Friday, November 25, 2022

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

የዛሬዋ ኢትዮጵያ የዘርፍ ፍጅት የፈጠሙን፣ ሕዝብን ለአስርተ ዓመታት ያሰቃዩን፣ ወህኒ በእሳት የጠበሱን ፈታ  የእድሜና የሙያ ባልጠጋውን ክቡር አቶ ታዲዮስ ታንቱን አስራ የምርድ ሲዖል የምታበላ አገር ናት፡፡ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ነፍሰ ገዳዮችና ሌባዎች የሚሾሙባት በማተባቸው በማድረቻቸው በድህነት የሚቆራመዱት እነ ታዲዎስ ታንቱ ወህኒ በእስተ እርጅና ከእነ ቅዱስ ጳውሎስ በከፋ ሁኔታ የሚሰቃዩባት ምድር ናት፡፡

“በማይጨበጥና በማይዳሰስ ነገር አላምንም” እያለ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ተረት የሚቆጥር ድስኩራም በሰላሳ ዓመታት ወስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኪያሄደውን የእውነት ተከታዮች መሰዋእትነት፣ የፈሪሳውያን ምሁራንን የነፈሰ ገዳዮች እግር ላሽነትና የጲላጦስ ዳኞችን ጭካኔ ይመልከት፡፡

ክቡር አቶ ታዲዮስ ታንቶ በፈሪሳውያን ከሳሽነትና  በጲላጦስ ዳኝነት እየተሳደዱና እየተንገላቱ ያሉ ብፁእ ቅዱስ አባት ናቸው፡፡ አቶ ታዲዎስ ብፁእ ቅዱስ ሲባሉ ከንፈርኑን እያሸራመመ የሚያሽሟጥጥ ከርሳምና እርኩስ ፈሪሳዊ አይጠፋም፡፡አቶ ታዲዎስ ታንቱ ለሚያምኑበት ታሪክ   እነ  ቅዱስ ጳውሎስ ለሚያምኑበት ወንጌል እንገታቸውን የሰጡትን ያህል አንገታቸው የሰጡ ቅዱስ አባት ናቸው፡፡ አቶ ታዲዎስ ታንቱ በመቶ ዓመት እንዴ በላንባ ዲና  ተፈልገው ተማይገኙት በለማተብ ሰዎች እንዱ ናቸው፡፡ ተዚህ ዘመን ከርሳም ፈሪሳዊ ምሁራን፣ ካህናት፣ ሼሆችና ፓስተሮች ጋር ሲነጣጠሩ አቶ ታዲዎስ ታንቱ ካባና ቆብ ያልደረቡ ብፁእ ቅዱስ አባት ናቸው፡፡

ስንቱ ካባ ደራቢ ጳጳስ፣ ስንቱ ጠምጣሚ ሼህ፣ ስንቱ አነብናቢ ፓስተር፣ ስንቱ ዲግሪ ጫኝ ፐሮፌስርና ዶክተር ለስጋው፣ ለገንዘብ፣ ለስልጣንና ለጉርሻ ተነፈሰ ገዳዮች ጀርባ ተሰልፎ ቂጡን እያማታ  በሚያረጠረጥበት ሰዓት አቶ ታዲዎስ የታሪክ መጻሕፍትን ተሽክመው የሚያምኑበት ታሪክ ያለመታከት የሚሰብኩ ሐዋርያ ናቸው፡፡ አቶ ታዲዎስ እንደ ሐዋሪያው ጳውሎስ፣ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስና ቡድሃ የስጋ ፍላጎታቸውን በእንዶድ አጥበው አስወግደው፤ ስልጣንን፣ ገንዘብንና መቅቡጥን ተጠይፈው፤ ተሚያምኑበት እውነት ጋር ቆመው ለማለፍ የተዘጋጁና የተመረጡ  ሰው ናቸው፡፡ ነቢይ በአገሩ አይከበር ሆኖ እኛ ባንገነባላቸውም አቶ ታዲዎስ ታንቱ ታሪክ ለጊዜው የማይታይ የምስክርነት ሐውልት ያቆመላቸው አባት ናቸው፡፡

አምላክ ሆይ! እውንን እስር ቤት ማደር የነበረባቸው ሕዝብ ለምን ይሞታል አያሉ የታገሉት አቶ ታዲዎስ ታንቶ ወይስ ሰላሳ ዓመታት ሙሉ በጆሮ ጠቢነት፣ በካድሬነትና በታጣቂነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲጨፈጭፉ የኖሩት አሳሪዎቻቸው? መለኮት ሆይ! እውንን ምሁራን የተባሉ ፈሪሳውያን መቆም የነበረባቸው ታሪክን ተሚመረምርቱ ፈላስፋ ታዲዎስ ታንቱ ጋር ወይስ በታሪክ ላይ ተሚፀዳዱት መሀይም አሳሪዎቻቸው ጋር!

ብፁእ ቅዱስ ታዲዎስ ታንቶ ሆይ! እኛ ፈሪሳውያን ከድተን ከጲላጦስ ዳኞችና ተአረመኔ አሳሪዎችዎ ጎን ብንቆም አይግረምዎ! በፈሪሳውያንም ዘመን የሆነው ይኸው ነው፡፡ የማታ ማታ አሸናፊው ግን እውነት ነው!

ይኸንን ሁሉ ግፍ የሚመለከተው መለኮት ለቅዱስ ጳውሎስና ጴጥሮስ የሰጠውን ጥናት ለእርስዎም ይስጥዎት!

 

መጀመርያ ሚያዝያ ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.ም. እንደገና ህራር ሁለት ሺህ አስራ አምስት ዓ.ም.

https://youtu.be/ge7b8K0TcyE
https://amharic-zehabesha.com/archives/177877

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...