Wednesday, August 2, 2023
በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
በመላእክትነት ተመርጦ የነበረው ሳጥናኤል እግዚአብሔርን ከድቶና ክርስቶስን ወደ ተራራ ወስዶ ከተማ እያሳዬ በንብረት ሊደልለው ሞከረ፡፡ የሳጥናኤል ተከታዮች ደግሞ ከዓለም በፊት እግዚአብሔርን እያመለከ የኖረውን አማራ አንድነት፣ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኢትዮጵያ ሱሴ ወዘተርፈ በሚሉ የቁማር ካርታዎች ሲያታልሉ ኖሩ፡፡ አማራ ክርስቶስን ስላለሆነ ተታለለ፡፡
በቁማር መጫዋቻ ካርታ መደለሉ የሰለቸው አማራ ራሱን ለማዳን መሰባሰብ ሲጀምር ደሞ እንደተለመደው ከሀዲዎች የአንድነት ፓርቲ ያስፈልጋል የሚል ሌላ የክህደት ወጥመድ በማጥመድ ላይ ይገኛሉ፡፡
ሳጥናኤል አዙሮ የምያይበት አንገትና ይሉኝታ እንደሌለው ሁሉ እነዚህ የአንድነት ድስኩር አቀንቃኝ ከሀዲዎችም ትናንት የሰሩትን ዞር ብለው የሚያዩበት አንገት፣ እንደ አቡጀዲ የሸረከኩትን ውሽት የሚያፍሩበት ህሊናና ይሉኝታ የሳጥናኤል ያህል እንኳ የላቸውም፡፡
አማራ በእነዚህ ከሀዲዎች የአንድነት ድስኩር እየተታለለ ለሃምሳ ዓመታት ሳይደራጅ በምቅረቱ እየደረሰበት ያለውን የዘር ፍጅት ሰው ቀርቶ በደመ ነፍስ የሚንቀሳቀሱት እንሰሳትም ሊረዱት የሚችሉት ግፍ ነው፡፡
እነዚህ ድርጅት በማፍረስ ሰይጣን እንኳን የማይሰተካከላቸው ጉዶች ዛሬም እንደ ወትሮው አዙሮ የሚያዩበት አንገትና ሊያፍሩ የሚችሉበት ህሊና ወይም ይሉኝታ ስለሌላቸው ከምድር ላለመጥፋት በመዋደቅ ላይ ያለውን አማራ ሊያዘናጉ የአንድነት ፓርቲ የምትባል ቁማር እንደተለመደው ይዘው ብቅ አሉ፡፡ ዳሩ ዛሬም በዚህ ከሀዲዎች እንደገና ተጠልፎ የሚወደቅ የአማራ የእንግዴህ ልጅ ምሁር ያጣሉ አይባልም፡፡ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱሴ አንድነት በሚሉ ይሁዳዊ ሰባኪያን የተንዘላዘሉና የተከንከረፈፉ ጅላጅል ምሁራን በዛሬው የአንድነት ፓርቲ ስብከትም እንደ ገለባ ተጠርገው የአማራ ማሳሳቱን አይቀጥሉም አይባልም፡፡
መጃጃል የማይሰለቻችሁ ምሁራን ሆይ! የወቅቱ የአማራ ትኩረት የመኖር ያለመኖር ትግል ነው፡፡ ህሊናና ይሉኝታ በሌላቸው ከሀዲዎች በአንድነት፣ በኢትዮጵያ፣ በአባይና በወደብ ስብከት መታለልና መጭበርበር በቃው!! አማራ ጊዜውን፣ እውቀቱን፣ ጉልበቱን፣ንብረቱንም ሆነ መንፈሱን ማዋል ያለበት ለራሱ ህልውና ብቻ ነው፡፡ አማራ እንደ ማርያም ጠላት በሚዋከብበት በዚህ ክፉ ዘመን የራሱ ልጅ እየተራበ ሌላውን አጎርሳለሁ የሚል፣ የራሱ እያረረበት የሌላውን የሚያማስል የእንግዴህ ልጅ ነው፡፡ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱሴ፣ አንድነት እያሉ የአማራ ምሁራንን ሲያጃጅሉ የኖሩት ቁማርተኞች ዛሬ ደሞ ለሃምሳ ዓመታት ሲጠለፍበትና ሲታረድበት የኖረውን የአንድነት ማዘናጊያ ወጥመድ አጥምደው አማራን ለመጥለፍና ለማስጨረስ እየተቅበዘበዙ ነው፡፡
አማራ ነቅተህ ጠብቅ! የከሀዲዎች አንድነት ፓርቲ ጆቢራ አማራን አዘናግቶ ለማስጨረስና ለመብላት ዛሬም እየዞረ ነው!
ዓባይን ማን መቼ ይገድበው? https://amharic-zehabesha.com/archives/126545
ፈንድ ፈንዳጅ ዲያስጶራ እባክህ ስማ! ለዘራፊዎች የማይነጥፍ ጥገት መሆንህ ይብቃ! https://amharic-zehabesha.com/archives/176751
https://zehabesha.com/the-genesis-of-ethiopian-problems-the-ghion-river-and-eyerusalem/
ነሐሴ ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.
https://amharic-zehabesha.com/archives/184619
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment