it? … But a second hand emotion ? “ ( Tina Turner ) አለች አሉ ፤ትልቁ ሰውዬ በ1997 ዓ/ም ምርጫን ተከትሎ “የአና ጎሚዝን “ እና የፕሮ ብርሃኑንን መሞዳሞድ አሥተውለው ¡¡
እኔም በአዲሳ አበባ ሉአላዊ አሥተዳደር ውሥጥ የቆዳ ማዋደዱ ፖለቲካ ምን አገባው ? ህዝብ እንደ ዜጋ በፍቅር አብሮ እየኖረ ሣለ ህዝቡን እንደ በግ፣ፍየል፣በሬ ፣ አህያ፣ላም ፣ዶሮ በአጠቃላይ እንደ ግል የቤት እንስሳ መመልከት ጤነኝነት ነው ፤ ትላላችሁን ? በማለት “ ትምህርት ውሥጥ የክልል አርማ ምን ጥልቅ አደረገው ? “ እላለሁ ። ሌላ ሥውር ነብጥብጥ አጀንዳ ከሌለ በሥተቀር ። “ ከወንዙ በላይ ሆነው ነፁህ ውሃ እየጠጡ ታች ከነሱ በታች እየጠጣ ያለውን ፣ ለምን ውሃውን ታደፈርሳለህ ብሎ መቆጣት ፤ ምን ማሐት ነው ? “ሣታሜከኝ ብላኝ ….” አለች …
ይኽ በማይሙ ና በሥሜት ተነጂው ህብረተሰብ ብቻ ሣይሆን በመላው አሥተዋይ የኢትዮጵያ ህዝብ ማላገጥ ነው ። የሚገርም ማላገጥ ።
የሚገርም ማላገጥ ፣ ያውም በሚሊዮኒ የአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ። የራስን ትርክት እያዳመጡ የአዲስ አበባ ህዝብ አቋም ይሄነው እያሉ መቀለድ ፣ ከደርግ ጀምሮ ሲተገበር የኖረ የሠለቸን ድራማ እንደሆነ እንዴት የዛሬ ባለሥልጣናት ዘነጉት ? የአዳነችም ሆነ የጃዋር አሥተሳሰብ መንጋውን በመፎገር ቢያንሥ ተንቀባርሬ እኖራለሁ የሚል ደርጋዊ እና ኢህአዴጋዊ በህዝብ ሥም የመቀሐድ አባዜ ነው ። የህሊና ቢስነት መንገድንም ነው ። እነዚህ ለጥቅም ሲሉ ብቻ ዘረኛ የሆኑ ፣ ሰውን በሰውነቱ ብቻ እንዳይመለከቱ ገነዘብ ና ምቾት አይናቸውን ያወራቸው እብድ ሰዎች ፤ ዜጎችን እንደ ሰው በኩል ደረጀሠ ያለማየት የአእምሮ ህመም አለባቸው ። ከህመማቸው የተነሳም ሰዎች እንደ ሰው ተፋቅረው እንዲኖሩ ፈፅሞ አይፈልጉም ። ሰዎች ተደበልቀው እንዳይኖሩ የሚያደርግ የሤጣን ሥርዓትን ለማንበር ነው ጥረታቸው ። ይኽ ደግሞ በዓለም የሌለ ሰው ጠል አሥተሣሠብ በመሆኑ ሊተገበር አይችልም ።
ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ 99% ሰውና ዜጋነኝ የሚል ነው ።1% ደግሞ ከሆዱ አኳያ ሰውነቱን ረስቶ ፣ ከዓለም ሥልጣኔ እና የዛሬ እና አሁን ማህበራዊ አኗኗር አፈንግጦ ፣ ለማግበሥበሥ እንደ ጅብ ተቧድኖ መንጋ በመፍጠር “ እኔ ቋንቋ ነኝ “ ባይ ነው ።
በዘር የተደራጁ ፣ ነፃ ሰው ሳይሆኑ የቋንቋ ባርያ የሆኑ በአገር ውሥጥ ሥልጣን ይዘው ፣ በጫካ ሰው ለማረድ መንጋውን አሠማርተው ፣ በውጪ አገር ( በነቃው እና ሰው መሆኑንን በተገነዘበው የበለፀገ አእምሮ ባለው ህብረተሰብ ውሥጥ እንደሰው ታቅፈው እየኖሩ ፣ ) በኢትዮጵያ ውሥጥ የእንስሳት ሥርዓትን ለማንበር ሌት ተቀን እየቸፍጨረጨሩ ነው ።
የዓለም ህዝብ ሰው ና ዜጋ ነኝ በማለት በጋራ በፍቅር እየኖረ ፤ አሜሪካ በዲቫ አያሌ አፍሪካዊያንን ዜጋዋ እያደረገች ( ዘመናዊ የባሪያ ንግድ ይሉታል ። አንዳንዶች ) ኢትዮጵያውያን ሰውና ዜጋ ሆነው ሣለ ፣ “ አንተ ቋንቋ ና ዘር “ ነህ ማለት ምን ማለት ነው ?
ይህ የኢንተርሃሙዬ ተግባር ነው ። አዲስ አበባ በደም እንድትታጠብ የፈለጉትም እና ጃዋር እና አዳነች አቤቤ ናቸው ( አዳነች አቤቤ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወይም ደሞ ሥኳር አቅመሰዋት ሊሆን ይችላል ። ጃዋር ግን በዓላማ እና በተላላኪነት እንደሆነ መቶ ፐርሰንት የተረጋገጠ ነው ። )
ጃዋርና ግብረ አበሮቹ ( በመንግሥት መዋቅር ውሥጥ ተሰግስገው ) ሁሌ በቁርጥና በውሥኪ ከርሳቸውን እየሞሉ እና በጥጋብ እያናፉ ፣ አፍንጫቸው ሥር ያለውን ሞት ዘንግተው ፤በምት ላይ ያላግጣሉ ። በቀን አንዴ ለመመገብ ጭንቅ የሆነበትን ምንዱባንን ፣ በሽብርተኝነት ይከሳሉ ። የፈረንሳዩን ሪቭሎሺን በገዛ እጃቸው ለማምጣት ይኽን በአሥተዋይነት ዝም ያለ ትውልድ ለምን በተዋጊ ጥፍራቸው የጎነትሉታል ? ዝም ያለ ትዕግሥተኛ ሰው ሁሉ ፣ ፈሪ ና ቧቅቧቃ ይመሥላቸዋልን ? …. አይናቸው በትዕቢት ሥለታወረ አያዩትም እንጂ ይህ ትውልድ በሁሉም ረገድ እጅግ የነቃ እሳት ትውልድ ነው ።
ወጣቱን አገር ተረካቢውን ፣ የተማረውን ፣ አሥተዋዩን ትውልድ ልቡን አላወቁትም ። አይነ ልቦናቸው ታውሯልና ! የታወረውም አገርን ለማሸበር በተለገሱት ገንዘብ ባፈሩት ሀብትና ንብረት እንደሆነ ይታወቃል ። ነገን በዕውርነታቸው ከቀጠሉ ፣ ያፈሩት ንብረት ብቻ ሳይሆን እነሱም ያለቀናቸው ትቢያ ሊሆኑ ይችላሉ ።
ልበ ዕውሮቹ ፣ ህሊና ቢሶቹ ፣ የነገን ጥፋት ማየት አይችሉም እና ይኽቺን ታሪካዊት አገር ኢትዮጵያን መነገጃ አድርገዋታል ። ህዝቧን ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ እያጭበረበሩት እና እያዘናጉት በሥውር ረብጣ ዶላር እየተቀበሉ አገርን እየሸጡ ነው ። አገር ፈርሳ የት እንደሚኖሩ ባናቅም ፣ ህሊና ሥለሌላቸው መንጋ በመፍጠር ፣ሰው ፣ እንሥሣ ሆኖ ሰውነቱን ረስቶ በቋንቋ ተቧድኖ እንደ ጥንቱ ኋላ ቀር ጦርነት በሥለት እንዲጨፋጨፍ እያዘጋጁት ነው ። ይሄንን ያልተረዳ ማንኛውም ኃቀኛ ዜጋ ደግሞ ነገ እጣ ፈንታው ጥርስ ማፋጨት እንደሚሆን ተገንዝቦ ይኽንን የህሊና ቢሶች ሴራ ለመቀልበስ ያለእንቅልፍ መታገል ይኖርበታል ። …
ለመሆኑ “ ኦሮሚያ “ በኢትዮጵያ ፣ ሥር ናት ወይስ ብቻዋን አገር የሆነች ናት ? ከቶስ ይኽቺን ኦሮሚያ የተሰኘች ምድር ማን ጠፍጥፎ ሰራት ? ኦሮሞ የተሰኘውን ሥያሜ ማነው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጣት ? እራሥህ መልሥ ? ዞረህ ዞረህ አዳምና ሄዋን ጋ ትሄዳለህ ። አንተ ሰው ነህ በቃ ። ሌላውን የፖለቲካ ዲሥኩርና ትርክት ወደዛ ጣልው ። ትልቅ እግዛብሔር እንጂ የሰው ወይም የዘር ትልቅ የለም ። “ ሁሉም ውሥጡ ሥጋና ደም ...” አለ በጣፋጭ ዜማ ፣ አብዱ ኪያር ።
ኦሮሚያ የተሰኘችው ክልል መሆኖን ነው የምናውቀው ። በኢትዮጵያ ጉያ ሥር ያለች ። በወያኔ ዘመን በነ ኩማ ደመቅሳና በእነ አልማዝ መኮ ፊት አውራሪነት የኦነግን የፖለቲካ አጀንዳ በኦህዴድ አማካኝነት እንድትተረጉም የተደረገችም ናት ኦሮሚያ ። የኦነግን አፍ ለማዘጋት በመለሥ ዜናዊ ለአክራሪና ለጠባብች እንዲሁም “ለቆዳ አዋዳጆች” የተለገሰች የጥቂቶች ኬክ ናት ኦሮሚያ ። “ አፋን ኦሮሞን “ ከግእዝ ፊደል ወደ ቀኝ ገዢዎቹ የላቲን ፊደል ያሸጋገረች ። ላቲን በእጅ ብልጫ የፀደቀላት ። ዘጠኝ ሰዎች በሚሊዮኖች የፈረዱባት ... ዛሬ እና አሁን ፣ የቆዳ ማዋደድ ጦሳቸው የዋሁን ዜጋ የሚያሳርድባት ፤ ናት ኦሮሚያ ።
ዛሬ ኢትዮጵያ " ዩቶጵያ " ለመሆን እየተንደረደረች ነው ። የምናብ ፣ የተምኔት ኢትዮጵያ ። መንግሥት እንደመንግሥት ሲሆን የማይታይባት ። ለሥልጣን ያበቁኝ ናቸው ውለታቸውን አልዘነጋም በማለት እውነትን አድበስብሶ ለማለፍ የሚጥርበት ። ሥልጣንን እንዳያጣት ንግሥናንን እሥከእርጅና ለመዝለቅ ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን ወደ ሥልጣን መወዳደሪያ መድረክ እንዳይመጡ የእሣት አለንጋ መያዙን የሚያሳይባት ናት ይኽቺ አገር ።
መንግሥት ሸንጋይ ሆኖ ፣ “ ላም አለህ በሰማይ ! “ ይልሃል ። ህዝብን ለማሞኘት በተመሣሣይ የሽንገላ ቃላት ዛሬም ይጠቀማል ። ነገሩ ይገርማልም ያሥቃልም ። ድራማው በኮመዲ የተጀመረ ትራጀዲ ፍፃሚ ያለው መሆኑ ነው እያሥገረመ የሚያሥቀው ።
ዛሬ ደግሞ የአሜሪካ መንግሥት ፖለቲካውን እንደ እግር ኮሥ ጫወታ አይቶታል ። እርግጥ ዛሬ እና አሁን ኳሷ በፕሬዝዳንት ባይደን እግር ሥር ናት ። እሳቸው በፈለጉት አቅጣጫ ኢትዮጵያን ለመውሰድ ይችላሉ ። የዛሬው የኢትዮጵያ ሁኔታም ለአሜሪካ መንግሥት አመቺ ነው ። “ ሌቦች የዘረፉትን ሀብት በአገሪቱ ኢንቨስት እሥካደረጉ ጊዜ ደረስ አትንኳቸው ። ተባብረን በመበዝበዝ እንበልፅግ ! ! “ ነው ፣ የአሜሪካኖቹ መፈክር ። ( it eat, Let me be soil , USA) ማለት ብቻ ነው የሚያዋጣው ። አፈር ሥህን እያሉ USA ን በአፍ ፣ በአፍዋ ማጉረስ ። ...
በተረፈ ዛሬ ማንም ህዝብን ለመሸንገል ብቃት የለውም ። ዓለም ዛሬ በእያንዳንዱ የኢንተርኔት አጠቃቀም ባወቀ ሰው ሁሉ መደፍ ውሥጥ ናት ። የዓለም መንግሥታት ከሥልጣን ውጪ የተለየ ኃይልና ጥበብ የላቸውም ። በቲዎሪ ደረጃ የሁሉንም ሙያዊ እና ጥበባዊ እውቀት ለማወቅ ወይም ቢያንሥ መሠረታዊውን ዕውቀት ለመጨበጥ እጅግ ቀላል የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል ። ለበረታ ደግሞ ቲዎሪውን እሥተጥግ ማወቅ ከባድ አይደለም ። እናም ማንም በትወራ እየሸነገለ በኢቲቪ ፣ በፋና ፣ በዋልታ ፣ " እየከደረ " ህዝብን በደምሳሳው መሸንገል ከቶም አይችልም ። እንደ ኢህአዴግ የአገዛዝ ዘመነሰ( ዛሬም ሹመኞቹ ኢህአዴጎች መሆናቸውን አላጣሁትም ። ) የበዛ ካድሬ እና የተደናበረ ግራናቀኙን የማያውቅ አፋሽ አጎንባሽን ሰብስቦ ከኢትዮጵያ ባንዲራ ይልቅ የኦሮሚያ አርማ በአዲስ አበባ ላይ ይንገሥ ማለት ቅዠት ነው ። ከኤቨረስት ተራራ በላቀ መልኩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ታላቅ ነው ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለምን ብሎ ሞተና !! ...
ይኽን ያለዕውቀት መንቀዥቀዥ ያመጣው ፣ ሥለዓለም ታሪክ ብቻ ሣይሆን ሥለ ሰው አፈጣጠር ፈፅመው ያለነበቡ ማይም የፖለቲካ ሰዎች በድንገት ፣ ፈፅመው ሳያሥቡት ፣ በ1983 ዓ/ም አራት ኪሎን በጠመንጃ ኃይል ሥለተቆጣጠሩ እንደሆነ በብዙ ጥናት ተረጋግጧል ። ዛሬም ሥልጣን እውቀትና ጥበብ የሚመሥላቸው ናቸው ፤ ራሳቸውን መምራት ሳይችሉ ፣ ህዝብን እንመራለን በማለት ዜጎችን ሠላም የሚያሳጡት ።
ከ1983 ዓ/ም በኋላ ፣ እውቀት እና ጥበብ ዓልባ ሰዎች ሚኒሥቴር ሆነዋል ። ባለሥልጣን ሆነዋል ። መኮንኖች ና ጀነራሎች ሆነዋል ። ዲሲፕሊን ገደል ገብቷል ።ሥልጣን ካለህ በሰማይ መንገድ አለ እና ዲግሪው ፣ ማሥትሬቱ በሲቪል ሰርቪሱ አማካኝነት ታድሏል ። አንዳንድ የምዕራብ ዩኒቨርሲቲዎችም በዶላር ዲግሪዎችን ሸጠዋል ። እናም መንግሥት በቀጣፊዎች ተሞልቷል ። ዛሬ ደግሞ ቀጣፊ አገርን እንደወረራት ታውቋል። እናም ያለዘረኝነት ሥልጣናችን ዘላለማዊ አይሆንም በማለት በቋንቋ ዘረኝነት የሚያላዝኑትን ሰው መሆኑንን የተገነዘበው አማርኛ ፣ ኦሮምኛ፣ትግሪኛ፣ ሱማሊኛ፣አፋርኛ፣ሲዳምኛ ፣ወላይትኛ፣ሃድይኛ ፣ ዶርዝኛ ፣ ቅማንትኛ ፣ ሐረሪኛ፣ሐመርኛ ፣ ወዘተ ። ተናጋሪው ፣ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ግን ፈፅሞ አይሰማቸውም ።
ዛሬ ፣ ለኢትዮጵያ ሠንደቅዓለማ እንሰዋለን የሚሉ ወጣት ጀግና ዜጎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ መሆናቸውን ያስተውሉ ። ከህፃንነት ጀምሮ የሰው ባልሆነ ዘረኝነት ልጆችን አግልሎ በማሥተማር ዘላለማዊ ንግሥና እናገኛለን ብሎ ማሰብ በራሥ ላይ እባብ መጠምጠም እንደሆነም እያሳዮቸው ነው ። በማህበረሠቡ ውሥጥ እየኖረ ያለን ወጣት እንደ ጋሪ ፈረስ ማድረግ ከቶም አይቻልም ። ለአንተ ለማይሙ እና ነገ ትቢያ ለምትሆነው ፤ ተንቀባሮ መኖር ሲል ሥለ ዓለምና ሥለ ሰውልጅ አፈጣጠር ከአንድ ፕሮፊሰር እኩል የሚያቅ የኦሮምኛ ተናጋሪ ወጣት ልጅ ፣ የአማርኛ ተናጋሪ ወጣት ልጅ ፤ የትግሪኛ ተናጋሪ ወጣት ልጅ ፤ የአፋርኛ ተነጋሪ ወጣት ልጅ ፤ የሱማሊኛ ተናጋሪ ወጣት ልጅ ፣ የአፋርኛ ተናጋሪ ወጣት ልጅ ።ወዘተ ። እንደትላንቱ በከንቱ በመንጋነት የሚሰዋልህ እንዳይመሥልህ ።
እርግጥ ነው ፣ ትላንት በቦናፓርቲዝም የተዘፈቀውን ህወሃትን ገንዘብ እየከፈሉ “ በመንጋ አብዮት “ ከሥልጣን ያሶገዱት የግብፅ ተላላኪዎች ነበሩ ። ህውሃት ከ1983 ጀምሮ በዘረኝነት ፣ በፀረ _ ኢትዮጵያዊነት እና በምሁር ጠልነት የፈፀመው ግፍ ፅዋው ሞልቶ በመፍሰሱ ፈጣሪ ቅጣቱን ሰጥቶታል ። ጥቂት ፣ የእጃቸውን ያላገኙት ግፈኞችም የእጃቸውን እንደሚያገኙ አልጠራጠርም ። በበኩሌ በፈጣሪ ተስፋ ቆርጬ አላውቅም ።
ዛሬ በአዲሰ አበባ እንገዛለታልን ፣ ገዢያችን ነው ያሉትን ፣ ህገመንግሥቱን በመጣሥ ፣ በማንኛውም ማህበረሳባዊ ግንኙነት የተጣመረውን ፣ አብሮ የሚበላና የሚጠጣውን የአዲስ አበባ ወጣት እርስ በእርሱ በማጋጨት ፣ የቀውስ እና የብጥብጥ ድግሳቸውን በመላው ኢትዮጵያ ለማዳረስ ጥረዋል ። ግን ግጭቱን በጠመቁት የኦሮሚያ የመንግሥት ባለሥልጣኖች እና በዘረኛ ፓርቲዎች እና ግጭት በመጥመቅ በታወቁ ግለሰቦች ላይ መንግሥት እርምጃ አልወሰደም ። የአዲስ አበባ ፖሊሥም ሆነ የፊደራል ፖሊሥ ሹማምንቶችም ከግጭት ጠማቂው የተበረከተላቸው የአፍ መዝጊያ የተቀበሉ ይመሥል ለመብቱ የታገለውን ወደ ማጎሪያ ካምፓቸው ወሥደውታል ።
ደጎስ ያለ ረብጣ የአፍ ማዘጊያ ና የመተባበሪያ ብር በመቀበል ፣ ባለ ቪላ ቤት ሆነዋል ና ለክፍያቸው እየተገበሩት ያለ አገር የሚያዋርድ ሥራ ነው ። ባለ መኪኖች ፤ በየከተሞቹም ባለ ቪላዎቹ ከፍተኛ የፊደራል ፖሊሥ ባለሥልጣናት እና የኦሮሚያ ፖሊሥ አባላት ናቸው ። ሥንቶቹ እንደሆኑ ለማወቅ ከፈለግህ ፣ በየ ከተማው ዙሪያ የተገነቡትን ቪላ የባለሥልጣናትና የፖየኦሮሚያ ፖሊሥ ና ልዪ ኃይል ቤቶች በላሥቲክ ቤት የሚኖረው ምንዲባን አንድ ሁለት ብሎ ቆጥሮ ይነግርሃል ። በዚች አገር እኮ የደም ነጋዴው ከእሥከ አይባልም ። ጥቂት የማይባልው የየቀበሌውና የየወረዳው ፖሊሥ አዛዥ በአዳዲስ ፎቆች ውሥጥ ባለ ሱቅ መህኑንም እወቅ ።
ከዚህ አንፃርም የብልፅግና መበስበስ እውን ሆኗል ማለት እንችላለን ። ብልፅግና በስብሶል ። የፖሊሥ አዛዥ ይቅርና ተራ የቀበሌ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ሥልጣኑንን ተገን አድርጎ ፣ ከሌባ እና ህሊና ቢስ ባለሀብት ተብዬ ያሻውን ይለገሳል ። ( ቤት ፣ መኪና ገንዘብ ፣ ወዘተ ።) ሁሉም ባይሆን ጥቂት የማይባለው በሚጢጢ ሥልጣኑ አማካኝነት ያልተገባ ጥቅም ያገኛል ። ዛሬ ብዝበዛው እና ዘረፋው በልማት ሥም የሚከወን ነው ። ብልፅግና ከኢህአዴግ የበለጠ መብስበሱን መሪው በውል የተገነዘበ አይመሥልም ። ብዙዎች ግን " አብይ ሿሿ እየተጫወተ ነው ። ሃቀኛውን ለማ በከንቱ ኮነነው ። " ይላሉ ። ...አንዳዶችም " ከቤቱ ሲወጣ የሚያቸው መልካም ነገሮች እጅግ የበሰበሰውን እና የገማውን የሰፊው ህዝብ መኖሪያና ህይወት እንዳያይ ጋርዶት ነው እንጂ እርሱ እጁ ከሌብነት የፀዳ ነው ። " በማለት ሿሿ ይጫወታሉ ። እንዲህ እና እንዲያ ይባል እንጂ አብይ ከቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ከኮሎኔል መንግሥቱ ውድቀትም ሆነ ፣ ከኃ/ማርያም እጅ መሥጠት የተማረ አይመሥልም ።
" እንዴት ? " በሉ ። እንዴት ማለት በጣም ጥሩ ነው ። የጥሩ አድማጭ ና አንባቢም ወግ ነው ።
እሥቲ ዞር ብላችሁ አሥታውሱ ከመጋቢት 24/ 2010 ዓ/ም በኋላ ባሉ 9 ወራቶች በጠቅላይ ሚኒሥቴር ዶ/ር አብይ አማካኝነት ተአምር የተባሉ ክስተቶች የኢትዮጵያ ህዝብ አይቶ ተደሥቷል ። በግፍ የታሰሩ የፖለቲካ እሥረኞች ተፈተዋል ። ከኤርትራ ጋር የኢትዮጵያ ህዝብ ፍቅር እንደሆነ አሳይተዋል ።
ይኽንን የሥርነቀል የለውጥ ጅምራቸውን ጀነራል አሣምነው ፅጌ በማድነቅ ዶክተሩን ፣ " ኢትዮጵያዊው ሙሴ " ብለዋቸው ነበር ። ይሁን እንጂ እኝህ ጀነራል በአምባቸው መኮንን ሞት ሰበብ እንዲገደሉ ተደርገዋል ። የአምባቸው መኮንን ምሥጢርም ከጀነራሉ ሞት ጋር ሊቀበር ችሏል ። እና ይህ እውነት ምንን ያመለክታል ። “ አብዮት ልጆቾን ትበላለችን ? “... ወይስ የሿሿ ጫወታን ?
https://amharic-zehabesha.com/archives/178286
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment