Wednesday, October 5, 2022

በፊደራል ደረጃ  ልዩ ትኩረት የተደረገበት  የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፣ የ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ  ፈተና ልዩ መረጃ  ።
 በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

በመሥከረም 28/ 2015 ዓ/ም በሶሻል ሣይንሥ ተማሪዎች ፈተና ይጀመራል ።

ይህ በፈተና አሰጣጡ ልዩ የሆነው አገር አቀፍ ፈተና ፣ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን ጥንካሬ እና ደካማ ጎን በግልፅ እና በተጨባጭ የሚያመላክት ፣ በትምህርት ጥራት ላይ በትጋት እንዲሰራ የሚያደርግ ነው ። ተብሎ ይጠበቃል ።

እንደሚታወቀው ገንዘብ ተኮር የትምህርት አሠጣጥ በሁሉም ትምህርት ቤቶች መኖሩን ( በግል ትምህርት ቤቶች በክፍያ በመንግሥት ተምህርት ቤቶች ኮራብት በሆኑ መምህራን የተነሣ ... )  በይፋ የሚያሳውቀን ይኽ በየዩኒቨርስቲ የሚሠጠው ፈተና በመሆኑ ፣ የትምህርት ሚኒሰትር  እና መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት እንደሰጡት ይታወቃል ።

ይህ ፈተና በአገር አቀፍ ደረጃ ፣ በፊደራል  ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ነው የሚካሄደው ። ፈተናው ልዩ ጥበቃ ይደረግለታል ። ፈታኝ መምህራንም በዕጣ ነው ፣ ለየዩኒቨርሥቲዎቹ የሚመደቡት ።   እያንዳንዱ አሥፈታኝ ትምህርት ቤት ፤ ተማሪዎች  እና ዩኒቨርስቲዎችን የሚመለከት ግዴታ ና መብትም በግልፅ ወጥቷል ።

ይህንን በተመለከተ ያገኘሁትን መረጃ አሣጥሬ ለተማሪዎች እና ለወላጆች አሣውቃለሁ ።

 የአሥፈታኝ ተምህርት ቤቶች ግዴታ

- የተፈታኝተማሪዎችንሥም ዝርዝር አሥቀድሞ ለሚመለከተው ክፍል ፕሮቶኮሉን በጠበቀ መልኩ ያሳውቃል ።

2 . በበቂ ሁኔታ ተፈታኙን ሥለ ዩኒቨርስቲው እና ሥለ ፈተናው ህግ ያሣውቃል ።

3 . በሳይኮሎጂ የተጎዱትን ተማሪዎች ( በኮቪድ እና በሶሻል ሚዲያ ውዠንብር ) ሞራል መገንባትና ከኩረጃ ይልቅ በራሳቸው አእምሮ መሥራት አማራጫቸው መሆኑንን በወጉ ያሥረዳል ። አቅማቸውን ሣይጠቀሙ ቀርተው ጠባቂ በመሆን እንዳይወድቁ አሥቀድሞ ያነቃል ።

4 . የትምህርት ቤት እና የአድሚሽን ካርዳቸውን እንዳይረሱ ያሳስባል ።

5 . እያንዳንዱ አሥፈተኛ ት/ቤት ፤ የማህበራዊ ሣይንሥ ተፈታኞችን በመሥከረም 28/01/2015 የተፈጥሮ ሣይንሥ ተማሪዎችን ደግሞ በጥቅምት 6/ 2015 ዓ/ም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርስቲዎች ቀጥሮ የማሥረከብ እና ፈተናቸውን ሲጨርሱ ቆጥሮ የመረከብ ግዴታ አለበት  ።

 

የተፈታኝ ተማሪውች ግዴታ 

- አንሶላ፣ብርድልብስ እና የሌሊት  ልብሶች ( ቱታ እና ፒጃማ ) ይዘው መምጣት አለባቸው ።

2 .ማንኛውንም ብልጭልጭ ቁሣቁሥ ፣ የመዘነጫ መነፅር ፣ የጆሮ ጌጥ ፣ ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ሌላ የጌጥ ቀለበት ማድረግ የለባቸውም ።

3.ማንኛውም  ሞባይል ሥልክ ፣ ላፕቶፕ ፣ ታብሌት ፣  ይዞ ወደ ዩነኒቨርስቲ መግባት ክልክል  ነው ።

4 . እርሳስ ፣ ላቢስ፣ መቅረጫ ፣ ማሥመሪያ መያዝ አለባቸው ።

5 . የትምህርት ቤታቸውን እና የመፈተኛ መታወቂያቸውን  የመያዝ ግዴታ አለባቸው ።

-  ዩኒቨርሲቲከገቡበኋላ በሚገለፅላቸው  በዩኒቨርሲቲው ህግ የመተዳደርና ህጉን የመጠበቅ  ግዴታ አለባቸው ።

- እርጉዝተማሪዎችመፈተን አይቹሉም ። ከወለዱ በኋላ የሚፈተኑበትን ሁኔታ መንግሥት ያመቻቻል ።

የዩኒቨርስቲዎች ግዴታ

1.አሥቀድሞ  በተጠቀሰው ተማሪዎችን የመቀበል ቀን ፣ ከሚመለከተው አካል አሥቀድሞ በተረከቡት ሰነድ ፣ አንድ በአንድ ተማሪዎችን ማንነታቸውን በማረጋገጥ እና ከላይ የተጠቀሰውን ግዴታ ተማሪው ማሟላቱን በማረጋገጥ ፣ ህጋዊ ፍተሻ አድርገው ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስቲዎቻቸው የማሥገባት ግዴታ አለባቸው ።

2 .  ለተፈታኝ ተማሪዎች ፣ የሚያድሩበት ክፍል ፣ አልጋ እና ፍራሽ አሥቀድሞ አዘጋጅተው የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው ።

- ለተማሪዎቹቁርስ፣ ምሣና እራት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ። ( በምግብ የሚነሳን ቅሬታ ከወዲሁ ለማሶገድ ዩኒቨርስቲዎቹ ትኩረት ሊያደርጉበት ይገባል ።)

4 . የተማሪዎቹ ፀጥታ እንዳይናጋ ፣ ማንኛውንም የፀጥታ ሥጋት እንዳይኖር ከፍተኛ ጥበቃና ምሥጢራዊ ክትትል ያደርጋል ።

-  ፈተናውንበተመለከተለተማሪዎቹ መብራሪያ እንዲሰጥ አደራሾችን ያመቻቻል ።
https://amharic-zehabesha.com/archives/177325

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...