Sunday, March 19, 2023

የራያ አላማጣ እና ባላ ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄያቸው ህጋዊ ምላሽ እንዲሰጠው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ
ባሕር ዳር: መጋቢት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) "አማራ ነን እንጅ አማራ እንሁን አላልንም፤ በጦርነቱ ወቅት በማንነታቸው ምክንያት ታፍነው የተወሰዱ ወንድሞቻችን በአስቸኳይ ይፈቱ፤ ማንነት እውነት እንጅ ፍላጎት አይደለም" የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን በማሰማት ነው የአላማጣ ከተማ፣ የራያ አላማጣ እና የራያ ባላ ነዋሪዎች የቆየ የአማራ ማንነት ጥያቄያቸው እንዲመለሥ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱት።

የፌዴራል መንግሥት በተደጋጋሚ ለጠየቁት የአማራ ማንነት ጥያቄ ሕጋዊ እውቅና እንዲሠጥ በሰላማዊ ሰልፉ ጠይቀዋል።

በማንነታችን ይደርስብን ከነበረው ግፍ ተላቀን የነጻነት አየር እንድንተነፍስ ላደረገን የጸጥታ ኀይል ምስጋና እናቀርባለን ያሉት ነዋሪዎቹ መንግሥት ለቆየ የማንነት ጥያቄያችን ሕጋዊ ምላሽ እንዲሰጠን አሁንም በአጽኖት እንጠይቃለን ብለዋል፡፡

በባለ ዓለምየ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
https://amharic-zehabesha.com/archives/180859

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...