Thursday, December 29, 2022

ያዱስ አባ ጣጣ ስሊቅ (Satire) - በቦቆቅሳ ለባክ
ግንቦት 2014

በቦቆቅሳ ለባክ

የአዱስ አበባ ከተማ ታሪካዊና ሕጋዊ ባሇቤት የእኛ ማሕበረሰብ ነው ሲለ የደር እንስሳት ነፃነት ግንባር (ደ.እ.ነ.ግ) ከፍተኛ ተወካዮች ዛሬ ከቀትር በኋሊ በቅርቡ በተመረቀው የአንዴነት ፓርክ የእንስሳት መዋያና መናፈሻ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግሇጫ አሳወቁ፡፡ በመግሇጫው አሰጣጥ ሥነ ሥርዏት ሊይ ከሁለም የሃገሪቱ ክፍልች ተመርጠው ሇእይታ የበቁት ታሊሊቅ የደር እንስሳት ተወካዮች እና ታዛቢዎች ተገኝተዋሌ፡፡ የደር እንስሳት ከፍተኛ ጉባኤ መሪዎች፣ ዋና አክቲቪስት ጦጣና አስመሳይ ነፃ አውጪ ዝንጀሮ በሰጡት መግሇጫ፣ የአዱስ አበባ ይዞታ ወዯ ቀዴሞ ታሪካዊ ባሇቤቶቹ

--የደር እንስሳት ዘር -- እንዱዛወር አስፈሊጊውን ሁለ እንዯሚያዯርጉ አሳውቀው ሇዚህ አሊማቸው መሳካት ሁለም ፅንፈኛ ሃይልች አስፈሊጊውን ትብብር እንዱያዯርጉሊቸው ጠይቀዋሌ፡፡

በመግሇጫው አሰጣጥ ሥነ ሥርዏት ሊይ የጉባኤው መሪዎች እንዯተነተኑት፣ የዓሇማችን ታሪክ እንዯሚመሰክረው የአዱስ አበባ ቀዲሚና ሕጋዊ ባሇቤቶች፣ እንስሳት፣ በተሇይም የደር እንስሳት መሆናቸውን ሁለም እንዱያውቀው አስረግጠን ሇማስገንዘብ እንፈሌጋሇን ብሇዋሌ፡፡ እነ ዴንቅ ነሽ - ለሲ (Australopethecus afarensis) እና እነ አርዱፒቲከስ ራሚዯስ (Ardipethicus ramidus) በአፋር አዋሽና ሃዲር አካባቢዎች፣ እነ ሆሞ ሃቢሉስ (Homo habilis) እና ሆሞ ኢሬክተስ (Homo erectus) ዯግሞ በኦሞ ሸሇቆዎች አካባቢ ብቅ ብቅ ከማሇታቸው በጣም ቀዯም ካሇ ጊዜ ጀምሮ የኛ ቀዯምቶች እነ ዲይነሶር (Dinosaur)፣ ማመዝ (Mammoth)፣ ሜጋሊኒያ (Megalania) እና ላልች ታሊሊቅ የደር እንስሳት ዘሮች የአካባቢው ባሇቤቶች እንዯነበሩ የዓሇማችን አመጣጥ ቅዴመ ታሪክ ምስክር ነው ብሇዋሌ፡፡

የጥንቱና የጧቱ እንኳን ቢረሳ፤ በቅርቡ እነ አንበሳ፣ ነብር፣ ዝሆን፣ የሜዲ አህያ፣ አውራሪስ፣ ቀጭኔ ጎሽና ላልችም በቦታው ሊይ ይርመሰመሱ እንዯነበር የሰው ሌጆች እፅዋትን እየጨፈጨፉና የወገኖቻችንን ቆዲ እያሇፉ የፃፏቸው የታሪክ መዛግብት ያስረዲለ ብሇዋሌ፡፡ እነ አያ ጅቦም እስከ አሁን ዴረስ የሰው ሌጆች ከርሳቸውን ሞሌተው ፈርሳቸውን የሚያስወግደበትን ምዴር በማሰስና ትርፍራፊ በመሌቀም እንዯ ቆሻሻ ሰብሳቢና አስወጋጅ ሇውሇታ ቢሱ የሰው ሌጅ የማይገባውን ጥቅም ሲሰጡ እንዯቆዩ ግሌፅ ነው ብሇዋሌ፡፡ ቀጨኔ የሚባሇው መኖሪያ ሰፈር መጠሪያ ባካባቢው የቀጭኔ ጎሳ አባሊት በብዛት ሰፍረው ስሇነበር የተሰጠው ስያሜ እንዯሆነ የሰው ሌጅ ምሁራን ሳይቀሩ የሚመሰክሩት ሃቅ መሆኑንም ሳይጠቅሱ አሊሇፉም፡፡

ትግሊችን፣ አለ ተወካዮቹ በመቀጠሌ፤ ትግሊችን የአዱስ አበባን ከተማ የደር እንስሳት ባሇቤትነት የማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን በክሌሌ ዯረጃ የመዯራጀትን፣ ራስን በራስ የማስተዲዯርንና እሰከመገንጠሌ የሚዯርስ መብት ማስከበርን እንዯሚያጠቃሇሌ ወዲጅም ጠሊትም ሉያውቀው ይገባሌ ብሇዋሌ፡፡ የሰው ሌጅ ጎሳዎች፣ ከእኛ በቁጥር በጣም የሚያንሱት እንኳን ሳይቀሩ፣ በጎጥ ተዯራጅተው ክሌልች

በመመስረት ራሳቸውን የማስተዲዯር ሙለ መብት ሲጎናፀፉ፤ በእኛ ዯረጃ ከፍተኛ ቁጥር፣ የታሪክና የቅሪተ አካሌ ማስረጃ ያሇው የቀዯመ አካሌ ይህን መብት መነፈጉ ኢፍትሃዊ ነው ሲለ አስረዴተዋሌ፡፡

በመቀጠሌም ሲያብራሩ፣ እቅዲቸው አዱስ አበባን የይዞታቸው ማዕከሌ አዴርጎ ማስመሇስ ብቻ ሳይሆን፣ በየብሔራዊ ፓርኩና በጥብቅ የተፈጥሮ ቦታዎች ተበትነው፣ ተሸንሽነውና ተከፋፍሇው የሚገኙትን የደር እንስሳት ግዛቶች በማሰባበሰብና አንዴ በማዴረግ ራሱን የቻሇ የታፈረና የተከበረ ክሌሌ መመስረት ነው ብሇዋሌ፡፡ ሁለም የደር እንስሳት ባህሊቸው፣ እሴቶቻቸው፣ የመጮህ፣ የማስካካትና የማጓራት መብታቸው፣ በተመቻቸው ቦታ የመጋጥ የመቦጨቅና የመፀዲዲት ተፈጥሮአዊ ፍሊጎታቸው ተጠብቆ እንዯፈሇጉ የሚፈነጩበትና የሚኖሩበት እንስስያ በመባሌ የሚጠራ ታሊቅ ክሌሌ ሇመመስረት የታቀዯ የትግሌ አቅጣጫ እንዯተነዯፈ ገሌፀዋሌ፡፡

የአዱስ አበባንም ስያሜ የቀዴሙትን አባቶቻቸውን ሇማስታወስ በእውቁ የቅዴመ እንስሳት ታሊቅ አባት ስም ‹‹ዲይኖፖሉስ›› ወዯሚሇው መጠሪያ ሇመቀየር አስፈሊጊውን ሁለ እንዯሚያዯርጉ አስረዴተዋሌ፡፡ በዚህ መሠረት በሃገሪቱ የሚገኙትን ብሔራዊ ፓርኮችና የደር እንስሳት ጥብቅ ቦታዎችን፣ ማሇትም እነ ያንጉዱ ራሳን፣ ባላን፣ ስሜንን፣ ጋምቤሊን፣ ነጭ ሳርን፣ ኦሞን፣ አቢያታ-ሻሊን፣ አሌጣሽን፣ ባቢላን፣ ማጎን፣ አዋሽን እና ላልችንም ያጠቃሇሇ ሁለም ክፍልች በአንዴነት የሚዋሃደበትና በዲይኖፖሉስ የአስተዲዯር ማእከሌነትና ዋና ከተማነት የሚተዲዯሩበት ጠንካራ የታሊቋ እንስስያን ነፃ መንግስት ሇመፍጠር እቅዴ እንዲሇ አሳውቀዋሌ፡፡

አዱስ አበባ ከቀዯምቶቻቸው ይዞታ ባስከፊ ጉሌበትና በከፍተኛ ጭካኔ የሰው ሌጅ በሚባሇው ክፉ ነፍጠኛ ከተወረረች በኋሊ የዯረሰውን አውዲሚ ጥፋት፣ ዴምሰሳና ስዯት አስታውሰው የህሉና ፀልት ያዯረሱት ተወካዮች በወገኖቻቸው ሊይ በዯረሰው በዯሌ የሚሰማቸው ሀዘን ከቀን ወዯ ቀን እያመረቀዘ፣ ከዘመን ዘመን እየከረረ፣ አየዯሇበ፣ ሇቂም በቀሌ፣ አገር ሇማጥፋት፣ ሇማውዯምና ሇመከፋፈሌ ወዯ ኋሊ እንዲይለ ዯመ ነፍሳቸውን እየገፋፋ እረፍት እየነሳቸው እንዯሆነ ገሌፀዋሌ፡፡ በዚህ ጊዜ ቦታው ሊይ ተገኝተው መርሃ ግብሩን ይከታተለ የነበሩ አንዴ የአዞ ጎሳ አዛውንት ያፈሰሱት እንባ እንዯጎርፍ እየወረዯ ቦታውን አጥሇቅሌቆት እንዯነበርና በርካታ የእንስሳውን ማሕበረሰብ አባሊት እንባ እንዲራጨ ሇመረዲት ተችሎሌ፡፡

የደር እንስሳት በተፈፀመባቸው ተዯጋጋሚ ወረራና ጭፍጨፋ ብዙዎች ቀዯምቶቻቸው ከምዴረ ገጽ እንዱጠፉ ምክንያት ሆኗሌ በማሇት የገሇፁት ተወካዮች፣ ከተዯጋገጋሚ ወረራ በኋሊ ባሁኑ ሰአት አዱስ አበባ ሊይ የሚታየው የሲሚንቶ፣ የእንጨት፣ የቆርቆሮ፣ የአስፋሌትና የብረታ ብረት ክምችት ቦታውን ወዯ ቀዴሞ ይዞታው መሌሶ ሇደር እንስሳት አመቺ ሇማዴረግ በጣም አስቸጋሪ እንዯሚያዯርግባቸው ገሌጠዋሌ፡፡ አዱስ አበባን፣ ወይንም በእነሱ አጠራር ‹‹ዲይኖፖሉስን››፣ ወዯ ቀዴሞ ተፈጥሮአዊ ይዘቷ ሇመመሇስ ከፍተኛ ጥረትና የሁለም እንስሳት አስተዋፅኦ እንዯሚያስፈሌግም አስታውሰዋሌ፡፡

ጭራቁ የሰው ሌጅ በሰፊው ወርሮ የሰፈረባቸውን ቦታዎችም ወዯ ህጋዊ ባሇቤቶቻቸው ሇማስመሇስ ግዛታችን ሊይ ሰፍረው አገር የሁለም መስሎቸው ኑሮአቸውን የሚገፉት የሰው ሌጆች መጤ በሚሌ ስያሜ ተሇይተው ቢቻሌ በግፊ፣ ካሌተቻሇ ዯግሞ ጥርስ በማፋጨት አያስፈራራን፣ ሲያስፈሌግም እየቦተረፍን ይዞታችን ነበር ብሇን የምናስበውን ቦታ በሙለ ሇቅቀው እንዱወጡሌን ሇማዴረግ እቅዴ ይዘናሌ ብሇዋሌ፡፡ በዚህ መሠረት አንዲንዴ ቦታዎች ሊይ መጤዎችን ሇማስሇቀቅ ባዯረግነው ሙከራ፣

በተሇይ ባሇፉት አራት አመታት፣ የተሳካ ውጤት ስሇታየ በዚሁ ቀጥሇን ሙለ በሙለ ቦታችንን ነፃ እስክናዯርግ ዴረስ ሇከፋውንና ቡትረፋውን እንቀጥሊሇን ብሇዋሌ፡፡

ቀዯም ሲሌ ወንዴሞቻችን እነ ምስጥና ትሊትሌ፣ እንዱሁም ሰርሳሪና ቦርቧሪ የማሕበረሰባችን አባሊት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ክፉውና ወራሪው የሰው ሌጅ የጀመረውንና የተከሇብንን የከተማ ግንባታ ሂዯት በመሸርሸርና በማስተጓጎሌ ከፍተኛ ትግሌ ሳያሰሌሱ ሲያዯርጉ የቆዩ ቢሆንም፣ የዘመኑ አስፋሌት፣ ሲሚንቶ፣ ብረትና ግንብ ግን ሇመቦርቦርና ወዯ አፈርነት ሇመቀየር በጣም አስቸጋሪ እየሆነ ስሇመጣ ወዯ ቀዴሞ ተፈጥሮአዊ ሁኔታው ሇመመሇስ የሚዯረገውን ጥረት ፈታኝ እንዯሚያዯርገው ሇማስገንዘብ ሞክረዋሌ፡፡ ሇዚህም በበሇፀጉት አገሮች በየእንስሳት ማእከልች ተወስዯው አጥሩ ስሇሰፋ በነፃነት እንኖራሇን ብሇው የሚያስቡ የደር እንስሳት ዲያስፖራዎች ሉያዯርጉት የሚችለት አስተዋፅኦ በቀሊለ ሉገመት አይገባውም ብሇዋሌ፡፡ የደር እንስሳት ዲያስፖራ አባሊትም ይህን ጥሪ ተቀብሇው አስፈሊጊውን ሁለ ከማዴረግ እንዲይቆጠቡ አሳስበዋሌ፡፡ በዚህ አካባቢውን ወዯ ተፈጥሮአዊ ይዞታው ሇመመሇስ በሚካሄዯው እሌህ አስጨራሽ ትግሌ የተሇያዩትን ባሇዴርሻ አካሊት አስተባብረው ወዯ ቀዴሞ ጠፍ ሁኔታው ሇመመሇስ የደር አሳማዎችን፣ ከርከሮዎችን፣ ጉማሬዎችን እንዱሁም የቀንና የማታ ጅቦችን ያካተተ የተረኞች ኮሚቴ እንዯሚቋቋም ገሌፀዋሌ፡፡

በታሪክ በተዯጋጋሚ ጊዜ የተሇያዩ ሰው የተባሇው እርኩስ ፍጡር ሌጆችና ጎሳዎች እየመጡ ቦታውን እየወረሩ የእንስሳትን ዘር ሲጨፈጭፉ እንዯኖሩ ገሌጠው፣ እዚህ ምዴር ሊይ የተፈራረቁት የሰው ሌጆች እርስ በርስ እየተፋጁ አንደ ላሊውን ሇማስገበር ሲያዯርግ በነበረው ግብ ግብ የገፈቱ ቀማሽ የነበሩት የእንስሳት ቀዯምቶች እንዯነበሩ አስረዴተዋሌ፡፡ የሰው ሌጆች የቀዯምቶቻችንን ተፈጥሮአዊ ይዞታ ሇመቆጣጠርና ቀዯምቶቻችንን ሇመመዝበር ያዯረጉት ጥረት ተሳክቶሊቸው አከርካሪያችንን ሇተወሰነ ጊዜ ቢሰብሩብንም፣ አሁን ግን አከርካሪያቸውን እየሰበርን በመመከት ዴሌ ሇመቀዲጀት እዛው አከርካሪያችንን የሰበሩበት ቦታ ምኒሌክ ቤተ መንግሥት መናፈሻ ዴረስ ዘሌቀን ገብተን ቦታ ቦታችንን በመያዝ፤ ሲቻሌ በግዴ እያሳመንን፣ ሳይመች ዯግሞ እያዯናገርን ወዯ ወሳኙ የዴሌ ምእራፍ ሇመዴረስ አመቺ ጊዜ በመጠባበቅ ሊይ እንገኛሇን ብሇዋሌ፡፡

ምንም እንኳን የሃገሪቱን ከፍተኛ የአመራር ሥሌጣን የተቆጣጠረው በአቻቻይነት ብቃቱ የተዯነቀው ባሇ ሁሇት ክንፉ የእኛው ጣዎስ ቢሆንም፣ የምናሌመውን የጠራና ያሌተዯበሊሇቀ እንስሳዊነትን የተሊበሰ፣ እኛን እኛን የሚሸትና በእኛ ረዥም ቁመና ሌክ የተዋቀረ ማህበረሰብ ሇመፍጠር ሇምናዯርገው ጥረት መሰናክሌ እየሆነ ስሊስቸገረ፣ ቢቻሌ በተንኮሌ ጠማቂዋና በጎሰኛዋ ጦጣ፣ ካሌሆነ ዯግሞ በመሠሪው ገመሬ ዝንጀሮ ተክተን ጠሊቶቻችንን በእጥፍ ዴርብርብ ሇመበቀሌ እንዴንችሌ አስፈሊጊውን የቡርቦራ ሥራ በአርኪ ሁኔታ እያቀሊጠፍን ነው በማሇት አሁን ያለበትን ሁኔታ አሳውቀዋሌ፡፡

የሰው ሌጆች እየተፈራረቁ አካባቢውን ሇመቆጣጠር ባዯረጉት ጥረት እርስ በርሳቸው እየተፋጁ ያዯረሱብን በዯሌ ከፍተኛ ነው በማሇት ያሇፈውን የግፍ አገዛዝ አስከፊነትም በሃዘን ገሌፀዋሌ፡፡ አንደ የሰው ሌጅ ጎሳ ላሊውን ሇማስገበር ሲያዯርግ በነበረው ፉክክር ብዙ ውዴመት ዯርሷሌ ያለት ተወካዮች፣ በተሇያዩ ጊዜያት የተሇያዩ የሰው ሌጅ ዘሮች ቦታውን ቢቆጣጠሩትም፣ ‹‹ኬኛ›› ውጪ ሇረጅም ጊዜ ባሇቤትነቱን ሇማስመስከር የሚችሌ አካሌ ከየትም ሉገኝ አይችሌም ብሇዋሌ፡፡

ከሁለም ነገር በፊት ባሇቤትነታቸው ሲረጋገጥ አንዴ ትሌቅ ሃውሌት አሁን መስቀሌ አዯባባይ እየተባሇ የሚጠራው ቦታ ሊይ ሇማቆም እቅዴ እንዲሇም ገሌጠዋሌ፡፡ ሃውሌቱ በጥይት፣ በጦር፣ በጎራዳና በወጥመዴ የወዯቁትን ውዴ የደር እንስሳት ሰማዕታት ሇማስታወስ፣ የተቦተረፉና የተዘሇዘለ የእንስሳት አካልችን በዯም ተሇውሰውና ተቆራርጠው በሚያሳይ መሌኩ ትውሌዴን በቂም በቀሌ ስሜት አናውዞ እንዱያርገፈግፍና ሇአመፅ እንዱያነሳሳ ተዯርጎ እንዯሚሰራ ገሌፀዋሌ፡፡

መሃሌ አዱሰ አበባ የሚገኘው ውሃ ይፈሌቅበት የነበረው ቦታም የቀዯምቶቻቸው ውሃ መጠጫ፣ መሰባሰቢያ፣ መንሸራሸሪያና ማዴፈጫ እንዯነበር ገሌጠው እሱንም ወዯ ቀዴሞ ሁኔታው ሇመመሇስ ከፍተኛ ጥረት እንዯሚዯረግ አስገንዝበዋሌ፡፡ በቀዴሞ ጊዜ እንጦጦ፣ መናገሻ፣ ኤረር፤ ወጨጫ ወዘተ… እያለ እንዯ እንስሳት ባህሊዊ ሌማዴ ዴንበሮቻቸውን በጠረናቸው በመከሇሌ ያስከበሯቸውን ቦታዎች በሙለ ወዯ ቀዴሞ ግርማ ሞገሳቸው ተመሌሰው ቦታውን የታፈረና የተከበረ የእንስስያ ክሌሌ ዋና መናሏሪያ ሇማዴረግ እንዯሚሰራ አስታውቀዋሌ፡፡ ሇዚህም እንዱረዲ ቀዯም ብል የተጀመረው የወጣት ቡችልችንና ግሌገልችን ጥርስ የመሞረዴ ሥራ እንዯቀጠሇና ጥርሳቸው የተሞረዯ ቡችልችና ግሌገልች የመናከስ ችልታቸውን አዲብረው በተመረጡ ቦታዎች ሊይ ተሰማርተው የማተራመስ ተሌእኳቸውን በሰፊው መያያዛቸውን አስረዴተዋሌ፡፡

ይህ በእንዱህ እንዲሇ፣ ራሱን የእፅዋትያ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (እ.ብ.ነ.ግ) በማሇት የሚጠራ የእፅዋትን ዘር እወክሊሇሁ የሚሌ ቡዴን በእንስስያ ወኪልች በኩሌ የተሊሇፈው መሌዕክት ብዙ ታሪካዊ ግዴፈቶች ያለበት ሃሰተኛ፣ ፅንፈኛና በዝቅተኝነት መንፈስ የተሞሊ ትርክት ነው ሲሌ ከሊይ የተሰጠውን መግሇጫ አጣጥሎሌ፡፡ ቀዯምት ከተባሇ ከእኛ ወዱያ ቀዯምት ነኝ ሉሌ የሚገባው ምንም ምዴራዊ አካሌ የሇም በሚሌ ኃይሇ-ቃሌ የጀመረው መግሇጫ እንዯሚከተሇው ይነበባሌ፡፡

ምንም አይነት ተንቀሳቃሽ ፍጡር ምዴር ሊይ ይታይ ካሌነበረበት የዓሇማችን መጀመሪያ ከነበረው የሩቅ ጊዜ ዘመን ጀምሮ አስከ አሁን በቀዯምት አባቶቻችን በነፈርን (Fern)፣ በነሞስ (Moss)፣ በነማግኖሉያ (Magnolia) እና በላልችም ግርማ ሞገስ በተጎናጸፉ የእፅዋት ዘሮች የተጀመረውን ዓሇምን አረንጓዳ በማዴረግ ሇሁለም ፍጡራን ማረፊያ፣ መጠሇያ፣ ምግብና ትንፋሽ ሰጪ በመሆን እኛ እፅዋት በትጋት ስናገሇግሌ ቆይተን ሇዚህ ሁለ ስኬት ያበቃናቸው የእንስስያ ተወካዮች እኛን በማግሇሌ ስሌጣን ሇመቆናጠጥ ባሊቸው የስግብግብነት፣ የዝቅተኝነትና የአተራማሽነት መንፈስ ሳያማክሩንና ፍሊጎታችንን ሳያካትቱ የሰጡት መግሇጫ አሳዝኖናሌ ብሇዋሌ፡፡

በመጥረቢያ፣ በመጋዝ፣ በገጀራና በሜንጫ እንዱሁም በአሰከፊ ሰዯዴ እሳት ሊሇፉት ረጅም ዘመናት፣ በአሁኑ ዘመን ዯግሞ በአካባቢ ብክሇትና ውዴመት የተጨፈጨፉት እፅዋትና ከምዯረ-ገፅ እንዱጠፉ ዯባ የተፈፀመባቸው ወገኖቻችን ሃዘን በቅጡ ሳይወጣሌን፤ በእንስስያ ተወካዮች በኩሌ ሥሌጣንን በመቀራመት ያንዴ ወገን ንብረት ሇማዴረግ የተዯረገው የስግብግብነት ሙከራ ከጁንታ አስተሳሰብ የሚመነጭ ሇመሆኑ የመግሇጫው መሠረተ ቢስነት ምስክር ነው በማሇት ዴርጊቱን ነቅፈዋሌ፡፡ መስቀሌ አዯባባይ ሊይ ሉሰራ የታቀዯው ሃውሌትም የቆራጣ ዛፍ ጉቶዎችን፣ የተጨፈጨፉ ቅጠልችን፣ ባጭር እየተቀጩ የጠወሇጉ አበባዎችን፣ አፍርተው ሇዘር ሉበቁ ሲለ የረገፉ ፍሬዎችን ምስሌ ሳያካትት እንዱሰራ የተወሰነው ውሳኔ አግሊይና ወገንተኝነት የተጠናወተው ነው በማሇት ኮንነዋሌ፡፡

የእንስስያ ማሕበረሰብ አብሮ የመኖር ባሕሌ ያዲበረና የተፈጥሮን ሂዯት ጠንቅቆ የሚረዲ፣ በትበብር፣ በፍቅርና በአንዴነት የሚያምን ነው በማሇት የቀጠሇው መግሇጫ፣ ከዚህ ማሕበረሰብ የወጡ ጥቂት ፅንፈኞች ግን በዝቅተኝነት ስሜት ተገፋፍተው አካባቢውን ሇማተረማመስ ቆርጠው መነሳታቸውን ከመግሇጫቸው መረዲት ይቻሊሌ ብሎሌ፡፡ ጦጣና ዝንጀሮ ሇባሇ አራት እግሮችና ሇላልች ፍጡራን እንዱሁም ከነሱ ሇየት ሊለ የደር እንስሳት የሚያሳዩትን ንቀትና ጥሊቻ ቀጥሇውበት በመሊው የደር እንስሳት ማሕበረሰብ ሊይ የበሊይነትን ሇመቀዲጀት ባሊቸው መሰሪ ፍሊጎት የተነሳ ካገር ጠባቂውና ከጀግናው አንበሳ ጀምሮ ብዙ የደር እንስሳትን በመሌቲነት ሲያወናብደ እንዯኖሩ ታሪክ ምስክር ነው በማሇት መግሇጫቸውን አጠቃሌሇዋሌ፡፡

በተጨማሪም በደር እንስሳት ነፃነት ግንባር (ደ.እ.ነ.ግ) ተወካዮች የተሰጠውን መግሇጫ በመቃወም የቤት እንስሳት አንዴነት ፓርቲ (ቤ.እ.አ.ፓ) የተሰጠው ከፋፋይ መግሇጫ የእኛን ማህበረሰብ በምንም መመዘኛ አይመጥንም፣ እኛን አይወክሌም፣ የእኛን አቋምም አያንፀባርቅም ሲሌ ማሰተባበያ ሰጥቷሌ፡፡ እኛ የቤት እንስሳትና አጋሮቻችን ከወንዴሞቻችን ከሰው ሌጆች ጋር ያሇንን ትስስር ሇማናጋት የሚዯረገውን ማንኛውንም አይነት ሙከራ አጥብቀን እናወግዛሇን ካሇ በኋሊ፤ የእኛና የሰው ሌጆች ግንኙነት በተፈጥሮ ሕግ የተሳሰረና ሸርሻሪዎች፣ ገንጣዮች፣ ጎሸኞችና ከፋፋዮች ሉሰብሩት የማይችለት ኃይሌ ስሇሆነ ፀረ የተፈጥሮ ሕግጋት ኃይልች ከዚህ ዴርጊታቸው እንዱቆጠቡ አጥብቀን እናስጠነቀቃሇን ሲሌ መግሇጫውን አሳርጓሌ፡፡

ከሊይ በሁሇቱ ቡዴኖች የተሰማው ተቃውሞ እንዯተጠበቀ ሆኖ፣ በደር እንስሳት ማሕበረሰብ ውስጥም እንዯተሇመዯው መከፋፈሌ እንዲሇ የሚያመሊክቱ ሁኔታዎች ተከስተዋሌ፡፡ በሆዴ ተሳቢዎቹን (አንዲንድች እግር አሌባዎቹ እያለ በንቀት ይጠሯቸዋሌ) የእባብንና የዘንድን ማህበረሰብ የሚወክሌ አንዴ ውሰጠ አዋቂ እንዯገሇፀው፣ ጦጣና ዝንጀሮ እንዲንዴ የደር እንስሳት ማህበረሰብ አባሊትን በንቀት እንዯሚመሇከቱና ከፖሇቲካ ተሳትፎ እንዱገሇለና የራሳቸውን እዴሌ በራሳቸው ሇመወሰን እንዲይችለ ግፊት እንዯሚዯረግባቸው ገሌጧሌ፡፡ ከዚህ በፊት ‹‹ቦፋ ጉራቻ›› የሚሌ ስያሜ ሇእርጉሙ የሰው ሌጅ በመስጠት እኛን ከመርዘኛው የሰው ሌጅ ጋር በማመሳሰሌ ብዙ የመከፋፈሌ ሴራዎች እየፈፀሙብን ሁኔታዎች ይስተካከለ ይሆናሌ እያሌን እስካሁን ብንዘሌቅም ያሇምንም ውጤት እስካሁን ቆይተናሌ ሲሌ አማሯሌ፡፡

እንዱህ አይነቱ ዘሇፋና ላልች ከፋፋይ ዴርጊቶች የእኛን በሆዴ ተሳቢ ፍጡራን መሌካም ሥነ ምግባር ከሰው ሌጅ ወረራና አሳፋሪ ዴርጊት ጋር በማመሳሰሌ ማሕበረሰባችንን ከደር እንስሳት መዴረክ ሇማግሇሌ ሆነ ተብል የተጠነሰሰ የቀጣይ ሴራ አካሌ በመሆኑ ጉባኤው ሊይ ሊሇመሳተፍ እንዯወሰኑ ገሌጧሌ፡፡ እኛን የመሰሇ ቅደስ ፍጡር ከአረመኔውና ከመርዛሙ የሰው ሌጅ ጋር ሇማመሳሰሌ በምሳላም ሆነ በላሊ ዘዳ የሚዯረገው ሙከራ ተቀባይነት እንዯላሇው እንዱታወቅሌን እንፈሌጋሇን ብሎሌ፡፡ ይህ በደር እንስሳው ማህበረሰብ መካከሌ ሌዩነት ሇመዝራት በጦጣና በዝንጀሮ አጋፋሪነት የተሸረበ አዯገኛ አካሄዴ የምናሌማትን ታሊቋን እንስስያ ሇመፍጠር በሚካሄዯው የተፋፋመ ትግሌ ሊይ ቀዝቃዛ የቀበናን ውሃ የመቸሇስ ያህሌ ነው ሲሌ ምሬቱን በእባብና በዘንድ ማህበረሰብ ስም ገሌጧሌ፡፡
https://amharic-zehabesha.com/archives/178481

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...