Wednesday, March 1, 2023

ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ በተጨባጭ ግን እያፈረሷት ነው-ሽፈራዉ ገሰሰ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ በተጨባጭ ግን እያፈረሷት ነው-ሽፈራዉ ገሰሰ (ዶ/ር)
የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም.

ኢትዮጵያ ማለት አገር ናት፣ አንድ አገር ደግሞ አገር ለመባል መሬቱ፣ ጫካው፣ ወንዙ፣ ሸንተረሩ፣ ባህሩ፣ ሀይቁ፣ ተራራው፣ ሜዳው፣ደጋው፣ ቆላው፣ ወይናደጋው፣ በረሀው በጠቅላላው መልክዓምድሩ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል። አገር ሲባል መሬቱ፣ ውሃ ሀብቱ፣ አየሩ፣ ሉዓላዊነቱ ብቻ ሳይሆን ዋነኛው በውስጡ የሚኖረው የአገሪቱ ባለቤት የሆነው ህዝብ ባህሉ፣ ቋንቋው፣ ወጉ፣ ልማዱ፣ ሃይማኖቱ፣ታሪኩ፣ ሰንደቅ አላማው፣ ብሔራዊ መዝሙሩ፣ መለያ አርማው፣ስርዓተ መንግሥቱ፣ አንድነቱ ስርዓተ ትምህርቱ፣ ስነ ጥበቡ፣ ስነ ህንፃው፣ ታሪካዊ ቅርሶቹ፣ ማህበራዊ መስተጋብሩ፣ ብሔራዊ በዓላቱ፣ ጀግኖቹ፣ የጦር ድሎቹ፣ የነፃነትተጋድሎ ታሪኩ፣ ምግብና የምግብ ስርዓቱ፣ኢኮኖሚው ወዘተ የሚያጠቃልል ነው።

ኢትዮጵያ የብዙ ሺህ አመታት ስርዓተ መንግሥት ያላት፣ በቅኝ ያልተገዛች ከዓለማችን ቀደምት ስልጣኔወች ካላቸው ጥቂት አገሮች ውስጥ አንዷ ስትሆን በአሁኑ ወቅት ግን ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስቴሩን ጨምሮ ሌት ከቀን በሚዲያ እየወጡ ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ እየለፈፉ በተቃራኒው ግን አገሪቱን እንመራለን ብለው የተሰየሙ ባለስልጣኖች፣ የእነርሱ አላማ ተባባሪ የሆኑ የፓለቲካ ድርጅቶችና ሌሎች አደረጃጀቶች በጋራ በመሆን በተጨባጭ ኢትዮጵያን እያፈረሷት ይገኛሉ።

እየሆነ ያለውን ከላይ ከዘረዘርኳቸው የአገር ምልክቶች ውስጥ ጥቂቶቹን ወስጀ ለማሳየት እሞክራለሁ። ሉዓላዊነት

አንድ ሉዓላዊ ወይም ነፃ የሆነ አገር የራሱ የሆነ በዓለም አቀፍ ህግ የታወቀ የየብስ የባህርና የአየር ክልል አለው። ይህ አገር ከሚሰጠው ፈቃድ በስተቀር በማንኛውም አገር ወይም አገሮች ሊደፈር ወይም ሊጣስ አይችልም። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በሰሜን ምዕራብ በሱዳን ጦር በደቡብ ምዕራብ በደቡብ ሱዳን አማፂ ኃይሎች ተደፍሮ ብዙ ኪሎሜትሮች አልፈው እርሻ እያረሱና ማዕድን እያወጡ ሲሆኑ የአገሩ ባለቤት የሆኑት ኢትዮጵያውያን ግን ንብረታቸው ተዘርፎ ህይወታቸውን ለማትረፍ ተፈናቅለው በየቦታው ተበትነው የስቃይ ህይወት እየገፉ ይገኛሉ። ይህ እየሆነ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያን እያሰተዳደርሁ ነው የሚለው መንግሥት ምንም እርምጃ አልወሰደም። የአገሪቱ ሉዓላዊነት መደፈርም ሆነ ከነዚህ አካባቢውች የተፈናቀለው ህዝብ ስቃይ ፈፅሞ ሲያሳስበው አልታየም። ሉዓላዊነቱ ረዘም ላለ ጊዜ ያልተከበረ አገር በመፍረስ ላይ ያለ አገር ተብሎ የሚቆጠርበት ዕድሉ ሰፊ ነው።

ስርዓተ መንግሥት

መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያና በአማራው ህዝብ ላይ ከነበረውየመረረ ጥላቻ የተነሳና ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመቸው በየትም አገር ህገ መንግሥት የማይገኝ የኢትዮጵያን ህዝብ በጨቋኝና ተጨቋኝ በመከፋፍል ተጨቋኝ ነበሩ የተባሉት ጨቋኝ ነበር በተባለው ህዝብ ላይ የማያባራ የዘር ማጥፋትወንጀል እንዲፈፅሙበት ህጋዊ ፈቃድ ሰጥቶ እስከ አሁን ድረስ ተለይቶ እየተጨፈጨፈ ይገኛል። ይህ አየተጨፈጨፈ ያለ ህዝብ ለነፃነቱና መብቱ በሙሉ አቅሙ መነሳቱ የማይቀር መሆኑን አስቀድሞ በመገንዘብ የመፍትሄ እርምጃ ሲወሰድ አይታይም። እንዲያውም ይባስ ብሎ መንግሥት ጨፍጫፊዎችን በግልፅ እያገዘ ስምሪት እየሰጠ ይገኛል። ታዲያ ይህ ሁኔታ እንዴት አገርን አፅንቶ ሊያስቀጥል ይችላል?

አገራዊ አንድነት

ህወሓት በፈለገው ጊዜ ከኢትዮጵያ ገንጥሎ ታላቋን ትግራይን ለመምስረት እንዲችል በህገ መንግሥት ታሪክ ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ አንቀፅ ፫፱ን የመሰለ የመገንጠል መብት የሚሰጥ አንቀፅ በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት



 

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/180326

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...