Wednesday, December 7, 2022
December 07, 2022
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን እጅግ ረዥም እድሜ አላት። ቤተ ክርስትያኒቱ ዛሬ አጉራ ዘለሎች እንደሚያንቋሹሻት ሳይሆን ለመንግሥት አካላት እውነትን በማስጨበጥና ምሬት በመስጠት እንዲሁም ትምህርትን በሃገሪቱ ከማሠራጨት አንስቶ በጦር አውድማ ከጠላቶችዋ ጋር እስከመፋለም መስዋዕት የከፈለች የእግዚአብሄር ቤት ነች። ከየኔታ እስከ መሪ ጌታ ከቀሳውስት እስከ ሊቀ-ሊቃውንት ያሉ የቤተ ክርስትያኒቱ አገልጋዮች ለኢትዮጵያ ትልቅ ውለታ የሠሩ የእግዚአብሄር ባርያዎች ናቸው።
የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን - "ክርስቶስ ከአብ ያንሳል" ያለውን አርዮስ፣ "መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ያንሳል" ያለውን መቅዶንዮስ፣ "ክርስቶስን ማርያም አልወለደችውም ወላዲተ አምላክ (Theotokos) ልትባል አይገባትም የክርስቶስ እናት (Christokos) ትባል" ያለውን ንስጥሮስ እንዲሁም አውጣኪስና ፍላቭያኖስን የመሳሰሉ ሃሠተኞችን ገና ከጠዋቱ ባደባባይ የሞገተች፣ ቀኖናዎችንና ዶግማዎችን ያጸናችና ታላላቅ ገድሎችን ያስመዘገበች ጽኑ የእግዚአብሄር ቤት ነች።
ኢትዮጵያ የኃይማኖቶች እኩልነት በጽኑ የሚተገበርባት አገር ነበረች። እስላም ክርስቲያኑ ተከባብሮ ተፋቅሮ የሚኖርበት አገር ኢትዮጵያ ነች። ሥርዓትን የሚከተሉ እንደ ደረጀ ከበደ ያሉ ጠንካራ ዘማርያንን ያፈሩ ግብረገብን የሚተገብሩ ጨዋ አማኞችን ያቀፉ የፕሮቴስታንት የእምነት ቤቶች ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። የዘመኑ መጨረሻ ሆነና ዛሬ የእምነት ቤቶች በተልካሻ ግለሰቦች ተሞሉ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ጥቅማቸውን ብቻ የሚያሳድዱ አድርባዮች እንደሚርመሰመሱባት ሁሉ የፕሮቴስታን ቤተ ክርስትያናትም በነዋይ አፍቃሪዎችና በዓይን አውጣ አለቆች እየታመሰች ትገኛለች።
በአንድ በኩል ህወሃትና ኦነግ የአማራውን ነገድ ለመጨርስ ሴራ ሸርበው ደም እንደጎርፍ በማፍሰስ ላይ ባሉበት ሁኔታ በሌላ በኩል ደግሞ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በተሰገሰጉት ባለ ሥልጣኖች አይዟችሁ ባይነት አንዳንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር ተብዬዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንን እምነት እየዘለፉ ይገኛሉ። የገንዘብ ፍርፋሬ የሚወረወርላቸው ጥቂት መምህር ተብዬዎች በተንኮል የተመረዘ ተንኮል እየወረወሩባት ሲሰድቧትና ሲያጥላሉዋት ብዙዎቻችን ዝም ብለናል።
የሁኔታዎች መዘበራረቅ፣ የመንግሥት ጥበቃ መነፈጓ፣ የምዕመኖቿ ድክመት እንጂ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ስትሟገት የቆየችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ነዋይን የማምለክ አባዜ በተጠናወጣቸው የምዕራቡ ዓለም አሸረጋጆች የሚዘበትባት አልነበረችም። ዛሬ ላይ የሚታየው - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንን ማጥላላትና ሥራዋን ማጠልሸት ብሎም በኅልውናዋ ላይ አደጋ መጋረጥ - የታቀደና በእቅድ የሚመራ ሤራ ነው። ሁሉም ነገር ከላይ እሰከታች መዋቅራዊ ነው። በቀደመው ጊዜ እንደ ላሊበላ ያሉትን ድንቅ ከዓለት የተፈለፈሉ ተዓምራትን የሠራችበት እምቅ የሂሳብና የሥነ-ህንጻ እውቀት የለበሰችውን ቤተ ክርስትያን፣ እነሆ - በደሉና ግፉ ቢፈራረቅባት - "የድንቁርና መሠረት ነች" ብሎ መዝለፍ እጅግ ያሳዝናል።
አብዛኛዎቹ የብልጽግና ባለሥልጣኖች የፕሮቴስታን እምነት ተከታዮች ናቸው። ይህ ሁኔታ ጥቂት አስተሳሰብ የጎደለቻቸውን የፕሮቴስታንት ሰዎችን ይበልጥ ደፋርና ዓይን አውጣ አድርጓል። ጊዜው የፈጠረው ማኅበራዊ መገናኛ አስተማሪ ሊሆኑ የማይገባቸውን ሁሉ ወንጌላዊና የፖለቲካ ተንታኝ አድርጓቸዋል።
"በኃይማኖት ካባ ስውር ደባን" የሚፈጽሙት ጥቂት ፕሮቴስታንት ነን ባዮች ከምስኪኑ ተከታዮቻቸው እንደ ዝናብ በሚሰፈርላቸው ንዋይ ናላቸው ረጥቦ ያች የተከበረችና የተወደደች ቤተ ክርስትያንን እየሰደቡ ነው። እነዚህ አጉራ ዘለሎች የአማራው ነገድ ሲደራጅና ራሱን ማስከበር ሲችል ብቻ ነው አደብ የሚገዙት።
የመጨረሻው ዘመን ነዋይ አሳዳጆችን፣ ቤተ ሠሪዎችን፣ ጉበኞችንና አታላዮችን ያበዛል። ነዋይን ታላቅ መስፈርት ያደረገው የመጨረሻው ዘመን የገንዘብን ጫፍ ለመጨበጥ የሚቅበዘበዙትን ራስ ወዳዶች ያበዛል። እግዚአብሄር በመጨረሻው ዘመን እንድንጠነቀቅ እንጂ ለቁሳቁሶችና ለጥቅም እንድንገዛ አላዘዘንም።
የአማራው ነገድ ራሱን አደራጅቶ ወደ ቀድሞ ቁመናው ሲመለስ ሥርዓትም እቦታዋ ትመለሳለች። ጠንካራ ድርጅት ተሳዳቢዎችንና ዓይን አውጣዎችን ሳይቀር ገደብ ያስይዛል። ታላቅ መስዋዕት በከፈለላት ኢትዮጵያ ላይ ይህ ሁሉ አሳፋሪ ድርጊት የሚፈጸመው የአማራው ነገድ ባለመደራጀቱና ባንድነት ባለመቆሙ ነው።
በኅልውናው፣ በእምነቱና በሚወዳት አገሩ ላይ መከራ የወረደበት የአማራው ነገድ መፍትሄ የሚያመጣው ዳተኛነቱን አሽቀንጥሮና አላስፈላጊ ምኞቶችን ገድቦ ራሱን ሲያደራጅና ለትግል ሲነሳ ብቻ ነው። ይህ ካልሆነ አማራው ነባር ኃይማኖቱን ማስናቅና በመስዋዕት የገነባትን አገሩን መነጠቅ ብቻ ሳይሆን የዘረኞች ሠለባ መሆን ብቻ ነው ቀሪ ዕጣ ፈንታው።
ወገኖቼ! የአማራው ነገድ በህወሃታውያን ጥይት እየተገደለና በኦነጋውያን ገጀራ እየተገዘገዘ መላ ዘመኑን ሲያነባ እንዲኖር እግዚአብሄር አልፈረደበትም። እግዚአብሄር ጥቃት የደረሰበት ሁሉ ራሱን እንዲከላከል ብልሃት አስታቅፎታል። የአማራው ነገድ ሆይ! "ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ፣ ባትጣፍጥ ግን ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሃል" የሚለውን የራስህን ብሂል መልሰህ መላልሰህ አጢነው።
https://amharic-zehabesha.com/archives/178106
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment