የተከበሩ አቢይ አህመድ ሁለት የተለያዩ አስተሳሰቦችን ባንድ ጊዜ፤ ሁለት አይነት እንቅስቃሴና ለሁለት የተከፈለ ባህርይ የሚያጣምር የአይምሮ ችግር ወይም የመገለልና የማንነት ቀውስ (dissociative identity disorder (DID)) ይኑራቸው አይኑራቸው በእርግጠኝነት መናገር አልችልም:: ነገር ግን ካስተዋልኳቸው ነገሮች በእርግጠኝነት በአንድ ራስ ሁለት ምላስ (Doublethink) ወይም ድርብ ተፃራሪ አስተሳሰብ ባለቤት መሆናቸውን እረዳለሁ::
ታላቁ ጆርጅ ኦርዌል 1984 በተሰኘው መፅሃፉ "በአንድ ራስ ሁለት ምላስ (Doublethink) ወይም መንታ ተፃራሪ አስተሳሰብን ሲገልፀው 'ሁለት ተቃራኒ የሆኑ ሀሳቦችን በአንድ ጊዜ መያዝና ሁለቱም ተፃራሪ ሀሳቦች እውነት ናቸው ነው ብሎ ማመንና አመራርንና ህዝብ ስነልቦናዊ መጠቀሚያ በማድረግ የሚከወን የፕሮፖጋንዳ አካል ነው" ይላል:: በመቀጠልም "በአንድ ራስ ሁለት ምላስ (Doublethink) አስተሳሰብ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ እንደ ፓርቲ ህዝቡ የራሱን ግንዛቤ እንዳይጨብጥ ህሊናውን የሚቆጣጠርበት ዘይቤ ወይም ብልሃት ነው:: በተጨማሪም ህዝቡን ለማሳመን ህዝቡ እውነትነቱን ከሚያውቀውን ጉዳይ ተቃራኒውን በማስቀመጥ እውነትን መበረዝና ማዛባትም ነው:: በአንድ ራስ ሁለት ምላስ (Doublethink) ማወቅና አለማወቅን በጥንቃቄ የተቀመሩ ውሸቶችን በመደርደር አስፈላጊ የሆኑ መዘንጋቶች እንዲሰፍኑ ማድርግ እንዲሁም አስፈላጊ ሆነው ሲገኙ እንደገና ለትውስታ ማብቃት እንደገናም ማስረሳት ነው::" ሲል የዘረዘረው የድርብ አስተሳሰብ ይዘትን ያሰፈረበት ዝነኛ መጣጥፉ አሳምሮ በሚገባ ይገልፃቸዋል::
ይሄው ነው!
https://amharic-zehabesha.com/archives/176305
Wednesday, July 27, 2022
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment