Friday, September 8, 2023

ጣምራ ፌደራሊዝም  ወደ ፍጹም ኅብረት ! - መጽሐፍ በ ገለታው ዘለቀ

ጣምራ ፌደራሊዝም  ወደ ፍጹም ኅብረት !  - መጽሐፍ  በ ገለታው ዘለቀ
 

በዓለም ላይ ሃገር የሚባለውን ግዙፍ ማህበር የመሰረቱ የሰው ልጆች ሁሉ ይህንን ማህበራቸውን ፍጹም የማይከፋፈል ማህበር አድርገው ና ይህንን ጠገግ የማይነካ ና የማይገሰስ አድርገው ይኖራሉ ። “ የማንከፋል አንድ ነን ….” “ህብረታችን ፍጹም ነው ….” ይላሉ። ወደ ሃገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ ደግሞ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የፈጠሩት ህብረት ፍጹማዊነት ይጎድለዋል። የሃገራችን ከፍተኛ ሰነድ የሆነው ህገ መንግስታችን ህብረታችን ፍጹማዊ እንዳልሆነ በጥብቅ ይገልጻል። ህብረታችን በማንኛውም ጊዜ ሊፈርስ የሚችል እንደሆነ ያሳያል። ኢፍጹማዊ የሆነ ህብረት ውስጥ ናት ሃገራችን። አስደማሚው ነገር ኢትዮጵያ በፍጹም ህብረት ውስጥ አለመግባቷና በየትኛውም ጊዜ ፈራሽ መሆኗ ብቻ ሳይሆን ይ ህንን ኢፍጹማዊ ህብረታችንን የዴሞክ ራሲዎች ሁሉ ጥግ አድርገን መረዳታችን ነው የችግሮቻችን ሁሉ መሰረት። ይህ ገዢ መተሳሰሪያ መርሆ ወደ ታች በፖሊሲና በኑሮ ሲገለጽ ብዙ ግጭትና መፈናቀል አምራች ሆኖብን አይተነዋል። ስለሆነም ኢትዮጵያ ለውጥ ያስፈልጋታል። ታዲያ እንግዲህ ለውጥ ስንል ተፈላጊውን ለውጥ ማጥናት ኣለብን። እንዴት ነው ወደ ፍጹም ህብረት የምንሄደው ? እንዴት ነው በፍጹም ህብረታችን ውስጥ ብዝሃነት የሚስተናገደው ? እንዴት ነው አምባገነናዊ ባህርያትን የምንቋቋመው ? የሚሉትን ጉዳዮች ማጥናትና ከለውጥ ባሻገር ኢትዮጵያ የምትገባበትን የለውጥ ቤት ቀድሞ መስራት ያስፈልጋል።  ይህ መጽ ሐ ፍ ያለው ፍላጎት ይሄ ነው።


PDF- ጣምራ ፌደራሊዝም መጽሃፍ 






ገለታው ዘለቀ

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/185667

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...