Saturday, June 3, 2023
በየማኅበራዊ መገናኛው የምንሰማው እውነት ከሆነ - ሐሰት የሚወራበት ምንም ምክንያት ያለ አይመስለኝም፣ የዐቢይና እሱ የፈጠረው የብልፅግና መንግሥት ከፋሽስቱ ኢጣልያንም የከፋ መሆኑን በተደጋጋሚ አረጋግጧል ማለት ትክክለኛ አገላለጽ መሆኑ የሚካድ አይመስለኝም። ታዲያ እነዚያ "አሁንስ ይብቃ" (No More) እያሉ ይጮኹ የነበሩት አፎች የት ገቡ። "ባዕድ ኀይል በአገራችን ጉዳይ አይግባ" ሲሉ ላንቃቸው እስከሚበጠስ ጮኹ፤ ዓለምንም ከጫፍ እስከጫፍ አነቃነቁ። አሁን ታዲያ ይኸው መንግሥት አገሪቷን በጭፍኑ ሲያጠፋ፣ ሲያወድም፣ ከሩዋንዳ በከፋ እንጂ በማያንስ መልክ ሕዝብን ሲያፈናቅልና ሕፃናትን ለጅብ እራት ሲዳርግ፣ ቅዱሳትንና ታሪካዊ መካናትን አላንዳች ርኅራኄ ሲደመስስ፣ ጆሯቸው ዳባ ለብሶ፣ አፋቸውም ተደፍኖ መቅረቱ ምን ይባላል።
ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የቤተክርስቲያኒቷ ጳጳሳትስ ለምን ዝምታ መረጡ። በሥልጣናቸው ሲመጣ ብቻ ነው ወይ እሳት ለብሰው፣ እሳት ጐርሰው፣ ምእመናኑን ከጐናቸው አሰልፈው፣ መንግሥትን መግቢያ መውጫ የሚያሳጡት፤ ሰማዕትነትን የሚመኙት። እንዴት አያፍሩም። "ኢትዮጵያዊ እንደመሆኔ የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል" ብለው ስለአገራቸውና ስለሃይማኖታቸው በኢጣሊያን ጦር ተኳሽ ቡድን ብርቅ ሕይወታቸውን የሠውት ያ ታላቁ አቡነ ጴጥሮስ ዛሬ በሕይወት ቢኖሩ እንደነዚህ ዐይነቶቹን አባቶች ምን ይሏቸው ይሁን።
ኢትዮጵያዊ መሆን እጅግ በጣም በሚያሳፍርበት ወቅት ነን ያለነው። የማያፍር ልበደንዳና ካለ፣ ሰው መሆኑ ራሱ አጠራጣሪ ነው ማለት ይቻላል።
ኀይሌ ላሬቦ
--
https://amharic-zehabesha.com/archives/183110
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment