Saturday, April 29, 2023
ግርማ የሽጥላን የገደለው የአብይ አስተዳደር ነው! ምናልባት ዛሬ የምንሰማው ነገር ይህ መንግስት ከግድያው ጀርባ አለበት የሚለውን የአንዳንድ ወገኖች ጥርጣሬ ውድቅ እንዳናደርገው የሚከለክለን ይመስላል።
በሶስት አቅጣጫዎች በጎጃም፡ ወሎና ሰሜን ሸዋ በብዛት የገባው የመከላከያ ሀይል እንቅስቃሴ በአማራ ክልል ለሶስት ወራት የታቀደውን ዘመቻ ምክንያታዊ ለማድረግ በመንግስት በኩል የተፈጸመ ግድያ ሊሆን ይችላልም ብሎ መገመቱ ተራ ግምት አይደለም።
እነአሜሪካን ኢራቅን ለመውረር፡ አፍጋኒስታን ላይ ጦራቸውን ለማዝመት የተጠቀሟቸው ስትራቴጂዎችን ስንፈትሻቸው መንግስታት እንዲህ ያለ ሴራ ጠምቀው፡ እግራቸውን ማስገቢያ ምክንያት ሰበብ የሚሆናቸው ነገር ያደርጋሉ። የአብይ መንግስት ከአማራ ህዝብ መሳሪያ ለመንጠቅ የሚያስችለውን ዘመቻ ይከፍት ዘንድ አቶ ግርማ የሺጥላን የመስዋዕት በግ ሊያደርጋቸው እንደሚችል መጠርጠሩ ተገቢነት ያለው ጥርጣሬ ነው።
አንዳንድ የኦሮሞ ኢሊቶች በአደባባይ እንደሚናገሩትም የአማራ ክልል ትንሽ በጥበጥ ማለት እንደሚገባውና ፋኖን የመሰሉ አደረጃጀቶችን ለማፈራረስ የሆነ ትርምስ መፈጠር እንዳለበት በግልጽ ሲጽፉ አይቼአለሁ። የእነዚህ ኢሊቶች ድምዳሜ የኦሮሚያ ብልጽግና አመራሮች ጋር በስፋት እንደሚታመንበት ይታወቃል። እናም የአብይ አስተዳደር ከአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያ ጀርባ አለ ብሎ የደመደመ ካለ 'ጸረ ለውጥ፡ የብልጽግና ጠላት፡ ጽንፈኛና ሴረኛ' እያልኩ አልሞልጨውም። በደንብ እሰማዋለሁ። የአብይ መግለጫ መፍጠኗም የምትጠቁመውን ነገር መዘንጋት አይገባምና
https://amharic-zehabesha.com/archives/182095
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment