Wednesday, April 26, 2023
አንዱ ዓለም ተፈራ እሁድ፣ ሚያዝያ ፲ ፭ ቀን ፳ ፻ ፲ ፭ ዓ. ም. (4/23/2023)
ይሄም ያልፋል ብሎ እጅና እግርን አጣጥፎ መቀመጥ . . .
ኢትዮጵያ ምን ጊዜም ቢሆን አትፈርስም ብሎ ምንም አለማድረግ . . .
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት በደም የጨቀየ ማንፀባረቅ፤ የት እንደነበረች ሰርዞ፣ ወደየት እንደምትሄድ አደብዝዞ፣ የጭንቅ ውጥረት መንገሱን አመላካች ነው። የአገር መሪዎች፤ ሰላምን ከማስፈን፣ ሕዝቡን በማንነቱ ከማኩራትና ልማትን ከማምጣት ይልቅ፤ ለትርጉም በሚያስቸግር መንገድ፤ ኢትዮጵያን ከዕለት ዕለት ወደ ባሰ የፖለቲካ አዘቅት እየመሯት ነው። አማራው ለአገሩና ለነገ ካማሰብ ይልቅ፤ ለሕልውናው በመጨነቅ ዓይኖቹን አፍጥጧል። ለምን ከዚህ መራራ እውነታ ውስጥ ገባን? ለምን ሰላም ማጣትንና መተላለቅን ያለ ነገር ብለን ተቀበልን? መቼ ነው ካለንበት ጨለማ ባንነን የምንነቃው?
እውነት የነገ ባለቤት እንሆናለን ወይ?
የትግራ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ነኝ ብሎ አገራችንን ለአስራ ሰባት ዓመታት አመሰቃቅሎ የገዛት ቡድን፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ከቦታው ሲወገድ፤ የተሻለ መንግሥት ይመጣል ብሎ ነበር። ከፋፋይና ዘረኛ ሆኖ ተስፋ መቁረጥን፣ አድልዖን፣ ሙስናን፣ በስውር መግደልን፣ ሁሉን ነገር ለትግራይ ብሎ ሌሎችን ማስረቆቱ ያነገሠው ይሄ ፀረ-ኢትዮጵያ ገዢ ቡድን፤ ከነአስራሩ ይወድማል የሚል ተስፋ ባገር ነግሦ ነበር። ያ ተስፋ ሳይውል ሳያድር፤ በትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ቦታ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሲተካ፤ በትግራይ ትቅደም ፈንታ ኦሮሞ ይቅደም ሲነግሥ፣ አድልዖው፣ ሙስናው፣ ሕዝብን መከፋፈሉና የነበረው አገዛዝ በግለሰቦች መቀያየር ተተክቶ መቀጠሉ ድብዛው ጠፋ። በዚህ መሓል አማራው አሁንም እንደ በፊቱ የሁሉም በትር ማረፊያ ዒላማ ሆነ። አማራነት ወንጀል መሆኑ በከፋ ሁኔታ ቀጠለ። የትናንቱ ነባራዊ ሁኔታ የዛሬም ሆነ። ለውጥ ስም ብቻ ሆነ። ሕዝቡ መከፋፈሉ አሁንም ቀጠለ።
አንባቢ ሆይ!
አሁን ይሄን በሚያነቡበት ወቅት፤ የፌዴራል መንግሥቱን የሚቆጣጠረው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የሚመራው አክራሪ የኦሮሞዎች ገዢ ቡድን የኦሮሞ ብልፅግናና ኦነግ፤ በአማራው ወገናን ላይ የአውዳሚ ዘመቻ ይዟል። በድብረ ብርሃን ከተማ የቀጥተኛ አማራን የማጥፋት ሂደቱን አፋፍሞታል። በወልቃይት ዙሪያ ሕዝቡንና መሬቱን ለፀረ-ኢትዮጵያው የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ለማስረከብ በመንደርደር ላይ ነው። በራያም በተመሳሳይ ድርጊት ተጠምዷል። አዲስ አበባና ዙሪያዋ የሚደረገውን ሕዝቡ በዓይኖቹ እያየ ነው። አንድ አማራ ወደ አዲስ አበባ ለመግባትና ከአዲስ አበባ ለመውጣት ያለበትን ስቃይና ዕንግልት፤ መግለጥ ያስቸግራል።
አሁን አማራው ያለው ምርጫ ምንድን ነው? በሥልጣን ላይ የተቀመጡት “ደም የጠማቸው ሹሞች!” የአማራውን ደም ያለምንም ቅሬታ እያፈሰሱት ነው! አማራው ራሱን ማዳን አለበት! አማራው ሕልውናውን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት።
https://amharic-zehabesha.com/archives/181990
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment