
እገባለሁ ጫካ - እገባለሁ ዱር፤
የበደልን ገፈት - ስጋት ከምኖር፤
አትገባም ወይ ጫካ - አትገባም ወይ ዱር፤
ተቀጥላ ዜጋ - ሆነህ ከመኖር ::
ትናንትም ተበዳይ - ዛሬም ጦም አዳሪ፤
የበይ ተመልካች - የጅቦች ገባሪ፤
የሃብቱ ተመጽዋች - ያገሩ ባይተዋር፤
የመብት ተነፋጊ - የባንዳዎች ገባር፤
ሁለተኛ ዜጋ - ሆኜ ከመኖር፤
እገባለሁ ጫካ - እገባለሁ ዱር ::
ባዕድ አምላኪዎች - ታሪክ ከላሾችን፤
ዘረኛ ጎሠኛ - አንድነት አፍራሽን፤
የ ’ድገት እንቅፋቶች - የኋሊት ጎታችን፤
አትፋለምም ወይ - አትገባም ወይ ከዱር፤
አንገት እየደፋህ - ዘወትር ከመኖር ::
አትሰማም ወይ ጥሪ - አትሰማም ወይ ጩኸት፤
ደሙ ሲተነፍግ - ሲንቀጫቀጭ አጥንት፤
በደም ተለውሶ - ባጥንት ያጠሩትን፤
አሳልፈህ ስትሰጥ - የጦቢያ መሬትን ::
ያ’ገሬ ቁልቁለት - ያ’ገሬ ተራራ፤
ጥንትም ያልተበገርክ - ለጠላት ወረራ፤
ለወገንህ ኩራት - መመኪያ ስለሆንክ፤
አብረኸኝ ተሰለፍ - ጠላት ለማንበርከክ ::
ዱሩ ቤቴ ብዬ - በቃ ወጥቻለሁ፤
በደልን በዓርነት - ፍቄ እመለሳለሁ ::
ወንዙ ጥም ቆራጬ - ደኑ ብርድልብሴ፤
አሸዋው ምንጣፌ - ድንጋዩ ትራሴ፤
ቅጠል ፍራፍሬ - ስራስር በልቼ፤
ሰንደቅ አበቅላለሁ - ነፃነት ዘርቼ ::
የዱር አራዊቶች - ሳትቀሩ ተነሱ፤
እምዬ ኢትዮጵያ ! - እያላችሁ አግሱ፤
ነብርና አንበሳ - አብሩ ባንድላይ፤
ከጣሊያን የባሰ - መቷል አገር ገዳይ ::
ጀግናው ጫካ ገባ - እሰይ በይ ምድሪቱ፤
እጅግ ቢበዛበት - የበደል ገፈቱ፤
ጉብል ከዱር ገባች - ዕልል በይ መሬት፤
ትግልን አርግዛ - ለመውለድ ነፃነት፤
በ’ኩልነት ጸንቶ - እንዲሰምር አንድነት ::
ጎበዝ ! « ጅቡ ከሚበላህ ጅቡን በልተህ ተቀደስ !! »
ለሥር ነቀል ለውጥ፤ በአንድነት በመነሳት፤ ነፃ ሕዝብ እንሁን !!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!
ነፃነት፤ እኩልነትና ወንድማማችነት ይለምልም !!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ !!
የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ( 06/03/2024 ) እኤአ
ለአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ተዘጋጅቶ ሳይላክ የዘገየ ::
.#AmharaGenocide😢💔 pic.twitter.com/qBgPyWzYn4— 👑ምኒልክ አማራዊት ጥቁር ሰው🦅 (@FanoAmhara21301) March 7, 2024
https://amharic.zehabesha.com/archives/189165
No comments:
Post a Comment