Saturday, June 3, 2023

በኦሮሚያ ክልል ገላን ከተማ በሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ በአፈና የቆዩ 38 ግለሰቦች ደርሶብናል ያሉትን ኢሰብአዊ ድርጊት ለችሎት ተናግሩ
#image_titleግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

አሻራ ሚዲያ ፣

ለተጨማሪ ምርመራ በሚልም ለሰኔ 5 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጧቸዋል።

በህቡዕ ተደራጅታችሁ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተንቀሳቀሳችሁ ነው፣ አማራ ክልል ድረስ አደረጃጀት ዘርግታችሁ ሁከት እና ብጥብጥ ቀስቅሳችኋል፣ ማነው መሪያቹህ? በሚል በጦር መሣሪያ በማስፈራራት እና ከፍተኛ የሆነ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጥቃት በመፈጸም አሰቃይተውናል የሚሉት በ3 መዝገብ የተከፈሉ 38 ግለሰቦች ከግንቦት 18/2015 ጀምሮ ወደ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሜክሲኮ መወሰዳቸውን ተከትሎ ግንቦት 21 እና 22/2015 ፍ/ቤት ቀርበዋል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የችሎት ውሎውን እና ተጠርጣሪ የተባሉ 38 ግለሰቦች ለፍ/ቤት ያቀረቡትን አቤቱታ በተመለከተ ጠበቃ ሰለሞን ገዛህኝን እና ጠበቃ ቴዎድሮስ ወልደ ሚካኤልን አነጋግሯል።

ጠበቆች በበኩላቸው ከእስረኞች የሚሰሙት የሰብአዊ መብት ጥሰት በእጅጉ እንደረበሻቸውና በጥሩ ስሜት ላይ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፤ ይህ የመከፋት ስሜትም በተመሳሳይ በዳኞች ላይም እንዳለ ገልጸዋል።

እጁን በጥይት የተመታ፣ ኩላሊቱን የተመታ፣ አንገቱን በከስክስ የተረገጠ፣ በመሳሪያ እና በዱላ የተደበደበ፣ ምግብ እንዳያገኝ ለቀናት የተከለከለ ሌላ ሌላም ከባድ የወንጀል ድርጊት የተፈጸመባቸው መሆኑን እስረኞቹ ስለመግለጻቸው አውስተዋል።

ጠበቃ ሰለሞን እና ጠበቃ ቴዎድሮስ እንደገለጹት ተጠርጣሪ የተባሉት ግለሰቦች በ3 መዝገቦች በ16፣ በ12 እና በ10 ተከፋፍለው ወደ ችሎት ቀርበዋል።

መዝገቡ የሚጠራውም:_

1) መላክ ምሳሌ መንግስቱ፣

2) ደበበ ባሻህውረድ እና

3) በበቀለ ቢራራ አባይ በሚባሉ ሰዎች ነው፤ በእነ በቀለ ቢራራ መዝገብ ከአጣዬ እና ራያ አካባቢ ተይዘው የመጡ ናቸው፤ በቆይታቸውም ከፍተኛ በደል የደረሰባቸው መሆኑን ለመረዳት መቻሉን ገልጧል።

እንደአማራጭ የተወሰደውም 38ቱ የግፍ እስረኞች እያንዳንዳቸው ደርሶብናል የሚሉትን አሰቃቂ በደል ሁሉ በጽሁፍ ፊርማቸውን አካተው ለጠበቆች እንዲሰጡ እና ጠበቆችም የሚከራከሩበት እና ለተለያዩ ሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋማት ለማድረስ መስራትን እንደሆነ ተገልጧል።

የግፍ ግፍ ተፈጽሞብናል ያሉት የ38 እስረኞች ስም ዝርዝርም:_

1) ቢኒያም አለማየሁ (ሲቪል ኢንጂነር)

2) መላክ ምሳሌ (መሐንዲስ)

3) ዳዊት ይፍሩ (ዋና ኢንስፔክተር)

4) ጌጤ አመኑ (ሳጅን)

5) ጌታወይ ታደሰ(ኮማንደር)

6) አወቀ ስንሻው (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኛ)

7) ይመር ምንተስኖት(ሲቪል ኢንጂነር)

8 ጌታነህ ብርሀኔ(ጤና መኮነን/ምኒልክ ሆስፒታል)

9) አብርሃም መልካሙ(ሳይካትሪስት/የአለርት ሆስፒታል)

10) ምኒበል ጀግኔ(ሳይካትሪስት/የጦር ሃይሎች ሆስፒታል)

11) ኤርሚያስ መኩሪያ(phd)

12) ደበበ ባሻህውረድ(ባለሃብት)

13) ንብረት አበጀ(የግሮሰሪ ባለቤት)

14) ይልማ በዛብህ(በቦሌ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ)

15) ቅድስት ከበደ(የቤት እመቤት)

16) ፍቃዱ መንግስቴ(ፋርማሲስት/ዘውዲቱ ሆስፒታል)

17) አንዷለም አሻግሬ(እንስፔክተር)

18) ማናየ አየለ(MBA/የግል ስራ)

19) አለም ሁሉምጤና(መምህር)

20) ይስሃቅ አይቼው(መርጌታ)

21) ጌታነህ ታከለ(የአየር መንገድ ሰራተኛ)

22) እንዳልካቸው እሸቱ(የሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅት ሰራተኛ)

23) ክበር አለማየሁ(መሐንዲስ)

24) ባሳዝን እርገጤ(የአንበሣ ባስ አሽከርካሪ)

25) መብራቱ አበራ(የኮንስትራክሽን ሰራተኛ)

26) ውበት አካል(ጥበቃ)

27) ዜና ሀይሉ(የኮንስትራክሽን ሰራተኛ)

28) ሰለሞን ደሴ(ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አካውንታንት)

29) በቀለ ቢራራ አባይ፣

30) ፍቃዱ አሰፌ አበበ፣

31) ኤርሚያስ ደረሰው ሰፊው፣

32) ዳንኤል ደምሰው ገሰሰው፣

33) በላይ ጋሻው አራጌ፣

34) ሄኖክ መንገሻ፣

35) ደጉ አያሌው ወርቁ፣

36) ክብረት ይርዳው ተመቼ፣

37) መላክ ደርብ ንጉሴ እና

38) ደፋሩ ሰማው ሞላ መሆናቸው ተገልጧል።

በግራ ቀኙ በኩል ክርክር ከተደረገ በኋላ የደረሰባቸው በደል በጽሁፍ እንዲቀርብ በፍ/ቤቱ ታዟል፤ ሁሉም ለሰኔ 5/2015 እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።

"ውድ የአሻራ ሚዲያ
https://amharic-zehabesha.com/archives/183145

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...