Tuesday, December 6, 2022
“ የእግዚአብሔርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ተቀመጠ፥ ደመናውም ስድስት ቀን ሸፈነው፤ በሰባተኛውም ቀን ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው። ”
— ዘጸአት 24፥16
ይኽ ፀሐፊ አንድ ጥያቄ የኢትዮጵያ ህዝብንና መንግሥትን ይጠይቃል ? ኢትዮጵያዊያን ሠላም አለ የምንለው እኛ መኖርያ ቤት ውሥጥ ሽፍቶች ፣ ወንበዴዎች ፣ ቀማኞች ፣ ዘራፊዎች ፣ አራጅ ና ገዳዮች ገብተው ቤተሰባችንን በጭካኔ ሥላልገደሉ እና ሥላልዘረፉ ነውን ? መንግሥትሥ “ ሠላም አለ ። “ የሚለን ፣ የተደራጀ ፣ ለሁሉም ግዳጅ ዝግጁ የሆነ የመከላከያ እና የፊደራል ኃይል ሥላለኝ ቤተመንግሥቴን እና ቤተሰቤን እሥከዛሬ ማንም ጫፋቸውን አልነካም ። " በማለት አሳቤ ነውን ? ...
አገር በሽብር ኃይሎች እየተናጠች ፤ እንዴት ሠላም አለኝሥ ይባላል ? በመንግሥት ውሥጥ ሌላ መንግሥት የመሠረቱ ህቡ ሃይሎች እያሉ እንዴትሥ በዜጎች አእምሮ ውሥጥ ሠላም ሊኖር ይችላል ? በሙሥና የተዘፈቀ ፣ በምቾትና በድሎት ባህር የሚዋኝ የደህንነት ከፍተኛ ባለሥልጣን እያለ እንዴት አገር ሠላም ትሆናለች ? እነ ብር አምላኩ በየክልሉ ሥልጣን ይዘው ፤ እግዚአብሔር ተረስቶ እንዴት አገር ሠላም ትጎናፀፋለች ?
ሥለ እግዜር ሲነሳ ፣ በቅርቡ ፣ አንድ የ19 ዓመት እንቦቃቅላ ልጃቸውን በዚህ ትርጉመ ቢሥ እምሮ ቢሥ የወሮበሎች ሥብሥብ ( ቋንቋን እንደመጨቆኛ መሣሪያ በማየትሰውን በቋንቋውና በመጠሪያ ሥሙ በሚፈርጅ ከዘመናዊ ሥልጣኔ እና ከዓለም ነባራዊ የኑሮ ዘይቤ እጅግ እርቆ በ15 ኛው ክ/ዘ አሥተሣሠብ እየኖረ ባለ አረመኔ ቡድን ። ያጡ እናትን ላፅናናቸው ቤታቸው ጎራ ብዬ እንዲህ አሉኝ "...እግዚአብሔር መፍትሄ ያምጣልን ? ' እርሱ ያብርደው ! ' ትለኛለህ ልጄ ! እርሱም አቅቶታል መሠለኝ ... ? ለዚች አገር ያለመከፋፈል ከእኔ ቤት እንኳን አምሥት ሥጋዎቼን ገብሬለሁ ? እና ምን ተገኘ ? አራቱ በሰሜን ተሰው ። ለዚች ዛሬም ሊከፋፍሎት ከሚጠሩ ሤጣኖች ጋር ተናንቀው ። ዛሬ ደግሞ እትብትህ በተቀበረበት በቀዬህ ፣ በታዛህ ፣ ' እግዜር በፈጠረልህ መሬት የአግዜሩን መሬት ቀምተውት የእኔ ብቻ ነው ። ' በማለት በቋንቋ ተቧድነው በጅብ መንገድ በሚጎዙ ኦነግ ሸኔ በተባለ ቅፅል ሥም በሚቀሳቀሱ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች እዚሁ መሐል አገር ልጄን ተነጠቅሁ ። ... ጎጆ ቀልሰህ ፣ አፈር ገፍተህ እየኖርክ ... ጠፍጥፎ ያልሰራትን መሬት ... የኔነው እያለ... ይሄ ገንዘብ አይኑንን ያወረው ህሊና ቢሥ ቅጥረኛ ንብረትህን አውድሞ አንተን በየቀኑ ሲያርድህ ... እንዴት ፈጣሪ ሠላም ያመጣል ብለህ ታሥባለህ ? " በማለት በምሬት ጠየቁኝ ።
እኔም ፤ " እውነት ብለዋል ። ሰው ከአራት ኪሎ ብዙም ሳይርቅ እየታረደ ነው ። ዕውቁ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ፣ ብዙም ባራቀ ወቅት በተራራ ሚዲያ በዩቲየቡ እንደተነበየው ፤ ' ይኽ ፅንፈኛ ... ድርጊት በአጭር ካልተቀጨ ጠቅላይ ሚኒሥትራችንን ዶክተር አብይ አህመድን የሚበላ ነው ። ' ምናልባትም ሰውየው ፣ ' ሤጣናቱ ምንም አያመጡም ! ' ብለው እጃቸውን አጣጥፈው ፣ በትወራ ብቻ ' አንድነት ! አንድነት ! ' እያሉ ከተሞኙ ፣ እርሱ እንዳለው ' አሥከሬናቸው በአራት ኪሎ ቤተመንግሥት ደጃፍ መጎተቱ አይቀርም ' ። " አልኳቸው ።
ዛሬ ና አሁን የምናሥተውለው የሤጣን ተግባር ይኽንኑ ቀፋፊ ትንቢት መልሰን እንድንል ያሥገድደናል ። ይኽንን ግምት " የሤጣን ጆሮ አይሥማው ። " ማለት አይቻልም ። ሤጣን እጅግ ተራብቶ ጆሮ ብዙ ሆኗልና ! ዛሬ እና አሁን ፣ በኦሮሚያ ባሉ የፊደራል ዩኒቨርስቲዎች እንኳን ጥቂት የማይባል “ የሤጣን ጆሮ አለ ። “ ( አሥደናቂው ነገር የፊደራል ዩኒቨርስቲዎች ዛሬም የሤራ ፖለቲካ መዘውር እና በኦህዲዳዊ ካድሬዎች ፤ በብአዴን ፤ በህወሓት ወዘተ ካድሬዎች መመራታቸው ነው ። ሜሪት አያሠራም ። ከኢህአዴግ እሥከ ግልብጡ ብልፅግና ያውና አንድ ብቻ ሣይሆን የባሰ ካድሬያዊ አመራር ቀበሌ ድረስ ተዘርግቶ ዛሬም ድረስ እንደ ጭከቃ ሹም ህዝብን ያሰቃያል ። ህዝብን ለፖለቲካ ወጥመድ የሚያዘጋጅና የምርጫ ማጭበርበሪያ ሥውር መድረክ የሆነው ፤ የካድሬ መናሀሪያ ፈርሶ በትክክለኛው የማዘጋጃ አገልግሎት ካልተተካ ሠላም በአገር ይመጣል ብሎ የሚያሥብ ጅላንፎ ብቻ ነው ። ወዳጄ እንደ ኮሮና የሚዛመተው ቫይረሥ መፈልፈያ ቀበሌ እንደሆነ ህዝብ ያውቃል ። የቫይረሱን በሽታ የሚያሥተላልፈውም ሆድ አደሩና በዘረፋ የተካነው ከኢህአዴግ ወደብልፅግና የተቀየረው ካድሬ ነው ። አካፋን ቀለም ብትቀባው ያምራል እንጂ ግብሩን አይቀይርም ። አካፋ አካፋ ነው ። ካድሬ ሆይ ብጠላኝም ጥለኝ ፣ ' መልከ ጥፉን በሥም መደገፍ አይቻልም ።' እልሃለሁ ። ደግሞም ግማሽ ሉጩ ግማሽ ጎፈሬ መሆን ለተመልካቹ ያሥጠላል ። ያደናግርማል ። በቀኝ በኩልና በግራ በኩል ሲታይ ። ቀኙ ተላጭቷል ግራው ጎፈሬ ነው ። ለእሥታይል ከሆነ ብቻ ይኽ አይነቱ “ በፍላሎታሞች “ የሚወደድ ይሆናል ። በፍላሎት ዓለም ለሚዎኙ “ አይፈራም ! ጋሜ አይፈራሞች ! “ ይኽ ኖርማል ነው ። ህይወትን በ360 ዲግሪ ለምንመለከት ግን ይህ እብደት ነው ። ' እሥቲ ከባላቶሊ ቁርጥ እና ከሜሲ ቁርጥ የቱ ያምራል ? ' ፍላሎታሞቹ ይመልሱ ። ...
ዛሬ ፣ ዛሬ የሤጣን ጆሮ የበረከተበት ፣ ቅዱሣን እና መልዓክት የፈጣሪን ይቅርታ ለማግኘት የሚማልዱበት ወቅት ላይ ደርሰናል ። ሙሴ ያጋጠመው ፈተና በኢትዮጵያዊያን ላይ ተደግሟል ። ኢ _ አማኒያን ሰዎችን ያለርህራሄ እያረዱ ነው ። በሴጣን ፈረሥ እየጋለቡ ። ኦሮሚያ እየተባለች በቋንቋ ነገሥታት በምትመራ ክልል በደም እጃቸውን እየታጠቡ ነው ። ትላንት እንደ ፊውዳል በትውልድህ ዘርህ ተቆጥሮ ለሹመት እና ለሥልጣን እንደምትበቃ ሁሉ ፣ ዛሬም በኦህዴድነት አሥመሣይ ካድሬነትህ እና በቋንቋህ እንዲሁም ምሥጢር ጠባቂ ሌባነትህ እየተሞላቀቅህ በሰው ደም እየሠከርክ ነው ። በአማራም ፣ በትግሬም ፣ በአጠቃላይ በሁሉም ክልሎችም በብዙም ሆነ በጥቂት ይኸው እውነት አለ ። በተመሣሣይ መልከ ነው ፣ ለሹመትና ለሽልማት የምትበቃው ። ህሊና እና የራሥህ እውቀትና እግር ካለህ በጥበብ የላቅህ ፣ ሰው መሆን ብቻ የምትፈልግ ኦሮሞ ፣ ትግሬ ፣ አማራ ፣ ሱማሌ ፣ ሲዳማ ፣ ወላይታ ወዘተ ። ግን ማንም እዚህ ጠባብ እና ህሊና ቢሥ ቡድን ውሥጥ እንድትገባ አይፈቅድልህም ።
እግዚአብሔር በፈጠራት ምድር ፣ በተለይም በኢትዮጵያ ህግ አሥከባሪ ፀረ _ ዳያቢሎሥ መንግሥት በወጉ ባለመደራጀቱ ነው ህሊና ላለው ለሥጋው ሳይሆን ለነፍሱ ላደረ ጠቢብ የከፍተኛ አመራርም ሆነ በተዋረድ ያሉ የህዝብ ማሥተዳደር ፣ የሥልጣን ክብር የተነፈገው ። እግዛብሔርን ሥለሚያከብር። እግዚአብሔር ግን አለ ። ሤጣኖቹ ግን በድፍን ኢትዮጵያ ሰውነትን ቀብረው ቋንቋ ሆነው ፀረ ሰው በመሆን የሥልጣን ወንበር ላይ ፊጥ ብለዋል ። በተለይም በኦሮሚያ ከግብፅ በመጡ ፣ በግብፅ በሠለጠኑ ፣ በግብፅ በሚከፈሉ ፣ በነጃዋር በህቡ በሚመሩ እና በወያኔ ፕላን ሲ ( Plan C ) በተካተቱ እጅግ ምሥጢራዊ በሆነ መንገድ " ኔት ወርክድ " በሆኑ ፤ እየተፈፀመ ያለው አገር የማፍረስ እንቅስቃሴ ሀገር ወዳዶች ቸል የማይሉት ተግባር ነው ።
በዚህ በረቀቀ መረባቸው እየፈፀሙት ያለውን ፀረ ሠላም እንቅሥቃሴ የኢትዮጵያ ልጆች ፣ በተለይም የአገር መከላከያ ሠራዊት ከቶም አይረሳውም ። ሣይበቀላቸውም በዝምታ አያልፍም ። የኢትዮጵያ ምሣሌ በመሆኑ ። መንግሥት ህዝብ ሠላም እንዳያገኝ ባለማሠለሥ እየጣሩ ባሉት ፤ በገንዘባቸው ኃይል ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ( የመከላከያን ፣ የፓሊሥን እና የደህንነትንም ይጨምራል ። ) በደካማ ጎናቸው ( በተደበቀ ሱሳቸው ፣ ፀባይ እና ዓመላቸው ) በመግባት የእነሱ ሎሌ በማድረግ ፣ አገርን በማያባራ ትርምስ ውሥጥ ለማሥገባት ፣ አገር ወዳድ መከላከያውን ፣ ፌደራል ፖሊሥን ለከንቱ መሥዋትነት የሚዳረጉትን በምሥጢራዊ ዕቅድ ማሶገድ ካልቻለ ፣ አገራችንን ጠላቶቻችን እና የውጪ ጅቦች ተቀራምተው እንደሚበሏት ዛሬ ይበልጥ ግልፅ እየሆነ መጥቷል ። እንዴት ቢሉ የአገር መከላከያ ሠራዊቱ ና የፊደራል ፖሊሱ እንዲሁም ሙያቸውን የሚያከብሩ የክልል ፖሊሶች በከንቱ ህይወታቸውን አሰየተነጠቁ ናቸውና ! ያልተገባ መሥዋትነት እነዚህ ውድ እና ብርቅ አገር ወደድ ኢትዮጵያዊያን መክፈላቸው ፣ ነገ የሚያመጣው ጦሥ ደግሞ እጅግ መጥፎ ሊሆን እንደሚችልም መንግሥት ማወቅ አለበት ። በበኩሌ ክፉው እና አገር አጥፊው ነገር ከመከሰቱ በፊት ፣ ጠቅላይ ሚኒሥቴር አብይ ኮሶን ለኢትዮጵያ ሲሉ በተገቢው አቅጣጫ በማሾር በህዝብ ቅቡልነት ያለው ማራኪ ግብ ቢያሥቆጥሩ እመርጣለሁ ። ይኽ እድል ለቀድሞው ጠ/ሚ መለሥ ዜናዊ በአንድ ወቅት ተሠጥቷቸው ነበር ። ሆኖም አልተጠቀሙበትም ። ...
ለጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ባልተሰወረ መልኩ ፣ በብሔር ብሔረሰብ ሥም ፣ እየተጠቀመ ያለው ህዝብ አይደለም ። የትም ክልል ደሃ ተከባብሮ እየኖረ ነው ። ከ85 % በላይ ህዝብ ደሃ ነው ። የቋንቋዊ ዘረፋም ተጠቃሚ አይደለም ። እድርና ባልትነው አንድ ነው ። ጉልቱ እና መኮመሪያ ጣሳው አንድ ነው ። እርፍ ና ደጋኑ አንድ እና ያው ነው ። ምጣዱ ፣ ድሥቱ ፣ ጀበናው አንድ ነው ። የሚበላው እንጀራ፣ ቂጣው ፣ ቆሎና ንፍሮው ሣይቀር አንድ ነው ። ያም ይኼም በጪሥ የሚጨናበሥ ነው ። ያም ይኼም በብድር መብራት እና በቤት ኪራይ መከራውን እየበላ ያለ ምሥኪን ነው ። ... የተቀረው ጥቂቱ 5% ደግሞ ለቋንቋ መሥፍንቶች እና መኮንንቶች በማደግደግ እና ጭራ በመቁላት ሀብት ና ንብረት ያፈራ ነው ። ...
ይኽ የሚያሣብቀው መንግሥት ማወቅራዊ ህመም እንዳለው ነው ። በሽታው እጅግ ጥልቅ እና ጋንግሪን የፈጠረ መሆኑ በግልፅ እየታየ ነው ። እናም አካሉን ጨርሶ ወደ ጭንቅላቱ ጋንግሪኑ ከመዝለቁ በፊት ፣ የተበላሹ እግሮቹን ቆርጦ ሊጥላቸው ግድ ይሆንበታል ። ይኽ ቱሁት ምክሬ ነው ።
ጋንግሪኑ ግልፅ ፣ የማይቀለበሥ አደጋ እያሥከተለ ነው ። የአገር አለኝታዎች እያሣጣ ያለ የሚያሥቆጭ ብቻ ሣይሆን እጅግ የሚያናድድ አደጋ እየጋረጠ ነው። በየቀኑ አሰያሥሞተ ነው ። ራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት ሁኔታ በጠራራ ፀሀይ ለግዳጅ የወጡ አልኝታዎቻችንን በከንተሐ እያጣን ነው ።አዲስ አበባ ባንዲራ አትስቀሉ በሚሉ በግብፅ ወሮበሎች ተከባለች ። ህዝብ ፣ ገንዘብ በሚከፈላቸው በታጠቁ ሺፍቶች በደፈጣ በየቀኑ ይረሸናል ። " ወታደራዊ ኦፕሬሽን እና ግዳጅ በጠራራ ፀሐይ " ውጡ እየተባለ የአይናችንን ብሌኖች በፈሪ በትር እናጣለን ። በሞታቸው እንበግናለን ። እርር ጭሥሥ እንላለን ። ህሊና አለንና ። የሞቱት እንደ እየሱስ ነውና !! ....
ከዚህ ተነስቼ አገር ወዳዱ የመንግሥት ከፍተኛ አመራር ፣ በኦሮሚያ ያለውን ህገወጥ አደረጃጀት ማፍረስ አለበት ። እላለሁ ። ሳይዘገይ ፣ ሚሊሻ የተባለውን ፣ ለመዝረፍ ከየቀበሌው የተመለመለውን በከተመሠም ሆነ በገጠር ያለውን ፣ ማፍረስ አለበት ። ሃምሳ ፐርሰንቱ ለዘረፋ የተሰማራ ነውና ። ያለአንዳች አሉባልታ ሃምሳ ፐርሰንቱ ጭለማን ተገን አድርጎ የሚዘርፍ ነው ። ይኽ ሐሰት እንዳይደለ የትኛውም የከባድ መኪና አሽከርካሪ ይነግራችኋል ። ከዚህ ይልቀሰ ወጣት የሆነውን የሚሊሻ ሃይል በጥንቃቄ መልምሎ “ የፈጥኖ ደራሽ “ ልዩ ኃይል በማቋቋም ፀረ ሽፍታ ኃይል በፊደራል ደረጃ ማቋቋም ይበጃል ። ይኽ ሃይል በሲቪልም በጋራ ተንቀሳቅሶ የሚሠራ ወይም ግዳጁን የሚፈፅም ሃይል ሆኖ ቢሠለጥንም መልካም ነው ። ካሥፈለገም ከልዩ ኩማንዶ ጋር በማቀናጀት በአጭር ጊዜ የተረጋጋ ሠላም በአገር ማምጣት ይቻላል ።
እንዲህ ዓይነቱን የሠለጠነ እና የነቃ ፣ በምሥጢርም የሚንቀሣቀሥ ልዩ የአገር ደህንነት ኃይል በመፍጠር የዛሬውን የፕላን C እንቅስቃሴ ማሥቆም እንደሚቻል አምናለሁ ። የእሾህ መድሃኒቱ እሾህ ብቻ ነው ። ነፍሰ ገዳይን ልትገድለው ይገባሃል ። ያለ አንዳች ምህረት ። የመንግሥት ተመጣጣኝ ይሉሃል ይኼ ነው ።
ዛሬ በከንቱ የሚሞላቀቅብህን አንተ ዘረኛ እና በዩልንታ የተሸበብክ ካልሆንክ በሥተቀር ቸል ልትለው አይገባም ። ቸልታ ካበዘህ የታምራት ነገራ ትንቢት ይፈፀማል ። ኦሮሞ ካልሆንክ ብቻ ሣይሆን አንተ “ ሰው ነኝ ። “ የምትል ኦሮሞ ከሆንክ አንተ በረሮ ነህና ትታረዳለህ ። የሚልህ የግብፅ ቅጥረኛ ከእሥር በለቀቅኸወሰ ሃይል በፕላኒ ቢ የሚመራ ኃይል ነበር ። ዛሬ ወደ ፕላን ሲ ተሸጋግሮልሃል ።...
ይኽ ኃይልበገንዘብ እጅግ የፈረጠመ በመሆኑ አንተን ገንዘብ በመሥጠት እያነሆለለ ፣ በተቀዳሚ ሥራህ ላይ እንዳታተኩር በማዘናጋት ወደ እርድህ እየገፋህ እንደሆነም እወቅ ። በቤትህ ውሥጥ ያለውን ወታደራዊ ዲሢፕሊንም መርምር ። ሥላለው ገንዘብ መናገር ከጀመረ እጅግ አደገኛ ሁኔታ ውሥጥ እንደምትወድቅ እወቅ ።የአገር መረመ በመሆንህም ጦሥህ ለአገር ይተርፋል ።
ገንዘብ መንጋ የመፍጠር ችሎታ እንዳለው ጋሼ ጃዋር ትላንት አሜሪካ ሆኖ አሣይቶሃል ። ዛሬ በፕላን ቢ ደግሞ የበለጠ እያሥመሠከረ ወደ ፕላን ሲ ተሸጋግሮልሃል ። የተማረውን ይኸው በመንግሥት ዩኒቨርስቲ በኔት ወርኩ አማካኝነት ገንዘቡን እየረጫ ፣ ሃሺሹን እያሥማገ ያሥጮኸዋል ። ያልተማረውን ደግሞ ፣ በየጫካው አሠልጥኖ እና በየከተማው እራሥህ የሠለጠንከውን ሚኒሻ መልምሎ በሃሰት ፕሮፖጋንዳው ጀንጅኖ ረብጣ ብር ከመክፈል ባሻገር ሥጋ እያበላ ና አረቄ እያጠጣ ነፍሰ ገዳይ እንዲሆነ ጫካ ወስዶ ሰው ያሳርዱሃል ። አሠልጣኞቹም አትዮጰያዊ ናቸው ብለህ በአውሮፕላን ይዘሃቸው የመጡ የግብፅ ሠላየች ናቸው ይባላል ። እነዚህ ፀረ ኢትዮጵያዊያን ከወያኔም ጋር ነበሩ ... ። ተመሬያለሁ ያልከውን በየዩኒቨርስቲ ያለኸውን የዓለምን ተፈጥሯዊ የዘመናት ጉዞ ፤ " ከአፈጣጠሮ ጀምሮ ያለውን የቅርቡን የ 5000 ዓመት ጉዞ " ያለመረዳትህ በእጅጉ ይገርማል ደ “ ለእዚህ ይመሥላል የታሪክ ትምህርት እንደ አንድ ጠቅላላ እውቀት በየዩኒቨርስቲው እንዳይሰጥ እና ይህ ፍላሎታም ወጣት ዓለምን ከሣይንሥ እና ከሃይማኖት አንፃር እንዳያውቃት የተደረገው ?
ዛሬ በመላው ኦሮሚያ የሚስተዋለው ይኸው ታሪክን ያለሠረዳት ድንቁርና ነው ። የግብፅ እና የቅኝ ገዢዎቻችን ሴራን ከታሪክ እና ከተፈጥሮ አንፃር ያለመረዳት ያመጣውም ጦሥ ነው ። ሙቅ የሚያኝኩት ባለ ረብጣ ብሮች ያሰማሯቸውን ፣ ከመንግሥት በላይ መንግሥት የሆኑትን ፣ ገዳይ እና አሠቃይ ጋንጊሥተሮች በመፍራት መንጋ ሆኖ መገኘት የከሰተው ችግር ነው ። ... ትላንት በነጀነራል ጃጋማ ኬሎ ዘመን ቅኝ ገዢዎች ይህንኑ የመከፋፈል እና የጭካኔ ሤራ ፈፅመዋል ። በአምሥቱ ዓመት የአርበኞች ትግል ወቅት ይኸው ተንፀባርቋል ። ዛሬ ና አሁን በጠቅላይ ሚኒሥቴር አብይ አህመድ መዋቅር ውሥጥ ለፈጣሪ ያደሩ ሰዎች ሤጣንን ተዋግተው ማሸነፍ እሥካልቻሉ ጊዜ ድረሥ ይኸው ግፍ ይቀጥላል ።
ሆኖም " ሊነጋ ሢል ይጨልማል ። " እንደሚባለው ፣ ይህ ሰቆቃ ከፈጣሪ ጆሮ አልደረሰም ማለት እንዳልሆነ ሁሉም ማወቅ አለበት ። ሠላም ያለውም የሚገኘውም በእግዚአብሔር ነው ። ዛሬ እና አሁን መንግሥት ይኽንን ተገንዝቦ " ይበቃል ! " እንደሚል ተሥፋ አደርጋለሁ ። ትላንት “ ፕላን C ይቀጥላል ። ይኽንንም ታዩታላችሁ ።" ብዬ እንደነበርም አትዘንጉ ! ይኽንን ያልኩት ፈጣሪ በሰጠኝ አእምሮ ያለማባራት ፣ የሚከሰቱ ፀረ - ሰው ድርጊቶችን ገጣጥሜ በማየት ነው ። ይኽንን እውነት ፣ አገር ወዳድ የመንግሥት የደህንነት ተቋም ዓባላት እና መከላከያ ሠራዊቱ እንዲገነዘብልኝ እፈልጋለሁ ። የኢትዮጵያ ጠላቶች ነገ “ በፕላን ዲ “ ሊከሰቱ እንደሚችሉም ቀድሞ በመረዳት ከወዲሁ መዘጋጀት እንዳለበትም ለማሳሰብ ነው ። ትላንት ቀድሞ ቢዘጋጅ ኖሮ በኦሮሚያ ዩኒቨርስቲዎች ፕላን C በተቀናጀ መልኩ አይከሰትም ነበር ።
https://amharic-zehabesha.com/archives/178087
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment