Tuesday, February 14, 2023

እኔን እሰሩኝ! ልጆቼን ልቀቁ ! - ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃም
በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ምክንያት መምህር ዐቢይ መኮንን፣ መምህር ምሕረተአብ አሰፋ፣ ወ/ሪ ፌቨን ዘሪሁንና ብሩክታዊት : መ/ር ሄኖክ ታዬ: ዲ/ን አማኑኤል አያሌው ዲ/ን ኪሩቤል አሰፋ : እጅግ ብዙ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በእስር ላይ ናቸው።

ስለ ቤተ ክርስቲያን መታሰር የሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን መገለጫዋ ነውና ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ ስለተገባቸው ዋጋቸው ከፍ ያለ ነው:: የታሰሩት ሁሉ በመንፈሳዊ ብርታት ሆነው እኛ ደህና ነን ስለቤተ ክርስቲያን ብቻ አስቡ ብለው እያበረቱንም ይገኛሉ::

እስሩ ካልቆመ ሕዝበ ክርስቲያኑን ጥርጣሬ ውስጥ የሚከትና ለሌላ ወሬ ጆሮ እንዲሰጥ የሚያደርግ ስለሆነ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን በፍጥነት እንዲፈቱልን እንጠይቃለን:: የታሰሩ ልጆችዋን ጉዳይ ቤተ ክርስቲያንዋ በቋሚ ሲኖዶስ ደረጃ በአግባቡ ይዛዋለችና ውጤቱን እንጠብቃለን::

ይህ እንዳለ ሆኖ :- ብዙ ማኅበራዊ ችግሮች ባሉባት ሀገራችን ድንገት መብራት ይጠፋና ቆይቶ ይመጣል:: ለሆነ ያህል ሰዓት ችግሮቹን ረስቶ የሰው ሁሉ ትኩረት ወደ መብራቱ መጥፋት ይሆንና ሲመጣ ደግሞ "መብራት መጣ" በሚል የደስታ ፉጨት ሰፈሩ ይደበላለቃል:: ዋናው ነገር የቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ ልዕልና እንዲጠበቅ የተጀመረው ተጋድሎ ሆኖ ሳለ እንደ መብራት መጣ ሔደ "እገሌ ታሰረ እገሌ ተፈታ" በሚል ዋነኛ አጀንዳችንን ግን አንቀይርም::

ስለ እኔ መታሰር ተጨንቃችሁ ለጠየቃችሁኝ ከቀናት በፊት ለመግለጽ ሞክሬ ነበር:: ወሬው ሲዛመት እያየሁ የፌስቡክ ገጼን ለሃያ አራት ሰዓት access ማድረግ ስላልቻልሁ ምንም ለማለት አልቻልሁም::,ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አይደለም መታሰር ብንሞትም ጸጋና ስርየት እናገኛለን እንጂ ምንም አናጣምና እንደ ቀደሙት ክርስቲያኖች "የጌታ ፈቃድ ይሁን" እያላችሁ በጸሎት አግዙ:: ወደ ሰማይ የምንወጣባት መሰላል ቤተ ክርስቲያን የምትሰበር ከሆነ እኛ ቀድመን ብሔድ ይሻለናልና እስራትም ሞትም ቢሆን በደስታ የምንቀበለው ነው::

ከዚያ ውጪ የተጀመረው ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የማስከበር ሥራ በቅዱስ ሲኖዶስ መሪነት በአግባቡ እየተሠራ ስለሆነ ፍጻሜ እስኪያገኝ የአባቶቻችንን ድምፅ ብቻ እየሰማን እንቀጥል:: በታሪካችን ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲህ አንድ ልብና አንድ ቃል ሆኖ ሊቃነ ጳጳሳት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ቤተ ክርስቲያንን ሲያኮሩ ባየንበት በዚህ ጊዜ ሌላ ጆሮ የምንሠጠው የሴራ ትንታኔ መኖር የለበትም:: ሌላ ማንንም አንስማ!

የጋለውን እንቅስቃሴ ውኃ ቸለሱበት እንደሞቀ ነበር መቀጠል እንጂ ለሚል ሰው ብፁዕ አቡነ አብርሃም የተናገሩትን ብሂለ አበው ተብሎ ለትውልድ የሚተላለፍ ወርቃማ ንግግር ልጠቅስ እወዳለሁ :-

“እኛ ሙቀቱ ሳይጠፋ ብለን የምንጣደፍበት ውሳኔ የለንም። የቤተክርስቲያን ሙቀት መንፈስ ቅዱስ ነው። መንፈስ ቅዱስ አንዴ ሞቅ አንዴ ደብዘዝ የሚያደርገን አይደለም። ሁሌም በሙቀቱ እቅፍ ውስጥ ነን። እኛ እና መንፈስ ቅዱስ ስንወስን እንጂ እኛና የወቅቱ ሞቅታ ወስነን አንነግራችሁም። መንፈስ ቅዱስ የሚመራት ቤተክርስቲያን ልኬቷ ፈቃደ እግዚአብሔር ነው”

ብፁዕ አቡነ አብርሃም

 

ልዩ ቆይታ | ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃም ጋር | ዛሬ ምሽት 2፡30 ይጠብቁን

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/179709

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...