Friday, November 24, 2023

የዕምነት ተቋማት ገለልተኛነት አስከ የት?   
በአንድ ወቅት በ17ኛዉ ክ/ዘመን የፈረንሳይ ንጉስ በዘመኑ ይታተም የነበር ወርኃዊ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መፅሄት “ቤ/ክርስቲያን እናትም ፍቅርም ናት  ”  ቅጂ  ንጉሰ መገስቱ እንዲደርሳቸዉ ይደረግ ነበር ፡፡

በዚህ የ17ኛ ክ/ዘመን ፈረንሳይ በሚያሳስብ ሁኔታ ቸነፈር እና ርኃብ ነበር ተንሰራፍቶ ህዝ ፈረንሳይ እንደ ቅጠል ሲረግፍ ቤ/ክርስቲያኗ ሠማይ ጠቀስ ፎቆችን ስታስገነባ ነበር ፡፡

ይህን የሚያዉቁት ንጉሰ ነግስት በዚያ የመከራ እና ጭለማ ዘመን ሲከነክናቸዉ የነበረዉ የዜጎች ስቃይ እና  የቤ/ክርስቲያን ዝምታ የመፅሄቷን ቅጂ በእጃቸዉ ሲቀበሉ ርዕሱን ቀይሩ ልጆቿ እያለቁ እያላት እና መድረስ ስትችል አይታ የማታይ እናት ስለማትኖር ቤተ ክርስቲያን እናትነቷን ትታለች እና የመፅሄቱን መጠሪያ “ቤ/ክ ፍቅር ናት”ማለት ትችላለች ብለዋል ፡፡

መቸም ፍቅር ይዋል የደር እንጂ እንደነበር አይኖርም እና ፍቅር ፍቅር በሉ እንጂ እናት አትለወጥም በልጆቿ መከራም ቤት አትገነባም እንደማለት ይመስላል፡፡

ዕዉነት ነዉ ወደ እኛ ስናመጣዉ ከቤትም ከአገርም በላይ የሁሉ መስሰሶ እና ማገር የሆነዉ ፣ በአርያ ስላሴ የተፈጠረዉ ፣ ህዝበ አማኒያን ሲሳደዱ ፣ ሲዋረዱ ፣ ሲታረዱ ፣ ሲነዱ እንድ ተራ ነገር በተለያየ ጊዜ እና ቦታ በልዩ ልዩ ሁኔታ ሲወገዱ ለምን እና ለማን የሚል ጠፋ ፡፡

ስንሰማ ድሮ ድሮ ቤ/ከርስቲያን የድሆች መጠጊያ ፣ ማረፊያ እና ዕጉም የሚባልባት እንደነበረች አይካድም ፡፡

ዛሬ ግን ቄሱም ፣መፅሀፉም ….ሆኖ ጭራሽ  የሰዉ ልጂ ለአገርም እና ለኃይማኖትም  እርሾ እና ጭዉ መሆኑ ተረስቶ ከቤተ ከርስቲያንም ከአገሩም እንዲርቅ እና በመሆኑ እንዲጨነቅ ሲሆን ድፍን አስርተ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

አገር ሲያለቅስ እና በስቃይ ሲመቅስ አይቶ ዝም የሚል የእምነት አባትም ሆነ ተቋም ያየንዉ ዛሬ በአገራችን በኢትዮጵያ ነዉ ፡፡

የቀደሙት አያት ቅድ አያት የዕምነት አባቶች ለአገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ ሲሉ የሚያልፈዉን ዓለም ንቀዉ የማያልፈዉን ስም እና ተግባር ለትዉልድ ትተዉ አልፈዋል ፡፡

ዛሬ ላይ አገር እና ህዝብ በመከራ ቋያ ለዘመናት እንደ ገና ዳቦ ሲነድባቸዉ የግል እና የቡድን ምቾት እንጂ የከርስቶስ እና የክርስቶስ በጎች ምናቸዉም አለመሆኑን በሆነዉ እና እየሆነ ባለዉ ሁሉ በምንቸገረኝነት ገለልተኛነትን መርጠዉ  ሠላሳ ዓመት በላይ ሌላ ሠላሳ ዓመት መኖርን ይናፍቃሉ፡፡

ህዝብ እና ቤተ ክርስቲያን የዓምልኮት ምክነያት እንጂ የጥቅም እና የገንዘብ ምንጭ ብቻ እንደሆኑ አድርጎ ስለመከራቸዉ እና ስደታቸዉ አይቶ እንዳላዩ የሚያልፍ እርሱ ቤ/ክስቲያንም ሆኑ ህዘበ ዓማኝ መገልገያ ሆኖ የዕምነት እና ኃይማኖት መሪዎች ተገልጋይ ሆነዉ መቀጠላቸዉ ከኃይመኖታዊ አስተምሮ ዉጭ ስለሚሆን ህዝበ አማኝ የሆነ ሁሉ ከርስቶስ ደካሞችን ሊታደግ እንጂ ክፉወችን እና ኃይለኞችን ሊያበረታታ መሆኑን በማወቅ የዕምነት አባቶች በህዘብ እና አገር ጉዳይ ገለልተኛነት አስከየት ነዉ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡

በጎች በቀበሮ እያለቁ ደምወዝ የሚከፈለዉ ዕረኛ ቢኖር ኢትዮጵያ ዉስጥ እንጂ ከእኛ በቀር ይቅር ፡፡ በጎችን ከቀበሩ መታደግ ባይችል የተኩላ ተባባሪ ላለመሆን አለመትጋት  ደቀመዝሙርነት  ወይስ ጠላትነት ይሆን ፡፡

Allen

አንድነት ኃይል ነዉ !
https://amharic-zehabesha.com/archives/187344

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...