Thursday, February 23, 2023
መግለጫውን የሚመጥን ዝግጅት ተደርጓል ወይ? አብይ ብቻውን ጦርነት አይገጥምም! - አሰፋ በድሉ
አብይ በራሱ የቁማር ቋንቋ ለመግለጽ ያህል ዕጁ ላይ የቀረው ስንት ካርድ ነው? ወያኔ እና አሜሪካ፤ ሱዳን? ሌላው አነግ ነው፡፡ቀሪው መላ ኢትዮጵያ ተፍቶታል፡፡ኢሳያስ ራሱ እንዲህም አይነት ሰውም አለ እንዴ ያለ ይመስለኛል፡፡ይህ ሰው ክህደትን እንደ ፖሊሲ በአገር ደረጃ ያስተማረ ፤ያለማመደ መሪ ነው፡፡ከዕሱ በፊት ያሉት መሪወች አምባገነን የሚባሉ ብቻ ናቸው፡፡ይህ ሰው ጭካኔን እንደ ትግል ስልት የሚጠቀም በላኤ ሰብ የሆነ ሳዲስት መሪ ነው፡፡የሞት መልክተኛ ነው፡፡ከዚህ መሪ ምን ዕሴት ልጆቻችን፤አገረችንስ ትማራለች፡፡በታገልኸው ቁጥር ጭካኔው ይጨምራል፤ለጨካኝ ወሮ በላ አሳልፎ ይሰጥሃል፡፡ያቤሎ እኒያን ቅዱስ አባት በቅጥረኞቹ የሰራው ስራ ገና ልጅ የልጅቻቸው የሚመልሱት፤አንገት ደፍረው የሚሄዱበት ነው፡፡እናም ይሄ ሰው ኢትዮጵያን እያገላበጠ በዕሳት ጠበሳት፡፡በቃህ እንበለው፡፡አገር የሚቆመው በህግ ነው፡፡ለይስሙላ እንኳን የህግ ነገር አያነሳም፡፡መመሪያው ከፍ ብየየገለጽሁት ነው፡፡የምታመልጥ መስሎህ የምትርመጠመጥ በተለይም የአማራ ምሁራን ይህ ህዝብ ይፋረድሃል፡፡አብይ በለውጡ ወቅት ኮሽ ባለ ቁጥር ሮጦ ባ/ዳር ነበር፡፡አሁን ግን ብአዴን የመጠቀሚያ ጊዜውን ጨርሷል፡፡እናም ስማቸውን እንኳን ለማስታወስ የምንቸገር ሰወችን ነው እየላከ የሚያስፈራራቸው፡፡ያም ቀርቶ በስልክ ነው ዕየታዘዙ ያሉት፡፡ጨርቃቸውን ጥለው መግለጫ አውጥተው እንኳን ያው ሁሌ እንደሚያደርገው መዝናኛ ቦታ ነበር፡፡ብአዴን ማለት ጥቃት ነው፡፡ሙት ይዞ ይሞታል የተባለው ነው የደረሰብን፡፡አካባቢያዊ፤አገራዊ፤ እና አለም አቀፋዊ ግምገማ አድርጋችኋል ወይ? ማን ከማን ጋር ነው? ወኔ ካላችሁ ይሄ ታላቅ ህዝብ እና ከኢትዮጵያ ውጭ ሌላ አገር በህሊናው የሌለው ኢትዮጵያዊ አቅሙ ብዙ ነበር፡፡ ቁማርተኛውና ዘረኛውን አብየው ወያኔን የሚያስናፍቅ ሆነ፡፡የአብይ ትዕቢት ዝም ብሎ አይደለም፡፡ካልተመቸው እግር ላይ ይወድቃል፤ጊዜ ጠብቆ ደግሞ ያርድና ይስቅብሃል፡፡ ይሄን በህወሃት አሳይቶናል፡፡በጊዜአቸው ከሳሞራ ስር ነበር፡፡ጊዜ ደግሞ ሲገፋቸው፤ ሮጦ ኢሳያስ ጋር ሄደ፤ማረጋገጫ ሲያገኝ፤የቀን ጅብ እያለ ሳቀባቸው፡፡ሌላ የሚጠራጠረው ከጂኖሳይድና እና ከጦርነት የተረፈ አማራ አለ፡፡አሱን ደግሞ ለማረድ የቀን ጅብ ያላቸውን አራት ኪሎ ጠራና ወልቃይት ይመለስላችኋል፡፡አማራ ቢያንገራግር አብራችሁን ትዋጋለችሁ ወይ አላቸው፡፡በደስታ አሉት! የትግራይ ወጣት ጨርሰን በባዶ እጅ እንዴት የትግራይ ህዝብ ፊት እንቆማለን አሉት፡፡ ንቀቱ ከጀግንነቱ ሳይሆን አብሮት ካለው ሌላ ሃይል መተማመኛ የመጣ ነው፡፡አብይ ብቻውን ተዋግቶ አያሸንፍም፡፡ወያኔና ኦነግ ሲመሰረቱ በአላማ ነው፤ትክክል ይሁንም አይሁንም በዚያው መስመር ዛሬ ደርሰዋል፡፡ብአዴን ለዕለት ጉርስ ማንነቱን በምስር ሸጦ ከአሽከርነት ወደ አሽከርነት ሲሸጋገር ግማሽ ክፍለ ዘመን ዕድሜ እየተቃረበ ነው፡፡ ብአዴን ለሌላ ማገልገሉን ትቶ ፖለቲካ ሀ ብሎ ጀመረ ካልን ይሄ መግለጫ በታሪክ የሚመዘገብ የመጀመሪያው ይሆናል፡፡እስከ አሁን መደራደር የሚያስችል ብዙ አጋጣሚወች ቢኖሩትም ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል፡፡ይሄ ተኩላ መሪ እጃቸው ላይ የወደቀበት አጋጣሚወች ነበሩ፡፡ ወደ መግለጫው ልመለስ፡፡
የአሁኑ መግለጫ ከኢህአዴግ ዘመን የካድሬ የቃላት ጋጋታ ይልቅ ሰውኛ በሆነ ለህዝቡ ቅርብ ሲያልፍም ቅኔያዊ በሆነ አቀራረብ የቀረበ መሆኑ ጥሩ ነው፡፡ይዘቱን በተመለከተ፤
- የታሪክ አረዳድንበተመለከተ፡ያለፈውን ታሪክ ለታሪክ ምሁራን ትተን እኛ ፖለቲከኞች የሚያስማማንንና በጎውን ይዘን እንቀጥል ሲል ብአዴን ያለፈው በጎ ያልሆነ ታሪክ ግን ጠበቃ አይደለንም በማለት ራሱን ያርቃል፡፡ቆሞ ቀር ያሏቸውን እነ ሽመልሰን ግን የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ ብለው አሁንም መቶ ዓመት ወደ ኋላ እያዩ ያላዝናሉ በሚል መልሰው ቆሞ ቀር ብለዋቸዋል፡፡የእኔ አተያይ ታሪክን በተመለከተ በጎውም መጥፎውም የሽመልስም፤የብአዴንም እንጂ አንድ ወገን ተለይቶ ወራሽ የለውም፡፡ዛሬ ላይ በጥቁር ክላሽ ጥቁር ታሪክ እየሰሩ (ዮሐንስ ቧያለው) ፤ዘር ማጽዳትና ዘር ማጥፋትን ትንሽ እንኳን ህሊናቸውን ሳይሰቀጥጣቸው አጋጣሚው እንዳያመልጠን በማለት ማረዳቸውን ሲያሳልጡ እያየን፤ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ለዚያውም ያልተረጋገጠ፤ተስፋየ ገ/አብ የጋታቸውን የባንዳ ሴራ ለዛሬ ክፋ ስራቸው እንደ አመንክዮ መጠቀም ሚዛን የሚደፋ አይደለም፡፡ቆሞ ቀር ማለት የተከበረውን የሰው ልጅ መራቢያ ሰልቦ ዘር እንዳይቀጥል ጂኖሳይድ የሚያስታውስን ባህል እንደ ጌጥ ጭንቅላቱ ላይ አስሮ የሚዞረው ሽመልስ ነው ቆሞ ቀር፡፡የበዳይ ተበዳይ ሂሳብ ትንተና ከመጣ ከቦረና ተነስቶ ትግራይ ደብረ-ዳሞ ሲደርስ ዛሬ እያደረገ እንዳለው፤የነፍሰ ጡር ሆድ እየቀደደ እንደነበር በታዋቂው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ሃይሌ ላሬቦ ሲቀርብ ሰምቼ ታሪክ እንደሂህም ራሱን ይደግማል ወይ ? ኦነግ ቆሞ ቀር ሳይሆን ወንዝ ውስጥ ያለ ድንጋይ ይመስላሉ፡፡በቀለ ገርባ ወኔው ካለው የቦረናውን አባ ገዳ ወይስ ዶ/ር ይልቃልን እመስላለሁ ብሎ መስታወት ፊት ይቁም፡፡አቡነ ሳዊሮስ አማራ ሲሆኑ ከኦነግ በላይ አነግ ለመሆን ሲሞክሩ ታይተዋል፡፡ለመደበቅ ይሁን ይበልጥ ለመታመን ከኦነግ በላይ ኦነግ ለመሆን እየሞከሩ ያሉት አብይን ጨምሮ ብዙ ናቸው፡፡
- የኦህዴድ ስልጣን የማጽናት ስልትን በተመለከተ-በኢትዮጵያውያን መካከል በዘር፤በሃይማኖት ተቃርኖ በመጥመቅ፤ደም በማፋሰስ ኢትዮጵያውያን በፍቅር በአንድነት እንዳይኖሩ የጭካኔ ስራ በመስራት በአለም ላይ ዛሬም ትናትም ያልታየ መንግስት ነው ይላል አቶ ብአዴን፡፡ይሄ ስልት ዕድሜ ማራዘሚያ ብቻ ነውም ብለውታል፡፡ኢትዮጵያን የሰው ቄራ አደረጋት ብለው ቢገልጹት የተሟላ አገላለጽ በሆነ፡፡
- ህብረ-ብሄራዊነትንበተመለከተ፤ወንድማማችነትን በጠባብ ቡድን ና ዘረኛ እንደሆነ መገለጹ ተገቢ ነው፡፡ ከህገ-መንግስትም ጭምር ታትቶ ቢቀርብ ጥሩ ነበር፡፡አንድ ኢኮኖሚያዊናማህበራዊ ህብረተሰብ ከመፍጠር፤የዜጎችን ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት፤በህይወት የመኖር መብት፤አገሪቱን በማያባራ የደም አዙሪት ውስጥ መክተቱ የዚህ ሃይል ዕዳ መሆኑ ሊታት ይገባ ነበር፡፡
መልስ የሚፈልጉ የህልውና ጥያቄወችን በተለከ በሌላ ጽሁፍ ልመለስ
- ወልቃይትን በተመለከተ-የደቡብ አፍሪካ ውል ዘላቂ ስላም ያስገኛል ወይ? ሌላ የድርድር ለወያኔ ተቀበለውም አልተቀበለውም ማቅረብ ይቻላል ወይ? ይቺን የአብይ ካርድ ካቃጠልናት የእሱ ጉዳይ ያበቃል፡የሚተማመንበት የጦር ሃይል የሚታይ ይሆናል
- አብይ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያን እንደ ገና ዳቦ እያገላበጠ እያቃጠላት ነው፤፤እንዴት እናስቁመው? የሚለውን ለአንድነት ሃይሉ፤ለብልጽግና አባለት፡ለየትኛውም የውጭ አጋር እንዴት ማቅረብ ይቻላል ?
- ክልላዊ፤አገራዊ፤አለማቀፋዊ አሰላለፋ ምን ይመስላል?
- ጎረቤትስ፤ሱዳን፤ኤርትራ ወዘተ? ከሱዳን ጋር ጸብ በዚህ ሰዓት ራስን እንደ ማጠፋት የሚቆጠር ውሳኔ ነው፡፡ታገሱ ባካችሁ፡፡ከተቻለ ወዳጅ ለማድረግ መጣር ነው?
- የዚህን ህዝብ ነፍስ ለማትረፍ ከየትኛውም ሃይል ጋር አጋር መፍጠር ሃጢያቱ ምኑ ላይ ነው?
መሃል ሰፋሪ በሁለት ጥይት ይመታል፡፡ብአዴን ወስን፡፡በሽመልስ ስድብ ንዴት የተሰጠ መግለጫ ከሆነ ህዝብም ዋጋ እንዳይከፍል በግማሽ ልባችሁ እያመነቱ ትግል የሚመራበት ዘመን አይደለም፡፡እየታገልን ያለነው ኦነግን ነው፡፡ ከውስጥ ያለን ተላላኪ በጊዜ ማጽዳት ነው፡፡ አባቶቻችን(አባ ባህረይ) ሳያዩ እንደማይጽፋ ራሱ ጊዜ ዳኛው መልሱን ሰጠኝ!
በዕውነቱ በደንብ እንደ ህዝብ፤እንደ አገር ማሰብ ያለብን መስቀለኛ መንገድ ላይ ራሳችንን አግንተነዋል፡፡
የግፋዓን አምላክ፤የኢትዮጵያ አምላክ ይረዳናል! እንበርታ፤ክፋን እንታገል፡፡ ሁሉም በያለበት ማበርከት የሚችለው ነገር አለ፡፡ እባካችሁ አስተዋጽኦአችሁን አሳንሳችሁ አትዩ!!!
https://amharic-zehabesha.com/archives/180088
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment