Wednesday, February 22, 2023
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዢ የፈጸመባቸው አውቶብሶች ዋጋ እጅግ አወዛጋቢ ከመሆኑ የተነሳ አስተያየት ለመስጠት እንኳን የተጸየፍኩት አጀንዳ ነበር። የአውቶብሶቹ ዋጋ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ የከተማዋን ነዋሪ ያስደነገጠ፣ ግራ ያጋባና ዘረፋ ለይቶለት ነፍስ ዘርቶና ስጋ ነስቶ በቅ ብሏል ያሰኘ አነጋጋሪ ክስተት ሆኖ መሰንበቱ ሳያንስ ጥያቄው ተገቢውን መልስ መነፈጉ አሳፋሪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
የአውቶቡሰሰ ግዢውን በሚመለከት ከተለያየ ገለልተኛ አካላት በሚቀርብላቸው መረጃ መሰረት የከተማችን ነዋሪዎች በከፍተኛ ደረጃ የመዘረፍና የመነጠቅ ስሜት አድሮባቸዋል። ተመዝብሯል የሚባለው የአውቶብሱ ግዢ የተፈጸመው ላባቸውን አንጠፍጥፈውና ከልጆቻቸው ጉሮሮ ነጥቀው ለጋራ ልማት ከሚገብሩት ግብር ላይ ተዘግኖ ስለሆነ ቁጭታቸው ፍትሐዊና ጥያቂያቸውም መልስ ከገለልተኛ አካል የሚሻ ጉዳይ ነው ።
የከተማዋ አስተዳደርም መረጠኝ ለሚለው ነዋሪ ታማኝነቱ የሚረጋገጠው ከቀረበለት ጥያቄ እራሱን ከመጋረጃ በስተጀርባ ደበቆ ወፈ ሰማይ ካድሬ በማሰማራት ሀቁን በርብርብ በማድበስበስና ሕዝብን ለማሸማቀቅ በመሞከር ሊሆን አይገባም።
ጥያቄው ከሕዝብ የመነጨ የሕዝብ ጥያቄ ነው። ገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ የጨረታ ሂደቱ፣ አሸናፊው የተመረጠበት መስፈርት፣ ተገኘ የተባለው የውጭ ምንዛሪ ምንጭ፣ የአውቶብሶቹ ዋጋና የጨረታ ኮሚቴው ገለልተኝነት ወዘተ ኦዲት ሊደረግ ይገባል። ሂደቱ ኦዲት ተደርጎና ሀቁ ተጣርቶ ውጤቱ በግልጽ ለሕዝብ መቅረብ አለበት።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ መርጦናል የምትሉት ሕዝብ ላቀረበው ፍትሐዊ ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለትና በካድሬ ትርክት ጥያቄውን ለማድበስበስ መሞከር ጥርጣሬውን በሐቅ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ከማረጋገጥና ብሶትና ጥላቻውን ከማባባስ ውጭ ፋይዳ ቢስ ጥረት ነው።
ይህ ደግሞ ለዘመናት የለመድነው "የምን ታመጣላችሁ" ማን አለብኝነት ስለሆነ ጊዜ ይፍጅ እንጂ ትናንት በሌላው ላይ የጠቆመ ጣታችሁ ተራውን በራሳችሁ ላይ ጠቁሞ በሙስና እንደሚፋረዳችሁና ታሪክ እራሱን እንደሚደግም ጥርጥር የለኝም ?!
በመሰረታዊነት የሚነሱና ሕዝብን ለበቂና አስተማማኝ ጥርጣሬ ከሚዳርጉ መነሻዎች በጥቂቱ
-ቻይና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባላት ኢኮኖሚያው ትብብርና (Bilateral ) የሁለትዬሽ የንግድ ግንኙነት መሰረት ቀጥታ ከአምራቹ ጋር ተደራድሮ አውቶብሶቹን መግዛት እየተቻለ ከሁለተኛ አቅራቢ መገዛቱ ?
- መንግስት ማቅረብ ያልቻለውን ከ70 ሚሊየን በላይ( በብሔራዊ የምንዛሪ ተመን መሰረት) የሆነ ዶላር የጨረታ አሸናፊው ማቅረባቸው፣ እንደ ብቸኛ አቅራቢ መወሰዳቸውና የዶላሩ ምንጪ አለመጠቀሱ ?
- ከ3.8 ቢሊየን ብር ወይም ከ70 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ የ200 አውቶቡስ ግዥ ዓለም ዓቀፍ ጨረታ አለመውጣቱ፣ ወጥቶም ከሆነ ውጤቱ አለመገለጹ ?
- የተጠቀሱት ዓይነት የከተማ አውቶብሶች አንድ አውቶብስ ብቻ ለመግዛት ለሁለት የቻይና አምራች( Higer, dongfeng,) ላቀረብኩላቸው ጥያቄ የተሰጠኝ ዋጋ ከ 80 ሺህ እስከ 130,000 (ልዩነቱ በሚገጠምላቸው አክሰሰሪና አውቶማቲክና ማንዋል ይመሰረታል) ዶላር የሚደርስ ሲሆን መስተዳድሩ ግን የአውቶብሶቹ ብዛት 200 ስለሆነ የመደራደርና ዋጋ የማስቀነስ አቅም እያለው ገዛኋቸው የሚለው ከ350,000 ዶላር በላይ ወይም ከ3 እጥፍ በላይ መሆኑ ? ወዘተ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።
https://amharic-zehabesha.com/archives/180040
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment