Sunday, September 3, 2023

እነ ጌታቸው ጉዲና ማጀቴ ላይ በቀል ፈፅመዋል!
እነ ጌታቸው ጉዲና እና ብርሃኑ ጁላ ማጀቴ ላይ በቀል ፈፅመዋል። የማጀቴና አካባቢው ሕዝብ የኦሮሚያ ብልፅግና ያዋቀረው "ኦነግ ሸኔ" ከከሚሴ ተነስቶ ሸዋን ሲያጠቃ ከጥቃት ተከላክሎ ራሱን አስከብሮ ቆይቷል። ማጀቴና አካባቢው ጥቃት ሲቀለብስ እነ ጌታቸው ጉዲና በመከላከያ ሲያስመቱት ኖረዋል። አሁን ሌላ የበቀል ጊዜ አገኙ።

ዛሬ ከ7_8 ሰዓት ማጀቴ አካባቢ ጦርነት ነበር። ፋኖ ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል ያሉት እነ ብርሃኑ ጁላ ኃይላቸው ሲመታ በቀላቸውን ንፁሃን ላይ አድርገዋል። ያኔ በብሔር ስም ሲያስወርሩት የተከላከላቸውን ሕዝብ ዛሬ በሰላም ማስከበር ስም ተበቅለውታል።

ጦርነቱ ካበቃ በኋላ ቤት ለቤት እየገቡ ሴት፣ ህፃን፣ ሽማግሌ ሳይሉ ረሽነዋል። ትልልቅ ሰዎች "እናንተ ናችሁ ፋኖን የምትቀልቡ" ተብለው ተገድለዋል። ይህ ያደረ፣ የከረመ በቀል ነው። የኦሮሚያ ብልፅግና አስታጥቆ የሚልከውን ኃይል የሸዋ አማራ ሲመክት እነ ጌታቸው ጉዲና፣ ብርሃኑ ጁላ ሲበሽቁ ኖረዋል። ዛሬ ሰበብ ፈልገው ንፁሃንን ቤት ለቤት እየዞሩ እየገደሉ ነው።

በአለቃቸው አብይ አህመድ በኩል የሰላም ጥሪ፣ በሚያዙት በኩል ደግሞ ጭፍጨፋ እያደረጉ ነው። ጦርነቱ የታወጀው በሕዝብ ላይ ነው። ይህ ለቡድናዊ ጥቅማቸው የሚያደርጉት ፀረ አማራ ተልዕኮ በሕዝብ ትግል ይከሽፋል።

Getachew Shiferaw
https://amharic-zehabesha.com/archives/185657

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...