Saturday, December 31, 2022
በየትኛዉም ዓለም ጥግ የሚደረግ ትግል እና የሚከፈል መስዋዕትነት ለሰዉ ልጆች በህይወት እና በነፃነት.የመኖር ተፈርሯዊ መብት ላለማጣት ወይም ለማግኘት ፡፡
ነገር ግን በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ዓመታት ታሪክ ዉስጥ በሶስት አስርተ ዓመታት የስቃይ እና ጭለማ ዘመን ሁለት ዋና ዋና ጦርነቶች ተካሄዷል ፡፡ በዚህ ሁለት የጦርነት ዕሳት ወላፈን የገረፋቸዉ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ብቻ ናቸዉ ፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ ታሪክ በየትኛዉም ዘመን ያልተመዘገበ የጦርነት ዕልቂት አገሬን ፤ድንበሬን ነፃነቴን ላሉት ዕርደ ከል ሆኖ የበሬ ግንባር በማትሆን ባድመ የዜጎች ደም ዕርደ ከል ቀርቶ ገዳይ እና አስገዳይ በህይወት ኖረዉ ለሌላ ብሄራዊ ክህደት እና ጦርነት እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡
ይህም ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ማግስት ለአገራቸዉ ሉዓላዊነት እና ለራሳቸዉ ነፃነት ዋጋ የከፈሉትን እና በህይወት የተረፉትን ዋጋ የሚያሳጣ ተግባር እንዲፈፀምባቸዉ ሆኖ በሹመት እና ሽልማት ፋንታ በማንነታቸዉ እና በቀናኢነታቸዉ ተገፍተዋል ፤ ተሳደዋል፤እንዲሞቱ ፤እንዲንገላቱ ሆኗል፡፡
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን በተለይም ህዝበ ዓማራ በአገር ልዑዋላዊነት ፣ በነፃነት እና ህልዉና ላይ በታሪክ አይቶ እንዳላየ ማለፍ የማይችለዉ በዘመነ ኢህአዴግ የግፍ ዘመን ክህደት ፣ ግድያ ፣ፍጂት እና ዉርደት መሸከም እንደማይችል በዘመነ ጭለማ የነፃነት ትግል እና የህልዉና ተጋድሎ አድርገዋል ፤እያደረጉ መሆኑን ነዉ ፡፡
በድህረ ኢህዴግ ዉድቀት በኢትዮጵያ እና ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ ክህደት የደረሰባቸዉ ሁሉ በኢትዮጵያ አንድነት እና የዜጎች ህልዉና ላይ በሚደርስ የዉስጥ እና የዉጭ ትንኮሳ ፣ ጫና እና ጭቆና ሲደርስ በግንባር ቀደም ዋጋ ከፍለዋል፡፡
ይሁነ እና ኢትዮጵያ እንደ አገር ፣ኢትዮጵያዊነት እንደማንነት ፤ ዓማራዉያንነት ጠላትነት ሆኖ በኢትዮጵያ የዉስጥ እና የዉጭ ፤የቅርብ እና ሩቅ ፤ የረጂም እና ሩቅ የኢትዮጵያን ዉድቀት የሚመኙ ታሪካዊ ጠላቶች ደጋግመዉ ዘምተዉባቸዋል ፡፡
በቅርቡም የዘመናት የጥላቻ እና የንቀት ቅርሻታቸዉን በመትፋት በዓማራ ህዝብ እና በኢትዮጵያ ላይ የተለመደዉን ማጥቃት እና ማዋረድ በይፋ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ተከፍቶባቸዋል ፡፡
በዚህም ይፋዊ ወረራ የኢትዮጵያ ግዛቶች ጎንደር ፣ወሎ ፣አፋር ከልል ፣ ሸዋ ለሶስት ተከታታይ ጊዜ ወረራ ተካሄዶ ከፍተኛ ሞት ፣ዕልቂት ፣ዉድመት እና ጥፋት በሠዉ ልጆች ታሪክ ሆኖ በማያዉቅ ይህ ቀረሽ የማይባል ግፍ ደርሷል፡፡
ለዚህ ዘግናኝ እና አስነዋሪ ግፍ ግንባር ቀደም ዳፋ የደረሰበት እና ይህንም በመከላከል ለሉዓላዊነት፣ ነፃነት እና አንድነት ከፍተኛዉን የህይወት እና የሞት ዋጋ የከፈለዉ ኢትዮጵያዊ ዓማራ እና የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸዉን ወዳጂ እና ጠላት የሚያዉቁት ፤ ሟች የሚመሰክረዉ ዕዉነት ነዉ ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች በተለይም ዓማራ ህዝብ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር እና ህለዉናዉን ከማይደራደርበት ነፃነት ጋር ለመረጋገጥ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በተቃራኒ ለግል እና ለቡድን ጥቅም ፣ስልጣን ለማስጠበቅ ትንቅንቅ ዉስጥ የገቡትን ከሞት ታድጓል፡፡
ዛሬ ግን የጀግኖች የነፃነት እና የልዑላዊነት ትግል ገለል ብሎ ዕንባቸዉ ሳይታበስ ፤ ደማቸዉ ሳይደርቅ እነሆ ርኩስ መዉጊያ ሆነዉ መስቀለኛ የክህደት ጎዳና ላይ ይገኛሉ ፡፡
ስለ አንድ ዕግርኳስ ሆነ ሌላ ለዚያዉም ከኢትዮጵያ ምድር ላልሆነ በዕድሜ ጠገብ ሟች የሀዘን መግለጫ ለመስጠት የሚሽቀዳደም ሁሉ ኢትዮጵያዉያን ኢትዮጵያን ሰርተዉ እና ጠብቀዉ በማቆየታቸዉ በማንነታቸዉ ጀምላ ፍጂት ለዘመናት ሲያልቁ እና ሲማቅቁ ፣ በዚህ በኢትዮጵያ እና ህዝብ ክህደት እና ዕልቂት ዋነኛ ተጠያቂዎች ሲሾሙ ሲሸለሙ ፤ ለዕናት አገራቸዉ እና ለህለዉናቸዉ ቀናዒ ሆነዉ ዛሬም እንደከዚህ ቀደሙ የከፈሉት ትዉልድ የማይረሳዉ መስዋዕትነት ዕንደዋዛ ሲተን ከዚህ በላይ ክህደት እና ሞት አይኖርም ፡፡
ለሞቱት መታሰቢ ፤ በህይወት ላሉት ክብር እና ሞገስ መስጠት እንደ መርገም በሚቆጠርባት አገር አገርነቷ የማን እንደሆነ ዛሬም ከአንድ ክ/ዘመን አጋማሽ በኋላ ጥያቄ ሆኖ ይገኛል ፡፡
ኢትዮጵያን ፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ዓማራን በማጥላላት እና በከንቱ ዉዳሴ በማዛጋት ኢትዮጵያ ማለት “ሠይጣንም ለዓመሉ….ከመፅሃፍ ቅዱስ ”……ይጠቅሳል እንዲሉ መታወቅ አለበት፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ዓማራ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና በራሱ ነፃነት ላይ ወደ ኋላ የማይለዉ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ የከፈሉት የህይወት ፣የአካል እና የሀብት ዋጋ ከትግል እና ጦርነት በኋላ ለዕስር ፣ ለባርነት ፣ለድህነት እና ለዉርደት እንዳልሆነ ይታወቃል ፡፡
በ19ኛዉ ክ/ዘመናት የኢጣሊያ ሁለተኛ ወረራ በሆነበት ጊዜ የወራሪዉ ጠላት መዉጫ ፤መግቢያ ያሳጡት አይረሴ የነፃነት ዋነኞቻችን ከነፃነት ትግል በኋላ ለነፃነት ያሏት አገር ዕስር ቤት ሆናለች ፡፡
ለዚህም የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ የነፃነት ትግል ተምሳሌትነት የሚሆኑት ደጃዝማች በላይ ዘለቀ የሚጠቀሱ ናቸዉ ፡፡
አግሪቷን እና የዘዉዱን ንጉስ ከስደት እና ዉድቀት በመታደግ ለዳግም ስልጣን ማብቃታቸዉ ወንጀል ሆኖባቸዉ ለዕስር እና ሞት የኢትዮጵያ ባለዉለታወች ሥጦታ ሆኗል፡፡
የሞትነዉም ሆነ የምንመተዉ ለነፃነት እና ለአገር ዳር ድንበር እና ክብር እንጂ ለሞት ፣ባርነት እና ዉርደት አለመሆኑን ዛሬም ለነፃነት ዋጋ በአንድነት ፣በንቃት እና ህብረት ዘብ መቆም አለብን ፡፡
ዛሬም “ኢትዮጵያ አገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ ፣
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ…” የሚለዉ የክቡር ዮፍታሄ ንጉሴ ስነቃል ትንቢት ብቻ ሳይሆን ትዉፊት መሆኑን በዘመናችን ደጋግመን አይተናል፤ ባይገባንም ፡፡
ምነዋ ሀበሻ ፣ ምነዋ የአገር ሠዉ ደጋግመህ ደጋግመህ ሆንብኝ ተላላ፣
አንተ እየሞትክለት እንዲኖር መፍቀድህ ያ ክፉ ጠላትህ የታሪክ አተላ፣
ዛሬም ተሰባስቦ አፉን ሲያዛጋብህ የምን ማንቀላፋት ለዚያ የአገር ተኩላ፡፡
“ነፃነት ወይም ሞት” !
Allen Amber!
https://amharic-zehabesha.com/archives/178519
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment