Thursday, June 22, 2023
ለበርካታ ዓመታት ዐይን ያልነበረው ሰው “ነገ ዐይንህ ድኖ ማየት ትጀምራለህ” ቢሉት “የዛሬን እንዴት አድሬ?” አለ ይባላል፡፡ እውነቱን ነው፡፡ የለመድከው ነገር ብዙም አያስጨንቅም፡፡ አዲስና የምትመኘው ነገር ሲቃረብ ለማየት ትጓጓለህ - ተፈጥሯዊም ነው፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በተለይ አንድን መጥፎ ነገር ከለመድን በኋላ ያን የለመድነውን ነገር ለመተው እንቸገራለን፡፡ መጥፎ ነገር ዕጣ ፋንታችን የሆነ ይመስል ለዘመናት ከተጣባን ክፉ የአስተዳደር ደዌ ነፃ ለመውጣት ስንታትር አንታይም፡፡ ወይም በሌላ አገላለጽ ሌሎችና ጥቂቶች ታግለውና መስዋዕትነት ከፍለው እኛ ምንም ወጪ ሳናወጣ ነጻ መሆንን ነው የምንሻ፡፡ ያደለው ሕይወቱን ቤት ንብረቱን፣ ትዳሩን …. ገብሮ ሀገርንና ሕዝብን ነጻ ያወጣል - እኛ ብዙዎቻችን ግን ገንዘባችንንም ወደን ነፍሳችንንም ወደን ነጻነትን በነጻ ለማግኘት እንመኛለን፡፡ ብቻ ኢትዮጵውያን በብዙ ነገር እንለያለን፡፡ እንደሚባልልን ስለመሆናችን እርግጠኛ ለመሆን ጥናት ያስፈልገዋል፡፡ አንድዬ ጥሎ አይጥለንም እንጂ ይህ መጥፎ ዐመላችን ከምድር ጨርሶ ሊያጠፋን ምንም ያህል የቀረው አይመስልም፡፡
እንደምን ሰነበታችሁ ውድ አንባቢያንና አድማጮች፡፡ ለተወሰኑ ጊዜያት አልተገናኘንም፡፡ ብዙዎች የሀገራችንን በፍጥነት እየተለዋወጠ የሚሄድ ታሪካዊ ክስተት በአርምሞ እየተከታተሉ እንደመገኘታቸው እኔም የዚያው አካል ሆኜ ነው ዝምታን የመረጥኩት፡፡ እንጂ እናውራ ብንል በቀን 24 ሰዓት አይበቃም፡፡
ከመስከረም 2016 በፊት የሆነ የንጋት ምልክት እንደሚታይ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ ብዙዎች ሲናገሩ ይሰማል፡፡ እኔም የዚያ ደገኛ ትንቢት ተጋሪ ነኝ፡፡ እናም ችግራችን ሊወገድ የቀሩን ጊዜያት ከሦስት ወራት አይበልጡም፡፡ ግን መጥፎ ሦስት ወራት ናቸው፡፡ የረጂምነታቸው መንስኤም እሱው ነው - መጥፎነታቸው፡፡ በአንጻራዊነት የትወራ እሳቤ - ሪሌቲቪቲ ቲዮሪ - ረገድ ካየነው የአንድ ቀን ደስታ በደቂቃዎች ሲገመት የአንድ ደቂቃ ስቃይ ለቀናትና ለወራት እንደሚሰማ ስቃይ ነው ይባላል፡፡ ሌላም እንይ፡፡ የሴት ጓደኛውን የሚጠብቅ ጎረምሳ ከተቃጠሩባት ሰዓት አሥር ደቂቃ ብትዘገይበት ለርሱ አሥር ሰዓት ነው፡፡ ከተገናኙ በኋላ የሚያሳልፉት አምስትና ስድስት ሰዓት ደግሞ የአምስት ደቂቃ ያህል ነው፡፡
ለዚህ ነው እኔም በርዕሴ እንደጠቀስኩት የኢትዮጵያ ሀገራችን የነጻነት ዘመን ሦስት መቶ ዓመታት ያህል የቀረው ሊመስለኝ የቻለው፤ እንጂ ደጃፋችን ላይ ቆሟል፡፡ ሁሉም ነገር አልቋል፡፡ ፊሽካውም ተነፍቷል፡፡ ጥሪው የደረሳቸው ጀግኖች ጀምረውታል፡፡ እግዚአብሔርም ከነሱ ጋር ነው፡፡
አማራውና የአማራው ወገኖች የሚያሸንፉት ወደው አይደለም፡፡ ተገደው ነው፡፡ ካላሸነፉ ኢትዮጵያን እርሷትና እነሱም ከምድረ ገጽ ስለሚጠፉ ነው፡፡ ኦሮሙማ ቀላል ኃይል አይደለም፡፡ ሰይጣንነት ላይ ዕብደትን ጨምሩበት፡፡ ዕብደት ላይ የዘር ጥላቻን አክሉበት፡፡ የዘር ጥላቻ ላይ ሆዳምነትንና ስግብግብነትን ደምሩበት፡፡ በሁሉም ላይ ደግሞ ድንቁርናንና ሰገጤነትን ጨምሩ፡፡ እነዚህ ኦሮሙማ የሚባሉ ጉዶች ዓለማችን አይታውና ሰምታው በማታውቀው የዕብደትና የሥነ አእምሮ ደዌ ተለክፈው ይይዙትንና ይለቁትን አጥተዋልና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደመጡበት ሲዖላቸው ይሸኛሉ፡፡
ትግሬዎች አትንካቸው እንጂ እንድትኖር ይፈቅዱልህ ነበር፡፡ ከነሱ አትብለጥ እንጂ ፍርፋሪ ሥልጣንም ሆነ የተወሰነ ሀብት ቢኖርህ ጉዳያቸው አልነበረም፡፡ ብልጦች ነበሩ፡፡ በብልጠታቸውም ላይ የተወሰነ ብልኅነት ነበራቸው - አሁን ዞሬ ሳስበው ነው ታዲያ፡፡ እነዚህኞቹ ግን ከምኑም ከምኑም ያልታደሉ ድኩማን ናቸው፡፡ ኃጢኣታችንና ክፋታችን ያመጣብን በሰው ቅርጽ የመጡ አጋንንት ናቸው፡፡
ተመልከት፤ አንድ አካል ካላበደ በስተቀር አንድን ማኅበረሰብ አጥፍቼ የራሴን የቅዠት ሀገር እመሠርታለሁ ብሎ አይነሳም፡፡ አንድ ሰው ሀገር ምድሩ በችጋርና በችግር እየተቆላ፣ በሰው ሠራሽ ጦርነት እየታመሰ፣ በኑሮ ውድነት እየተንገበገበ፣ በዘር ፖለቲካ እየታመሰ … ይህን ሁሉ ችግር የፈጠረው ግለሰብም እንበለው ቡድን ከመሬት ተነስቶ ሚሊዮኖችን እያፈናቀለና ቤት አልባ እያደረገ በሌለ በጀት በትሪሊዮን ብር የሚገመት ቤተ መንግሥት እሠራለሁ ብሎ አይነሳም፡፡ ይህን ድርጊት በዕብደት ብቻ መግለጽ ራሱ በቂ አይደለም - ሌላ አዲስ ቃል መፈጠር አለበት፡፡ ከአእምሮ በላይ ነው፡፡
ለዚህ ቤተ መንግሥት መሥሪያ ተብሎ ከድሃ ዜጎች በግብርና በቀረጥ የሚዘረፈው አንሶ አሁን ደግሞ በንብረት ታክስ ለማያዝበት የመኖሪያ ቤት፣ ንብረቱ ላልሆነ የመንግሥት ሀብት ቀረጥ ክፈል ተብሎ ሕዝቡ ያለ የሌለ አንጡራ ሀብቱን እየተገፈገፈ ነው፡፡ ለዚያውም በራሱ ፈቃድ ሌሊት ሳይቀር ወረፋ እየያዘ የሚከፍለውን ሰው ስታይ ኢትዮጵያውያንን ምን ነካቸው፣ ምንስ አስነኳቸው ብለህ ትጨነቃለህ፡፡ ለአንዲት ደሳሳ ጎጆ ከሃያ ሽህ ያላነሰ ብር በዓመት ይጠይቃሉ፡፡ ሕዝቡም እየከፈለ ነው፡፡ ዕንቆቅልሽ ሕዝብ ማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፡፡ የሚበላው ቢያጣ ለመንግሥት የሚከፍለው አያጣም፡፡
አዲስ አበባ እያበደች ነው፡፡ ቲማቲም መቶ ብርን እየታከከ ነው፡፡ ነጭ ሽንኩርት እንደቡናው ከ300 ብር አልፏል - አይቀመስም፡፡ ቀይ ሽንኩርትም ብር 80 እና ከዚያ በላይ ነው፡፡ ነገሩ ሆን ተብሎ አዲስ አበቤን የማሳበድ ሥራ እየተሠራ ነው፡፡ እንደሰማሁት አንድ አትክልት ይዞ የሚገባ የጭነት መኪና መንገዱን እንዲያልፍ ለኦነግ ሸኔ በመቶ ሽዎች የሚቆጠር ብር ይከፍላል አሉ፡፡ ያን የከፈለውን ለማወራረድ ታዲያ ዕቃው ላይ ይከምሩበታል - ለዚያውም ለማለፍ ከተፈቀደለት፤ አለበለዚያም ከፍሎም ዕቃው ላይሰጠው ይችላል - በተለይ አማራ ከሆነ፡፡ እናም በ5 ብር የገዙትን አትክልት አዲስ አበባ ሲገባ ዋጋው ሰማይን ያልፋል፡፡ በነገራችን ላይ ሰው ብቻ ሳይሆን ዕቃም እየታገተ ከፍተኛ ገንዘብ እየተጠየቀበት ነው፡፡ የሰሞኑን የሹፌሮች እገታ ግን አንድዬ ይግባበት - የሚጠየቅባቸውም በሰው አንድ ሚሊዮን ብር ነው፡፡ እግዜር ይግባበት የምለው ከልምድ በመነሳት የተጠየቀው ገንዘብ ቢከፈልም እንኳን የመትረፍ ዕድላቸው አነስተኛ በመሆኑ ነው፡፡ የስኳር ፋብሪካዎችም በአቢይና ሽመልስ ይሁንታ በሸኔ ተይዘዋል፡፡
ቀድመን ተናግረናል፡፡ የተናገርነው እየሆነ ሲታይ መደመም ብቻ ነው፡፡ አማራም ሆነ ሌላው ዜጋ ከእንግዲህ በአዲስ አበባ መኖር አይችልም፡፡ እንኳን አዲስ አበባ በወያኔ ተሰፍሮና ተለክቶ በተሰጠው ክልል ተብዬ አካባቢም መኖር እንዳይችል ጨፌ ኦሮምያ ወስኖ ኦነግ ሸኔ እየተላከበት ነው፡፡ ብአዴን የተባለው መጋጃም የኦነግ ተባባሪ ነው፡፡ ለርሱ መላ ካልተፈለገለት የአማራ መጨፍጨፍ በቀላሉ አይቆምም፤ ነጻነትም ከሦስት ወር ባለፈ ሊዘገይ ይችላል፡፡
በዚህ አጋጣሚ አማራ ሆኖና አማራን በማንኛውም ረገድ ወክሎ እያለ ለኦሮሙማ አድሮ ይህን የዋህና ቅን ሕዝብ የሚያስጨፈጭፍ አማራም ሆነ ሌላ ዜጋ ጥቁር ውሻ ይውለድ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ሁሉም በሠራው ልክ እንደሚከፈለው ብረዳም አማራን እወክላለሁ ብሎ አማራን ለጭዳነት እንደሚዳርግ ሆዳምና ኅሊናቢስ ሰው በንዴት የሚያጨሰኝ የለም፡፡ እርግጥ ነው - ክርስቶስን የሸጠው የራሱ ወገንና እንዲያውም የራሱ ደቀ መዝሙር ይሁዳ ነው፡፡ ይሄ ሆድ የሚሉት ትንግርተኛ ነገር ሰውን የማያደርገው የለምና እነደመቀ መኮንንንና አገኘሁ ተሻገርን፣ ሰማ ጥሩነህንና ተመስገን ጥሩነህን ባሪያ ቢያደርጋቸው ከዕውቀታቸው ማነስም አኳያ ብዙም አይፈረድባቸውም፡፡ ግን መሽቶባቸዋል፡፡ በወደዱት ቆርበዋልና በቆረቡት ሰይጣናዊ ሥጋ ወደሙ ሊኮነኑበት የፍርድ ሚዛኑ አጠገባቸው ደርሷል፡፡
ለማንኛውም አማራው እንዳያርስም፣ እንዳይነግድም፣ ተዘዋውሮ ባመቸው ሥፍራ በገዛ ሀገሩ እንዳይኖርም ከተደረገ ቆዬ፡፡ አማራ ሸገር ከሚባለው የምናብ ከተማ ሲባረር ለቤቱ ማፍረሻ ብር ከፍሎ፣ እምቢ ካለም ከነሚስትና ልጆቹ ተገድሎ፣ ሀብት ንብረቱንና ቆርቆሮውን ሳይቀር በአፍራሾቹ ተዘርፎ፣ ባካባቢው ልከራይ ቢል ተከልክሎና ላከራይ የሚል ኦሮሞ ቢኖር እንኳን በብርና በእሥራት ተቀጥቶ፣ … ብዙ ነው ታሪኩ ወገኖቼ - ሲዖላዊ ሕይወት እየገፋ ነው አሁን የሚገኘው፡፡ የዚህን ሁሉ ግፍና በደል የዞረ ድምር ማን እንደሚከፍል የሚተርፍ ያየዋል፡፡ ወንድሞቼ ኦነግ አሁን በርትቷል፤ እሽቅንድር አድርጎታል፡፡ ሽመልስ አብዲሣም የሚያደርገውን ብቻ ሳይሆን የሚናገረውንም አሳጥቶታል፡፡ ሲሻው ሶፍት ያድለናል፤ ሲሻው “ገና ምን አይታችሁ! በመቶ ሽዎች የሚገመቱ ቤቶችን እናፈርሳለን!” እያለ ያስፈራራናል፡፡ ከተራበ ለጠገበ መታዘኑ ለዚህ ነው፡፡ እኛ ርሀባችንን ስንችል እነሱ ጥጋባቸውን መቻል አቃታቸው - እንደዘመናዊው አገላለጽ - ጥሩ አማርኛ!! ወይ ኦሮሙማ፡፡ ጥላቻ እንዲህ ያሳብዳል? ብለው ብለው እኮ “ህጋዊ ድሃ” የሚል ዘዬ ፈጥረው በ“ቋንቋ ዕድገት”ም እያስደመሙን ነው፡፡
ልብ በል፡፡ አማራ በአዲስ አበባ መኖር ከተከለከለ አምስት ዓመታትን አስቆጠረ፡፡ አሁን እየኖሩ ያሉ አማሮችም በገንዘብ ኃይል እንጂ ደልቷቸው አይደለም፡፡ ይህም ዕድል በቅርቡ ይጠፋል፡፡ አማራ ከሆንክ አዲስ አበባ ውስጥ መነገድም ሆነ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ሠርተህ መኖር አትችልም፡፡ ጉሊትና የሸቀጥ መደብሮች ሁሉ እየፈራረሱ ነው፡፡ የሳጠራና የሸራ ቤቶች ሁሉ እየፈረሱ ውድማ ሆነዋል - ፒያሣን እይ ለምሣሌ፡፡ እነዚያ ለአራዳ ክፍለ ከተማ ውብ ጌጥ የነበሩ መነጽር ቤቶች ዛሬ ፈራርሰው በረሃ መስለዋል፡፡ ለምን ሲባል አንድ የኦነግ ባለሥልጣን ቋንቋም እንደካልሲ አጥሮት “በሸራ ቤቶች ውስጥ የጦር መሣሪያ ለማግኘት ሞክረናል” ሲል እንዳሳቀን ሁሉ በየአርከበ ሱቆቹ ውስጥ ታንክና መትረየስ እየተገኘ የአማራ ጸንፈኛ ህገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ ሙከራ ሲያደርግ የተደረሰበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነው የሚገኝ፡፡ ጉድ ነው ኦነግና ኦሮሙማ የሚያሳዩን ድራማ፡፡ በማከያው ግን አዲስ አበባ ውስጥ በተለይ ቀምሶ የሚያድር ሰው በጣት የሚቆጠር ሊሆን ጥቂት ጊዜ ብቻ ይቀራል፡፡ ሁሉም ወደ ድህነት እየተገፋ ነው፡፡
አዲስ አበባ አሁን ያለች ትመስላለች፡፡ ግን የለችም፡፡ ኦሮሙማ እንዳሻው የሚፈነጭባት ካምሱሯ የተቀጣጠለ ባግዳድና ደማስቆ ናት - ያኔ ዱሮ በሰላማዊነቷ ዓለም የሚያውቃት አዲስ አበባ፡፡ ማን እንደሚተርፍ ልናይ ነው - ፈጣሪ በፀጋው የሚሸፍናቸው ነገን ያያሉ፡፡ አማራው ግን በርታ፡፡ በቅድሚያ ታዲያ ቤትህን አጽዳ፡፡ ጓዳ ጎድጓዳህን ከመዥገሮችና ከነቀዞች ሳታጸዳ ትግል ብትጀምር በቀላሉ ስኬታማ አትሆንም፤ ብዙ ዋጋ ትከፍላለህ፡፡ ድሉ ያንተው ነው - በዚህ ጥርጥር አይግባህ፡፡ ግን መጠንቀቅ ያለብህ ከራስህ ጉዶችና ከድል አጥቢያ አርበኞች ነው፡፡ ሁሉንም መናገር አይገባኝም፡፡ ትግሉ ከአስመሳዮች፣ ከሌሊት ወፎችና ከእስስቶች፣ ከጅቦች፣ ከተኩላና ቀበሮዎች ከዓሣማዎች ነጻ ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያን ከመፈራረስ አማራንም ከተደገሰለት ዓለም አቀፍ የጥፋት ዐዋጅ መታደግ ይቻላል፡፡
እዚህ ላይ ሳልጠቅሰው ማለፍ የሌለብኝ ነጥብ አለ፡፡ እሱም የሃይማኖት ጉዳይ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ጥፋት ከዋና ግብኣትነት ባልተናነሰ ኦርቶዶክስ ውስጥ የተሰገሰጉ የአጋንንት ወኪሎች ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ ይሄ በሁለት ቢላዎ የሚበላ የሃይማኖት አባት ነኝ የሚል ሁሉ ሊጸዳ ጥቂት ጊዜ ቢቀረውም እየሠራው ያለው ደባ ግን መታወቅ አለበት፡፡ ሃይማኖታችን በማን እንደተያዘ እናውቃለን - በአለባበስና በአነጋገር አንታለልምና የውስጡን ለቄስ አባቶችን ገመና የማናውቅ ከመሰላቸው ተሳስተዋል፡፡ ደመወዝ ብዙ ይናገራል፤ የኑሮ ዘይቤ ብዙ ይናገራል፤ የሰውነት አቋም ብዙ ይናገራል፡፡ አካባቢና ጎረቤት ብዙ ያውቃል፡፡ ከቫቲካን እስከ እስክንድርያና እስከ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሣጥናኤል እንደተቆጣጠረ ከግምት ባለፈ እናውቃለን፡፡ ብዙ ምሣሌ መጥቀስ ቢቻልም ደብረ ኤልያስ ገዳም አንድ መነኩሴ እስኪቀር ሲደበደብና ንዋየ ቅድሳት ሲዘረፉ፣ ሲቃጠሉና ሲወድሙ አንድም የሲኖዶስ አባልና ሲኖዶሱም ራሱ ትንፍሽ አላሉም፡፡ ይህ የሚጠቁመን ሃይማኖቱም በዓለማውያን ቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ እንጂ አንድ ጴጥሮስና አንድ ተክለ ሃይማኖት ቢኖሩን ኖሮ ይሄኔ የተወሰነ ለውጥ ማየት እንችል እንደነበር መገመት አይቸግርም፡፡ ስለዚህ ቤተ መንግሥቱ ብቻ ሳይሆን ቤተ እምነቱም መጽዳቱ የሚጠበቅ ነው - ሁሉንም የተቆጣጠረው አንድ ኃይል ነውና፡፡ በተለይ ስለሃይማኖቱ የተናገርኩት በጣም ትንሽ መሆኑን እንድትረዱልኝ እፈልጋለሁ፡፡
https://amharic-zehabesha.com/archives/183793
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment