Sunday, April 2, 2023

በኦሮሚያ ክልል የተደረገው ሰልፍ እንደውም የዘገየ ነው
በተያዙት መፈክሮች እንደተገለፀው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወይም የብልፅግና ስርሃትን አሻግሮናል፤ እንደግፋለን ነው።

ይሄ ስርዓት እኮ!

#image_title

➡ኢሬቻውን በደብረዘይት ማክብር የተቸገረ ከነበረ አልፎ አዲስ አበባ ድረስ አርቴፊሻል ሀይቅ ሰርቶ እንዲያከብር የካሰ ስርዓት ነው፣

 ➡ለውጥ ስለጠየቀ ይታሰር ከነበር ወደ አሳሪነት የቀየረ ስርዓት ነው፤

 ➡በወያኔ ተዘቅዝቆ ይገርፈው የነበረ ኦሮሞ ዘቅዝቆ እንዲሰቅል የፈቀደ ስርዓት ነው፤

  ➡ኦሮሞ ያልሆኑትን ገድሎ ንብረት ሲያቃጥል በጠሚር ገና ጥቅሙን መቼ አስከበረ ተብሎ ያሞገሰ ስርዓት ነው፤

➡ኦነግ ጥይት ጠሽ አድርጎ ጫካ መሮጥ ከነበረበት ዘመን እንደጫጩት እንዲጨፈጭፍ የፈቀደ ስርዓት ነው፣

➡ከባንክ ጠባቂነት ወደ ባንክ ዘራፊነት የቀየረ ስርዓት ነው፣

 ➡በቋንቋው መናገር ይሸማቀቅ ከነበረ ወደ እፃናት በግዳጅ ቋንቋውን እንዲማሩ ያደረገ ስርዓት ነው፤

 ➡ከኦሮሞ ውጪ የሆነ ጋዜጠኛ እና አክቲቪስት እስከ ዶክተር እና ጀነራል እያፈነ አስሮ በድብደባ እያሰቃየ የካሰ ስርዓት ነው።

➡ኦሮሞ አይደሉም ያሏቸውን መኖሪያ ቤት በስካቫተር እየናደ ቤት አልባ ያደረገ ስርዓት ነው፤

➡ ይሄ ስርዓት እኮ ለህክምና ከሀገር ለመውጣት ቋንቋ መናገርን መስፈርት ያደረገ ነው፤

➡ይሄ ስርዓት እኮ ከተፈናቃይነት ወደ አፈናቃይነት የቀየረ ስርዓት ነው።

➡ መታወቂያ በማደል ሲቭል ሰርቪሱን የአንድ ብሄር ከለር የቀየረ ስርዓት ድጋፍ ማድረግ ቢያንሰው እንጂ አይበዛበትም።

ችግር የሚሆነው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ሌላው ሲረገጥለት ለመደሰት ነበር ወይ የሚል ጠያቂ ሲመጣ ነው።

ችግር የሚሆነው በዚህ መልኩ የአንድ ሀገር ህዝቦች መሆን እንችላለን ወይ የሚል ጠያቂ ኦሮሞ ሲመጣ ነው።

ችግር የሚሆነው ተበቃይ ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑን ማሰቢያ ሲያሰፋልን ነው።
https://amharic-zehabesha.com/archives/181484

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...