Tuesday, August 30, 2022
ወልድያ በጠላት እንደተያዘች የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት መኾኑን ዞኑ አረጋግጧል።
የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋው ባታብል አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኀይል በዞናችን በድጋሜ ወረራ ለመፈፀም ያለ የሌለ ኀይሉን አሰባስቦ ለሁለተኛ ጊዜ ጦርነት አውጆብናል ብለዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋው ባታብል ዛሬ የሰጡት መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኀይል በዞናችን በድጋሜ ወረራ ለመፈፀም ያለ የሌለ ኀይሉን አሰባስቦ ለሁለተኛ ጊዜ ጦርነት አውጆብናል።
ከትናንት ስህተቱ የማይማረው የትህነግ ወራሪ ኀይል መንግስት ያቀረበለትን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው ለትግራይ ሕዝብ ግድ የሌለው መኾኑን በተግባር ማረጋገጡን ገልጸዋል።
ጦርነትን እንደ ዋነኛ ግብ ቆጥሮ፣ በሰው ደም ላይ የሚረማመደው የትህነግ አሸባሪ ቡድን፤ ዛሬም ከትናንት ስህተቱ ሳይማር የጦር ነጋሪት ሲጎስም ከከረመ በኋላ ሀገር የማፍረስ አጀንዳ አንግቦ ወደ ጦርነት ገብቷል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በየዘመናቱ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ጠላቶች ሲገጥሟት ኑሯል ። ከጥንት ጀምሮ የገጠማትን የውሰጥና የውጭ ጠላቶችን አሸንፋ በድል እየተረማመደች የመጣች የጥቁር አፍሪካ ሕዝቦች የነፃነት ፈርጥ መሆኗን የታሪክ ድርሳናት አስረግጠው ይመሰክራሉ።
ወራሪው የትግራይ ኃይል በመንግስት በኩል የቀረበለትን የሰላም አማራጭ አልቀበልም ብሎ ጦርነትን አማራጭ ያደረገው ለትግራይ ሕዝብ አስቦ ሳይሆን የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት፣ የባንዳነት ተልዕኮውን ለማስፈፀም አበክሮ እየሠራ ስለመኾኑ አንዱ ማሳያ ነው።
ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ሉአላዊነትና አንድነት ላይ የማይደራደሩ፣ በደምና በአጥንታቸው አፅንተው ያቆሟትና ሀገር የመሠረቱ ያፀኑ የእንቁ ልጆች ባለቤት ናት ። ዛሬም ቢኾን ከዚህ ከፍታዋና ክብሯ ማንም ዝቅ ሊያደርጋት አይችልም።
የሀገራችን ትናንት በደምና በአጥንት ያቆሟት ጀግኖች ልጆች እንደነበሯት ሁሉ፤ ዛሬም የሀገራቸውን ሉአላዊነትና አንድነት በደምና በአጥንታቸው የሚያፀኑ ጀግኖች ልጆች አሏት።
ወራሪው ኀይል በዞናችን ወረራ ሲፈፀም ትናንት ይጠቀምባቸው የነበሩ የሀሰት ቅስቀሳና ፕሮፖጋንዳዎች አሁንም ተጠናክሮ ሕዝብን ለማደናገር በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።
ይህ የሽብር ቡዱኑ ፕሮፖጋንዳ በማህበራዊ ሚዲያ ተከፋይ አክቲቪስቶች ብቻ የሚተገበር ሳይሆን የፈጠራ ወሬዎችን በሚያራግቡ እና የጠላት ፕሮፖጋንዳ ከውሰጥ ሁነው በሚደግፉ ስዎች ጭምር የሚተገበር በመኾኑ ዛሬም እንደለመደው ወልድያን ተቆጣጠርኩ እያለ ያራግባል ።
ስለዚህ ኅብረተሰቡ ከእንደዚህ ዓይነት የሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን ሊጠብቅና አጠራጣሪ መረጃዎችን ሲመለከት ለመንግስት የፀጥታ መዋቅር ጥቆማ መስጠት ይጠበቅበታል።
የዞናችን ሕዝብ በወራሪው ኃይል የደረሰበት የሰብዓዊ፣ ስነ ልበናዊና ቁሳዊ ውድመት መንገር ለቀባሪ እንደማርዳት ይቆጠራ፤ የችግሩ ቀጥተኛ ተጠቂና ገፈት ቀማሽ ነው።
ሰለሆነም ወራሪው ኃይል እንደ ሀገር ወረራ ሲፈፀም ዞናችን ቀጥተኛ የትግሉ ቦታ ላይ የሚገኝ በመኾኑ ፤ ከትናንት ችግሮች ትምሕርት በመውሰድ ያለ የሌለ አቅማችንን አሟጠን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኀይልና ፋኖ ጋር ደጀን በመኾን አጋርነታችንን እንደ ወትሮው አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል።
ሰላማችን የሚረጋገጠው በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም። መንግስት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነትና አማራጭ አሟጦ ተጠቅሟል። ለሰላም ሲባል ረጅም ርቀት በመንግስት በኩል የተወሰዱ አዎንታዊ እርምጃዎች የሚደነቁ ናቸው። ያም ሆኖ በጠላት የቀረበለትን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን ብሎ ጦርነትን እንደ ብቸኛ አማራጭ ተጠቅሞ ዳግም ወረራ ከፍቷል።
ሰለሆነም የዞናችን ሕዝብ የተቃጣብንን ወረራ የኀልውና ጉዳይ በመሆኑ አያጠያይቅም። ትናንት ብዙ ትምህርት ወሰደናል፤ ዛሬ ለነፃነታችንና ለአንድነታችን ዘብ መቆም ይጠበቅብናል።
ነሐሴ 24/2014 ዓ.ም
ወልድያ
https://amharic-zehabesha.com/archives/176760
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment