Thursday, September 7, 2023

አክራሪ ብሄረተኛነት የሚፈጥረው የራስን-ነገድ ብቻ እጅግ አብልጦ የመውደድ ስነልቦና ምን ይመስላል?
ክፍል ሶስት ----› ከክፍል ሁለት የቀጠለ

በዶክተር አሰፋ ነጋሽ ---› የኢሜይል አድራሻ --› Debesso@gmail.com Amsterdam (the Netherlands) - ሀምሌ 19 ቀን 2010 ዓ. ም.

አክራሪ ብሄረተኛነት እንዴት የአንድ ነገድ ተወላጆች ራሳቸውን ብቻ አብልጠው እንዲወዱ ያደርጋል?

የራስን-ነገድ ብቻ አብልጦ የመውደድ ስነልቦናስ ምን ይመስላል?

አንድ ሰው በአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት ሲያብድ በራሱ የግል አይምሮ እያሰበ ህይወቱን እንዲመራ የሚያደርገውን የግለሰብ ነጻነቱንም ያጣል፤ የግል ማንነቱም ተሸርሽሮ ይከስማል። አንድ ሰው የአክራሪ ብሄረተኛ ድርጅት ወይም እንቅስቃሴ አባል ወይም ተከታይ ሲሆን እንደ አንድ ነጻ ግለሰብ በራሱ ህሊና እየተዳኘ ህይወቱን መምራት ይሳነዋል፤ እንደ አንድ ነጻ ሰው እሱን እንደ ሰብዓዊ ፍጡር የሚገልጸውን አይምሮውን ተጠቅሞ በሚኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ የሚከሰቱ ሁኔታዎችን አመዛዝኖ ህይወቱን መምራት አይችልም። አንድ ሰው አክራሪ ብሄርተኛ ሲሆን እንደ ግለሰብ ከሌላ ሰው የሚለየውን የግል ማንነቱን አጥቶ በራሳቸው አስተሳሰብ መመራት የማይችሉና በደመነፍስ (instinctively) አድርጉ የተባሉትን ሁሉ ካለአንዳች ጥያቄና ማወላወል የሚፈጽሙ የሰዎች መንጋን (human crowd) ይቀላቀላል። የሰው መንጋ ቡድንን የተቀላቀሉ የአንድ ነገድ ተወላጆች ከጊዜ ወደ ጊዜ አስተሳሰባቸው ከእውነታ እየራቀና (their reality testing is impaired) የሚያስቡትን ነገር ሁሉ በእርግጠኛነት ማድረግ የሚችሉ (delusional state of mind) እየመሰላቸው ይመጣሉ።

 

የአክራሪ ብሄረተኛነት በሚፈጥረው ህሊና አሳዋሪ ስሜት ምክንያት ያበደ የአንድ ነገድ ተወላጅ የራሱን የግል ማንነት ድንበር አፍርሶ ከሌሎች እንደ እሱ የግል ማንነታቸውን ድንበር ካፈረሱ የነገድ/የጎሳ አጋሮቹ ጋር አንድነት በመፍጠር ሀሴትን ያደርጋል፤ የአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት በሚፈጥረው የፈንጠዚያ ዓለም (ecstatic world created by ultra-nationalism) ውስጥም ይገባል። በዚህ ሁኔታው ውስጥ አንድ ሰው የአንድ ማህበረሰብ አባል ሆኖ በህይወቱ ውስጥ ለሚወጥናቸውም ሆነ ለሚያደርጋቸው ነገሮች ኃላፊነት መውሰድ ያቆማል። በአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት ያበደ ሰው ህይወቱን እንደ አምላክ ለሚያመልከው የራሱ ነገድ ድርጅት አሳልፎ ይሰጣል። አክራሪ ብሄረተኛነትና በእሱ የማዕዘን እራስ ላይ የቆመው የፋሽስት ርዕዮተዓለም የተከታዮቻቸውን ህሊና በማሳወር የእያንዳንዱን ሰው የግል ማንነት የሟሟሸሽ ችሎታ አላችው። በዚህ መልክ ነው ግለሰቦች እንደ ሰው የሚገልጻቸውን ግለሰባዊ ማንነታቸውን በአክራሪ ብሄረተኛነት መሰዊያ ላይ በማቅረብ ህልውናቸውን ለፋሽስት መሪዎቻቸው አሳልፈው የሚሰጡት። (The individual cedes his indivdidual freedom to a group led by fascist ideology the latter of which is premised on ultra-nationalism)። በአክራሪ ብሄረተኛነት ፍልስፍና ለሚመራ ቡድን ወይም መንግስት የራሳቸውን የግል ማንነት አሳልፈው የሰጡ የአንድ ነገድ ተወላጆች በስሜታዊነት አነሳስቶ የሚመራቸውን ብሄረተኛ የፋሽስት መሪ ወይም ድርጅት በጭፍን ተከትለው እንደ አንድ ሰው፤ በአንድ ሃሳብ፤ በአንድ ልብና መንፈስ ይንቀሳቀሳሉ። እንደ ቦይ ውሃም አብረው በአንድ መስመር ይነጉዳሉ። በዚህ ከላይ በጠቀስኩት ሁኔታ በሚነሳ የአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት ያበደ ሰው ተው ክፉ አትስራ የሚለውን የህሊና ልጓሙን አሽቀንጥሮ በመጣል በራሱ ሃሳብ መመራት የማይችል ጀሌ ሆኖ እንደ እውር በጭፍን የሚጓዙ የሰዎች መንጋን ይቀላቀላል።

ሲግሙንድ ፍሮይድ (Sigmud Freud) የተባለው የሃያኛው ክፍለ ዘመን ታዋቂ የስነ አይምሮ(psychiatrist) ሊቅ ጤናማ አይምሮ የነበራቸው ግለሰቦች ህሊናቸውን አሽቀንጥረው (suspension of the superego1) በመጣል፤ የሞራልና የሰብዓዊነት እሴቶችን ከአይምሮአቸው በመፋቅ የሰው መንጋን እንደሚቀላቀሉ ያስተምራል። የሞራልና የስነ-ምግባር መሪና ኮምፓስ ሆኖ የሚያገለግለን ህሊናችን አክራሪ ብሄረተኛነትን በመሰለ ህሊና-አሳዋሪ ፍልስፍና ሲፋቅ፤ የሰው ልጆች ማናቸውንም ኢ-ሞራላዊ (ግብረገብ-የለሽ/ዒ-ሰብዓዊ/ሰይጣናዊ) የሆኑ ድርጊቶችን ለመፈጸም የሚከለክላቸው፤ ተው ክፉ አታድርግ ብሎ የሚቆጣቸው ኃይል ወይም የውስጥ የህሊና ድምጽ

(inner voice of the conscience) አይኖርም። በዚህ ዓይነት ነው ሰዎች በአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት ሲታወሩ የራሳቸውን ህሊና አሽቀንጥረው ጥለው የግለሰብ ማንነታቸውንና የግል ነጻነታቸውን ለአንድ ጽንፈኛ የሆነና በአንድ ነገድ ስም የተደራጀ አምባገነን ድርጅት አሳልፈው በብሄረተኛነት መሰዊያ ላይ የሚያቀርቡት። በዚህም ምክንያት አብዛኞቹ በአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት ያበዱ የአንድ ነገድ ተወላጆች አንድ-ወጥና ተመሳሳይ የሆነ ሥነ-ምግባር ወይም ጠባይ ያሳያሉ(ultra-nationalism creates a group of people or a crowd with a homogeneous thought process, sentiment and behavior)። ቀደም ብዬ በገለጽኩት ምክንያት የአንድ ነገድ ተወላጆች የሆኑ የአንድ አክራሪ ብሄረተኛ ድርጅት ተከታዮች (ፕሮፌሰር፤ ዶክተር፤ ምሁር ወይም መሃይም፤ ፓፓስ ወይም ዲያቆን፤ መሪ ወይም ተራ ሰው፤ ሽማግሌም ሆነ ወጣት ሳይባል) በአስተሳሰባቸው፤ በስሜታቸው፤ በጠባያቸው ሆነ በድርጊታቸው ተመሳሳይ ሆነው የሚገኙት። በጀርመን ውስጥ በናዚዎች ጊዜ፤ በጣሊያን ውስጥ በፋሽስቶች ዘመን፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በበርካታ የትግራይ ተወላጆች ዘንድ ያየነው ይህን መሰል ክህሰተት ነው። እነዚህ አንድን

 

አክራሪ ብሄረተኛና ፋሽስት የሆነ መንግስት በጭፍን የሚከተሉ የአንድ ነገድ ተወላጆች እንደ አምላክናምድራዊ ኃይል የሚያዩት ድርጅታቸውና መንግስታቸው አካል በመሆናቸው ታላቅነትና ጥንካሬ፤እንደዚሁም የማንአህሎኝነት ስሜት ይሰማቸዋል። ህይወታቸውን ለዚህ ኃያል ብለው እንደ ፈጣሪአምላክ ለሚያዩት መሪ ድርጅታቸው አሳልፈው ከሰጡ በኋላ እፎይ ብለውና ተደላድለው ይህንንየሚመራቸውን የፋሽስት ድርጅት ወይም መንግስት በጭፍን ይከተላሉ። እነዚህ በአክራሪ ብሄረተኛነትያበዱ የአንድ ነገድ ተወላጆች በማናቸውም ጉዳዮች ሁሌም ትክክል ነን የሚል ስሜት ይሰማቸዋል። በዚህም ምክንያት የተነሳ በሚኖሩበት ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ማህበራዊ እውነታ መገንዘብ ያቅታቸዋል። ከእነሱ ነገድ ውጭ ያሉ አብረዋቸው የሚኖሩ የሌሎች ነገዶች ተወላጆች የሚሰማቸውን የሥቃይ ስሜትም ሆነ የሚገኙበትን የጣር ህይወት ለመረዳት ያዳግታቸዋል። እነዚህ በአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት ያበዱ የአንድ ነገድ ተወላጆች በህይወታቸው ውስጥ እንደ ነጻ (independent) ሰው በግላቸው ኃላፊነት መውሰድ ስለሚሳናቸው ወይም ስለሚያቅታቸው በአምባገነን ፋሽስት መሪዎቻቸው ላይ ሙሉ እምነታቸውን ይጥላሉ። በእነዚህ በአክራሪ ብሄረተኛነት ያበዱ የአንድ ነገድ ተወላጆች እንደ አምላክ የሚያመልኩትና ተስፋቸውን ሁሉ የጣሉበት አምባገነን ኃይል/ድርጅት ወይም ፋሽስታዊ መንግስት በዕለት ህይወታቸው ውስጥ እየገባ ስለ እነሱ ሆኖ በእነሱ ሥም ሲወስን በጸጋ ይቀበላሉ። እነዚህን ሁሉ አክራሪ ብሄረተኛነት የሚፈጥራቸውንና የሰው ልጆች ህሊናቸው ታውሮ የፋሽስት ድርጅት ጭፍን ተከታዮች የሚሆኑበትን ሁኔታ ታዋቂው ማህበረሰባዊ የስነልቦና ሊቅ (social psychologist) ኤሪክ ፍሮም በሚከተለው መንገድ አሳምሮ ገልጾታል።

 

“ታዛዥነቴ የማመልከው ኃይል አካል ያደርገኛል፤ ስለሆነም ጥንካሬ ይሰማኛል። ይህ የማመልከው ኃይል ስለ እኔ ሆኖ ስለሚወስንልኝ እኔ ስህተት ልሰራ አልችልም። ይህ ኃይል እኔን ስለሚጠብቀኝ እኔ ብቻዬን ልሆን አልችልም2”. ከላይ በጥቅስ ያሰፈርኩት የኤሪክ ፍሮም ጽሁፍ በአብዛኛው የወያኔ

- - Sigmud Freud, Group Psychology and the Analysis of the Ego, 1921

- - Fromm, Erich. “Disobedience as a Psycological and Moral Problem, 1963

ድርጅት አባሎችና ደጋፊዎች የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ዛሬ የሚገኙበትን አሳዛኝ ሁኔታና የተያያዙትን ወደ ገደል የሚከት የጭለማ ጉዞ ይገልጻል ብዬ አምናለሁኝ። ይህ ሁኔታ አብዛኞቹ የአንድ ማህበረሰብ አባሎች አክራሪ ብሄረተኛነት በሚፈጥረው ተፅዕኖ ምክንያት የግል ነጻነታቸውንና ማንነታቸውን በማጣት እንደ ሰው በሚዛናዊነት ማሰብ የሚያቆሙበትን አሳዛኝ ሁኔታ ያሳያል። ባብዛኛው በናዚዎች ሥር የነበሩት የጀርመንና በፋሽስቶች ሥር የነበሩት የጣሊያን ህዝቦች በዚህ አሳዛኝ የሆነ ስነልቦናዊ ዝቅጠት ውስጥ አልፏል። በእኔ እምነት ዛሬ በትግራይ ውስጥ የሚገኘው ማህበረሰብ ትላንት በጀርመንና በኢጣሊያ የነበረው ህዝብ ባለፈበት አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚገኘው። ይህ ትላንት በናዚ ጀርመንና በፋሽስት ጣሊያን የተከሰተው ሁኔታ፤ ዛሬ ደግሞ በትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ እናየዋለን። ይህንን መሰሉን ሁኔታ ታዋቂው የአይምሮ ሀኪም ፕሮፌሰር ቮልካን societal regression ተብሎ ገልጾታል። Societal regression በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ሰዎች በአንድ የታሪክ ወቅት በሚከሰት አክራሪ ብሄረተኛነትና የእሱ መገለጫ በሆነው የፋሽስት ፍልስፍና ምክንያት እንደ ግለሰብ ለማሰብ የሚችሉበት መብታቸውን አጥተው፤ በውዴታም ሆነ በግዴታ የአንድ እጅግ ጠባብና ጭፍን አምባገነን የሆነ የልሂቃን ድርጅት አስተሳሰብ ተሸካሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ የሚያመለክት ነው። በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ የአንድ ማህበረሰብ አባሎች ወይም የአንድ ነገድ ተወላጆች የሆኑ ሰዎች በቡድናዊ አስተሳሰብ (group think) ላይ በተመሰረተና የግለሰቦችን ነጻነት የሚያሟሽሽ የአክራሪ ብሄረተኛነት ፍልስፍና ሰለባ በመሆን በአስተሳሰብ ደረጃቸውም ዝቅ ይላሉ። በእኔ እምነት ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት አብዛኛዎቹ የትግራይ ማህበረሰብ ተወላጆችች የሆኑ የወያኔ ድርጅት አባሎችና ደጋፊዎች የሚገኙበት ሁኔታ ይህን ይመስላል።

 

አክራሪ ብሄረተኛነት በነገሰበት ማህበረሰብ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ዓለምን በሁለት ተጻራሪ ጎራ ብቻ ከፍለው በማየት የእነሱን አመለካከት የማይጋራውን ሁሉ በጠላትነት ይፈርጁታል። ከእነሱ አስተሳሰብ ውጭ የሆኑትን ሁሉ እነሱን ለማጥፋት እንደሚያሴሩ አድርገው ያስባሉ። አክራሪ ብሄረተኛነት በነበሰበት ማህበረሰብ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ዓለምን በሁለት ተጻራሪ ወገኖች ከፍሎ የሚያይ ጽንፈኛ የሆነ አስተሳሰብ ሰለባም ስለሆኑ ሌላው ሊያጠፋን ነው ከሚል ፍራቻ ሁልጊዜ በተጠንቀቅ ይጠባበቃሉ፤ ህይወታቸውም እንደ ቆቅ በሥጋት ተከቦ ይኖራል። አክራሪ ብሄረተኛነት በነገሰበት ማህብረሰብ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በውዴታም ሆነ በግዴታ የአክራሪ ብሄረተኛው ድርጅትና መሪዎች የሚጭኑባቸውን ሃሳብ ተሸካሚ በመሆን በሚኖሩበት ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን እውነታ እንኳን በቅጡ መረዳት ያቅታቸዋል። ለዚህም ነው ዛሬ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከትግራይ በታች በተለይም ኦሮሚያና አማራ እንደዚሁም በተወሰነ ደረጃ በደቡብ (በኮንሶ፤ በጉራጌ ወዘተ) ህዝብ ተነስቶ የወያኔ ፋሽስት አገዛዝ ያብቃ የሚልበት በአብዛኛው ህጋዊና ሰላማዊ የሆነ ተቃውሞ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ተደርጎ በበርካታ የትግራይ ተወላጆች ዘንድ የሚቆጠረው። በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ባለፉት ሶስት ወራት በዶ/ር ዓቢይ አመራር ሰጪነት የተወሰዱት አንዳንድ ማሻሻያዎች በመደገፍ ህዝብ ሰልፍ እየወጣ ከፍተኛ ድጋፉን ሲያሳይ የትግራይ ማህበረሰብ ደግሞ ያኮረፈበት ምክንያት ለውጡ እኛ ጥቅምና ህልውና ላይ ያነጣጠረ ነው በሚል አስተሳሰብ ነው።

 

የትግራይ ተወላጆች ዝምታ ከምን የመነጨ ይሆን?

የትግራይ ብሄረተኞች ትግላቸውን በጀመሩበት ወቅት የዚህን ድርጅት ፀረ-ኢትዮጵያና አክራሪ ብሄረተኛ ዓላማ በመቃወም በርካታ የትግራይ ተወላጆች ተገድለዋል፤ ተሰቅለው አካላቻቸው በእሣት ተጠብሷል፤ ጉድጓድ ውስጥ የፀሃይ ብርሃን እንዳያዩ ተደርገው ከተሰቃዩ በኋላ ለሞት ተዳርገዋል፤ ሌሎችም ተሰደዋል። የኢትዮጵያን ታሪክ ጠንቅቀው የሚያውቁ፤ የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ታግሎ ይህቺን ሀገር በነጻነት እንዳቆያት የሚመሰክሩ፤ የወያኔ ትግሬዎች በጠላትነት የፈረጁትን የአማራ ህዝብ በወንድምነት እንጂ በጠላትነት ሊያዩት እንደማችሉ የተናገሩ የትግራይ ሽማግሌዎች በወያኔዎች ተገድለዋል፤ ታስረዋል። ለእነዚህ ስለ ኢትዮጵያ ሲሉ ለተሟገቱ፤ የሚያውቁትንና የኖሩትን እውነት በመናገራቸው ህይወታቸውን ላጡ የትግራይ ተወላጆች ያለኝ አክብሮት ከፍ ያለ ነው። አፈር ይቅለላቸው፤ ነፍሳቸውንም ይማርልኝ እላለሁ። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጽመው ድርጊት ትክክል አለመሆኑ የሚሰማቸው የትግራይ ተወላጆች የሉም ለማለት አልችልም። እጅግ ጥቂቶችም ቢሆኑ በእርግጠኛነት የወያኔን መንግስት ኢ-ፍትሃዊነት የሚረዱ የትግራይ ተወላጆች አሉ ብዬ አምናለሁኝ። በወያኔ መንግስት ጫና ይሁን በሚኖሩበት አካባቢ ባሉ የወያኔ መንግስት ደጋፊዎች ተፅዕኖ ምክንያት አደባባይ ወጥተው ይህንን በልባቸው ውስጥ ያለ ስሜታቸውን መናገር የማይደፍሩ፤ የሚሰማንን ስሜት አደባባይ ላይ ወጥተን ብንገልጽ በማህበረሰባችን እንገለላለን፤ እንዋከባለን ወዘተ ብለው የሚፈሩ የትግራይ ተወላጆች እንዳሉ እገምታለሁኝ። ይህንን እዚህ ጋ ያነሳሁት በአክራሪ ብሄረተኛነት ህሊናቸውን ያልሳቱ ነገር ግን ህሊናቸው የሚነግራቸውን ትክክለኛውን ነገር በተቃውሞ መልክ በወያኔ መንግስት ላይ ለመግለጽ የማይደፍሩም የትግራይ ተወላጆች እንዳሉ ለማመልከት ነው። ግን ይህ ሁኔታ ዝምታቸው ትክክልና ተገቢ ነው ወደሚል ድምዳሜ ሊወስደን አይችልም። እስቲ አንድ ጥያቄ ላንሳ። በአብዛኛው በትግራይ ተወላጆች የተገነባውና በአልሞ-ተኳሾች(snipers) የተሞላው የአጋዚ ጦር ቃታ መሳብ የሚቀለው በትግራይ ሰልፈኞች ላይ ነው ወይስ ትግርኛ-ተናጋሪ ባልሆኑት የአማራ፤ የኦሮሞ፤ የአፋር፤ የደቡብ፤ የኢትዮጵያ ሶማሌዎች ወዘተ የሆኑ ነገዶች ተወላጆች ላይ? በ2008 ዓ. ም. ባህር ዳር ላይ በተደረገ ሰልፍ በአጋዚ ጦር ከሰባ በላይ ወጣቶች በአንድ ቀን ተገድለዋል። በአንድ ቀን ብቻ እኔ ተወልጄ ባደግሁባት የሀረርጌ ክፍለ ሀገር ውስጥ በምትገኘው ትንሿ የጨለንቆ ከተማ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ አምስት የአንድ የኦሮሞ ቤተሰብ አባላት በአጋዚ ወታደሮች ተገድለዋል። ለመሆኑ አልሞ-ተኳሾች በሆኑ የትግራይ ተወላጆች የተሞላው የአጋዚ ጦር ወታደሮች አማራና ኦሮሚያ በሚባሉት ክልሎች የተደረጉትን የመሰሉ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች በመቀሌ፤ በአዲግራት፤ በአክሱም ወይም በአድዋ ወዘተ ቢደረጉ ኖሮ ወገኖቻቸው በሆኑት የትግራይ ተወላጆች ጭንቅላት ላይ እያነጣጠሩ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍሎች የፈጸሟቸውን ዓይነት ግድያዎች ያካሂዱ ነበርን? ይሄ የትግራይ ተወላጆች ሊመልሱት የሚገባቸው ጥያቄ ነው። ከትግራይ በታች ባሉት የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሚያደርጉት ሰላማዊ ተቃውሞ በአጋዚ ጦር የሚደርስባቸው ሞት፤ እስራት ሆነ መሳደድ እንዳልበገራቸው አይተናል። በቄሮ፤ በፋኖ፤ ዘርማ፤ በኮንሶ ወጣቶች ወዘተ የተደረገው ተቃውሞ በሺዎች የሚቆጠር የህይወት ዋጋ ተከፍሎበታል፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከትግራይ ክልል በታች ያሉ የኦሮሞ፤ የአማራ፤ የኢትዮጵያ ሶማሌዎች፤ የአፋር፤ የሲዳማ፤ የጌዴኦ፤ የጋምቤላ፤ የጉራጌ፤ የኮንሶ ወዘተ ተወላጆች ተፈናቅለውበታል።

 

በዛሬዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ባብዛኛው የትግራይ ተወላጆች የሆኑ የእስር ቤት ኃላፊዎች፤ መርማሪዎችና ገራፊዎች የወንድ ታሳሪን ብልት እየቀጠቀጡና ሁለት ሊትር ውሃ በብልት ላይ እያንጠለጠሉ ያኮላሻሉ። የኢትዮጵያን ሴቶች ራቁታቸውን አስቁመው የነገዳቸውን ሥም እየጠሩ፤ አስነዋሪ የሆነ ስድብ እየሰደቧቸው ማንነታቸውን ያዋርዳሉ። የታሳሪዎችን ጥፍሮች በጉጠት እየነቀሉ ያሰቃያሉ። ወያኔዎች እስር ቤቶች ውስጥ ምን አይነት ዘግናኝ ግፎችን እንደሚፈጽሙ ለመረዳት የእነ ወ/ት ንግስት ይርጋን፤ የእነ አቶ ከፍያለው ተፈራን3፤ የእነ አቶ አበበ ካሴን፤ የእነ አቶ አሸናፊ አካሉን፤ የእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤን4 ወዘተ ሰቅጣጭ ምስክርነት መስማት ይበቃል። ወያኔዎች የወንድ እስረኞችን ራቁታቸውን በማቆም ሴቶች ብልቶቻቸውን እየጎተቱ እንዲያዋርዷቸው ያደርጋሉ። የወንድ አሳሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ አሳሪዎችና ገራፌዎች ሴት እሥረኞችን ራቁታቸውን እንዲሆኑ አድርገው

 

- - ይህ ወጣት ኢትዮጵያዊ የኦነግ አባል ነህ ተብሎና በጥርጣሬ ተይዞ እጅግ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የተፈጸመበትና በደረሰበት ድብደባ ብዛት ሁለት እግሮቹ በእነዚሁ የወያኔ ሰዎች ትዕዛዝ ተቆርጠዋል። ይህ እጅግ ዘግናኝ የሆነ የወያኒዎች የግፍ ሰለባ የሆነ ወጣት Oromo Media Netwerk በሚባለው ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ ስለደረሰበት ሥቃይ ሲናገር አንዳችም አይነት የምሬት ቃል አልወጣውም። ታሪኩ እጅግ አሳዛኝና አስለቃሽ፤ ሲሆን ይህ ሁሉ ግፍ ግን ሰብዓዊነቱን ዝቅ ሊያደርገው አልቻለም። በእውነትም እንደ ስሙ ከፍ ያለ ሰው፤ ከፍ ያለ ሰብዓዊነት የተላበሰ ኢትዮጵያዊ ነው። እግዚአብሄር ብርታቱን ይስጥህ።

 

- - የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤን፤ የአቶ አበበ ካሴን፤ የአቶ አሸናፊ አካሉን የእስር ቤት የሥቃይ ቆይታ በአማራ ቴሌቪዥን ተከታተልኩት። በጣም የሚያሳዝን ግፍ ነው የተፈጸመባቸው። የመቶ አለቃ ማስረሻ በነገዱ ማንነት ምክንያት ይወርድበት የነበረውን አስጸያፊ የሆነ የስድብ ውርጅብኝ በህዝብ መካከለ ጥላቻን እንዳይዘራ በማለት አልፎታል። ይኸ ትልቅነቱን የሚያሳይ ነው። እነዚህ በዚህ ጽሁፌ ውስጥ የጠቀስኳቸውና ሌሎችም የግፍ ሰለባዎች የደረሰባቸው ሁሉ ለትውልድ ማሰተማሪያ እንዲሆን የግፍ ሰለባዎች ማህበር አቋቁመው ልምዳቸው በደንብ ተዘግቦ ለዛሬውም ሆነ ለመጪው ትውልድ ማስተማሪያ ቢሆን፤ ትላንት በደርግም ሆነ በወያኔ ሥርዓት የግፍ ሰለባ የሆኑትን ታሪክ መዝግቦ በመጽሃፍ መልክ ታትሞ ለትውልድ ማስተማሪያ የሚሆንና በዚህ ያብቃ የሚል ተቋም ቢቋቋም ለሀገራችን ሰላም፤ በኢትዮጵያ ለመትከል ለምንፈልገው የዲሞክራሲ፤ የእኩልነትና የፍትህ ሥርዓት ትልቅ አስተዋጽዖ ያደርጋል። በዚህ ዓይነት ተቋማት ዙሪያ ደግሞ የህግ ባለሙያዎች፤ የአይምሮ ሀኪሞች፤ የስነልቦና ባለሙያዎች፤ የማህበራዊ አገልግሎት ባለሙያዎች፤ የሃይማኖት መሪዎች ወዘተ ሊሳተፉ ይችላሉ። ያዩዋቸዋል፤ እስፓርት ስሩ ብለው ያሯሩጧቸዋል5። የወንድ እስረኞችን ራቁታቸውን አቁመው እየገረፉ

“አማራን ሱሪውን አስወልቀነዋል፤ ከእንግዲህ አማራ ከሺህ ዓመታትም በኋላ ወደ ሥልጣን አይመጣም” እንደዚሁም “ጉራጌ ሌብነት እንጂ ፓለቲካን የት ያውቃል” እያሉ በማንአህሎኝነትና በእብሪት መንፈስ ይደነፋሉ። የትግራይ ገራፊዎች አቶ ዘመነ ምህረቴ የሚባል የመኢህአድ ድርጅት አመራር አባል እስር ቤት በቆየበት ጊዜ ላዩ ላይ ሽንታቸውን ሸንተውበታል። ይህም ትግሬዎች በአማራ እስረኛ ላይ ሽንታችውን በመሽናት የአማራን ተወላጆች ማዋረድ እንደሚችሉ ያሳዩበት “የጀግንነት ድርጊት” መሆኑ ነው። አዲስ አበባ ማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ የወጣው አቶ ሃብታሙ አያሌው

 

በሰጠው ምስክርነት “ማዕከላዊ 99% (ዘጠና ዘጠኝ ከመቶው) ገራፊዎች ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው። ሲገርፉም ትግሬ ማለት እንደዚህ ነው። ግርግዳ ግፉ እያሉ ግርግዳውን ሲያስገፉ ያስቆዩንና እየሞከራችሁት ያላችሁት ይህንን ነው። እኛ ማለት እንደዚህ ነን እያሉ ወክለው ነው የሚነግሩን6”። ሀብታሙ አያሌው ያቀረበውን የእሥር ቤት ችግር በዝርዝር ለመረዳት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑና ያዳምጡ። https://www.youtube.com/watch?v=1sKcOSLbcws

 

እነዚህ ድርጊቶች በየዕለቱ የሚፈጸሙት የአማራ፤ የኦሮሞ፤ የጉራጌና የኢትዮጵያ ሶማሌ፤ የቤኒሻንጉል፤ የኮንሶ፤ የጋምቤላ ወዘተ ነገዶች ተወላጆች ላይ ነው። ከላይ ሃብታሙ እንደገለጸው ማዕከላዊን በመሳሰሉት የማሰቃያ ቦታዎች እነዚህን አስጸያፊና ዘግናኝ ድርጊቶች በእስር ላይ በሚገኙ ታሳሪዎች ላይ የሚፈጸሙት በአብዛኛው የትግራይ ተወላጆች የሆኑ የእስር ቤት ኃላፊዎች፤ መርማሪዎችና ገራፊዎች ናቸው። ለመሆኑ እነዚህ የትግራይ መርማሪዎችና ገራፊዎች እነዚህን የመሰሉ ዘግናኝና የግለሰቦችን ነገዳዊ ማንነት የሚነኩ አስጸያፊ ድርጊቶች ትግሬዎች በሆኑ ወገኖቻቸው ላይ ይፈጽማሉን? ከላይ የዘረዘርኳቸው ግፎች እንዴት በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ስሜት በአበዱ የአንድ አናሳ ነገድ ተወላጆች እንደሚፈጸሙ ለማወቅ ይረዳችሁ ዘንድ አዲስ አበባ በሚገኘው የማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ የመንግስት ግልበጣ ሙከራ አድርጋችኋል ተብለው በጥርጣሬ ተይዘው በነበሩ ታሳሪዎች ላይ በትግራይ ፋሽስቶች የተፈጸመውን ዘግናኝ ዘገባ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ (link) በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ። http://www.ethiomedia.com/augur/4316.html

 

ይህንን 36 ገጾች ያለውን የወገኖቻችንን ሰቆቃ የያዘውን የአማርኛ ዘገባ ከሰባት ዓመት ተኩል በፊት ውጭ አገር እረፍት ላይ በነበርኩበት ጊዜ ኢትዮሚዲያ በተባለው ድህረ-ገጽ ላይ አግኝቼ ነው ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ የተረጎምኩት ነው። ይህ ሰነድ በእነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ፤ ጄኔራል አሳምነው፤ ኮርኔል ደምሰው ወዘተ የክስ መዝገብ ውስጥ ተካተው የተሰቃዩትን የእነ ወይዘሮ እማዋይሽንና በርካታ ሌሎች ወገኖቻችንን ሥቃይ የያዘ ነው።

 

የወያኔ ትግሬዎች እኛ ትግሬዎች ስለሆንንን የደርግ መንግስት የግፍ ሰለባዎች ሆንን ብለው ያምናሉ። ለመሆኑ የትግራይ ተወላጆች ጨካኝ የአማራ መንግስት7 ነው ብለው በሚከሱት የደርግ ሥርዓት ውስጥ የነበሩ የእስር ቤት ኃላፊዎች እነዚህን መሰል አስጸያፊ ስድቦችን እየሰደቡ የትግራይ ተወላጆችን በማንነታቸው አዋርደዋል፤ አሸማቀዋል? ለመሆኑ የደርግ ገራፊዎች የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ወንድ ታሳሪዎችን ብልት ቀጥቅጠዋል? ለመሆኑ የደርግ ገራፊዎች የትግራይ ሴቶች እሥረኞችንስ ራቁታቸውን አቁመው በነገዳቸው ማንነት ምክንያት አዋርደዋል? ይህን መሰል ግፍ የወያኔ ትግሬዎች ዛሬ አምርረው በሚኮንኗቸውና በአማራነት በሚጠቅሷቸው የንጉሱም ሆነ የደርግ መንግስታት ዘመን አልተፈጸመም። ኢትዮጵያውያን ዛሬ ልንረዳው የሚገባን ነገር ባለፉት አርባ ሶስት ዓመታት የትግራይ ማህበረሰብ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ የወጡ፤ የኢትዮጵያን የቆዩ የጨዋነትም ሆነ ግብረገባዊ እሴቶች የሚጻረሩ እሴቶችን ያዳበረ ማህበረሰብ መሆኑን ነው። ባለፉት አርባ ሶስት ዓመታት ውስጥ በትግራይ ማህበረሰብ

- -ይህ ማህሌት ፈንታሁን እና አዶም ካሣዬ በሚባሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን ሴት ታሳሪዎች ላይ ተፈጽሟል።

- - ሀብታሙ አያሌው በአሜሪካ ካደረገው ንግግር የተወሰደ። ለዝርዝሩ ዩቲዩቭ ላይ published by Tenaadam on Apr 9, 2017 በሚለው ሥር ይመልከቱ።

- -ወያኔዎች የደርግ መንግስት የአማራ መንግስት ነው ብለው ያምናሉ። በነሃሌ 1983ዓ. ም. ህወሃት ሥልጣን ላይ ከወጣ ሁለት ወር ተኩል በኋላ the Hague (ሄግ) በሚባለው የኔዘርላንድ ከተማ ውስጥ Institute of Social Studies (ISS) በሚባለው ውስጥ በተደረገ ስብሰባ ላይ አረጋዊ በርሄ የተባለው የቀድሞ የወያኔ ድርጅት መሪና የጦር አዛዥ የደርግ መንግስት ከአማራ ህዝብ ጋር ስለንበረው ትሥር የሚከተለውን ብሎ ነበር። “ለእኛ ለትግራውያን የደርግ የማህበረሰባዊ መሰረቱና ዋና የድጋፍ ምንጩ የአማራ ህዝብ ነበር” ብሏል። በዚህም ግንዛቤ ነው የአማራ ህዝብ ባለፉት ህወሃት ትግል ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ዋነኛ የወያኔ የጥቃት ሰለባ የተደረገው።

 

ውስጥ የትግራይ አክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት እየተጠናከረ በመምጣቱ በርካታ ሰዎች ህሊናቸው ከመታወሩም በላይ በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያዊነት እሴቶች አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ስሜት በመጠናከሩ ምክንያት ተመናምነዋል። በዚህም የተነሳ በትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ከላይ የገለጽኳቸውን ግብረገብ-የለሽና ኢሞራላዊ የሆኑ ከባህላችን የወጡ ጸያፍ ድርጊቶችን በጠላትነት በሚያዩዋቸው የሌሎች ነገዶች ተወላጆች ላይ ለመፈጸም ወደ ኋላ የማይሉ ሰዎች ተፈጥረዋል። የወያኔ ትግሬዎች እነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች በማውገዝ ፈንታ እንዲያውም እነዚህን ድርጊቶች በሌሎች ነገዶች ላይ በመፈጸማቸው በጀግንነት የሚኩራሩ የትግራይ ተወላጆች በብዛት ተፈጥረዋል። ባለ ትዳር የሆኑ የወልቃይትና ጸገዴን አባ ወራዎች አስሮ ሴቶቻቸውን ማስወለድን እንደ ጀግንነት የሚቆጥር የትግራይ ትውልድ ተፈጥሯል። ወንዶችን በወንዶች ማስደፈር በኢትዮጵያ ባህል ውስጥ የሚታወቅ ልማድ አይደለም። ዛሬ ግን የትግራይ ወያኔዎች በሚያስተዳድሩዋቸው እስር ቤቶች ውስጥ እነዚህ ጸያፍ ድርጊቶች የታሳሪዎችን ማንነት ለመፋቅና ለመደምሰስ ሲባል ይፈጸማሉ። በርካታው የጀርመን ህዝብ በናዚዎች የአገዛዝ ዘመን በጀርመን አክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት ታውሮ ናዚዎች በይሁዲዎች፤ በጀርመን ኮሚኒስቶች፤ በእስላቮች፤ ጂፕሲዎች ወዘተ ላይ ይፈጽሙ የነበሩትን ኢ-ሞራላዊና ግብረገብ-የለሽ ድርጊቶች ይደግፍ ነበር። የጀርመን ህዝብ ይህንን ያደረገው በተፈጥሮው ክፉ ስለሆነ ሳይሆን በአክራሪ የጀርመን ህዝብ ብሄረተኛነት በፈጠረው የናዚ/የፋሽስት ፍልስፍና ተፅዕኖ ምክንያት ነው። ማናቸውም አክራሪ ብሄረተኛ የሆነ የነገድ ድርጅት ያንን እወክልሃለሁ የሚለውን የራሱን ህዝብ በስሜት አነሳስቶ የማሳወርና ክፉ የማድረግ ችሎታ አለው። ፍሬድሪክ ኬልነር የሚባል ህሊና የነበረው የጀርመን ተወላጅ ናዚዎች ሥልጣን ላይ በወጡበት ጊዜ አብዛኛው የጀርመን ህዝብ የሂትለር ደጋፊ እንደነበር በቁጭት ጽፏል8። በእኔ እምነት ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ህወሃት ከትግራይ በታች ባለው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይህ ሁሉ በደል ሲፈጽም አብዛኛው የትግራይ ህዝብ ተቃውሞ አለማሰማቱ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ስሜት ስለታወረ ነው ብዬ አምናለሁኝ። ከዚህ በቀር ደግሞ ይህ የአፓርታይድ ሥርዓት የአንድን ነገድ ተወላጆች በበላይነት ተጠቃሚ ማድረጉ በርካታ የትግራይ ተወላጆች ህወሃትን በጭፍንነት እንዲደግፉ አድርጓል። በእኔ እምነት ይህ አብዛኛው የትግራይ ተወላጅ ለህወሃት የሚሰጠው ድጋፍ የጀርመን ህዝብ ለናዚዎች ከሰጠው ድጋፍ ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ይህ ደግሞ የሆነው የትግራይ ተወላጆች በተፈጥሮአቸው ክፉዎች ስለሆኑ ሳይሆን የፋሽስት ፍልስፍና መገለጫ የሆነውና በአንድ ህዝብ ማንነት ላይ የሚያጠነጥነው አክራሪ ብሄረተኛነት በዛሬው የትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ገዢ ርዕዮተዓለም (dominant ideology) ሆኖ ስለወጣና የዚህንም ማህበረሰብ አባሎች አመለካከት ሥር-ነቀል በሚባል ደረጃ ስለቀየረው ነው። በሥር-ነቀልና ጽንፈኛ (radical and extremist) አመለካከታቸው የሚታወቁ አክራሪ ብሄረተኛነትን የመሰሉ ፍልስፍናዎች በዓለም ታሪክ ውስጥ ህዝብን አሳውረው ገደል የከተቱባቸውን አጋጣሚዎች ታሪክ ዘግቧል። የናዚ ፍልስፍና በጀርመን ውስጥ፤ የፋሽስቶች ፍልስፍና በጣሊያን ውስጥ፤ ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ደግሞ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ማዕዘን ላይ ቆሞ ብቅ ያለው የወያኔ ትግሬዎች ፋሽስታዊ ሥርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ይህንን አሰመስከርዋል።

 

በዚህ ትውልድ ውስጥ ያሉት የኢትዮጵያ ወጣቶች ልብ ሊሉ የሚገባው ጉዳይ ትላንት የትግራይ ተወላጆች የሆኑ በወቅቱ ተራማጅ የሚባሉ ወጣቶች የዐጼ ኃይለስላሴንም ሆነ የደርግን መንግስታት በመቃወም ረገድ ግንባር ቀደም ሆነው ይሰልፉ እንደነበረ ነው። ምናልባትም ያኔ እኔን መሰል ሞኞች ስለ ዲሞክራሲና የህዝብ እኩልነት በጋራ የምንታገል መስሎን ተራማጅ9 ይሰኙ ከነበሩ የትግራይ

 

- -Friedrich Kellner, My Opposition, the Diary of Friedrich Kellner, A German Against the Third Reich, Cambridge University Press 2011

- - ከዛሬው ህወሃት ድርጅት አንዱ መሪ የሆነው አባይ ጸሃዬ በ1966 ዓ.ም. ድሮ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኑቨርሲቲ በሚባለው ውስጥ የነበረው የተማሪዎች ማህበርStruggle የሚባል መጽሄት የእንግሊዘኛው ክፍል አዘጋጅ ነበር)። የዚህ መጽሄት የአማርኛ ክፍል አዘጋጅ የነበረው ግርማቸው ዓለሙ የአስበተፈሪ ልጅ ነበር (ዛሬ በህይወት የለም ነፍሱን ይማረው)። አባይ ጸሃዬ (የቀድሞ ስሙ አመሃ ነበር) ተራማጅ የሚባልና ዓለም አቀፋዊነትን፤ በጭቁን መደቦች አጋርነት ላይ የተመሰረተ የህዝቦች ወንድማማችነትን የሚያስተጋባና የሚሰብክ የግራ ፍልስፍና ተከታይ ነበር። ይህ ሰው ዓለም አቀፋዊነንትንና በመደብ አጋርነት ላይ የተመሰረተ ወንድማማችነትን እንዳልሰበከ፤ የራስ ነገድ አምልኮን ወደሚሰብከው የአክራሪ ብሄረተኞች ዓለም ገብቶ እሱን ከመሰሉ የትግራይ ተራማጆች ጋር የፋሽዝምን ችቦ በኢትዮጵያ አቀጣጠለ። አባይ ጸሃዬና ጓደኞቹ ደደቢት ላይ የለኮሱት የትግራይ አክራሪ ብሄረተኛነት

ተወላጆች ጋር አብረን ስንጮህ እነሱ ግን እነዚህን ዛሬ በአማራነት የሚፈርጇቸውን ሁለት የቀድሞ መንግስታት የሚቃወሙትና የሚዋጉት የአማራ መንግስታት ናቸው ብለው ከምር ያምኑ ስለነበረ ነው። እኔ ይህንን መራራ ሀቅ የተረዳሁት ወያኔ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ነው። ከወያኔ መንግስት ሥልጣን ላይ መውጣት ጀምሮ የትግራይ ተወላጆች ድምጻቸውን ጨርሶ አጥፍተዋል ማለት ይቻላል:: በምዕራቡ ዓለም የህወሃትን ሥርዓት በአስመሳይ ተቃዋሚነት ሳይሆን በተግባር በግንባር ቀደምትነት እየተቃወሙ ያሉት ሁለት ግለሰቦች አቶ ጌታቸው ረዳና አቶ ገብረመድህን ዓርዓያን የመሰሉ ጥቂት ግለሰቦች ብቻ ናቸው። የትግራይ ተወላጆች በንጉሱም ሆነ በደርግ ዘመን በእነዚህ ሁለት መንግስታት ላይ በዓመጽ ተነስተዋል (ቀዳማይ ወያኔንና የሁለተኛውን የወያኔ እንቅስቃሴ ብቻ መጥቀሱ ይበቃል)። የትግራይ ተወላጆች እነዚህን ሁለት መንግስታት በመቃወም ረገድ በግንባር ቀደም ረድፍ የሚቀመጡ ነበሩ። በተለይም አውቀዋል፤ ተምረዋል የሚባሉት የትግራይ ልሂቃን እንደሚነግሩን ትግሬዎች ድምጻቸውን ያጠፉት በዛሬው ጊዜ ጋዜጦች ትግራይ እንደልብ ስለማይገቡና በትግራይ ውስጥ ያለው ህዝብ ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ በባሰ ሁኔታ ስለታፈነ አይደለም። የትግራይ ተወላጆች ትላንት በነበሩት ሁለት የንጉሱና የደርግ መንግስታት ዘመን ግንባር ቀደም ተቃዋሚ የሆኑት ትላንት ከዛሬው በተሻለ ጋዜጦች ስለሚያነቡና ባለፉት ሁለት መንግስታት ዘመን ጋዜጦች በትግራይ ውስጥ በብዛት ይሰራጩ ስለነበረ አይደለም። ዛሬ እንዲያውም የኢንተርኔት ሥርጭትን ብንመለከት የትግራይ ክልል ከአማራው፤ ከኦሮሞውም ሆነ ከደቡቡ ክልል የተሻለ ይዞታ ላይ ይገኛል። ታዲያ ቢያንስ የተሻለ የመረጃ ምንጭ (በፌስቡክ፤ በትዊተር፤ በኢሜይል) ያላቸው የተማሩት ትግራውያንና ከተሜዎች ለምን በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን ዲሞክራሲያዊ የነጻነት ትግል መቀላቀል አቃታቸው? ከሁሉም ግን አስገራሚው ጉዳይ ከሀገር ተሰደው እንደ እኔ በምእራቡ ሀገራት የሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች የወያኔ መንግስት ይህንን ሁሉ ግፍ በኢትዮጵያውያን ላይ ሲፈጸም ሃያ ሰባት ዓመታት ሙሉ ዝምታን መምረጣቸው ነው። የትግራይ ተወላጆች ዴሞክራሲያዊ በሆኑ የምዕራብ ሀገራት እየኖሩ በወያኔ ተፅዕኖ ይደረገብናል ብለው የወያኔን መንግስት የሚደግፉበት ምክንያት ለእኔ አይገባኝም። ምክንያቱም እዚህ በነጻ ሀገር ስለምንኖር ማንም ይህን አስበሃል ወይም ይህን አድርገሃል ብሎ አንድን ሰው ሊያስር ወይም ሊገድል ማንም አይችልምና።

 

የትግራይ ተወላጆችን ዝምታ የሚገልጹ የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም በእኔ እምነት ለዝምታቸው በዋነኛነት እንደ ምክንያት ሊጠቀስ የሚገባው ጉዳይ ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የተዘረጋው የአፓርታይድ ሥርዓትና ይህ ሥርዓት በአንጻራዊ መልኩ ለትግራይ ተወላጆች የሰጠው ጥቅም፤ ለትግራይ ክልል ያመጣው ልማትና እድገት ነው። እስቲ ሌላውን ትተን የመቀሌን ከተማ እድገት በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ከነበሩ ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች እድገት ጋር አነጻጽረን እንመልከት። በትግራይ ክልል ውስጥ ባለፉት ሀያ ሰባት ዓመታት ውስጥ የተገነቡትን የልማት መዋቅሮች ስርጭት (መንገዶች፤ ትምህርት ቤቶች፤ ፋብሪካዎች፤ የመብራት ኃይል ማመንጫዎች፤ ሰፊ የመብራት፤ የንጹህ ውሃ መስመሮች፤ ግድቦች፤ ወዘተ)። ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ጋር እያነጻጸርን እንመልከት። ዛሬ የትግራይ ተወላጆች በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኝ የሆነ ድርሻ ይዘዋል። እስቲ ሰናይት መብራቱ በምትባል የትግራይ ተወላጅ የተጻፈውን እንመልከት።

 

“ባሁኑ ሰዓት ትግራዋይ በሃገሪቱ የኢኮኖሚ የበላይነት እየያዘ ይገኛል። አሁን ባለው መረጃ መሠረት ትግራዋይ ከሃገሪቱ ሃብት 70% በመቶ መቆጣጠር ችሏል። ግባችን ትግራዋይ ከሃገሪቱ ሃብት 85% በመቶ እንዲቆጣጠር ማድረግ ነው። የፖለቲካ የበላይነት የኢኮኖሚ የበላይነትን ተከትሎ ይመጣል። ይህ ሊሆን የሚችለው ጠንካራ ሕወሓት ሲኖርና ዋና ዋና ሥልጣን መቆጣጠር ሲችል ነው። ስለዚህ

ችቦ ትግራይን ገንብቶና አልምቶ፤ ከትግራይ በታች ያለወን የኢትዮጵያ ክፍል አንድዶና አክስሎ እነሆ አሁን ወደ መክሰሚያው የተቃረበ ይመስላል። ቁርጡ ግን ገና በውል አለየም፤ መዘናጋት አይገባም። ለምን ቢሉ ፋሽስቶች ማሸነፍን እንጂ መሸነፍን አያውቁም፤ የፓለቲካ እምንታቸው እንደ አክራሪ ሃይማኖት ጭፍን ነው። ስለሆነም ኃይላቸው ተበታትኖ እስከሚጠፋ ድረስ እስከመጨረሻው በእምነታቸው ይጸናሉ። የዓለም ታሪክ የሚመሰክረው ይህንን ነው። ዛሬ የምናየውን የኢትዮጵያን ሁኔታ አሁንም ቢሆን በጥርጣሬ ማየት ያለብን ገና የአክራሪ ብሄረተኛነት መሰረት ከነበረው በነገድ ማንነት ላይ የተመሰረተ አሰራር ስላልወጣን፤ ለግለሰብ መብት ቅድሚያ የሚሰጥ አሰራር ገና በግልጽ ስላላየን፤ የዲሞክራሲ ተቋማዊ መሰረት የሚሆኑ መንደርደሪያዎችን ገና ጅምራቸውንም ስላላየን ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን ከኛ ቁጥጥር ውጪ ከሆነ የያዝነው የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነት ዋስትና አይኖረውም ማለት ነው። ዋስትና አይኖረውም ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ትግራዋይ ለአደጋ ይጋለጣል። እስካሁን ያካበትነው ሀብትም ሊወረስ ይችላል። ስለዚህ ሥልጣኑ ከኛ ቁጥጥር ዉጪ ሆኖ ትግራዋይ ለአደጋ ከሚጋለጥ ድርጅቱም ኢህወዴግ ቢፈርስ ይሻላል10”።

እነዚህ ጉልህ የሆኑ ልዩነቶች ከምንም ነገር በላይ የትግራይን ተወላጆች ዝምታ ይገልጹልናል። ለመሆኑ ድሮስ ቢሆን የትግራይ ተወላጆች ለምን ጠመንጃ አንስተው ለአስራ ሰባት ዓመታት ታገሉ? በኢትዮጵያ ውስጥ እኩልነትን፤ ዲሞክራሲያዊና የህግ ሥርዓትን ለመፍጠር ወይስ የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር? ይህንን ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በህወሃት የአፓርታይድ ሥርዓት ውስጥ ሲሰቃይ የነበረው፤ በራሱ ሀገር ባይተዋርና የበዪ ተመልካች የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊመልሰው የሚገባ ጥያቄ ነው። የወያኔ ትግሬዎች በተመለከተ እነሱን ጠመንጃ አንስተው እንዲዋጉ ያደረጓቸው ምክንያቶች በሚከተለው መልክ በድርጅቱ መስራች፤ የድርጅቱ የቀድሞ ሊቀመንበርና የጦር አዛዥ በአረጋዊ በርሄ ጉልህ በሆነ መንገድ ከዚህ በታች ተገልጿል።

 

“ትግላችን የፖለቲካ ስልጣንን ጉዳይ፤ የኢኮኖሚ ዋስትናንና ደህነነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ነበር። ይህ ነበር የትግራይ ብሄረተኛ ትግል ዓላማ። ይህም የወያኔ ሀርነት ትግራይ ዓላማ ባለፉት የአማራ መንግስታት ዘመናት እኛ ትግሬዎች ያጣናቸውን መብቶች ማስመለስ ነበር። የወያኔ ድርጅት ግጥሞች፤ ዘፈኖች ሁሉ በቅርጽና በይዘታቸው የትግራይ ህዝብ በተከታታይ የአማራ መንግስታት ዘመናት የተነጠቀውንና ያጣውን መብት እንዴት ማስመለስ እንደሚችልና እነዚህንም የተነጠቃቸውን መብቶች ለማስመለስ ምን ዓይነት መስዋእትና ዋጋ መክፈል እንዳለበት የሚያመለክቱ ነበሩ። በሌላ አነጋገር ጨቋኙን የአማራ ብሄር ለመዋጋት ህዝቡን የሚያነሳሳና የሚያንቀሳቅስ ቅስቀሳ ይደረግ ነበር። ከዚህም በቀር ለትግራይ ህዝብ

 

ጨቋኙ አማራ ደመኛ ጠላቱ ስለሆነ የወያኔ መገናኛ ብዙሃን (ሬዲዮ፤
https://amharic-zehabesha.com/archives/185641

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...