ፂዮን ዘማርያም
ኢት-ኢኮኖሚ-ET- ECONOMY
አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት አገሮች የህዝብ ቁጥር እንዲቀንስ ጦርነቶች በማስፋፋትና የጦር መሳሪያዎች በመሸጥ የህዝብ እልቂትን ያበረታታሉ፡፡ በኢትዮጵያ ግማሽ ሚሊዮን ወጣቶች በጦርነት ተማግደዋል፡፡ መሠረተ-ልማቶች ወድመዋል፡፡ የወረቀት ነብሩ፣ የአሜሪካ መንግሥት ባወጣው H-R-6600 እና S-3199 ረቂቅ ህግጎች በሰሜኑ ጦርነት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ የስብዓዊ መብት ጥስት፣ የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል የጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ የህወሓትና የብልፅግና ጦር አበጋዞች ጋር የፖለቲካ ሽርሙጥና በመፈፀም ለወያኔ በመወገን ወልቃይት ጠገዴ፣ ራያ ወያኔ እንዲይዝና ለድርድር ከብልፅግና ጋር እንዲቀመጥ በማድረግ የፖለቲካ ሴራ ነድፋ የኢትዮጵያ ህዝብ በጦርነት፣ ርሃብ፣ ስደት እንዲሰቃይ አድርጋለች፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የነጮቹን ዘረኝነት በተመለከተ
“Until the philosophy which holds one race superior and another inferior is finally and permanently discredited and abandoned...Until there are no longer first class and second class citizens of any nation...Until the color of a man’s skin is of no more significance than the color of his eyes...Until the basic human rights are equally guaranteed to all without regard to race…Until that day, the dream of lasting peace...will remain but a fleeting illusion, to be pursued but never attained.” ቦብ ማርሌ በራስተማን ቨይብሬሽን የቀኃሥን ንግግር ለግማሽ ምዕተ አመታት አስተጋብቶታል፡፡
የትህነግ ጦር አበጋዞች የሰው ማዕበል ጥቃት፣ human wave attack, የሰው ማገድ ጥቃት human sea attack!!!
- ትህነግ በቆቦ ግንባር 100,000 (መቶ ሽህ ) ህዝብ በጦር ግንባር ህፃናትን፣ ሴቶችን፣ አረጋዊያን በማሰለፍ፣ በሰው ማዕበል ቆቦን በመውረር ተሰማርተው ቆቦን ተቆጣጥረዋል፡፡
- ትህነግ በራያ ግንባር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ) ህዝብ፣ የሰው ማዕበል ራያን ለመውረር ተሰማርተዋል፡፡
- ትህነግ በወልቃይት ጠገዴና ሁመራ ግንባር 300,000/400,000 (ሦስት እስከ አራት መቶ ሽህ ) ህዝብ፣ የሰው ሞገድ ወልቃይት ጠገዴና ሁመራን ለመውረር ተሰማርተዋል፡፡
- ትህነግ በአፋር ግንባር 100,000/ 200,000 (አንድ እስከ ሁለት መቶ ሽህ ) ህዝብ፣ የሰው ሞገድ አፋርን ለመውረር ተሰማርተዋል፡፡ ቀይ እንባባና ማንጁስ በማለት ህፃናትን በጦርነት ሜዳ በማሰለፍ በግፍ ማገዱአቸው፡፡
የትህነግ 570,000 (አምስት መቶ ሰባ ሽህ) ሊትር ነዳጅ ከዓለም ምግብ ድርጅት በመዝረፍ የሰው ማዕበላዊ ጥቃት፣ human sea attack ወይም የሰው ማገዳዊ ጥቃት human wave attack ያረጀ ያፈጀ የአንደኛው የዓለም ጦርነት ስልት በኢትዮጵያ ትህነግ፣ በአማራና አፋር ምድር ላይ የመንጋ ወረራ ማካሄድ ጀምሮል፡፡ https://TPLF-marching-to-war-_-Kobo.mp4 ………(1) የሚለውን የትህነግ ቪዲዬን ተመለከቱ፡ ትህነግ የትግራይን ህዝብ በጦርነት በመማገድ የመጨረሻ የእብደት ጉዞ ላይ እንዳለ ለአቅመ አዳምና ሄዋን ያልደረሱ ህፃናትን የጦር መሣሪያ በማስታጠቅ “ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው” በማለት ህሊናቸውን አጥቦ ወደ ሲኦል በመጎዝ ላይ ነው፡፡ በቪዲዬው ላይ እንደምታዩት ህፃናትን፣ ሴቶችን፣ አረጋዊያን በጦርነት አሰልፎ ለመማገድ፣ በሰው ማዕበል በዘፈን፣ በከበሮ፣ በፉከራና በሽለላ ንፁሁን የአማራና የአፋር ገበሬዎች ለመግደልና ሃብትና ንብረቱን በመዝረፍ ተሰልፈዋል፡፡ ትህነግ ታሪካዊ ጠባሳ አኑረዋል፡፡ የዛ ‹‹የወርቃማው የነጻ አውጪ›› ዘመናቸውን በሽብርተኛነት አረከሱት፡፡
በአንደኛው የዓለም ጦርነት የራሽያ የኮዛክስ ፣የፈረንሳይ ባዬኔት ቻርጂ፣ የቻይና የኮርያ ጦርነት እንዲሁም የኢራንና ኢራቅ የሰው ማዕበላዊ ጥቃት ሰልት በመጠቀም ብዙ ሚሊዮን ህዝብ እንዳለቀ ታሪክ ይመሠክራል፡፡ በ1950እኤአ በኮርያ ጦርነት (1950-53) በቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ዘመን በሦስት አመታት በተደረገ ጦርነት በሚሊዬኖች የሚቆጠሩ የሰሜንና የደቡብ ኮርያ ህዝብ ሞተዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ኃይል የተሰው አንድ መቶ ሽህ ወታደሮች በታሪክ ይዘከራሉ፡፡ ‹‹In 1950, the Cold War heated up with the outbreak of the Korean War (1950-53). This three-year bloody and brutal struggle left millions of North and South Koreans dead, and over 100,000 casualties for the United Nations forces involved.›› የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሃገሪቱን ሉዓላዊነት ለመታደግ ሳይሆን የአብይንና የደብረፂዮን ስልጣን ለመታደግ ሲሆን በህዝባዊ መዕበል እየተመመ ወደ ጦርነቱ እሳት የሚገባ የአማራ ወጣቶች፣ የአፋር ወጣቶች፣ ትግራይ ወጣቶች፣ ወዘተ በመጀመሪያው ጦርነት ግማሽ ሚሊዮን ወጣቶች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በ2014 ዓ ም የክረምት ወራት ለመጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኙት የህወሓትና የብልፅግና ‹‹ህዝባዊ ሠራዊት›› ሚሊዮን የአማራ፣አፋር፣ የትግራይ ወዘተ ወጣቶችን በማሰልጠንና በማደራጀት ‹‹ህዝባዊ ጦርነት›› ለማካሄድ በከሸፈ ‹‹የስብዓዊ ማዕበል የጦርነት ስልት››፣ የእግረኛ ሠራዊት እልቂት ለመድገም በነሃሴ ወር ድግስ ተደግሏል!!! ጥንት ጠመንጃዎቹ አንድ ጎርሰው የሚተኮሱ፣ ቆመህ ጠብቀኝ፣ የሚባሉ ዲሞትፎር፣ ቤልጂግ፣ ሰነኔ፣ ነጭ ቃታ ቤልጂግ፣ሞውዤር ወዘተ አነስተኛ የተኩስ አቅም ያላቸው ዘመን ነበር የሰው ማዕበል የጦርነት ስልት እልፍ አእላፍ ህዝብ በማዝመት ከጠላት ምሽግ ገብቶ በእጅ መተናነቅ የጦርነት ስልት የነበረው፡፡
‹‹“The human wave attack, also known as the human sea attack, is an offensive infantry tactic in which an attacker conducts an unprotected frontal assault with densely concentrated infantry formations against the enemy line, intended to overrun and overwhelm the defenders by engaging in melee combat. The name refers to the concept of a coordinated mass of soldiers falling upon an enemy force and sweeping them away with sheer weight and momentum, like an ocean wave breaking on a beach.” (From Wikipedia, the free encyclopedia)››
አብይና ደብረፂዮን ወጣቶችን የሚማግዱበት የፃረ-ሞት የጦርነት ዘመቻ ደግሰዋል፡፡ ጦርነትን በወታደር ብዛት፣ በሰዎች ጎርፋና ማዕበል ጦርነትን ማሸነፍ፣ የጦር መሳሪያው የመተኮስ አቅም ዝቅተኛ የነበረበት ዘመን ሲሆን በዚህ ዘመን ጊዜ ያለፈበት ‹‹ህዝባዊ ሠራዊት፣ ለህዝባዊ ጦርነት›› የከሸፈ የጦርነት ስልት ነው፡፡ በህወሓትና ብልፅግና የእግረኛ ሠራዊት እንደቅጠል እንዲረግፍ የሚያደርግ እልቂት በሃምሌ ወር ደግም ተደግሏል !!! ዘመናዊው የጦርነት ስልት በጦር መሳሪያው ዓይነትና ብዛት የማውድም ኃይል የሚለካ ሲሆን ለምሳሌ ዘ ሄክለር እና ኮች ጂ አስራአንድ ጠመንጃ (The Heckler and Koch G11 Assault Rifle Can Fire 2,100 Rounds Per Minute) አንድ ወታደር በደቂቃ 2100 በአንድ ዙር ጥይቶች የመተኮስ አቅም ሲኖረው፣ በሰዓት መቶ ሃያ ስድስት ሽህ፣በቀን ሦስት ሚሊዮን ሃያ አራት ሽህ ጥይቶች የመተኮስ አቅም ስላለው፣ ምንያህል ወታደሮች እንደሚፈጂ በዚህ ቀላል ምሳሌ መረዳት ይቻላል፡፡ አንድ እናት አንድ ህፃን ለማሳደግ አስራ ስምንት አመታት ሲፈጅባት፣ ዘ ሄክለር እና ኮች ጂ አስራአንድ በደቂቃዎች የጠመንጃ ቃታ በመሳብ ሚሊዮኖች እንዴት እንደሚያልቁ ያስረዳል፡፡ ፋየር ፓወር፡- የመተኮስ አቅምና የማውደም አቅም መለኪያ ሲሆን ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎች ጠመንጃዎች፣ ሚሳኤሎች፣ወታደራዊ ኃይል (የሰው ኃይል ቁጥርና የመሳሪያ ዓይነትና ብዛት ያገናዘበ መለኪያ ነው፡፡) fire-power፤-the destructive capacity of guns, missiles, or a military force (used with reference to the number and size of guns available).
በአፄ ሚኒሊክ የአድዋ ጦርነት በአስራስምንተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ‹‹ህዝባዊ ሠራዊት፣ ለህዝባዊ ጦርነት›› ሰልትን በመጠቀም የጦልያን ጦርን አሸንፈዋል፡፡ እግረኛ ሠራዊት እንደ አንበጣ ወረራ በእልፍ ወታደሮች የጠላት ምሽግን፣ ታንክን፣ ከባድ መሣሪያዎችን በድንገት በማጥቃት በሰው ኃይል የማሸነፍ የውጊያ ስልት ነበር፡፡ አብይና ደብረፂዮን በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ይህን ስልት በመተግበር ሚሊዮን ወጣቶችን በጦርነት በመማገድ ላይ ይገኛሉ፡፡ በእልፍ ጦር በድንገት የማጥቃት እምነትና ህግ መሠረት በጣም ጥሩ ዘመናይ የጦር መሣሪያ የድል መንገድ ጠራጊ ነው፡፡ በወታደር ብዛት የስብዕዊ ማዕበል ዘመን አከተመ፡፡ ዛሬ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ ዓይነትና ብዛት በአነስተኛ የሰው ኃይል የጦርነት ስልት ዘመን ተተክቷል የእስራኤልና የአረቦች ጦርነትን ልብ ይበሉ፡፡
ህዝባዊ ማዕበል፣(human waves) የቻይናዎች የጦርነት ስልት ነው፣ ብዙ እግረኛ ጦር ሠራዊቶች፣ ጠላታቸውን ለማጥቃት ወደፊት በመገስገስ በጦርነት ዘመቻ የሚተሙበት ታክቲክና ስትራቴጅ ሲሆን ዓላማውም በሁለቱም ጎራ በሠራዊት ጎርፍ፣ በእግረኛ ወታደር ማዕበል በማሰለፍ በሙታን ላይ እየተረማመዱ ወደፊት የሚተሙበት አሰቃቂ ሰው ሰው ያልሸተተ የጦር ስልት ነው፡፡ ዘመናዊ የጦርነት ስልት ለአንድ ወታደር ህይወት የሚጨነቅ ሲሆን አመራሩም የዘመኑን የወታደራዊ ሳይንስ ጥበብ የተማሩና ስብዓዊነትን የተላበሱ መሪዎች መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ‹‹The Chinese tactic meaning human waves was a charge of too many soldiers, too many soldiers rushing forward in attacks against their opponents.›› የብልፅግና ህወሓት የጦር አበጋዞች በሰሜኑ ጦርነት ዘመን ባለፈበት ታክቲክና ስትራቴጅ፣ በሁለቱም ወገን ህዝባዊ እግረኛ ሠራዊት እንደ መንጋ በማሰለፍ በግንባር በማሰማራት ወጣቶቹን ቦንብ ጠራጊ፣ ጥይት አብራጅ፣ ምሽግ ደርማሽ፣ የታንክ አጋች፣ የጠብመንጃ አፈሙዝ ያዥ፣ በማድረግ የምስኪኖቹን እልፍ አእላፍ ወጣቶችን ህይወት አስገበሩ፡፡ የብልፅግና ህወሓት የጦርአበጋዞች የሥልጣን መንበራቸውን ለማስጠበቅ በውሽት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት አንደኛው ሌላኛውን በሃገር ክህደት፣ በአገር በመሸጥ፣ በሃገር ላይ በማሴር ወንጀል ወዘተ በመካሰስ የእርስ በእርስ ፀባቸውን በህዝብ ስም በሃገር ስም በማድረግ አንድን ህዝብ ለሁለት ከፍለው ወንድም ወንድሙን እንዲወጋ፣ ጦር እንዲሰብቅ፣ ጋሻ እንዲነቀንቅ፣ እንዲፎክር እንዲያቅራራ በማድረግ የወጣቶችን ህሊና በማጠብ ውድ ህይወታቸውን በከንቱ እንዲያጡ አደረጉ፡፡ ለአብይና ደብረፂዮንና ኢሳያስ ጂኒ ህይወታቸውን እንዲገብሩ ‹‹ወጣት የነብር ጣት!!!››…‹‹ማን ይፈራል ሞት!...ማን ይፈራል!›› በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ወጣቶቹን ‹‹በእናት ሃገር ስም›› ‹‹በእምዬ ኢትዮጵያ ስም›› ‹‹በትግራዋይ ስም›› ወጣቶችን ለመስዋትነት ያቀረቡበት ለሃገራችን ህዝብ ጨለማው ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡
“Who does not shudder to hear of the "human wave" tactics reportedly being used by Iran in its invasion of Iraq? The phrase summons up the image of thousands, perhaps tens of thousands of soldiers, many still young boys, marching "fanatically" to certain death for a cause rendered dubious fecisely by the extreme means employed to serve it. Often the term, human wave, comes with a definition of it as a "Chinese tactic," from the Korean War. The implication is that Western or white soldiers would never lend themselves to any such mass display of mindlessness and barbarism.”…………..(3)
የሰው ማዕበል "human wave" የጦርነት ስልት ኢራንና ኢራቅ በወረረች ጊዜ ተጠቅማበት ነበር፡፡ በጦርነት በሽዎችና በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ ጦርነት ዘመቻ ተመሙ በጭፉን እምነትና በከንቱ የሃገር ፍቅር ስሜት ወደሚጠበቀው ሞት አመሩ፡፡ ህዝባዊ ማዕበል ‹‹የቻይናዎች ስልት›› ሲሆን በሰሜን ኮርያ ጦርነት ጊዜ የተጠቀሙበት የጦርነት ስልት ነበር፡፡ ምዕራባዊያን ወይንም የነጭ ወታደሮች በፍፁም እራሳቸውን በጅምላ ማቅረብ፣ እራሳቸውን በመንጋ ማሳየት በድንቁርና ያለመሠልጠንና አረመኔያዊነትና ኃላቀርነት ነው፡፡ ሰው ሰው ያልሸተተውን የጦርነት ስልትን በመሆኑ የጦርነት ስልቱን አይቀበሉም፣ ይቃወማሉም፡፡ የአንበጣ ወረራ ፀሓይን ይጋርዳል፣ የምድር እፅዋትንና ሠብልን ዶጋ አመድ አድርጎ ወደፊት ይገሠግሳል፡፡ ስብዓዊ ማዕበል የጦርነት ዘመቻ የረገፈው ረግፎ፣ በደመነፍሳቸው በሙታኖች ሬሳ ላይ እየተረማመዱ የመዋጋት ስልት ሲሆን፣ እንደ አንበጣ ወረራ ምግብ ፍለጋ ወደፊት ብቻ የመገስገስ ዓይነት ነው፡፡ በምድረ እንግሊዝ በሰው ሰራሽ ክህሎት የተሠሩ ሮቦቶች በወህኒ ቤቶች ያሉ እስረኞችን አጥርና ከተንበሬ መዕልት ወ ለሊት እስረኞች እንዳያመልጡ ይጠብቃሉ፡፡ እንደ ጢያራዋ ሰው አልባ ድሮውን ወደፊት እግረኛ ሰው ሰራሽ ወታደራዊ ሮቦቶች ከህያው ወታደሮች ጋር የሚዋጉበት የዲጅታል ቴክኖሎጅ ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ በጦርነት ጥርሳችንን ነቅለናል ለሚሉት የዘመናችን ሲሊቨስትሪ ስታሊየኖች አብይና ደብረፂዮንና ኢሳያስ፣ የጦር አበጋዞች ወጣቶችን በእሳት መማገድ በእግዚያብሄር ያስጠይቃል እንላለን፡፡ ለዓለም አቀፍ የጦር ፍርድ ቤት መቅረባችሁ ግን በፍፁም አይቀርም፡፡ መንግሥት ያልፋሉ ህዝብ ግን አያልፍም፡፡የኤርትራ፣ የትግራይ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ጥንት እንደ ጠዋቱ በፍቅር፣ በሠላምና በአንድነት ይኖራል፡፡
ከአምስት መቶ አመታት ገደማ ከክርስትና ዘመን በፊት፣የቻይና ፈላስፋ ሊቀ ሊቃዉንት ኮንፊሽየስ እንዳለዉ ‹‹ለአንድ አመት እቅድ ካወጣህ፣ዘር ትከል፡፡መቼም! ዘር በዘራህ ግዜ የአንድ ግዜ ምርት/አዝመራ ትሰበስባለህ፡፡ ለመቶ አመታት እቅድ ካወጣህ ህዝቡን አስተምር፡፡ መቼም! ህዝቡን ካስተማርክ የአንድ ምዕተ ዓመት የምሁራን መህር ትሰበስባለህ፡፡››Around 500 years before the Christian era began, the ancient Chinese sage Confucius said: “If you plan for a year, plant a seed. If for a hundred years, teach the people. When you sow a seed, you will reap a single harvest. When you teach the people, you will reap a hundred harvests.” የህወሓት ማሌሊት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ከ1967ዓ/ም እስከ 2015ዓ/ም ድረስ ለግማሸ ምእተ ዓመት ወጣቶቹን በማሰልጠን ለገደላ፣ ለዘረፋ፣ ለወረራ ወዘተ አሰለጠኑአቸው ቃታ መሳቢያ ገዳይ ጣታቸው ተቆልምማ ከስታ መነመነች፣ አነጣጣሪ ግራ ዓይናቸው ፈዛ አነሰች፡፡ የአዲስ አበባ ሰው፣ ማንም ሰው አይቶ ተዋጊ መሆናቸውን ተጠቆቁሞ አወቃቸው፡፡ የመለስ የኮንፊሽየስ አስተምርሆት በመቀየር ‹‹ለአንድ አመት እቅድ ካወጣህ፣በኢትዮጵያ ምድር የብሔር ዘር ትከል፡፡ መቼም! ዘር በዘራህ ግዜ የአንድ ግዜ ምርት/አዝመራ ትሰበስባለህ፡፡ ለመቶ አመታት እቅድ ካወጣህ ህዝቡን ስለ ዘር ማጥፋት፣ አስተምር፡፡ መቼም! ህዝቡን ካስተማርክ የአንድ ምዕተ ዓመት የምሁራን በትረ -ሥልጣን ትጨብጣለህና ባንኩም፣ ታንኩም፣ ወርቁም፣ መሬቱንም ትሰበስባለህ፡፡››
‹‹“የህወሓት/ማሌሊት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ሌላ አማራጭ መንገድ የማያውቁ በስታሊናዊ ጨካኝ አስተሳሰብ ተኰትኩተውና እንደ ዓሳራ ግመል ፊታቸውን ተሸብበው ያደጉ ናቸው:: መለስ ዜናዊም ብልጥ ነው:: ሆን ብሎ የህወሓት ማሌሊት ሶፍት ዌር ፕሮግራም በጭንቅላታቸው ውስጥ የገጠመላቸው ስለሆኑ ከዚያ አጥር ወጥተው ሌላ ሰፋ ያለ ዓለምና ሳይንስ የሚያዩበት መነፅር የላቸውም:: ቢተኩሱም! ቢነግሱም! ቢማሩም ያው ናቸው ምንም አይለወጡም:: ቀደም ብሎ በአእምሮኣቸው ከተገጠመላቸው የሶፍት ዌር ፕሮግራም ውጭ ሌላ የሚያውቁትና የሚናገሩት ሰላማዊ ቋንቋ የላቸውም:: ሁሉ ጊዜ “አካኪ ዘራፍ!! በለው ደምስሰው!! - ያዘው ልቀቀው” የሚሉትን ቃላቶች ብቻ ናቸው በአእምሮኣቸው የሚታዩባቸው:: ሕግ አይገዛቸው! ባህል አይገዛቸው! ታሪክ አይገዛቸው! ሀይማኖት አይገዛቸው! ጊዜ አይለውጣቸው! ዕድሜያቸው ልክ አንድ ዓይነት መዝሙር እየዘመሩ ጭንቅላታቸውን በማሌሊታዊ ሰይጣናዊ አስተሳሰብ እንደተቆለፈ ያልፋሉ:: በመሆኑም አሁን እየታየ ያለው ትልቁ አሳሳቢ ጉዳይ የህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው በማሌሊት ሶፍት ዌር ፕሮግራም መደንዘዛቸው ብቻ አይደለም ችግሩ:: ነገር ግን ከጫካ ይዘውት የመጡት መድሃኒት አልባ በሽታ ወደ ሌሎች ክልሎችም በፈጣን ሁኔታ እየተዛመተ መምጣቱ ነው:: ስለዚህ “ቤቱን ሳይቃጠል በቅጠል” እንደተባለው እኛም በተራችን ሳንታመም የመከላል ዘዴ መፍጠር ይኖርብናል፡፡”›› አንድ የትግራይ ተወላጅ ምሁር ከዓመት በፊት በአንድ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ያደሩት ንግግር ዛሬም ድረስ ህያው ነው፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅ!!!
ምንጭ
(1) TPLF-marching-to-war-_-Kobo. mp4
(2) https://youtu.be/7cbwBgnYU5Q
(3)"We Were Lied To": How Story, Culture & Manufactured Identities are Weaponized in Africa - YouTube)
(4) 'Human Waves' - The Washington Post/By Stephen S. Rosenfeld/March 9, 1984
(5) Robots aren’t better soldiers than humans/ The Boston globe/ mary wareham/ Oct. 26, 2020
https://amharic-zehabesha.com/archives/176765