ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
ብአዴኑ አበባው ታደሰ ኦነጋዊ ጌታውን ጭራቅ አሕመድን ለመስደሰት በመቻኮል፣ ሺ ዓመታት ያስቆጠረውንና ቀፎው እንደተነካበት ንብ በነቂስ የተነሳውን ፋኖን በሁለት ሳምንት ውስጥ አጠፋለሁ ብሎ ተነስቷል። ይህ ችኮላው ግን ለፋኖ ትልቅ ዕድል ይከፍትለታል። ፋኖ ማድረግ ያለበት በችኮላ እየተሯሯጠ የታጠቀውን ያበባው ታደሰን ጦር አድፍጦ ከመታ በኋላ እያሯሯጠ ትጥቁን ማስፈታት ነው። ለዚህ ተግባር ደግሞ በተግባር የተፈተኑት የማኦ ዜዶንግ ሦስቱ ስልታዊ ትእዛዞች (The Three Tactical Commandments) ፍቱን ናቸው።
- ጠላትሲበረታ አፈግፍግ
- ጠላትሲዳከም አጥቃ
- ጠላትሲያርፍ አውክ
እነዚህ ስልታዊ ትዕዛዞች ተተግብረው፣ ያበባው ታደሰ ጦር ተባሮ ቀበሌወችና ቀጠናወች ነጻ ሲወጡ ደግሞ፣ ፋኖን ይበልጥ በማጠናከር ትግሉን ይበልጥ ለማቀጣጠል፣ የማኦ ዜዶንግ አሥሩ ስነስርዓታዊ ትዕዛዞች (The Ten Disciplinary Commandments) የግድ መተግበር አለባቸው።
- ያለቃህንትእዛዝ ቅንጣት ሳትጠራጠርና ላፍታ ሳታንገራግር ፈጽም፡፡
- የሕዝብን ንብረት አትንካ፣መርፌም ብትሆን፡፡
- ከሕዝብስጦታ አትቀበል፣ ክርም ብትሆን፡፡
- ከሕዝብምንም ነገር አተዋስ፣ የግድ መዋስ ካለብህ ደግሞ የተዋስከውን ወዲያውኑ ተጠቅመህ በተዋስክበት ሁኔታ መልስ፣ ካበላሸህም ትክክለኛ ዋጋውን ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)፡፡
- ከገበያምሆነ ከየትም ቦታ ለምትገዛቸው ወይም ለምትሸምታቸው ነገሮች ሁሉ ተገቢ ዋጋቸውን ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)፡፡
- በውጊያወቅት ላወደምከው ወይም ላጠፋኻው ወይም ለጎዳኻው የሕዝብ ሐብት፣ ንብረትና ሂወት ተገቢውን ካሳ ሙሉ በሙሉ ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)፡፡
- የውጊያግርግር ለዘራፊ ያመቻልና፣ በግርገሩ የተዘረፈን፣ የተበዘበዘን ወይም የተመዘበረን የሕዝብ ሐብትና ንብረት አስመልስ፣ ማስመለስ ካልቻልክ ደግሞ ተገቢውን ካሳ እራስህ ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)፡፡
- ሴት፣ወንድ፣ ሕጻን፣ አረጋዊ ሳትል ማናቸውንም ሰው ስታናግር ሁልጊዜም በትሕትና አናግር፣ በተቻለህ መጠን ደግሞ እርዳ፡፡
- ልጃገረድ፣ኮረዳ፣ ባለትዳር፣ ፈት፣ ጋለሞታ፣ ሴታአዳሪ ሳትል ሴትን አክብር እንጅ በጭራሽ እንዳትደፍር፡፡ ግዳጅ ላይ እስካለህ ድረስ ከሩካቤ ሥጋ ፈጽሞ ታቀብ፡፡
- ምርኮኛምሆነ እስረኛ አታጎሳቁል፣ በተቻለህ መጠን ተንከባከብ፡፡
ፋኖ የጭራቅ አሕመድን ጭራቃዊ ጦር አከርካሪውን መምታት ያለበት መውጫ መግቢያውን በደንብ በሚያውቀው፣ ለሽምቅ ውጊያ ምቹ በሆነው ባማራ ክልል ላይ ነው። የጭራቅ አሕመድ ጭራቃዊ ጦር አማራ ክልል ላይ አከርካሪው ተመትቶ ፍርክርኩ ከወጣ፣ ሌሎቹን የጦቢያ ክፍሎች ለመቆጣጠር የሚያስፈልገው የጭራቁን ርዝራዦች የማጽዳት ዘመቻ (mopping operation) ብቻ ይሆናል።
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com
https://amharic-zehabesha.com/archives/184590
Sunday, July 30, 2023
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment