
የሀገር ዳር ድንበር ሕዝቡን አሰከባሪ:
የኢትዮጵያ ህልውና ዋሰትና ተጠሪ።
መከላከያ ጦር ጋሻና መከታ:
የዓይናችን ብሌን ነው የአንድነት አለኝታ።
እናት አባት ትዳር ... ቤተሰቡን ትቶ:
በዱር በገደሉ... ጫካ ተሰማርቶ:
እንቅልፋን ሳይተኛ ቀን ከሌሊት ነቅቶ ።
በረሀብ በጥማት ሰውነቱ አልቆ:
በፍልሚያው አውድማ ጠላትን ተናንቆ::
ሞቶ የሚያኖረንን ወጥቶ አደር ውለታ:
በምንም አንከፍለው አንዘንጋው ለአንድ አፍታ::
አንበሳው ጥምር ጦሩ ታግሶ ታግሶ:
አትንኩኝ ሲላቸው በእብሪት ተተንኩሶ::
የወያኔን ጀሌ አይቀጡ እየቀጣ:
ይገቡበት ዋሻ ...መድረሻ እያሳጣ::
ባንዳ ተረፍርፎ... ምርኮ እንደ አሸን ፈልሶ:
ድንፉታ ፋከራው ...እብሪቱ ተንፍሶ:
አየህልኝ አይደል የአሽባሪን ለቅሶ!
ጥይቴን ተኩሼ.. ዘረኛን ሳልጨርስ:
እጄን አትያዙ ብሎአል ላይመለስ:
ሰውነትክን ረስተህ ዘር... ሀረግ ስትመዝ
ነቅፈህ ስትቃወም ጠልተህ ስታወግዝ::
አንድ ቀን ሮንድ ዞረህ ጠብቀህ የማታቅ
የከተማ ፋኖ ...አውደልዳይ ተጠንቀቅ::
ሞቶ የሚያኖርህን ወጥቶ አደር ውለታ
በምንም ላትከፍለው በምንም ላተካ
ቀይ መስመሩን አልፈህ ዘብህን አትንካ::
አንተ ጠዋት ወጥተህ ማታ የምትገባው
ከሆቴል ቤት ገብተህ ምግብ የምትበላው
ውስኪ ቢራ አረቄ አልኮል የምጠጣው
የኔቢጤም ከሆንክ ሰው የምትለምነው።
አርሰህም ነግደህ... ሰርተህ የምትገባው
አንተን በሚጠብቅ መከላከያ ነው።
ቆስሎ አካሉ ጎሎ... ሕይወት እየሰዋ
ኢትዮጵያን ያኖረ መከታ አለኝታዋ::
ውረድ ግፋ በለው ወደፊትህ ገስግስ
ድል አድራጊው ጀግና በክብር ተመለስ::
ከሽመልስ ተሊላ::
https://amharic-zehabesha.com/archives/177071
No comments:
Post a Comment