Friday, November 24, 2023
ጨለማ ሊወገድ ሲል ጣጣው ብዙ ነው፡፡ ድቅድቅ ጨለማ ተወግዶ በምትኩ የብርሃን ፀዳል ሊፈነጥቅ ሲል በሚያጋጥም የዐይን መጥበርበር እምብዝም መደናገጥ አይገባም፡፡ ጨለማው ሊወገድ ነው፡፡ ብርሃንም ሊመጣ ነው፡፡ ስንጠብቀው የነበረ ነገር ነው፡፡ ይሁንና አማራው በአለኝታው በኩል የጨበጠው የነብር ጅራት ሊለቅ አይገባውም፤ አይሆንም እንጂ ቢለቀው ግን ከምድረ ገጽ ይጠፋል፤ “አማራ የሚባል ነገድ በምሥራቅ አፍሪካ ይኖር ነበር” ተብሎም በታሪክ ይወሳል፡፡ ለዚህ የአማራ ውድመት ከጠላቶቹ ጋር ተሠልፈው ከውስጥም ከውጪም የሚወጉት የአማራው ነገድ አባላት ቁጥር መብዛቱ ግና የአማራውን የነጻነት ተጋድሎ እያወኩና የትንሣኤን ዘመን እያዘገዩም ይገኛሉ፡፡ በሆዳቸው የሚያስቡ ብአዴናውያን አማሮች ባያስቸግሩት ኖሮ አማራ ይሄኔ ራሱን ቀርቶ ሀገሩን ኢትዮጵያን ነጻ አውጥቶ ነበር፡፡ ግዴለም ይሁን፡፡ ለበጎ ነው፡፡ መጥራት ያለበት ነገር እንዲጠራም ሊሆን ይችላል ይሄ ሁሉ የመከራ ዶፍ መዝነብ ያለበት፡፡ ትልቅ ሰው ሲዋረድ፣ ትንሽ ሰው ሲከብር ማየት የሚቻለው በዚህን መሰሉ የችግርና የመከራ ዘመን ነው፡፡
እየታዬ ያለው ቅጥ ያጣ ሃይማኖት የለሽነትና ሆዳምነት፣ ምግባረ ብልሹነትና ሰይጣናዊነትም ቀድሞ ያልታወቀና ያልተነገረ አይደለም፡፡ ገና ከዚህም የከፋ ሁኔታ ሊገጥመን እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡ ግን ይነጋል፡፡ ሊነጋ ሲል የንጋቱ ጎርፍ የሚጠራርገው የሕዝብ ቁጥር ግን ከሚታሰበው በላይ ነው፡፡ ለወርቃማው ዘመን አድረሰኝ ብሎ ራስን ከኃጢኣት በማቀብ መጸለይ ግን ወሳኝ ነው፡፡ የሚታመኑ በከዱበትና ለከርሳቸው በተንበረከኩበት ወቅት ቆንጆዎቹ ካላሰብነው ቦታ ይወጣሉ፡፡ እንጠብቅ፡፡
ሀገራችን ከላይ እስከታች በዕብዶች የተወረረች ናት፡፡ ይሄ የዘረኝነት ልክፍት በፖለቲካው ውስጥ ከገባብን ወዲህ ላለፉት ዐርባና ሃምሣ ዓመታት የተዘራው የክፋትና የጎጠኝነት ልክፍት ያላበላሸው ሰው የለም፡፡ ትልቁም ትንሹም በዚህ በሽታ ተለክፎ ከሃይማኖትና ከሞራል፣ ከሰብኣዊነትና ከባህል ወጥቷል፡፡ ስለሆነም በሚታዬው የተዘበራረቀ ነገር ብዙም ማዘን አእምሮን ወደማሳጣት ያመራልና እንጠንቀቅ፡፡ ከዘረኝነትና ከሆድ ዕዳ ነጻ በወጡት በነፋንታሁን ዋቄ እንጽናና፤ በነታምራት ነገራ እንጽናና፤ በኢትዮሰማዩ ጌታቸው ረዳና በዶክተር ኃይሉ አርአያ እንጽናና፡፡ እንጂ እንደተዘራው የዘረኝነት እንክርዳድ ቢሆን ኖሮ አብቅቶልን ነበር፡፡
ፍቅርሲዝም የሚባል ሃይማኖት መሠረትኩ የሚለውን ነቢ ደምሳሽ የሚባል ዕብድ የምታውቁት ታውቁታላችሁ፤ ሥራ ስንፈታ አንዳዶቻችንን በጣም ያዝናናናል፡፡ የማርያም እህት ነኝ የምትል ሌላ ወፈፌም አለች፤ በርሷም እንዝናናለን፡፡ በየቸርቹ ሁሉ የሚሰማውና የሚታዬው በክርስቶስ ኢየሱስ ስም የሚደረገው የቁጩ ፈውስና ድራማ ሲታይ ደግሞ በርግጥም እምቢልታ ነፊዎቹ መላእክት ሰንፈው እንጂ የመጨረሻው ዘመን ፊሽካ መነፋት ከነበረበት ጊዜ በእጀጉ እንደዘገዬ መረዳት አይከብደንም - ችግሩ እንግዲህ የእግዜሩና የኛ የሰዎች የዘመንና የቀን አቆጣጠር በእጅጉ መለያየቱ ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ትብታባዊ አፍዝ አደንግዝና የዕብዶች ቱማታ ዋና አለቃና ቁንጮው ሰውዬ ደግሞ አቢይ የተባለው ዕብድ መሆኑ ሊካድ አይገባውም፡፡ ይህ ሰው የሥነ ልና ችግሮች አንድም ሳይቀሩ የሰፈሩበት ዋናው የሣጥናኤል ልዑክ ነው፡፡ የሰይጣን ቁጥሮች 13 እና 666 ደግሞ ከአፉም ከአለባበሱም አይጠፉም፡፡ እዩና ታዘቡ፡፡
የሚገርመው ታዲያ ለዚህ ዕብድ ሰውዬ የሚያሸረግደው ሰው መብዛት ነው፡፡ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ የተሰለፈው የዚህ ሰውዬ አሽከርና ደንገጡር ሲታይ እውነትም ሰይጣን ኃያል ጣዖት መሆኑ ይከሰትልናል፡፡ ከዲያቆን እስከ ጳጳስ፣ ከምሁር እስከ ማይም፣ ከሕጻን እስከሽማግሌ … ይህን ወፈፌ እንደአምላኩ ተቀብሎ የሚሰግድለት ወገን ሲታይ አግራሞታችን ከፍ ይላል፡፡ ዕዝ እኮ ነው!
ከሰሞነኛ ጉዳዮች አንዱን ብንወስድ ለምሣሌ በጣም እወዳቸውና አከብራቸው የነበሩ አንድ ጳጳስ ባልጠበቅሁት መንገድ ከተሣፈሩባት ሕዝባዊ መርከብ ሸርተት ብለው ወደጨለማው የሣጥናኤል ግዛት ወደሚነጉደው የአቢይ መርከብ መዛወራቸው ነው፡፡ ለውጥ ያለና የሚኖር ቢሆንም አንድ ሰው ሲለወጥ ከክፉ ወደ ጥሩ እንጂ ከጥሩ ወደ ክፉ ብዙም የተለመደ አይደለምና የዚህ ሰውዬ ከእግዚአብሔራዊ መንገድ አፈንግጦ ወደሣጥናኤል ጎራ የመቀላቀሉ ነገር ብዙዎቻችንን አስደንግጦናል፤ አሸማቆናልም፡፡ ይህች አንዲት ሆድ አንድን ሰው ምን ያህል እንደምታዋርደው እያየን ነው፡፡ በሚገርም የነገሮች ሂደት ውስጥ እንገኛለን፡፡ በስመ አብ!!
እኔ ስገምት ይህን ሰው ለዚህ ውርደት የዳረገው እነዚህ ሰይጣኖች አንድ የያዙበት ማስፈራሪያ ነገር ቢኖር ነው፡፡ “ይህን ብለህ ካተናገርህ እንትን ስታደርግ የያዝነውን እንትን ለሕዝብ እንትን እናደርገውና እንትን ትሆናለህ ….” የሚል መስፈራርቾ ሳያደርበት የቀሩ አይመስለኝም፡፡ እንጂ በጤናው ሀገራችንን አሁን በያዘው መልክ ብትንትኗን ያወጣ ሰው ለሀገር እንደሚጠቅምና አለ የሚባለውም መከላከያ በርግጥም የኢትዮጵያ እንደሆነ አምኖ ሊሆን አይችልም፡፡ ሁሉም ነገር እኮ የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡
ይህ ሰው አንዴ ራሱን በቁም ገድሏል፡፡ በዚህ ሰውዬ ጊዜን ማባካን አይገባም ባይ ነኝ፡፡ የሚያስጠላው ግን የልቡን ተናግሮ ሲያበቃ ወግ አይቀርምና የክርስቶስን ዘመን የስቅሎ ታሪክ በማውሳት ስቅሎ ስቅሎ አሉኝ ብሎ መናገሩ ነው፡፡ ሌላህን ብላ በሉት፡፡ ሴተኛ አዳሪዋ “አጭበርባሪ አይተኛኝም” ብላለችና ማንም ቅልስልስ የልቡን ሠርቶ ይቅርታ የሚልበት ዘመን ማለፉን ንገሩት፡፡ አሁን አካፋን አካፋ ማለት የተለመደበት የመጨረሻ ወቅት ነው፡፡ አማራንና ትግሬን እያባላ ስንትና ስንት ወንጀል የሠራን የኦሮሙማ ቅልብ ጦር እንደሀገር መከላከያ በመቁጠር አትንኩብኝ ማለቱና ፋኖን “የትም አትደርሺም፤ አርፈሽ ተቀመጪ፤ መሣሪያሽንም አኑረሽ አርሰሽ ብይ” የሚልን ወምበዴ ጳጳስ ከእንግዲህ አማራ ይቀበላል ማለት ሣጥናኤል የሚወዳትን ሲዖልን ትቶ ከገሃነም ወደ መንግሥተ ሰማይ ተመለሰ እንደማለት ነውና ይህ የሚታሰብ አይመስለኝም፡፡ “ነገር ከአፍ ሲያመልጥ ፀጉር ሲመለጥ አይታወቅም፡፡” ሰውዬው በሀብት አማላይነት ተሸንፎም ይሁን፣ በሆነ እንትን ነገር ተይዞም ይሁን አንዴውኑ አማራንም ኢትዮጵያንም ክዶ ለሰይጣን አምላኪዎቹ ተንበርክኳልና ኦርቶዶክስ ራሷም በአጋንንቱ ዓለም ባትያዝ ኖሮ ሥልጣነ ክህነቱ ጭምር ተገፎ ገዛው በተባለው ትልቅ ሆቴል ውስጥ አልጋ አንጣፊ ወይንም ቦይ ሊሆን በተገባው ነበር፡፡ ጊዜው ሲደርስ በግልጽ እንነግረዋለን፡፡ ንስሃ የማያጠፋው ይሁዳዊ ታላቅ ጥፋት ነው ያጠፋው፡፡ ክርስቶስም አለ “የሰውን ልጅ አሳልፎ የሚሰጥ የወፍጮ መጅ በአንገቱ ታስሮ ወደጥልቁ ባህር ይጣል፡፡” እውት ነው፡፡ የሚሊዮኖች ነፍስ ይህን አስመሳይ ጳጳስ ነኝ ባይ ፋረዱታል፡፡ የሚቃጠለው የአማራ ሰብል ይፋረደዋል፡፡ የደብረ ኤሊያስ 570 ካህናትና ቀሳውስት ነፍሳት ይፋረዱታል፡፡ በየቀኑ በድሮን የሚያልቀው የአማራ ሕዝብ ነፍስ እሳት ሆኖ ይፈጀዋል፡፡ “ሁለተኛ አማራ አልሆንም” ያለችው ሕጻን ነፍስ ያቃጥለዋል፡፡ …. አሁንም አደግመዋለሁ - ልጅ አይውጣለት፡፡ (የለውም እንዳትሉኝና እንዳታስቁኝ!)
ሲጀመር አንድ ጳጳስ የሚሊዮኖች ብር ኢንቬስትመንት ባለቤት እንዴት ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ መንኮሰ ሞተ ማለት እንደሆነ እንሰማለን፡፡ የሞተ ሰው ታዲያ የመቶ ሚሊዮን ብር ሆቴል መክፈትና ሲሞት ደግሞ አንድ ሚሊዮን ለእገሊት፣ አንድ ሚሊዮን ለእገሌ እያለ ሚሊዮኖችን በኑዛዜ መስጠት ከምን የመጣ ነው? ኢትዮጵያ ለዓለማችን ጉድ ማሳየቷን ቀጥላለች፡፡ ጳጳሣቷ ጉድ እያፈሉ ነው፤ ካህናቷ በብልጭልጩ ዓለም ጠፍተው በጎቿን በተኩላና ቀበሮ እያስበሉ ነው፡፡ ልጅ አይውጣላቸውና አሁንስ በጣም አበዙት፡፡ በቀደም ለት የሞተው ጳጳስ እኮ ነው ደግሞ በአሥር ሚሊየኖች ለሚፈልጋቸው ሰዎች ተናዞ የሞተው፡፡ ቅሌታሞች!
ፋኖ ጠንቀቅ በል፡፡ የሃይማኖት አባት የለም፡፡ ታቦትና መስቀል በሰይጣን እጅ ገብቷልና አይሠራም፡፡ ቄስ የለም፡፡ ሁሉም ለዲያቢሎስ ሰግዷልና ትክክለኛው የሃይማኖት አባት እስኪገኝ ድረስ አጭርባሪን ጳጳስና ቄስ እግር እግሩን እያልክ ዶሮ ጠባቂ አድርገው፡፡ የአቢይ ተላላኪ ሁላ ዋጋውን ካላገኘ ኢትዮጵያ አትነሳም፤ አማራም ያበቃለታል፡፡ በቃ፡፡ ጊዜው ሰይጣን የሰለጠነበት ነውና ለሰይጣንም ዕድል ተሰጥቶታልና ሁላችንም በያለንበት እንጠንቀቅ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ቀድሞ ጨርሶታል - “ንቁም በበኅላዌነ እስከ ንረክቦ ለአምክነ፡፡” በማለት፤፤ በቅርቡ ቸር ያሰማን፡፡ እንሰማለንም፡፡ እንዲህ ሁሉንም ያንቀዠቀዣቸው ማብቂያቸው መድረሱን አባታቸው ስለነገራቸው ነው፡፡
https://amharic-zehabesha.com/archives/187340
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment