Saturday, September 30, 2023

የአገዛዙ ሰራዊት ጭካኔ ቃላት የሚገልጹት አይደለም። እውን የኢትዮጵያ ማህጸን ያፈራችው ሰራዊት ነው? - መሳይ መኮንን
እጅግ የሚሰቀጥጡ ነገሮችን እየሰማን ነው።

በወልዲያ በሆስፒታል ህክምና ላይ ባለ አንድ የፋኖ ታጣቂ ላይ አንገቱን በማረድና በተሽከርካሪ ጎማ በመጨፍለቅ የፈጸሙት ጭካኔ ለታሪክ ተመዝግቦ ይቀመጥ። በማዕከላዊ ጎንደር ከፍተኛ ሽንፈት የገጠመው የአገዛዙ ሰራዊት 12 አርሶአደሮችን በመረሸን ብልታቸውን ቆርጦ ሜዳ ላይ በትኖ የሄደበትም አሰቃቂ ድርጊት ነገ ፍርድ የሚያገኝ እንደሚሆን አልጠራጠርም።

የፋኖዎች ተግባር በተቃራኒው አስደማሚ ነው። ማርከው፡ አብልተው፡

ቁስለኛ አክመው፡ የፈለገ አብሮአቸው እንዲታገል፡ ያልፈለገ ደግሞ መታወቂያ እንዲሰራለት ተደርጎ ወደ ቤተሰቦቹ የሚሸኝበት ሁኔታ ልብ ይነካል። የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው እንግዲህ። አንዱን ለቅዱስ ተግባር ይፈጥረዋል። ሌላውን የሴጣንን ባህሪ ያለብሰዋል።

ቪዲዮው በቴሌግራም ቻናላችን ተለቋል ጆይን እያላችሁ ተቀላቀሉ
https://amharic-zehabesha.com/archives/186117

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...