ኢትዮጵያ እናት ዓለም
ባለ ሶስት ቀለም
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ
ካንቺ አልፎ በሌላ ሀገር
ሰንደቅ ሁኖ ሲውለበልብ
የማይቀና የለም.....
እንድትጠፊ ሲመኙ
ለሆድ አድረው ሲናኙ
አሁኑም ተገኙ
ሲያሟርቱ፣ የቃልቻ ድቤ ሲደልቁ
በቁም የደረቁ
አቴቶ እንቱፍ፣ ሴና አባን ቀሎ
እየሰገረ እንደ ፈረስ፣ እየዘለለ እንደ በቅሎ
ይዞራል ከቦታ ቦታ፣ ከሀገር ሀገር
ፈርሳለች ብሎ ለማብሰር
አይ አለማወቅ፣ ወይ አለመገንዘብ
የአባት እናቶች መጀን፣ መአት እንደሚያዘንብ
በቁም እንደሚሰልብ
ፀሎታቸው ጠብቋት
ደምቃ እንደከዋክብት
የገበሩት ህይወትና አጥንት
ለትውልደ ትውልድ ነፃነት
ደም ከአፈር ተለውሶ፣ የሆነው ግርግዳ
እንዳይገባ ባዳ
አዲስ ትውልድ ባላአደራው
የባንዳ ሟርት የመረረው
ዱሩ ቤቴ ብሎ፣ ከምሽግ የገባው
ስጋውን አሞራ ሳይበላው
አጥንቱ ሳይከሰከስ
በህይወት እያለ፣ ኢትዮጵያ እንደሁ አትፈርስ!!!
እወቀው ምድረ ባንዳ፣ የናት ጡት ነካሽ
አሏት ልጆች የክፉ ቀን ደራሽ
ቃል በድር በሰማይ፣ ብለው የማሉ!!
አዲስ ትውልድ አሉ!
ጦቢያን የነካ
እንደ አተር ይከካ
ሞቶ ይፍረስ
ያደረ ለከርስ
ብለው የማሉ፣ ቃል የገቡ አሉ!!!!
ኢትዮጵያን ፣ ኢትዮጵያዬ ያሉ!!!!!
ተመባ መስከረም 18/2014
https://amharic-zehabesha.com/archives/177320
Monday, October 3, 2022
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
By Ameyu Etana BBC Afaan Oromoo, Nairobi/BBC In the latest sign of the deep crisis that has engulfed Ethiopia, conflict in the vast Oromia...
-
የሃገር መሪዎች በዘመናት መካከል የራሳቸውን አሻራ ጥለው ማለፋቸው እሰየው የሚያስብል ሲሆን ይህን አሻራቸውን መጭው ትውልድ ሲያስታውሰው ይኖር ዘንድ ፣ በስማቸው ቤተመንግስቶችን ፣ ሃውልቶቻቸውን እና መሰል ቋሚ ህንፀቶችን ...
-
The west is rigidly stuck in its heydays of colonialism and slavery. And it has a very good reason for being so stuck, albeit sentimental. ...
No comments:
Post a Comment