Sunday, April 23, 2023
#image_title
ተቸግረን ተለቅተን፣ተጨምተን ታግሰን
ስንጠብቅ፣ስንጠብቅ...
አንድ ቀን ይነጋል፣ዕናያለን ጮራ
ለውጥ ይመጣል ብለን፣ሰማይ ብናንጋጥጥ
የውሃ ሽታ ነው፣በእውን ማይከሰት
የቁልቁል እንሽርት፣መዝቀጥ ዝቅ ማለት
ዕያለሙ ወደፊት፣የኋሊት መገስገስ፣ማነስ ከሰውነት
ከማጥ ከጭቃ ውስጥ፣ገብቶ መጨማለቅ።
አወይ የኛ ሀገር?
አቤት የኛ ሕይወት?
አቤት የኛ ኑሮ?
ቅጥ አምባሩ የጠፋ፣የተዘባረቀ፣ትርጉም ፍች የሌለው
ውሉ ማይታወቅ፣ማንም ሚዘውረው::
ደረጃም የሌለው፣መስፈርትም የማያውቅ
ለመውጣት፣ለመውረድ
ከምንም ተነስቶ፣ዘሎ ፊጥ ማለት
ሲወርዱም መከስከስ።
ሀገርን መገንቢያ፣ሕዝብን ማገልገያ
የሥልጣን ዙፋንን፣ክብሩን አጥፍተን
ፍጥረተ ሰብእ ንቀን፣ገዝፈን ከተፈጥሮ
ምንኖር መስሎናል፣ተከብሮና ታፍሮ::
ሕግ ሥርአት ሽረን፣ወግ ልማድ ቅርስ ባህልን አውድመን
ፍርሀት ሽብር ነዝተን፣ሕዝብ ብናቀጠቅጥ
ለጊዜው ነው እንጂ፣ብዙም ዕድሜ አይዘልቅ።
"ለምጣዱ ሲባል፣አይጧ ትለፍ" እንደ ሚለው ብሒል
ሲሰደብ ሲንቋሸሽ፣ሲበደል ሲገፋ፣ሲቀማ ሲዘረፍ
ሰምቶ እንዳልሰማ፣ዐይቶ ዕንዳላየ በይደር ያለፈ
እንደ እዮብ ጸንቶ፣በብርቱ የታገሰ
በሠላም ለመኖር፣ለሀገር ተብሎ እንጂ
አንገቱን ሚደፋ፣ሆዱን ባንጀቱ አስሮ
ውሃ ተጎንጭቶ፣ጥሬ ሚቆረጥም
ከለየ ነገሩ፣ከቆረጠ አጀቱ
የጥፋትን መንገድ፣ማንም አያጣውም!!::
ዓለም ሲሰለጥን፣ሲሻሻል ኑባሬው
አለን እኛ ብቻ፣አመድ እያፈስን
በወገን አስከሬን፣አፈር እየገፋን
ብካይ እየዘራን፣ከል እንደለበስን
በጎውን አልመን፣ጥፋትን ታግሰገን
አረንና ከስለን፣ነፍረንና ቆስለን
በጅብ ተኩላ መንጋ፣ዙሪያውን ተከበን::
~***•°•***•°•***~
ለኢትዮጵያ ወቅታዊ ኑባሬ
መዘከሪያ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ሚያዚያ ፲፫/፳፻፲፭ ዓ.ም
April 21/2023
አርብ)12:20 ምሽት(ሚኪ.ላ/አ.አ
©ያመጌዕ
https://amharic-zehabesha.com/archives/181994
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment