Sunday, February 12, 2023

የእሁድ እንጉርጉሮዬ - የእሁድ እንጉርጉሮዬ
የእሁድ እንጉርጉሮዬ

ጨለማው ረዘመ~ ምንም አልታየን፣

ጀንበር ብልጭ ብላ~ቀን በወጣልን።

በረጅም ሩጫ ~ ኖረን ስናሸንፍ፣

ወደ ሁዋላ ሆነ ~ላጭሩ ስንከንፍ ።

በጊዜ ውንበዳ~ መላ የለው ዘንድሮ፣

ቤተሰላም ሆነ~ጉልት ላምባጉሮ።

ስንበሌጥ ከመርን~ በጊዜ ገለባ፣

ድንጋይ ቤት አፍርሰን~ጎጆ ልንገነባ ::

ጸጥተኛ ቦታ ~ የነበረ ብቻ፣

በድንገት ሆነብን ~ አመጽ መዶለቻ።

ምን ይለው ነበረ~ ዋናው አስተማሪ፣

ትምህርቱ ሲጠፋ ~ ሳይቀር ፍርፋሪ?

ከመቶዎች በፊት ~ታሪክ መዝገቦታል፣

ጠብ መንጃና መስቀል~አንድ ላይ አይቶታል።

ማነው ተው የሚለው~ ሰላምን መካሪ፣

ሽማግሌ ሆኖ ~ዋናው ጸቡን ጫሪ ?

እንዴት ይጸለያል~ወዴት እንባ ይረጫል?

አስታራቂ የነበር~ ቀን በቀን ያጋጫል።

መለዮውን ጥለው~ ሥልጣን ላይ ሲወጡ፣

እልቂትን ነው እንጂ~ሰላም መቼ አመጡ?

አሸናፊ ዋቀቶላ፣ ሕ/ዶ - ፌብሩዋሪ 11፣ 2023

 

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/179662

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...