Sunday, March 19, 2023

ቀዳዳው አብይ መንታ ምላሱ (እውነቱ ቢሆን)
ቀዳዳው አብይ መንታ ምላሱ

መርህ የለሹ እርባና ቢሱ

ውርዴት ቀለቡ መዋሸት ሱሱ

የሰው ደም ሆኗል ምሳና ቁርሱ

እልቂት ድግሱ ተስፋው እንኩቶ

ሬሳ መቁጠር በዘር ለይቶ

ጀሌው የመንጋ ተከታዩ ከብት

ክርፋት ወንጀሉ የገደለበት

አይሰቀጥጠው ውሸት ሲናገር

ውሸት ሲያቦካ ወንጀል ሲጋግር

ያመሻል ያድራል ሴራ ጉንጎና

የአገር ጥላቻ የህዝብ አፈና

ሰይጣን ወንድሙ ዲያቢሎስ ጓዱ

አብይ አ.ው.ሬ ነው ጥልቅ ጉድጓዱ

ማን በነገረው መራሩን እውነት

እንደተተፋ በህዝቡ አንደበት

ጽፍኩኝ ይለናል እንቶና ፈንቶ

“ግዙና አንብቡ” የእርሱን ድሪቶ

እንኳን ሊገዛ መጽሀፉን

ህዝቡ አይፈልግም ሊያየው ፊቱን

አውጥቶ አውርዶ ህዝቡ አሰላስሎ

ስለተገኘ ቀልሎና ጎድሎ

ወስኗል ህዝቡ “በቃሀን” ብሎ

ሲቃው በዝቶበት ያንገፈግፈው

ህዝቤ ተነስቷል ወጥቷል ከቀፎው

ከባድ የሆነው የድል መንገዱ

አሁን ይለያል ምርትና ግርዱ

ጊዜው ተቃርቧል የድሉ ብስራት

ህዝብ ሊያሸንፍ ከፍሎ መስዋእት

አብይ ሊቀጣ በፍርድ ሊሞት
https://amharic-zehabesha.com/archives/180863

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...