Thursday, October 20, 2022
በተወለደበትና እትብቱ በተቀበረባት አገሩ መኖር የለብህም ተብሎ ለአርባ አመታት ያህል በትህነግ የትግራይ ወራሪ ሃይል በሰው ልጅ ሊፈፀም የማይገባውን አሰቃቂ በደል ሲደርስበት የኖረው የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና፣ የራያ አማራ ህብረተሰብ እንዲሁም የአፋር ወገኖቻችን የአሸባሪውን የመከራ ቀንበር ተሰብሮ ከሰሞኑ ነፃ በመውጣታችሁ የተሰማን ልባዊ ደስታ ወደር የለውም።
ይህ የነፃነት ቀን እንዲመጣ ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን ከምስረታው ጀምሮ ሁለንተናዊ ትግል ሲያደርግ እንደነበረ እያስታወስን አሁንም ቢሆን የጋራ ጠላታችን ትህነግ/ወያኔ ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ ህዝባችን ወደ መደበኛ ኑሮው እስኪመለስ ድረስ ከተነሳነበት ዓላማ ስንዝር ወደ ኋላ እንደማንል ለማረጋገጥ እንወዳለን። ይህ አሁን የተገኘ ድል እንዲሁ የተገኘ ሳይሆን የብዙ ቆራጥ ወገኖቻችን የሕይወት መስዋእትነት ተከፍሎበት፣ በርካቶቹ የአካል ጉዳት ዋጋ ከፍለውበት፣ የኢኮኖሚ፣ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ እልህ አስጨራሽ ሁለንተናዊ ትግል ተደርጎበት የተገኘ ድል ነው። በመሆኑም ይህን ውጤት እንዲመጣ ለተሰጠው ቆራጥ አመራር እና ጥምር ሃይላችን ለከፈለው መስዋእት ታላቅ ክብር አለን።
ይህ አሸባሪና ባንዳ ድርጅት ሲጠነሰስ ጀምሮ ኢትዮጵያን ለመበታተን ቅድሚያ በአማራ ላይ የውሸት ትርክት በመፍጠር በሌሎች ኢትዮጵያን ወገኖቹ እንዲጠላ በማድረግ፣ እንዲሁም አገር ጠል የሆኑት ባእዳን ከጎኑ ካሰለፈ በኋላ ሃይሉን በመጠቀም በ27 ዓመታት የስልጣን ዘመኑ ያበረከተው ነገር ቢኖር ጥላቻን፣ መለያየትን፣ ሌብነትና ውሸትን ብቻ ነው። ነገር ግን ታጋሹ የኢትዮጵያ ህዝብ ያ አሉ ችግርና መከራ ካሳለፈ በኋላ ከጀርባው አሽቀንጥሮ እንደጣለው መቀሌ ከተማ ላይ መሽጎ ዳግም ኢትዮጵያን ለመበተን ሲኦል ድረስ ለመውረድ የነበረውን ፍላጎት በጋህድ ነግሮናል።
አሁን ላይ በኢትዮጵያ ውድ ልጆች ክቡር መስዋዕትነትና አኩሪ ተጋድሎ የአማራ ሕዝብ ከፋሽሽቱ ሃይል ወረራና ስቃይ ነጻ ወጥቷል፡፡ በዚህም ታላቅ ደስታና ኩራት እንደተሰማን ሁሉ የጀግኖቻችን ውለታ በሕዝባችን ዘንድ ከትውልድ ትውልድ ሲዘከር ይኖራል፡፡
መንግስት የኢትዮጵያን ሉዓላዊ የግዛት አንድነትና የዜጎችን ሁለንትናዊ ደህንነት የማረጋገጥ ሃለፊነትና ግዴታውን ይወጣ ዘንድ የጀመረውን ህግ የማስከበር ታሪካዊ ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥልና ለቀሪው ዓለምና ለመጭው ትውልድ ጭምር ትምህርት በሚሰጥ ሁኔታ ይቋጭ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን። በዚህ ህግ የማስከበርና ፋሽሽቱን የትግራይ ወራሪ ሃይል ሽብርተኛ አመራሮችና የጦር ወንጀለኞች ለፍርድ እስኪቀርቡ ድረስ አስቀድሞ የገባነውን ቃል በማደስ በምንችለው ሁሉ ከጥምር ሃይላችን ጎን እንደምንቆም ለማረጋገጥ እንወዳለን። በመጨረሻም ይህንን ቀን ያሳየንን ፈጣሪያችንን እያመሰገን የህዝባችን ነፃነት ፍጹም ይሆን ዘንድ ከምንግዜም በላይ እንታገለን።
https://amharic-zehabesha.com/archives/177410
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment